The Power of Thought
Open in Telegram
ሀሳቦቻችን እጣፈንታችንን ይወስናሉ። Transform Your Thinking. Transform Your Life. Think. Grow. Succeed. Contact us @RadiantEphrem
Show more456
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
ትናንት አልፏል፣ ነገ ደግሞ ገና አልመጣም። ያለን ብቸኛ ውድ ሰዓት አሁን ነው።
ብዙዎቻችን ትናንት በሰራነው ስህተት እየተቆጨን ወይም ስለ ነገ እየተጨነቅን የዛሬውን ውብ እሁድ እናባክነዋለን። 🛑 ባለፈው ሳምንት የሆነው ነገር ሁሉ ትምህርትህ እንጂ እስር ቤትህ አይደለም!
🌿 ዛሬ እሁድ፣ አእምሮህን በሰላም ሙላውና ለሚቀጥለው ሳምንት በንፁህ እና በአዲስ መንፈስ ተዘጋጅ።
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
In business, you cannot control everything—but you can control your attitude, your thoughts, your response, and your actions.
Change your thinking.
Improve your attitude.
Take consistent action.
And watch your results begin to change. 🚀
Your biggest business breakthrough may begin with one new thought.
https://t.me/The_PowerOfThought
🛋️ ቅዳሜ ሳምንታዊ እረፍት የምናደርግበት ቀን ቢሆንም፣ አእምሯችን ግን እረፍት አያውቅም። ዛሬ ስልካችንን ስንከፍት የምናየው እያንዳንዱ የሶሻል ሚዲያ ቪዲዮ (Reels) አእምሯችን ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል።
📴 ዛሬ ለጥቂት ሰዓታት ስልክህን አጥፍተህ ከራስህ ጋር ጊዜ ብታሳልፍስ?
🗺️ ወደፊት የት መድረስ እንደምትፈልግ በፀጥታ ብታስብ? እውነተኛ እረፍት እና ንቃት የሚገኘው ከውጫዊው ጫጫታ ርቀን የውስጣችንን ድምፅ በረጋ መንፈስ ስንሰማ ነው።
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
💎 ታላላቅ ነገሮችን ለማሳካት የግድ ትልቅ ቦታ ላይ መሆን አይጠበቅብህም፤ ነገር ግን ትልቅ ቦታ ለመድረስ ዛሬ ባለህበት ቦታ ሆነህ በትናንሽ ነገሮች ታማኝ መሆን አለብህ።
🏁 የሳምንቱ የመጨረሻ የስራ ቀን ላይ ደርሰናል። ዛሬ ስራህን ስታከናውን በግዴለሽነት ሳይሆን፣ የወደፊት ትልቅ ህልምህን እየገነባህ እንደሆነ አስበህ በሙሉ ልብህ ስራው! 🛠️
🌟 ጥራት ያለው ስራ ጥራት ካለው አስተሳሰብ ይመነጫል።
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
If you put the bananas and money in front of the monkeys ... JACK MA
በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው።
ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡- ‘’ ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!
አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።
ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው።
ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!
እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል።
በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’ ይላል ጃክ ማ። እውነት ነው እኛም አገር ያለው ነባራዊ እውነታ ይሕ ነው። ምክንያቱም ተቀጥረህ በምታገኘው የወር ደመወዝ ሀብት፣ ጥሪት፣ ቤት እና ራስህን ለውጠህ ሌላ ሰው መርዳት አትችልም። እርግጥ ነው የወር ደመወዝ ሲኖርህ የምትፈልገውን ማድረግ ባትችልም በገቢህ ልክ መኖርን ትለምደዋለህ።
ለማንኛውም በሥራ ፍለጋ ጊዜ ከማባከን በትንሹም ቢሆን የግል ስራ የምትጀምሩበትን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።
http://t.me/The_PowerOfThought
🚫 ፍርሃት ትልቅ ውሸታም ነው!
