en
Feedback
The Power of Thought

The Power of Thought

Open in Telegram

ሀሳቦቻችን እጣፈንታችንን ይወስናሉ። Transform Your Thinking. Transform Your Life. Think. Grow. Succeed. Contact us @RadiantEphrem

Show more
456
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
📖 ከጥበቃነት ወደ ሚሊየነርነት — የእውነተኛው ጃክ ማ (Jack Ma) ታሪክ! ዛሬ የዓለማችን ትልቁ የኢ-ኮመርስ ድርጅት (Alibaba) መስራች የሆነው ጃክ ማ፣ ስኬታማ ከመሆኑ በፊት ህይወቱ በሙሉ በውድቀት የተሞላ እንደነበረ ታውቃለህ? የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 3 ጊዜ ወድቋል። KFC ቻይና ውስጥ በተከፈተ ጊዜ ለስራ ቅጥር ከተወዳደሩት 24 አመልካቾች መካከል 23ቱ ሲቀጠሩ የተቀነሰው እሱ ብቻ ነበር! በፖሊስነት ለመቀጠር ሲያመልከትም አልተቀበሉትም። ነገር ግን የጃክ ማ ህይወት የተቀየረው ከአንድ የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset Shift) በኋላ ነው! 💡 የአስተሳሰብ ለውጡ ምንድን ነው? አብዛኛው ሰው በውድቀትና በ አይሆንም መልሶች  "እኔ እድል የለኝም" ብሎ ተስፋ ይቆርጣል። ጃክ ማ ግን ውድቀትን እንደ  እንቅፋት ሳይሆን እንደ ትልቅ የትምህርት እድል ተመለከተው። እ.ኤ.አ በ1995 ወደ አሜሪካ በሄደበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት ከተመለከተ በኋላ አእምሮው በአዲስ አስተሳሰብ ተከፈተ፦ አብዛኛው ሰው ኢንተርኔትን ለመዝናናት እና ለመጫወቻነት ሲጠቀመው፣ እኔ ግን የሰዎችን የቢዝነስ ችግር ለመፍታት እጠቀምበታለሁ! አለ በኪሱ ምንም አይነት የቴክኖሎጂ እውቀትና ትልቅ ገንዘብ ሳይኖረው፣ በአስተሳሰብ ለውጡና በፅናቱ ብቻ በቤቱ ሳሎን ውስጥ አሊባባን (Alibaba) ጀመረ። ዛሬ ላይ ያ አእምሮውን የለወጠ ወጣት ከቢሊየነሮች ተርታ ተሰልፏል! 🧠 የታሪኩ ትልቁ ትምህርት፦ 1️⃣ ትልቁ ሀብትህ አስተሳሰብህ ነው፦ ጃክ ማ ሲጀምር ገንዘብ ወይም የቴክኖሎጂ እውቀት አልነበረውም። የነበረው ትልቁ ካፒታል "ይቻላል" የሚል አስተሳሰብ ብቻ ነበር። 2️⃣ አመለካከትህን ቀይር፦ የሚገጥምህን ችግር ወይም ውድቀት እንደ ማቆሚያ ሳይሆን፣ አዲስ መንገድ መፈለጊያ አድርገህ ተመልከተው። "ዛሬ ከባድ ነው፣ ነገ ደግሞ የባሰ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ ከነገ ወዲያ ግን ድንቅ የፀሐይ ብርሃን ይታያል ብዙ ሰው ግን ነገ ማታ ላይ ተስፋ ይቆርጣል!"ጃክ ማ 💬 የዛሬው ጥያቄ፦በህይወትህ የገጠመህ ውድቀት ያበቃህበት ቦታ ነው ወይስ አዲስ አስተሳሰብ ያስጨበጠህ? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇 🚀 የፋይናንስ እና የስኬት አስተሳሰብህን የሚቀይሩ መረጃዎችን ለማግኘት ዋናውን ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉 @The_powerOfthought 📥 ያለህበትን ሁኔታ ቀይረህ ከእኛ ጋር በትርፍ ጊዜህ አዲስ የቢዝነስ ታሪክ ለመጻፍ ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦👉 @RadiantEphrem

