The Power of Thought
Open in Telegram
ሀሳቦቻችን እጣፈንታችንን ይወስናሉ። Transform Your Thinking. Transform Your Life. Think. Grow. Succeed. Contact us @RadiantEphrem
Show more456
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
💡የአይቻልም እስረኛ
🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀
⛓ልጁ በእንስሳት ማቆያው (Zoo) ሲያልፍ ትልቁ ፍጥረት ዝሆን በግን በምታስር ቀጭን ገመድ እግሩን ታስሮ ሲመለከት “በእሱ ጉልበት እንዴት ይችን ገመድ በጥሶ ወደ አሻው ቦታ አይሄድም? ለምን እራሱን ነፃ አያወጣም ?” እያለ ሲገረም በአቅራቢያው የተመለከተውን የዝሆኑን ባለቤት አግራሞት ስለፈጠረበት ክስተት ጠየቀው፡፡ የዝሆኑ ጌታም እንዲህ መለሰለት፡፡
⛓“ዝሆኑ ገና በልጅነቱ ምንም አቅም ሳይኖረው ለማሰር የምንጠቀምበት ገመድ ይችው አሁንም የታሰረባት ገመድ ነች፡፡ በልጅነቱ ገመዷን በጥሶ ለመሄድ ቢሞክርም አቅሙ ስለልፈቀለደት አልቻለም፡፡ እያደጎ ሂዶም አሁን በምታየው ደረጃ ቢደርስም ገመዷን መበጠስ እደማይችል እምነት አሳድሯልና ገመዷን መበጠስ የሚስችል አቅም እንደሌለው አምኖ ተቀብሏል፡፡ ምክንያቱም የበፊቱ ማቃት ተቀርጾበት ቀርቷልና ነው፡፡”
⛓ስንቶቻችንስ በሕይወት ጎዳና ከዚህ በፊት ስላቃተን ብቻ እንደዝሆኑ የልማድ እስረኛ ሁነን ልንስራው አንችልም ብለን እራሳችንን በአይቻልም መንፈስ የሸበብንባቸው ስንት ጉዳዮች ይኖሩን? እናም የትላንት ውድቀታችን የነገ ህልማችንን ጥላ እንዲያጠላበት አንፍቀድለት፡፡
🚀 ጠቃሚ ሆኖ ካገኘኸው ለምትወዳቸው ሼር አድርጋቸው
@The_PowerOfThought
📥 አስተሳሰብህን ከሚገነቡ እና በትርፍ ጊዜያቸው አዲስ የገቢ ምንጭ ከሚፈጥሩ ሰዎች ጋር አብረህ መስራት ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦👉 @RadiantEphrem
ጥሩ የሚባለው ጥሩው ብቻ ነው!!
አብዛኞቹ ሰዎች መጥፎና ጥሩ ስሜቶችን ለይተው ያውቃሉ። ይሁንና አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፉት በመጥፎ ስሜት ውስጥ መሆኑን አይረዱትም። ሰዎች መጥፎ ስሜት ማለት ብስጭት ፣ ንዴት ፣ ፍርሐትና ሃዘንን እንጂ አሉታዊ ስሜቶችን በሙሉ የሚያጠቃልል አይመስላቸውም።
አብዛኛውን ጊዜ "ደህና" የሚባለው ስሜት ካጋጠመህ አዎንታዊ ስሜት ላይ ያለህ ሊመስልህ ይችላል። በመጥፎ ስሜት ውስጥ ቆይተህ "ደህና ነኝ" ወደምትልበት ስሜት ከመጣህ በእጅጉ የተሻለ ይሆንልሃል። ነገር ግን የምንም አይልም ስሜት አብዛኛውን ጊዜ የመጥፎ ስሜት መገለጫ ነው። ምክኒያቱም "ምንም አይልም" ከመልካም ስሜት የተለየ ነው። ጥሩ ስሜት ማለት ጥሩ ስሜት ነው። መልካም ስሜት ማለት ደስተኛ፣ በሐሴት የተሞላ፣ የተነቃቃ፣ ትጉህ እና ፅኑ የሆነ ማለት ነው። ስሜትህ የምንም አይልም ፣ መካከለኛ፣ ወይም ስሜት አልባ ከሆነ ሕይወትህም ምንም የማይል፣ መካከለኛ፣ ወይም ትርጉም አልባ ይሆናል። ያ ደግሞ ጥሩ ኑሮ አይደለም። መልካም ስሜት ማለት እውነተኛ መልካም ስሜት ነው። እውነተኛው መልካም ስሜት ካለ ደግሞ ሕይወት በእጅጉ መልካም ይሆናል።
🚀 ጠቃሚ ሆኖ ካገኘኸው ለምትወዳቸው ሼር አድርጋቸው
@The_PowerOfThought
📥 አስተሳሰብህን ከሚገነቡ እና በትርፍ ጊዜያቸው አዲስ የገቢ ምንጭ ከሚፈጥሩ ሰዎች ጋር አብረህ መስራት ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦👉 @RadiantEphrem
ምን ያህሎቻችሁ አንድን ነገር ማድረግ እየቻላችሁ... ማድረግም እየፈለጋችሁ... ነገር ግን በፍርሃት ወይም ሰበብ በማብዛት አራዝማችሁ ታውቃላችሁ? 🙋♂️
አንድን ነገር ለማድረግ ስታስቡ አእምሯችሁ ሰበብ ማደራደር ሳይጀምር አሁኑኑ እርምጃ ለመውሰድ የ 5 ሰከንድ ህግ (5-Second Rule) ተጠቀሙ!
ህጉ በጣም ቀላል ነው፦ አንድ ነገር የማድረግ ሀሳብ ሲመጣልህ አእምሮህ እንዲያወላውል እድል ሳትሰጠው 5 - 4 - 3 - 2 - 1 ብለህ ወደ ኋላ ቁጠርና ወዲያውኑ እርምጃ ውሰድ!