ብዙ ጊዜ ፍርሃት በአእምሯችን ውስጥ የሚያሳየን ትልቅ እና አስፈሪ ገደል 🧗♂️፣ በተግባር ገብተን ስንጋፈጠው ግን ትንሽ እርምጃ ሆኖ እናገኘዋለን።
🏆 ስኬታማ ሰዎች ፈርሃት-አልባ የሆኑ ሳይሆኑ፣ ፍርሃት እያላቸውም እንኳ ወደፊት ለመራመድ የሚደፍሩ ናቸው።
🔥 ዛሬ ሐሙስ፣ በጣም የምትፈራውን ያንን አንድ ስራ ወይም ውሳኔ በቁርጠኝነት ተጋፈጠው። ከፍርሃትህ በስተጀርባ የምትፈልገው ታላቅ ማንነትህ ተደብቋል!
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
ጥያቄ እንጠይቃችሁ!!
አሁን እየሰራችሁት ያለው ስራ፤ እየዋላችሁት ያለው ውሎ የዛሬ አስር አመት ወደ ምትፈልጉት ቦታ እንደሚያደርሳችሁ እርግጠኛ ናችሁ? ከአስር አመት በኋላ ለምትፈልጉት ህይወት አሁን ምን እየሰራችሁ ነው? አእምሮዋችን ከሚዋሸን ውሸት አንዱ በአቋራጭ ወደ ምንፈልገው ቦታ እንደምንደርስ ነዉ። ያ ግን ውሸት ነው ከመሬት ተነስቶ የሚመጣ ስኬት የለም።
መልካም ቀን 🙏
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
፡
🧠 የሀሳብ ኃይል (The Power of Thought)
በህይወታችን የምናያቸው ታላላቅ ስኬቶችም ሆኑ ውድቀቶች በሙሉ የሚጀምሩት በአንድ አነስተኛ ነገር ነው—እሱም "ሀሳብ" ነው።
ብዙ ጊዜ ህይወታችንን የሚቀይሩት ውጫዊ ሁኔታዎች (የምንኖርበት አካባቢ፣ የኪሳችን ሁኔታ ወይም ያጋጠሙን አጋጣሚዎች) ይመስሉናል። ነገር ግን እውነታው ፍጹም ተቃራኒ ነው። ህይወታችንን የሚመራው ውጫዊው ዓለም ሳይሆን፣ በውስጣችን በየቀኑ የምናስተናግደው የሀሳብ ጥራት ነው።
"የህይወትህ ደስታ እና ስኬት የሚወሰነው በሀሳቦችህ ጥራት ላይ ነው።"
አእምሯችን ልክ እንደ ለም እርሻ መሬት ነው። መሬቱ የዘራንበትን እንጂ የምንፈልገውን ዝም ብሎ አያበቅልም። በውስጡ የፍርሃት፣ የጥርጣሬ እና አልችልም የሚሉ የውድቀት ዘሮችን ከዘራን የምናጭደው እሱኑ ተስፋ መቁረጥ ነው። ነገር ግን የጥንካሬ፣ የይቻላል እና የዕምነት ዘር በጥንቃቄ ከዘራን፣ የምንሰበስበው አስደናቂ ስኬትን ይሆናል።
እንጠይቅ እስኪ
👉 "አብዛኛውን ጊዜ አእምሮዬን የምመግበው ምን አይነት ሀሳብ ነው? የሚያሳድጉኝ ወይስ ወደኋላ በሚያስቀሩኝ?"
t.me/The_PowerOfThought
የአሊባባ ኩባንያ መስራች የሆነው ጃክ ማ አነቃቂ ንግግሮች...