💡 "አንተ ማሰብ የምትችለውን ያህል አእምሮህ የመፍጠር አቅም አለው።"ጀምስ አለን (As a Man Thinketh) አእምሮህ በትክክል እንደ ለም መሬት ነው። በዚያ መሬት ላይ የምትዘራው ሀሳብ (በጎም ሆነ ክፉ) በጊዜ ሂደት ፍሬ ማፍራቱ አይቀሬ ነው! ብዙ ጊዜ በህይወታችን የምናየው ውጤት፣ የምንኖረው ህይወት እና የምናገኘው ገቢ በአእምሮአችን ውስጥ ደጋግመን ዘርተን ያሳደግነው ሀሳብ ውጤት ነው። 🌱 3 የእለት ተእለት የአስተሳሰብ ህጎች፦ 1️⃣ የምትዘራውን ሀሳብ መርጥ፦መሬት የዘራህበትን እንጂ ያልዘራህበትን አያበቅልም። አእምሮህ ውስጥ ፍርሃትን፣ መጠራጠርን እና "አልችልም" የሚል ሀሳብ ካበቀልክ፣ ውጤትህም ያው ይሆናል። 2️⃣ የእይታህን ድንበር አስፋ፦ጀምስ አለን እንዳለው፤ አእምሮህ ማሰብ እና መገመት የሚችለውን ያህል የማሳካት አቅም አለው። ትልቅ ማሰብ ስትጀምር፣ አእምሮህ ትላልቅ መፍትሔዎችን ማፍለቅ ይጀምራል። 3️⃣ አስተሳሰብህን በጥበብ ጠብቅ፦አእምሮህ እንዳይበላሽ የሚያዩትን፣ የሚያነቡትን እና የሚሰሙትን ነገሮች በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል። "አንተ የሀሳብህ ውጤት ነህ፤ ዛሬ የምታስበው ነገር ነገ የምትሆነውን ይወስናል!" 💬 የዛሬው ጥያቄ፦ዛሬ አእምሮህ ውስጥ የዘራኸው አዎንታዊ ሀሳብ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇 🚀 የአስተሳሰብ አቅምህን የሚገነቡ እና አእምሮህን የሚያንጹ ትምህርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉 @The_powerOfthought 📥 ከእኛ ጋር በአስተሳሰብ እና በፋይናንስ አብረው ማደግ የሚፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩን፦👉 @RadiantEphrem