ጠዋት ከአልጋ ለመነሳት፦ 5-4-3-2-1 ... ቀጥ ብለህ ተነሳ!
አዲስ ሰው ለማናገር፦ 5-4-3-2-1 ... ሰላም በለው!
ስክሮል ማድረግ አቁመህ ወደ ስራ ለመግባት፦ 5-4-3-2-1 ... ስልኩን አስቀምጠህ ስራህን ጀምር!
አእምሮህ ፍርሃትና ሰበብ እንዲፈጥርብህ አትፍቀድለት፤ ቆጠራውን ጀምርና እርምጃ ውሰድ! 🚀
💬 የዛሬው ጥያቄ፦አሁን ላይ ለማድረግ አራዝመህ በ '5-Second Rule' አሁኑኑ ልትጀምረው የወሰንከው ስራ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇
🚀 ጠቃሚ ሆኖ ካገኘኸው ለምትወዳቸው ሼር አድርጋቸው
@The_PowerOfThought
📥 አስተሳሰብህን ከሚገነቡ እና በትርፍ ጊዜያቸው አዲስ የገቢ ምንጭ ከሚፈጥሩ ሰዎች ጋር አብረህ መስራት ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦👉 @RadiantEphrem
Cashflow Quadrant — ገንዘብ የምታገኝበት አራት አቅጣጫዎች
በፋይናንስ ዓለም ውስጥ እጅግ ታዋቂው ፀሐፊ ሮበርት ኪዮሳኪ ሰዎችን ገንዘብ በሚያገኙበት መንገድ በ 4 አቅጣጫዎች (Quadrants) ይከፍላቸዋል።
በዓለማችን ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ በነዚህ 4 አቅጣጫዎች ውስጥ ይገኛሉ፦
1️⃣ E - Employee (ተቀጣሪ)
የስራ መንገድ፦ጊዜህንና ጉልበትህን በደሞዝ ትለውጣለህ።
አስተሳሰብ፦ዋስትና ያለውና ደሞዝ የሚያስገኝ ቋሚ ስራ እፈልጋለሁ።
በቀን የምትሰራበት ሰዓት የተገደበ ስለሆነ የወሩ መጨረሻ ላይ የተወሰነ(Fixed income) ነው የምታገኘው።
2️⃣ S - Self-Employed (የግል ስራ / አነስተኛ ባለሙያ)
የስራ መንገድ፦የራስህ ስራ አለህ፤ ነገር ግን ስራውን የምትሰራው አንተ ነህ (ዶክተሮች፣ ጠበቆች፣ አነስተኛ ሱቅ ያላቸው...)።
አስተሳሰብ፦ከእኔ የተሻለ የሚሰራው ስለሌለ ራሴ መስራት አለብኝ።
Time flexibility ቢኖርም አንተ ስራ ካልገባህ /ከስራ ከቀረህ ገቢህ ይቆማል
3️⃣ B - Business Owner (የቢዝነስ ባለቤት /ሲስተም የሚገነቡ)
የስራ መንገድ፦ ሰዎችና ስርዓት (System) ለአንተ እንዲሰሩ ታደርጋለህ። አንተ ሲስተም ትገነባለህ ሲስተሙ ገቢ ያስገኝልሀል።
አስተሳሰብ፦ከእኔ የበለጠ ጎበዝ ሰዎችንና በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ስርዓት እፈልጋለሁ።
ስኬት፦አንተ በቦታው ባትኖርም ቢዝነስህ ገንዘብ ማስገበቱን ይቀጥላል!
4️⃣ I - Investor (ኢንቨስተር)
የስራ መንገድ፦ገንዘብህ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያመጣልህ ታደርጋለህ (አክሲዮኖች፣ ንብረቶች ሌሎች ነገሮች ላይ ኢንቨስተ በማድረግ.)።
አስተሳሰብ፦ ገንዘቤ እንዴት ይስራችልኝ? ገንዘቤን ምን ላይ ኢንቨስት ላድርግ?
ስኬት፦ እውነተኛ የፋይናንስና የጊዜ ነፃነት የምታገኝበት ቦታ ነው።
Hard truth :-በዓለማችን 95% የሚሆነው ህዝብ በ E እና S ስር የሚገኙ ሲሆን እነዚህ 95% ህዝብ ግን የዓለምን ሀብት 5% ብቻ ነው ያላቸው።
በአንፃሩ 5% የሚሆነው ህዝብ በ B እና I ስር የሚገኙ ሲሆን፣ 95% የሚሆነውን የዓለም ሀብት ይቆጣጠራል!
🧠 የት መሆን ትፈልጋለህ?
ከቀኝ ወደ ግራ (ከ E እና S ወደ B እና I) የመሸጋገር ምስጢር የካፒታል ማነስ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset Shift) ነው! በትርፍ ጊዜህ ስርዓት (System) ያለው ቢዝነስ መገንባት ስትጀምር ወደ B አቅጣጫ መሸጋገር ትጀምራለህ።
❓አሁን ላይ ያለኸው በየትኛው አቅጣጫ (E, S, B, I) ውስጥ ነው? ወደ የትኛውስ ለመሸጋገር ታቅዳለህ? ከታች በኮሜንት አጋራን!
@The_PowerOfThought
📥 ከ E እና S አቅጣጫ ወጥተህ በትርፍ ጊዜህ የራስህን ቢዝነስና ስርዓት (Business System) መገንባት ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦
👉 @RadiantEphrem
---
🤔 አካባቢህ አንተን እየገነባህ ነው ወይስ እየገደለው?
🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀
በስነ-ልቦና ዓለም ውስጥ እጅግ የታወቀና አንድ እውነት አለ "አንተ አብረሃቸው ብዙ ጊዜ የምታሳልፋቸው የ 5 ሰዎች አማካይ ውጤት ነህ" የሚል ነው።
አብዛኞቻችን አላማችን ትልቅ ነው፤ ስኬታማ መሆን፣ የገንዘብ ነፃነት ማግኘት እና የተሻለ ህይወት መኖር እንፈልጋለን። ነገር ግን በየቀኑ የምናሳልፈው ጊዜ፣ የምንሰማቸው ንግግሮች እና አብረን ጊዜ የምናሳልፋቸው ሰዎች ወደ ፊት የሚገፉን ሳይሆን ወደ ኋላ የሚጎትቱን ናቸው ለዚህም ነው ባለንበትየምንቆየው።
❓ እስኪ ቆም ብላችሁ አነዚህን 3 ጥያቄዎች እራሳችሁን ጠይቁ
1️⃣ አብሬ ጊዜ የማሳልፋቸውን ሰዎች ስለ ምን ያወራሉ?
አብዛኛውን ጊዜ የሚያወሩት ስለ ሌሎች ሰዎች ስህተት ወይም ሐሜት፣ ስለ ችግርና ስለ አገሪቱ ሁኔታ ችግር በየጊዜ የሚያወሩ ... ወይስ ስለ አዳዲስ ቢዝነሶች፣ መጻሕፍትና ህልሞች?
2️⃣ አዲስ ሀሳብ ስታነሳ ምላሻቸው ምንድን ነው?
አይሆንም፣ አትልፋ፣ ሰዎች ሞክረው አቅቷቸዋል ብለው ፍላጎትህን ያጠፉታል... ወይስ እንዴት ሊሳካ እንደሚችል ደጋፊ ሀሳብ ይሰጡሀል ያበረታቱሃል?
3️⃣ ከእነሱ ጋር ካሳለፍክ በኋላ ምን ይሰማሃል?
የደካማነት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይሰማሃል... ወይስ የመስራት እና የመለወጥ የመነቃቃት ፣ የመጀመር ስሜት ይሰማሀል?
አካባቢህ አስተሳሰብህን እየገደለው ከሆነ ሁለት አማራጮች አሉህ፦ አካባቢህን መቀየር ወይም የምትቀላቀላቸውን ሰዎች መቀየር!
ስኬታማ መሆን ከፈለግክ ከአንተ በላይ የሚያስቡ፣ ትልቅ ራዕይ ያላቸው እና ለውጥን የማይፈሩ ሰዎችን ፈልገህ ተቀላቀል። በአካል ማግኘት ባትችል እንኳን በኦንላይን እነሱን ተከታተል ጓደኛ አድርጋቸው።
ንስር ለመሆን ከዶሮዎች ጋር መዋል አቁም!
🚀 ጠቃሚ ሆኖ ካገኘኸው ለምትወዳቸው ሼር አድርጋቸው
@The_PowerOfThought
📥 አስተሳሰብህን ከሚገነቡ እና በትርፍ ጊዜያቸው አዲስ የገቢ ምንጭ ከሚፈጥሩ ሰዎች ጋር አብረህ መስራት ከፈለግክ በውስጥ መስመር አናግረን፦👉 @RadiantEphrem
ከችግሮቼ እንዴት ልውጣ?
🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀
እለት እለት ከዛሬ ጀምረህ
1. በሀሳብህ
2. በተግባር
3. በቃልህ
የምትፈልገው ላይ ብቻ አተኩር
በሀሳብህ
የምትፈልገውን ውጤት አሰላስል: ጠይቅ: በምናብህ ውጤቱን አግኝተህ እና ሆኖልህ እይ:
በተግባር:
ስለምትፈልገው ውጤት የሚያውቁ ሰዎች ጋር ዋል: የውጤትህን መንገድ የሚያሳዩህን ሚድያዎች ብቻ ተከታተል: የምትፈልገውን ውጤት እንዴት እንደምታገኝ የሚያሳዩህን መፅሀፎች አንብብ:: በየቀኑ በነፃም ቢሆን የምትፈልገው ነገር ላይ የሚያደርስህን ስራ በፍቅር ከልብህ ስራ:: ችግርን በህሊናህ እያውጠነጠንክ ለመሸከም ፈቃደኛ አትሁን::
በቃልህ
ዘወትር ፍላጎትህን ተናገር: ስለሆነው ነገር ሳይሆን እንዲሆንልህ ስለምትፈልገው ነገር ብቻ ብዝርዝር አውራ: ፃፍ:
በቃ እነዚህን በየቀኑ በማድረግ አዋዋልህን ማታ ማታ አጢን እና ለነገ የሚስተካከለውን አስብና አርመው::
ማታ ከመተኛትህ በፊት ለሀያ ደቂቃ አልጋህ ላይ ሆነህ መሻቶችህ ተሳክተው የምትኖረውን ህይወት በምናብህ በዝርዝር እንደ ፊልም ተመልከተው::
ጠዋት እንደነቃህም ይህንኑ አድርግ:: አንተ በፈቃድህ ይህንን ስትደርግ ህሊናህ በልምድ ወደችግር ሀሳብ ይወስድሀል:: ያኔ በፈቃድህ ህሊናህን ወደ መሻቶችህ ሀሳብ ውሰደው:: በቃ ይህ ማለት ህሊናን መግራት ማለት ነው:: ይህንን በድግግሞሽ ስታደርገው ለብዙዎች በሚድያ ጭምር የምታስተምርበትን ተአምራዊ ውጤት ታገኝለህ::
ሰው በምድር ላይ የአስተሳሰቡ ውጤት ነው:: አንድ ቀን የስኬት ታሪክህን ለህዝብ ስታቀርብ አይሀለሁ::
👇👇👇
@The_PowerOfThought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ከጠቀመህ ለጎደኛህ አጋራው
አስተሳሰብን መቆጣጠር
አስተሳሰብን መቆጣጠር ማለት ወደ እኔ የሚመጣውን ወይም በውስጤ የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ወፍጮ” በመሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡
ጤና ቢስ አመለካከቶችን ለማስወጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. በሕይወትህ የምታሰላስላቸውን ሃሳቦች ለይተህ እወቅ፡፡
ለማንነትህና ለሕይወትህ አላማ የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህንን ለይተህ ስታውቅ በሃሳቦች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብህ ጥርት ባለ መልኩ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡
2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አታስተናግዳቸው፡፡
የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሮህ ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለጤናማ አመለካከትህና ላስቀመጥከው የሕይወት ከፍታና ደረጃ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ ተቃወመው፡፡ ይህንንም ልምምድ የዘወትር አድረገው፡፡
3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማ አስተሳሰብ ቀይር፡፡
ከዚህ በፊት በውስጥህ ያስተናገድካቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር አለብህ፡፡ ከአእምሮህ ክፉውን ሃሳብ አስወጥተህ በጤናማው ካልተካኸው ሌላ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም፡፡
@The_PowerOfThought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ከጠቀመህ ለጎደኛህ አጋራው
🚀ከዶሮ መካከል የወደቀ ወፍ አትሁን🚀
🔹ከእለታት አንድ ቀን ምድር የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰባት፤ መንቀጠቀጡ መሬት ላይ ያለውን ሁሉ ማነቃነቁ አይቀርምና ሁሉም ተናወጠ። በወቅቱ ከዛፍ ላይ አንድ የወፍ ጎጆ ነበረች፤ ይህች የወፍ ጎጆ በውስጧ እንቁላሎችን ይዛ ነበር። መሬቱ ሲንቀጠቀጥ ግን እንቁላሎቹን ይዛ ከነበረችው ጎጆ ውስጥ አንዱ እንቁላል ከዶሮዎች መንደር ወደቀ።
ዶሮዎቹ እንቁላሉን እንደ እራሳቸው እንቁላል ተንከባክበውና ታቅፈው እንዲፈለፈል አደረጉት። ወፉ እንደ ዶሮ ከዶሮዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ማደግ ጀመረ። እነሱኑ መስሎ ዶሮነቱን አምኖ ኑሮውን መግፋቱን ቀጠለ። ከእለታት አንድ ቀን ከዶሮ ቤተሰቦቹ ጋር አንድ ላይ ሆነው በመሬት ሲንሸራሸሩ ወፎች በሰማይ ሲበሩ ተመለከቱ። ይሄኔ ወፉ “ እኒህ በሰማይ በነፃነት የሚበሩት ወፎች ምነኛ የታደሉ ናቸው ፤ ምናለ እኔም እንደነሱ መብረር ብችል “ ሲል እራሱን እየተመለከተ ተናገረ። አብሮ አደጎቹ ዶሮዎች በወፉ ተሳለቁበት “ አንተ እኮ ዶሮ ነህ እንዴት እንደወፍ ለመብረር ታስባለህ “ ብለው ሃሳቡን አጣጣሉበት። ወፉ ምንም እንኳን መብረር የሚችል ወፍ ቢሆንም እንደ ዶሮ ከዶሮ መሃል ስላደገ ዶሮ ነኝ ብሎ አምኗል። ማንነቱን ለውጦ አቅሙን አሳንሶ እራሱን ሳያውቅ ሌሎች ዶሮዎች በነገሩት ብቻ አለመብበሩን አምኖ ኖረ። ክንፎቹን ታቅፎ ሌሎች ወፎች ሲበሩ እየቀና እድሉን እያማራረ ኖሮ ሞተ። መብረር ተፈጥሮው ሆኖ፤ አልበርም ብሎ በማመኑ ብቻ ወፍ ሆኖ ተወልዶ ዶሮ ሆኖ ምድርን ተሰናበተ።
የዚህ ወፍ ታሪክ የሁላችንም ታሪክ ነው። የምንመኘውን ነገር ለማድረግ ሁሉ ተሰጥቶን እያለ ሉሎች አይቻልም ስላሉን ብቻ፤ አንችልም ብለን በማመን የፈለግነው ኑሮ ሳንኖር እንሞታለን። እንደዛ ምስኪን ወፍ ከሌሎች መሃል ወድቀን ሌለችን እንሆናለን። ማንነታችን ሌሎች እየነገሩን እራሳችንን ሳናውቅ እድሜያችን ይገፋል። አቅማችንን ሌሎች እየለኩት ችሎታችንን እና ተሰጥዖዋችንን ሳንጠቀምበት ህይወታችን ያልፋል።
እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ የወደቅነው ከማን መካከል ነው? ይቻላል ይሳካል ከሚሉት ወይስ አይቻልም አይሳካም ከሚሉት? ወፉ መብረር እየቻለ ከዶሮ መሃል ስላደገ እና ዶሮ ነኝ ብሎ ስላሰበ መብረር ምንም እንኳን ቢመኝ ሳይበር ቀረ። የብዙዎቻችን ህይወት ከዚህ ብዙም አይለይም። ሁሉ ነገር እያለን ሌሎች ሲሞክሩት ስላላየን ብቻ የማይቻል መስሎን ምኞታችን ምኞት ብቻ ይሆንብናል።
የእለቱ መልዕክት:- አስታውስ በባነነበት ሰዓት የሮጠ ሁሉ አረፈደ አይባልም። ነቅተን ዙሪያችንን እንመልከት፤ የከበቡንን እናስተውል። በዙሪያችን ያሉት አይቻልም ስላሉ ብቻ አይቻልም ብለን እራሳችንን ወደ ኋላ አናስቀረው።
ከዶሮ መሃል እንደወደቀ ወፍ አትሁን። አቅምህን ተጠቀምበት፤ ፍላጎትህን ኑረው፤ ምኞትህን እውን አድርገው። እራስህ መመልከት ከቻልክ አንተ ከምታስበው በላይ ታላቅ ሰው መሆንህን ትደርስበታለህ። ማህበረሰብ፤ ቤተሰብ፤ ጓደኛ ባወጣልህ መስፈርት እና መመዘኛ እራስህን አትመዘን፤ ይልቁንም እራሰህን በስራህ ፈትነው። ብዙዎች እንደ ወፍ ተወልደው እንደዶሮ ሞተዋል። ያ ክፉ እድል እኛን እንዳይገጥመን ሁላችንም የወደቅንበትን እንመልከት………ሌሎች መብረር ካልቻሉ አንተ መብረር አትችልም ማለት እኮ አይደለም።
@The_PowerOfThought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ከጠቀመህ ለጎደኛህ አጋራው
"ግብ አስቀምጦ እንዴት ይሆናል ብሎ የሚጨነቅ ሰው ዘር ዘርቶ ተፈጥሮአዊ ጊዜውን እና አበቃቀሉን ከመጠበቅ ይልቅ እንዴት ? የሚለው ላይ ያተኮረ እንደሚበቅል ያላመነ ገበሬን ይመስላል "
ተፈጥሮን ያላመነ ገበሬ መሬት ውስጥ መቆየቱ ስለሚያሳስበው አለጊዜው እየቆፈረ ለማረጋገጥ ይሞክራል ዘሩንም ያበላሻል። ዘሩን ከመሬት ያገናኘ ገበሬ በቅሎ እስኪያየው ድረስ በእምነት ይጠብቃል ምክንያቱም መሬት ውስጥ ነው ያለው ማለት በወቅቱ መሬቱን ሰንጥቆ አይታይም ማለት ስላልሆነ ነው ። ምን የዘሩት እና የሚያጠጡት ህልም አልዎት ? አለመብቀሉ የሚያሳስብዎት ?