"እኛ የገንዘብ እጥረት የለብንም፡፡ እኛ ያለብን እጥረት ለህልሙ የሚሞት ባለ ራዕይ ነው።"
" አለማችንን መለወጥ ከፈለግን በቅድሚያ እራሳችንን መለወጥ ይገባናል፡፡"
"ከሁሉም ነገር በላይ ሊኖርህ የሚገባ ነገር ቢኖር ትዕግስት ነው፡፡"
"ተስፋ መቁረጥ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ምክንያቱም ተስፋ ካልቆረጥክ አሸናፊ ልትሆን የምትችልበት እድል ሊኖርህ ይችላል፡፡"
"ከተቀናቃኞችህ ልትማር ይገባል፡፡ ነገር ግን መኮረጅ ፍፁም የለብህም፤ ኮርጅና መጨረሻህ ይሆናል!፡፡
"በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስኬታማ መሆን ከፈለክ፤ ሌሎችን ልታነቃቃ ይገባሃል፤ ሌሎች ከአንተ የተሻሉ ሰዎች እንዳሉም ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ይሄን ማድረግ ከቻልክ ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡"
"ስለ ተቀናቃኖችህ ማሰቡን አቁም፡፡ ስኬታማ መሆን ከፈለክ ትኩረትህን ደንበኞችህ ላይ ብቻ አድርግ፡፡"
"የእኔ ስራ በርካታ ሰዎች ስራ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡"
"ሁሉም ሰው ህልም ሊኖረው ይገባል፡፡"
+1
#Ambo
ዓለም እንድትለወጥ አትጠብቅ። አስተሳሰብህን ለውጥ፣ ያኔ በአካባቢህ ያለው ዓለም መለወጥ ይጀምራል።
ዕድገት በአእምሮ ውስጥ ይጀምራል።
ዛሬ ሌላ ፐርሰናል ዴቬሎፕመንትና ቢዝነስ ስልጠና በአምቦ ተሰጥቷል—ምክንያቱም ማንኛውም ታላቅ ለውጥ የሚጀምረው በታደሰ አእምሮ ነውና።
አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀
t.me/The_PowerOfThought
+2
Don't wait for the world to change. Change the way you think, and the world around you will begin to change.
Growth begins in the mind.
Today at Asela
ማጣጣም ልመድ !
ድግስ ላይ ከቡፌው የምትፈልገውን የምግብ ዓይነት ሁሉ አንስተህ ስትጨርስ ምግቡን ፊት ለፊትህ አስቀምጠው አይንህ እንዲያየውና አፍንጫህ እንዲያሸተው ብቻ ቢደረግ አያበሳጭም?
በህይወትም ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች አንብበህ፣ ሰምተህ፣ በአይምሮህ ሰብስበህ ግን ተግባር ላይ ካላዋልከው አሪፍ ምግብ ሳይበሉ ከማሽተት በምንም አይለይም። ብዙ ነገር ማወቅህ ጥሩ ነው፤ ወደ ተግባር ሲለወጥ እውቀት ኃይል ይሆናል።
ሰናይ ቀን ይሁንልን🙏
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በአንድ ወቅት በአንድር መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዙ ተገኘ
ይህ #እምነት ይባላል፡፡
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌅 ፀሀይ ስትወጣ አዲስ ተስፋ አብሮ ይወጣል!
እንኳን አደረሳችሁ ለአዲስ ቀን!
በህይወታችን ውስጥ ትልቁ ስጦታ በህይወት መኖር እና አዲስ ቀን ማየት ነው። ጉዟችን የቱንም ያህል ረጅም ቢሆን፣ በየቀኑ የምናደርጋት አንዲት እርምጃ ወደ ግባችን ታደርሰናለች።
እቅድህን በልበ ሙሉነት ጀምር!
ችግሮችን ወደ እድል ቀይር!
አእምሮህን በበጎ አስተሳሰብ ሙላው!