በማንኛውም ዘርፍ 3 አይነት ሰዎች አሉ

📚 ከ "Think and Grow Rich" የተወሰደ ታላቅ ትምህርት — ሀሳብን ወደ ቁስ የሚቀይሩት 2 ቁልፎች! ናፖሊዮን ሂል ከ500 በላይ የሚሆኑ በዓለማችን እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን (እንደ ቶማስ ኤዲሰን፣ ሄንሪ ፎርድ ያሉ) ለአስርተ ዓመታት ካጠና በኋላ ያረጋገጠው አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ "ማንኛውም በአእምሮህ ውስጥ ያለ ሀሳብ፣ ህልም ወይም ግብ ወደ ተጨባጭ ሀብትና ስኬት የሚቀየረው በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ነው!" 1️⃣ ጠንካራ(የሚነድ) ፍላጎት (Definite Burning Desire) ዝም ብሎ "ስኬታማ ብሆን ደስ ይለኛል" ወይም "ሀብታም ብሆን ደስ ይለኛል" የሚል ተራ ምኞት (Wish) ስኬትን አያመጣም። ናፖሊዮን ሂል እንደሚለው፤ የስኬት መነሻ የሚነድና ወደ ኋላ መመለስን የሚያጠፋ ፍላጎት ነው። መርከብህን አቃጥለህ ወደ ፊት ብቻ ለመጓዝ ስትወስን አእምሮህ መንገዱን መፈለግ ይጀምራል። ግብህ በየቀኑ የምታስበው፣ የሚያነሳሳህ እና የምትኖርለት ሊሆን ይገባል! 2️⃣ ጽናት (Persistence) በአብዛኛው ሰዎች እና ህልሞቻቸው መካከል ያለው ልዩነት ጽናት ነው። አብዛኛው ሰው የመጀመሪያው እንቅፋት ሲገጥመው ይተዋል። ጽናት ማለት ውድቀት፣ ተስፋ መቁረጥ እና የሰዎች ትችት ሲመጣ እንኳን ወደ ፊት የመጓዝ የአእምሮ ሁኔታ (State of Mind) ነው። ጽናት ከሌለህ ገና ጉዞ ሳትጀምር ትቆማለህ፤ ጽናት ካለህ ግን ውድቀት ሁሉ ለመማር ደረጃህ ይሆናል! 💡 የዛሬው ማጠቃለያ፦ህልምህ ወይም ግብህ ምንም ያህል ትልቅ ቢሆን፣ የሚነድ ፍላጎት ካለህ እና በጽናት ከተጓዝክ የማታሳካው ነገር የለም። ሀሳብህ ወደ እውነታ የሚቀየረው ባንተ ቁርጠኝነት ነው! 💬 የዛሬው ጥያቄ፦በህይወትህ በጽናት በመታገል ያሳካኸው ትልቁ ግብህ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇 🚀 የፋይናንስ አስተሳሰብህን እና አቅምህን የሚገነቡ ጥበቦችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉 @The_powerOfthought ለሌሎችም እንዲደርስ  ያጋሩ

💡" የምትሰራው ስራ ደሞዝ የሚከፍልህ ለመኖር ሲሆን፣ በትርፍ ጊዜህ የምትገነባው ቢዝነስ ግን ሀብታም ያደርግሃል!" ጂም ሮን (Jim Rohn) ብዙዎቻችን የቀን ስራችንን (Job) ጨርሰን ወደ ቤት ስንመለስ ቀኑ እንደተጠናቀቀ እናስባለን። ነገር ግን እውነተኛው የፋይናንስ ለውጥ የሚጀመረው ከቀን ስራ መልስ ባሉት ከምሽቱ 12:00 እስከ ማታ 4:00 ባሉት ሰዓታት ውስጥ ነው! ለእለት ተእለት ወጪህ፣ ለቤት ኪራይና ለምግብ የሚሆን ገቢ ከቀን ስራህ ታገኛለህ። ነገር ግን የነፃነትህ እና የሀብትህ መሰረት የሚጣለው ከስራ ሰዓት ውጭ በትርፍ ጊዜህ በሚታገዝ ጥረትህ ነው! 📌 በቀን 2 ሰዓት ብቻ በትርፍ ጊዜህ ብትጠቀም፦ 🤜በሳምንት 14 ሰዓት ያህል ታገኛለህ 🤜በወር ከ 50 ሰዓት በላይ አዲስ ክህሎት እና ቢዝነስ ለመገንባት የሚያስችል ጊዜ ይኖርሃል ጊዜ የለኝም ብለህ አታስብ፤ ሁላችንም የተሰጠችን 24 ሰዓት እኩል ነው። ልዩነቱ ጊዜያችንን በምን ላይ እንደምናውለው ነው! 💬 የዛሬው ጥያቄ፦ ከስራ ወይም ከትምህርት መልስ ያለውን ትርፍ ጊዜ ለምን ታውለዋለህ? ከታች መልዕክት መላክያ ላይ አጋራኝ!