የሰው ልጅ ማተኮር ያለበት ዘሩ ላይ እና ከእርሱ የሚጠበቀው እንክብካቤ ላይ ነው። ሌላው ተፈጥሯዊ ጊዜውን ጠብቆ ይከናወናል።
ማንጎ የተከለ እና ስንዴ የዘራ በእኩል ወቅት እንዲበቅል አይጠብቅ ፣ አፈሩን አለስልሶ የተከለ እና እንዲሁ ደረቅ መሬት ላይ የዘራም እኩል ውጤት አይጠብቅ ፣ በየወቅቱ ያጠጣ የተንከባከበ እና ዘርቶ አረም እንዲውጠው በግድየለሽነት የተወ እኩል ምርት አይጠብቅም ።
ወዳጆቼ ;
1. ምንድነው የዘራውት ?
2. በየጊዜው እየተንከባከብኩ ነው ?
3. ውጤቱን አውቀዋለው ?
4. ትኩረቴ እንዴት ላይ ነው ወይስ የምሻው ውጣት ላይ ?
ሌላው ተፈጥሯዊ ነው ። በእምነት መጠበቅ ብቻ ነው !!!
ሲሳይ ምህረት
ነሀሴ 11,2013 ዓ.ም
ህይወት ምርጫ ፣ ሂደት እና ውብ ናት !!!
“ይቅርታ… በሀሳብ ጠፍቼ ነበር!”
ስንት ጊዜ እራሳችንን ይህን ስንል እናገኛለን?
ከሰው ጋር እያወራን ነው… ግን አእምሯችን ሌላ ቦታ ነው።
እየበላን ነው… ግን ስለሌላ ነገር እያሰብን ነው።
እየነዳን ነው… ግን ትናንትን እየደጋገምን ነው።
ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ነን… ግን ስለነገ እየተጨነቅን ነው።
ሰውነታችን እዚህ ነው፤ አእምሯችን ግን ሌላ ቦታ ነው።
አብዛኛዎቻችን የቀኑን ብዙ ጊዜ ሕይወታችንን እየኖርን ሳይሆን፣ ስለ ሕይወታችን እያሰብን እናሳልፋለን።
“ምን ይሆናል?”
“ለምን እንዲህ ሆነ?”
“ቢሆንስ?”
“ባይሆንስ?”
“እንዴት እሆናለሁ?”
“ሰዎች ምን ያስቡብኛል?”
ይህ የማያቋርጥ የሀሳብ ጫጫታ ግን ዋጋ አለው።
ጭንቀት።
ውጥረት።
ፍርሃት።
ድካም።
መረበሽ።
የአእምሮ ድካም።
ነገር ግን ችግሩ ሀሳብ መኖሩ አይደለም።
ችግሩ በሀሳባችን ውስጥ መጥፋታችን ነው።
ሀሳብን ማቆም አያስፈልገንም።
ከሀሳብ ውጪ በመሆን ሀሳባችንን ማየት ነው ያለብን።
ሀሳብ ሲመጣ… አስተውለው።
ሳትዋጋው ፍቀድለት።
ከዚያም… ወደ አሁኑ ተመለስ።
ወደ አሁኑ ስትመለስ ከምታገኛቸው ፍሬዎች፦
🕊 ሰላም
✨ ግልጽነት
😊 ደስታ
🌱 መረጋጋት
⚡️ ኃይል
ሰላም ማለት ከስኬት መራቅ አይደለም።
በተቃራኒው፣ ሰላም ውጤታማ ያደርገናል።
ሰላም ግልጽነትን ይፈጥራል።
ግልጽነት የተሻለ ውሳኔን ያመጣል።
የተሻለ ውሳኔ የተሻለ እርምጃን ይመራል።
የተሻለ እርምጃ ደግሞ የተሻለ ውጤትን ያመጣል።
ወደ አሁኑ ተመለስ ❤️ ሕይወትህ እዚህ ነው
©DD
🚀 **የአስተሳሰብ አቅምህን የሚገነቡ እና ከአካባቢ ተፅዕኖ ነፃ የሚያወጡ ትምህርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 @The_PowerOfThought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ከጠቀመህ ለጎደኛህ አጋራው
Comfort Zone እና የአካባቢ ተፅዕኖ — እድገትህ እንዳይቀጥል ያሰረው ሰንሰለት!