እራስህን እመን፤ አንተ ካሰብከው በላይ ጠንካራ እና ትልቅ አቅም ያለህ ሰው ነህ።
መልካም እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ! 🌟✨
@The_secretsOfsuccess
💡 አዲስ ቀን፣ አዲስ እድል!! ✨
ትላንት ታሪክ ነው፣ ነገ ደግሞ ገና ያልተገለጠ ምስጢር ነው። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ያለ እውነተኛ ስጦታ ነው። ትላንት የጀመርነውን ለመጨረስ፣ ያቀድነውን ለማሳካት እና ወደ ህልማችን አንድ እርምጃ ለመጠጋት ዛሬ ምርጥ ቀን ነው።
ስኬት በድንገት የሚመጣ ተአምር ሳይሆን፣ በየቀኑ በምናደርጋቸው ጥቃቅን እና ተከታታይ ጥረቶች የሚገነባ ህንጻ ነው። ዛሬ የምናፈስሰው ላብ እና የምናሳየው ቁርጠኝነት የነገውን ማንነታችንን ይወስናል።
የዛሬው መፈክራችን፦
ትልልቅ ነገሮችን ለማሳካት መጀመሪያ በትናንሽ ስራዎች ላይ ታማኝ እና ጠንካራ መሆን አለብን።ዛሬን በሙሉ ሀይል፣ በጎ አስተሳሰብ እና በታላቅ መነሳሳትን እንጀምር! ስኬታማ እና ፍሬያማ ቀን ይሁንላችሁ! 💼🚀 https://t.me/The_secretsOfsuccess
ኃይልን እወቅ!
በዚህች አለም ላይ 98%ከመቶ የሚሆኑት የሰው ልጆች የሚኖሩት የተሰጣቸው ኃይላቸውን ለመጠቀም መንገዱ ጠፍቷቸው ነው በእነዚህ 2% በሚሆኑት ሰዎች ሥር ይኖሩታል። እግዚአብሐር ሰው ልጅን ሲፈጥር ብዙ ስጦታዎችን ሰጥቶናል ከእነዚህ ስጦታዎች አንዱና የተለየ ስጦታ አለ እሱም አዕምሮ ነው።
አዕምሮ በእግዚአብሔር ከተሰጡን ስጦታዎች ሁሉ ለሰው ልጅ የተለየ ነው ይህን ጥቂቶች ተረድተውት በአለም ቁንጮ ላይ ተቀምጠዋል አንዳንዶች ደግሞ በሕይወታቸው በማማረር አለም ውስጥ ያሳልፋሉ።ስለዚህ አሁን እኔ የምለው ይህንን ስጦታ በአግባቡ እንጠቀም ያለፈው ትናንት ላይመለስ ነው የሄደው ነገ ደግሞ የማይታይ ምሥጢር ነው ዛሬ ደግሞ ለሕይወታችን የተሰጠች ውዷ ቀን ነች ስለዚህ የተሰጠችንን ቀን በአግባቡ በመጠቀም ስፖርት መሥራት ካለብን ዛሬ በመሠራት ያሰብነው ቢዝነስ ካለ አሁን በመጀምር ማድርግ ስንትችል መጽሐፍ ማንበብ ክለብን አሁን መጀምር። እንደዛ ማድረግ በጀመርን ሰዓት የአዕምሮን ኃይል መጠቀም እንጀምራለን። ቁጭ ካልክን እንደ ብረት አዕምሮ መዛግ እንጂ ምንም አይነት ለውጥ አያመጣም።
የስጠና መድረክ ጥቆማ 📢
ቅን መድረክ የግል ስብዕና ማበልፀጊያ ስልጠና ፕሮግራም 🚀
ከ20 አመት በላይ የማሰልጠን ልምድ ያለው 🎓
አሰልጣኝ ዳንኤል መስፍንን ከካናዳ 🇨🇦
በግሩም ስልጠና ይዞላችሁ ይቀርባል! ✨
በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ሚያዚያ 10/2018 📅
ምሽት ከ3:00-4:30 ⏰
በ Tiktok live stream 📱
ባለራዕይ ቅን ጤናማና ባለጸጋ ትውልድ ማፍራት! 👨👩👧👦
በፍፁም እንዳያመልጦ! 🙏
Tiktok Link 🔗
tiktok.com/@genuinestage