📖 የ 4-Minute Mile ታሪክ የሰው ልጅ ገደብ አእምሮው ውስጥ ነው! እ.ኤ.አ ከ1954 በፊት በስፖርቱ ዓለም አንድ የጠነከረ እምነት ነበረ፦ አንድ ሰው 1 ማይል (1.6 ኪሎ ሜትር) ከ4 ደቂቃ በታች ሊሮጥ አይችልም፤ ቢሞክር እንኳ ልቡ ፈንድቶ ይሞታል! የሚል ነው   እንዲሁም የህክምና ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞች እና ሳይንቲስቶች ይህንን ማድረግ በፊዚዮሎጂ ደረጃ ለአካላችን በፍጹም አይቻልም ብለው ደምድመውት ነበር። ነገር ግን ግንቦት 6 ቀን 1954 ዓ.ም ሮጀር ባኒስተር (Roger Bannister) የተባለ ወጣት አትሌት የሁሉንም አስተሳሰብ ገለበጠው። 1 ማይልን በ 3 ደቂቃ ከ59.4 ሰከንድ በመሮጥ ታሪክ ሰራ!💡 ነገር ግን ከታሪኩ ትልቁና አስደናቂው ክፍል አሁን የሚመጣው ባኒስተር ይህንን ታሪክ ከሰራ በኋላ ምን የተከሰተ ይመስላችኋል? ለሺህ ዓመታት  ከ4 ደቂቃ በታች ሊሮጥ አይቻልም ተብሎ የቆረው ክብረ ወሰን ሲሰበር፣ በዚያው ዓመት ውስጥ ሌላ ሁለተኛ ሰው ያንን ክብረ ወሰን ድጋሜ ሰበረው! በቀጣዮቹ 3 ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ16 በላይ አትሌቶች 1 ማይልን ከ4 ደቂቃ በታች ሮጡ። ምን ተቀየረ? የሰዎች የአካል ብቃት ወይም የሰውነት መዋቅር? በአንድ ጀምበር አልተቀየረም። የተቀየረው ይቻላል የሚለው እምነት (Belief) ብቻ ነው! ባኒስተር «አይቻልም» የሚለውን የአእምሮ አጥር ስለሰበረው፣ የሌሎች ሰዎች አእምሮም ነገሩን እንደ እውነት ተቀብሎ ተግባራዊ አደረገው ተቻለም። 🧠 የዛሬው የህይወት ትምህርት፦በህይወታችን፣ በስራ ወይም በቢዝነስ ውስጥ "ይህ ለእኔ አይሆንም""ይህንን ማድረግ አልችልም" ወይም "በእኛ ሀገር አይሰራም" ብለህ ያጠርናቸው የአእምሮ አጥሮች አሉ? አብዛኞቹ እንቅፋቶች ሰውነታችን ወይም አቅማችን ላይ ያሉ ሳይሆኑ በአእምሮአችን ውስጥ የገነባናቸው ምናባዊ ድንበሮች ናቸው።  አእምሮህ «ይቻላል» ብሎ ሲያምን፣ አካልህ መንገዱን ያገኛል! 💬 የዛሬው ጥያቄ፦በህይወትህ «አይቻልም» ብለህ አምነህ አሁን ግን አድርገኸው ያስደነቀህ ነገር ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋሩኝ! 👇🚀 የአስተሳሰብ አቅምን በመገንባት የማይቻሉ የሚመሰሉ ነገሮችን ወደ እውነት ለመቀየር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @The_powerOfthought