ብዙ ሰዎች ህይወታቸው፣ ገቢያቸው ወይም አስተሳሰባቸው ከአንድ ቦታ በላይ ፈቀቅ ማለት ሲያቅተው ምክንያቱ የአቅም ማነስ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ዋናው ምክንያቱ በለመዱት ምቾትና ደህንነት (Comfort Zone) ውስጥ መሸሸጋቸው እና *የከበቧቸው ሰዎች ተፅዕኖ ነው።
ሩሚ የተባለው ታላቅ ፈላስፋ እንዲህ ብሎ ነበር፦
> ላባችሁን ዘርግታችሁ መብረር እየቻላችሁ፣ ለምን በጉልበታችሁ ለመሳብ ትመርጣላችሁ?
💡 Comfort Zone (የለመድነው የመደላደል ቀጠና)፦
ኮምፈርት ዞን ማለት ምንም አይነት ስጋት፣ ፈተና ወይም አዲስ ነገር የሌለበት፤ ነገር ግን ምንም አይነት እድገትና ለውጥ የማይመጣበት ቦታ ነው።
አዲስ ነገር ለመጀመር ስታስብ የሚሰማህ ፍርሃት፣ የሰዎች ትችት ስጋት እና "ባይሆንልኝስ?" የሚል መጠራጠር የአዕምሮህ የተፈጥሮ መከላከያ ነው።
ነገር ግን ትልቁ የስኬት እድገት የሚገኘው ከዚሁ ፍርሃትና ምቾት ቀጠና ወጣ ብለህ እርምጃ ስትወስድ ብቻ ነው!
👥 2. የአካባቢ ተፅዕኖ (Law of Environment)፦
ጂም ሮን (Jim Rohn) የተናገረው ታዋቂ ህግ አለ፦
"አንተ አብረሃቸው ብዙ ጊዜ የምታሳልፋቸው የ 5 ሰዎች አማካይ ውጤት ነህ!"
አብረሃቸው የምታሳልፋቸው ሰዎች አስተሳሰብህ፣ የገቢህ ልክ፣ ህልምህ እና የእለት ተእለት ልማድህ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።
ከ 5 ሰነፎች ጋር ካሳለፍክ... 6ኛው ሰነፍ አንተ ትሆናለህ።
ከ 5 የቢዝነስና የፋይናንስ እድገት አላማ ካላቸው ሰዎች ጋር ካሳለፍክ... 6ኛው ስኬታማ ሰው አንተ ትሆናለህ!
🧠 የዛሬው ትልቅ ትምህርት፦
1️⃣ ምቾትህን ሰብረህ ውጣ፦ በየቀኑ የሚያስፈራህን፣ አዲስ ነገር የሚያስተምርህን እና ከለመድከው ወጣ ያለ አንድ እርምጃ ውሰድ።
2️⃣ አካባቢህን መርጥ፦ እድገትህን፣ ህልምህን እና አስተሳሰብህን የሚደግፉ አዎንታዊ ሰዎችን በዙሪያህ ሰብስብ።
"ታላላቅ ነገሮች በፍጹም በ Comfort Zone ውስጥ አያድጉም!"
💬 የዛሬው ጥያቄ፦
ከ Comfort Zoneህ ወጥተህ ለማድረግ የምትፈራው ነገር ግን ካደረግከው ህይወትህን ሊቀይረው የሚችለው እርምጃ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇
🚀 **የአስተሳሰብ አቅምህን የሚገነቡ እና ከአካባቢ ተፅዕኖ ነፃ የሚያወጡ ትምህርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 @The_PowerOfThought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ከጠቀመህ ለጎደኛህ አጋራው
በየቀኑ የሚደረግ የ 1% የማደግ አቅም
ጄምስ ክሊር (James Clear) «Atomic Habits» በተሰኘው ዝነኛ መጽሐፉ ላይ አንድ አስደናቂ የስኬት ህግ ያብራራል፦
"ትላልቅ ስኬቶች የሚፈጠሩት በአንድ ጀምበር በሚደረግ ትልቅ ዝላይ ሳይሆን፣ በየቀኑ በሚደረጉ ትንንሽ የ 1% ማሻሻያዎች ድምር ውጤት ነው!"
ብዙዎቻችን ህይወታችንን ለመቀየር ስናስብ በአንድ ጀምበር ትልቅ ለውጥ ለማምጣት እንሞክራለን፤ ነገር ግን ጥቂት ቀናት እንሰራን ተስፋ እንቆርጣለን። እውነተኛው ምስጢር ግን በትግስት በየቀኑ የምናደርጋቸው ትንንሽ ልማዶች ናቸው!
📈 የ 1% የሂሳብ ቀመር አስደናቂ ውጤት፦
በየቀኑ በ 1% ብቻ ራስህን፣ እውቀትህን ወይም ቢዝነስህን ብታሻሽል፤ በ365 ቀናት (በአንድ ዓመት) ውስጥ 37 እጥፍ (3700%) የተሻለና የበረታህ ሰው ትሆናለህ!