🧠 Reticular Activating System (RAS) አእምሮህ የሚያየውን አንተ ታያለህ! አንድ አዲስ ስልክ ወይም ሌላ ነገር ለመግዛት አስበህ ታውቃለህ? ያንን ስልክ ወይም እቃ ካወክበት ቀን ጀምሮ መንገድ ላይ በሄድክበት ቦታ ሁሉ በፖስተር ላይ ተለጥፎ ወይም ሶሻል ሚዲያ ላይ ይሁን ሰዎች ላይ ጭምር ያንን ስልክ ወይም ለመግዛት ያሰብከውን ነገር ደጋግመህ ታየዋለህ ።ለመሆኑ እሄ ስልክ ድንገት ነው የበዛው? ወይስ አእምሮህ ማየት የጀመረው ያንን ብቻ ስለሆነ ነው ነው? አንጎላችን ውስጥ RAS (Reticular Activating System) የሚባል ልዩ የማጣሪያ መዋቅር (Filter) አለ። አእምሮህ በቀን የሚያስተናግዳቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መረጃዎች አጣርቶ አንተ ትኩረት ያደረክበትን ብቻ ነጥሎ በብዛት እንዲታይህ ያደርጋል። 💡 ይህ በአስተሳሰብህ ላይ ያለው ትርጉም ምንድን ነው? 👉በችግር እና በእንቅፋት ላይ ካተኮርክ፦ አእምሮህ (RAS) በየቦታው ምክንያት፣ እንቅፋት እና "አይቻልም" የሚሉ ማረጋገጫዎችን ብቻ ነጥሎ ያሳይሃል። 👉በመፍትሔ እና በእድሎች ላይ ካተኮርክ፦ አእምሮህ ከዚህ በፊት ያልተመለከትካቸውን በርካታ አዳዲስ መንገዶች፣ የስራ እድሎች እና አዎንታዊ ሰዎችን መመልከት ይጀምራል።"ዓለም የምትታይህ እንዳመጣጧ ሳይሆን እንደ አስተሳሰብህ መነጽር ነው!"ዛሬ አእምሮህን በምን አይነት መረጃ እና ሀሳብ እየመገብከው ነው? ትኩረትህን ወደ መፍትሔ እና ወደ እድሎች አዙር፤ አእምሮህ መንገዱን ያሳይሃል! 💬 የዛሬው ጥያቄ፦ዛሬ ውሎእችሁ ውስጥ ያተኮራችሁበትና ያያችሁት መልካም ነገር ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋሩን! ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉 @The_PowerOfThought 📥 ከእኛ ጋር በአስተሳሰብ እና በፋይናንስ አብረው ማደግ ለሚፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩን፦👉 [ @RadiantEphrem ]

ትላንት ባቀረብነው መጠይቅ (Poll) ላይ በርካቶቻችሁ ድምፅ ሰጥታችኋል። 🔹 "ሀ" ወይም "ሐ"ን ለመረጣችሁ፦ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ “ለእኔ አይሆንም” ወይም “ቀድሜ አውቅ ነበር” ብሎ ማሰብ የአእምሮአችን Self-Defense Mechanism (የመከላከያ መንገድ) ነው። አእምሮህ ተጨማሪ ህመም እንዳይሰማው ሲል ነገሩን ቀድሞ ለመቀበል ይሞክራል። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ አዳዲስ እድሎችን እንዳታይ በር ይዘጋብሃል እንዲሁም ካጋጠመን ነገር እንዳንማር ያደርገናል 🔹 "ለ"ን ለመረጣችሁ፦ ይህ Growth Mindset / የእድገት አስተሳሰብ/ ይባላል። ስኬታማ ሰዎች ከሌሎች የሚለዩበት ትልቁ ምስጢር ውድቀት ስለማያጋጥማቸው ሳይሆን፣ ከውድቀት በፍጥነት ትምህርት ወስደው ወደፊት ስለሚራመዱ ነው።💡 ማወቅ ያለብን ነገር ሁኔታዎችን መቀየር ባንችል እንኳን፣ ለሁኔታዎቹ የምትሰጠውን ምላሽ (Response) የመምረጥ ሙሉ አቅም አለን!💬 በቀጣይ አስተሳሰብህን በመቀየር ህይወትህንና ገቢህን የምታሳድግበትን መንገድ ማወቅ ትፈልጋለህ? በውስጥ መስመር @RadiantEphrem ብላችሁ አናግሩኝ። ይቀላቀሉን @the_powerOfthought

ችግር ሲያጋጥማችሁ የመጀመሪያ ሀሳባችሁ ምንድን ነው? በተለይ ደግሞ ያሰባችሁት ነገር እናንተ በፈለጋችሁት መንገድ ሳይሄድ ሲቀር
Anonymous voting

ወሳኝ ፀሎት! ፈጣሪ ሆይ 'መቀየር የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል እርዳኝ፤ መቀየር የምችላቸውን እንድቀይር ድፍረቱን ስጠኝ ከሁሉ በፊት ግን ሁለቱን መለየት እንድችል ማስተዋሉን ስጠኝ።'  እርካታ የሞላው ህይወት ለመኖር ወሳኝ ፀሎት ነው። መልካም ቀን http://t.me/The_PowerOfThought

የራስ መንገድ! ሁልጊዜም የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም፤ መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ። አየህ በህይወት ውስጥም የሚገጥሙህን ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች፣ አስቸጋሪ የሰው ፀባዮችን ሁሉ መቆጣጠር አትችልም፤ ያንተን ህይወት ግን እንዲወስኑት አለመፍቀድ ያንተ ምርጫ ነው ምክንያቱም የመርከብህ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ! መልካም ቀን http://t.me/The_PowerOfThought

❌ በህይወት ውስጥ ትልቁ ውድቀት ስህተት መስራት ሳይሆን፣ ስህተት እሰራለሁ ብሎ በመፍራት ምንም ሳይሰሩ መቅረት ነው። 🧗‍♂️ እያንዳንዱ ውድቀት ወደ ስኬት የሚወስድህ ደረጃ ነው። ከተሳሳትክ አዲስ ነገር ተምረሃል ማለት ነው፤ ካልተሳሳትክ ግን ምንም አዲስ ነገር አልሞከርክም ማለት ነው። 🔥 ዛሬ ማክሰኞ፣ ስህተትን አትፍራ፤ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር ድፍረቱ ይኑርህ! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

🔥 አዲስ ሳምንት መጥቷል! ላለፉት ቀናት ስለ አስተሳሰብ ኃይልና ስለ ማይንድሴት ለውጥ ስናወራ ቆይተናል። አሁን ግን ዋናው ደረጃ ላይ ደርሰናል—እሱም "ተግባር" ነው! 🏃‍♂️ ⚙️ ምርጥ አስተሳሰብ ኖሮህ በተግባር ካልደገፍከው ምንም ዋጋ የለውም። ሀሳብ መነሻ ነው፣ መዳረሻህ ግን በምታደርገው ዕለታዊ ተግባር ይወሰናል! 🚀 ዛሬ ሰኞ፣ ካሰብከው ታላቅ ሀሳብ ጀርባ ትልቅ ተግባር አስከትልና ጉዞህን ጀምር! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

የረፍት ቀን ቁልፍ ጥያቄ፡ "በህይወትህ ውስጥ ሾፌሩ ማነው? አንተ ወይስ ስሜትህ?" 🏎️ ስኬታማ ሰዎች ስሜታቸው ስለፈለገ ብቻ ሳይሆን፣ ማድረግ ስላለባቸው ስራውን ይሰራሉ። ፍላጎት ወይም ስሜት እስኪመጣ ከጠበቅክ ስራህን ፈጽሞ አትጀምረውም! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

👥 አካባቢያችን እና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በአስተሳሰባችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አላቸው። "ጓደኞችህን አሳየኝና የወደፊት ህይወትህን እነግርሃለሁ" እንደሚባለው። 🔍 ዛሬ ቅዳሜ፣ ቆም ብለህ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች አስተውል። የሚያበረታቱህና የሚያሳድጉህ ናቸው ወይስ ተስፋ የሚያስቆርጡህ? 🦅 ከፍ ለማለት ከፈለግክ፣ አንተ ወደምትፈልገው ከፍታ ከሚመሩህ ንቁ ሰዎች ጋር ተቀላቀል! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

🗣️ ሰዎች ስለ አንተ የሚያስቡት ወይም የሚናገሩት ነገር የአንተን ማንነት አይገልፅም። የአንተን ዋጋ የሚወስነው አንተ ለራስህ የምትሰጠው ክብርና ግምት ነው! 🛡️ አእምሮህ በሰዎች ትችትና አሉታዊ ወሬ እንዳይሞላ በጥንቃቄ ጠብቀው። አንተ የተሰጠህ ታላቅና ልዩ አቅም አለህ። 👑 ዛሬ አርብ፣ የውጭውን ጩኸት ቀንሰህ የውስጥህን ታላቅ አቅም የምታዳምጥበት ቀን ይሁን! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