በአንፃሩ በየቀኑ በ 1% አሉታዊ ልማድ ውስጥ ብንገነባ ፤ በዓመቱ መጨረሻ አቅምህ ወደ ዜሮ ተጠግቶ ይወርዳል! $)
💡 3 የ «Atomic Habits» ዋና ዋና ትምህርቶች፦
1️⃣ The Power of Compounding፦በየቀኑ 10 ገጽ ማንበብ፣ 20 ደቂቃ ስፖርት መስራት ወይም 1 አዲስ የቢዝነስ ክህሎት መማር በወቅቱ ትንሽ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ህይወትህን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል።
2️⃣ Make it Small(በትንሽ ጀምር) ፦ትልቅ ግብ አቅደህ ከምትተው፣ ለመተግበር እጅግ ቀላል በሆኑ ትንንሽ ልማዶች ጀምር። (ለምሳሌ፦ "በቀን 1 ሰዓት አነባለሁ" ከማለት ይልቅ "በቀን 2 ገጽ አነባለሁ" ብለህ ጀምር)።
3️⃣ ትኩረትህ System ላይ ይሁን፦ግብ ማቀድ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ግብህ ላይ የሚያደርስህን የእለት ተእለት ስርዓትና ልማድ መገንባት አለብህ።
"በህይወትህ የምታገኘው ውጤት የእለት ተእለት ልማዶችህ ድምር ውጤት ነው!"
💬 የዛሬው ጥያቄ፦በየቀኑ በ 1% ማሳደግ የምትፈልገው አዎንታዊ ልማድ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇
🚀 የአስተሳሰብና የእለት ተእለት ልማዶችህን ለማሳደግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉
@The_powerOfThought
📊 በቀን ውስጥ በአማካይ ስንት ሰዓት ሶሻል ሚዲያ (ቴሌግራም፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ...) ላይ ታሳልፋለህ?
⏰ The Golden Hour
የጠዋት 1 ሰዓት ህግ ህይወትህን እንዴት ይቀይራል?
ሮቢን ሻርማ የተባለው ታዋቂ ፀሐፊ እንዲህ ይላል፦
"የቀንህን የመጀመሪያ 1 ሰዓት እንዴት እንደምትመራው፣ ቀሪውን 23 ሰዓትህን እንዴት እንደምትኖረው ይወስናል!"
አብዛኛው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ የመጀመሪያው የሚያደርገው ነገር ስልኩን ማንሳት፣ ሶሻል ሚዲያ ስክሮል ማድረግ ፣ የሰዎችን አሳዛኝ ወይም አስደናቂ ዜናዎችን ማንበብ ነው። በዚህም ሳታውቀው አእምሮህን ገና በጠዋቱ በጭንቀት፣ በንፅፅር እና በግርግር እንዲሞላ ታደርገዋለህ።
💡 ህይወትህን የሚቀይረው The Golden Hour (ወርቃማው 1 ሰዓት) ምንድን ነው?
ከእንቅልፍህ እንደነቃህ ያሉትን የመጀመሪያ 60 ደቂቃዎች ሙሉ በሙሉ ለራስህ፣ ለአእምሮህ እና ለውስጥ ሰላምህ ብቻ መስጠት ነው!
🎯 የ 20-20-20 ቀመር (The 20-20-20 Formula)፦
ወርቃማዋን 1 ሰዓት በሶስት ቦታ ከፍለህ ተጠቀምባት፦
1️⃣ የመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃ (አካልን ብቃት እንቅስቃሴ)፦ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ወይም ውሃ መጠጣት። ይህ በደማችን ውስጥ ያለውን የኮርቲሶል (የጭንቀት ሆርሞን) መጠን ይቀንሳል።
2️⃣ ሁለተኛው 20 ደቂቃ (ማሰላሰልና ማቀድ)፦ፀጥ ባለ ቦታ ተቀምጦ ማሰላሰል (Meditation)፣ ለተሰጡህ ነገሮች ምስጋና ማቅረብ እና የቀኑን ዋና ዋና ግቦች በደብተር ላይ መጻፍ።
3️⃣ የመጨረሻው 20 ደቂቃ (አእምሮን መመገብ)፦ማንበብ፣ አነቃቂ ድምፅ (Audiobook/Podcast) መስማት ወይም አዲስ እውቀት መቅሰም።
🧠 ውጤቱ ምንድን ነው?
ይህንን ልማድ ለ30 ቀናት በወጥነት ከተከተልከው፣ አእምሮህ ከተከታይነት (Reactive Mode) ወጥቶ ወደ መሪነት (Proactive Mode) ይሸጋገራል። ቀኑን በሙሉ በከፍተኛ ትኩረት፣ በኃይል እና በተረጋጋ ስሜት እንድታሳልፍ ይረዳሃል።
"ስልክህን ከመመገብህ በፊት አእምሮህን መግብ!"
💬 የዛሬው ጥያቄ፦ከእንቅልፍህ ስትነቃ የመጀመሪያው የምታደርገው ነገር ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት እውነቱን አጋራን! 👇
🚀 የአስተሳሰብ እና የእለት ተእለት ልማዶችህን በማሳደግ ህይወትህን ለመቀየር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉
@The_powerOfthought
@RadiantEphrem
🚘ይህን መልዕክት ጠዋቱን በአግባቡ እንዲጠቀም ለምትፈልገው ጓደኛህ ላክለት።
🔄 Subconscious Mind (ድብቁ አእምሮ ) — ህይወትህን የሚመራው ትልቁ አእምሮህ!
የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እንደሚያረጋግጡት፤ የእለት ተእለት የህይወት ውሳኔዎቻችን፣ ልምዶቻችን እና የፋይናንስ ውጤቶቻችን 95% የሚመሩት ድብቁ አእምሮአችን (Subconscious Mind) ነው!