ጄምስ ክሊር (James Clear) "Atomic Habits" በተባለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-
📈 "በየቀኑ በ 1% ብቻ ራስህን ካሻሻልክ፣ በአንድ አመት ውስጥ 37 እጥፍ የተሻልክ ሰው ትሆናለህ።"
🚶‍♂️ ትልቅ ለውጥ በአንዴ አይመጣም። ዛሬ ሀሙስ፣ ትልቁን ግብህን ትናንሽ ቦታዎች ላይ ከፋፍለውና የአንዱን ቀን ስራ ብቻ በብቃት ለመጨረስ አስብ። 🏆 ትናንሽ ዕለታዊ ድሎች በሂደት ትልቅ ተራራ ይሆናሉ! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

🧲 አስተሳሰብህ ልክ እንደ ማግኔት ነው! በውስጥህ የምታስበውንና በፅኑ የምታምነውን ነገር ወደ ህይወትህ ትስባለህ። 📉 ሁልጊዜ ስለ እጥረት፣ ስለ ችግር እና ስለ ውድቀት የምታስብ ከሆነ፣ በዙሪያህ የሚታዩህ እነሱ ብቻ ይሆናሉ። ነገር ግን ስለ መፍትሄ፣ ስለ ዕድገትና ስለ ስኬት ማሰብ ስትጀምር 📈፣ ከዚህ በፊት ያላየሃቸው በርካታ አዳዲስ ዕድሎች በፊቱህ ይከፈታሉ! 💡 ዛሬ ረቡዕ፣ በትኩረትህ ላይ ስራ። ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሄው ላይ አተኩር! አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

ታላቁ የስኬት መሪ ጂም ሮን (Jim Rohn) እንዲህ ይላል፡-
📜 "ህይወትህ በአጋጣሚ ሳይሆን፣ በምታደርገው ለውጥ ነው የሚሻሻለው።"
🔄 ትናንት ካሰብከው በተለየ መንገድ ዛሬ ካላሰብክ፣ ነገም ልክ እንደ ዛሬው ነው የሚሆነው። ስኬት በድንገት የሚመጣ የሎተሪ ዕድል አይደለም፤ 🎯 በየቀኑ የምታደርጋቸው ጥቃቅን የአስተሳሰብ እና የተግባር ለውጦች ውጤት ነው። 🌱 ዛሬ ማክሰኞ አንድ ትንሽ አዎንታዊ ልምድ በህይወትህ ላይ ጨምር። አንድ ገፅ መጽሐፍ አንብብ 📚፣ ወይም ለአንድ ሰው መልካም ነገር አድርግ። አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought

አዲስ ሳምንት፣ አዲስ ሀይል! ብዙ ጊዜ አዲስ ህይወት ለመጀመር አዲስ አመት ወይም አዲስ ምዕራፍ እንጠብቃለን። ነገር ግን እውነታው አዲስ ህይወት የሚጀምረው አዲስ ውሳኔ እና አዲስ አስተሳሰብ በወሰንንበት ቅፅበት ነው። ዛሬ ሰኞ ጠዋት ስራ ስትጀምር ለአፍታ ቆም በልና አስብ፤ ያቀድከውን ነገር እንዳታሳካ የሚከለክልህ ውጫዊው ፈተና ነው ወይስ በውስጥህ የሚመላለሰው "አልችልም" የሚል ድምፅ? አእምሮህ ሊረዳህም ሊጎዳህም ይችላል—ምርጫው ግን የአንተ ነው። ዛሬ ቀኑን ስትጀምር አሸናፊ እንደሆንክ ለአእምሮህ ንገረው። አስብ። እደግ። ስኬታማ ሁን። 🚀 t.me/The_PowerOfThought