ንቁው አእምሯችን (Conscious Mind) 5% ብቻ ቦታ ሲኖረው፤ ድብቁ አእምሮአችን ግን ልክ እንደ ኮምፒውተር ሃርድ ድራይቭ (Hard Drive) ከትንሽነታችን ጀምሮ የሰማነውን፣ ያየነውን እና ያመንንበትን መረጃ በሙሉ አስቀምጦ የያዘ ነው።
💡 ለምሳሌ፦
በልጅነታችን ገንዘብ የችግር ሁሉ ምንጭ ነው ወይም"ሀብታም ለመሆን ማታለል ያስፈልጋል/ ሀብታም ማለት ውሰኛ ነው/ የሚል ሀሳብ ደጋግመህ ሰምተህ ካደግክ፤ ድብቁ አእምሮህ ገንዘብን እንደ አደጋ ስለሚቆጥረው ሳታውቀው ገንዘብ እንዳታገኝ ያደርግሃል ምክንያቱም አእምሮህ ሀብት የችግር ምንጭ ነው ብሎ ሰለሚያምን።
🧠 ድብቁ አእምሮህን (Subconscious Mind) በበጎ ሀሳብ ፕሮግራም ማድረጊያ 3 መንገዶች፦
1️⃣ የቃላት አጠቃቀምህን ቀይር (Self-Talk)፦ደብቁ አእምሮህ ቀልድና እውነትን አይለይም፤ የምትናገረውን ሁሉ እንደ ትእዛዝ ይቀበላል። አልችልም፣ አይሆንልኝም፣ ደሃ ነኝ ከማለት ይልቅ፤ እየተማርኩ ነው፣ ይሆናል ፣ በየቀኑ እያደግኩ ነው የሚሉ አዎንታዊ ቃላትን ተጠቀም።
2️⃣ በምናብ ማየት (Visualization)፦አእምሮህ በስዕል መልኩ ነው የሚረዳው ነገሮችን። የምትፈልገውን ግብ፣ የስኬት ደረጃ እና የህይወት መንገድ ከወዲሁ በአእምሮህ እንደደረስክበት አድርገህ ደጋግመህ ተመልከት።
3️⃣ማታ ልንተኛ ስንልና ጠዋት እንደተነሳን (Alpha State)፦ከመተኛትህ በፊት ባሉት 30 ደቂቃዎች እና ከእንቅልፍህ እንደነቃህ ባሉት የመጀመሪያ 30 ደቂቃዎች ድብቁ አእምሮህ ሙሉ በሙሉ ክፍት ነው። በዚያ ሰዓት አዎንታዊ ሀሳቦችን እና መጻሕፍትን ማንበብ አእምሮህን በአዲስ መልኩ ፕሮግራም ማድረግ።
አእምሮህን ካልቀየርክ፣ የምትቀይረው ነገር የለም!
💬 የዛሬው ጥያቄ፦ድብቁ አእምሮህ ውስጥ ተቀርጾ የነበረና አሁን ላይ ለመቀየር እየታገልከው ያለህ አሉታዊ አስተሳሰብ ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇
🚀 የአስተሳሰብህ እና የአእምሮህ ኃይል በመገንባት ህይወትህን ለመቀየር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦👉
@The_PowerOfThought
📥 ከእኛ ጋር በአስተሳሰብ እና በፋይናንስ አብረው ማደግ የሚፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩን፦👉 @RadiantEphrem
🎯ገቢህ =የአስተሳሰብህ ልክ ነው
በአንድ ታዋቂ የፋይናንስ መጽሐፍ ላይ የተጻፈ ድንቅ እውነት አለ፦"ገቢህ በአጋጣሚ ከፍ ሊል ይችላል፤ ነገር ግን በአስተሳሰብ እና በእውቀት ካላደግክ በስተቀር ተመልሶ ወደ አስተሳሰብህ ልክ መመለሱ አይቀሬ ነው!"
አብዛኛው ሰው የገቢውን መጠን ማሳደግ ይፈልጋል፤ ነገር ግን የገቢው መጠን የሚወሰነው በሚፈጥረው የእሴት/የዋጋ (Value) መጠን እንደሆነ ይረሳል። የፈጠረው እሴት ደግሞ በ አስተሳሰቡ እና በእውቀቱ ልክ የተገደበ ነው!
💡 የአስተሳሰብ እና የገቢ እድገት 3 ህጎች፦
1️⃣ በራስህ ላይ ኢንቨስት አድርግ፦አእምሮህን በበጎ ሀሳቦች፣ በመጻሕፍት እና አዳዲስ ክህሎቶችን በማስተማር ስታሳድገው፣ ዋጋህ(Value) ይጨምራል።
2️⃣ ከአስተሳሰብህ በላይ አታድግም፦በአእምሮህ ውስጥ "እኔ በወር የሚገባኝ ይህ ያህል ነው" ብለህ ወስነህ ያጠርከው አጥር አለ ከዛ ገደብ አልፈህ ገቢ አታገኝም ብታገኝም ትመለሳለህ።
3️⃣ ትክክለኛ አካባቢን ምረጥ፦ከአንተ የተሻለ የፋይናንስ እና የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ስትቀላቀል፣ የአንተም አስተሳሰብ አብሮ የመስፋፋት እድሉ ከፍተኛ ይሆናል።
🔥 የሳምንቱ ልዩ አጋጣሚ (Special Opportunity)!
ባለፈው 1 ሳምንት በቻናላችን የአስተሳሰብ መሰረቶችን ስንገነባ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ያንን አስተሳሰብ ወደ ተጨባጭ የቢዝነስ እና የገቢ እድገት ለመቀየር ወስነናል!
በዚህ ወር ከእኛ ጋር ቅርብ በሆነ ክትትል (Mentorship)፡
የአስተሳሰብ አቅማቸውን ማሳደግ የሚፈልጉ፣
በትርፍ ጊዜያቸው አዲስ የገቢ ምንጭ መገንባት የሚፈልጉ 3 ቁርጠኛ ሰዎችን ብቻ ለይተን አብረን ለመስራት ተዘጋጅተናል!
💬 የዛሬው ጥያቄ፦የአስተሳሰብህን ልክ ለማሳደግ በየቀኑ የምታደርገው ጥረት ምንድን ነው? ከታች በኮሜንት አጋራን! 👇
🚀 የአስተሳሰብ አቅምህን የሚገነቡ ትምህርቶችን ማግኘትን ለመቀጠል ቻናላችንን ተከታተል፦
@The_PowerOfThought
📥 ከላይ ከተጠቀሱት 3 ሰዎች አንዱ በመሆን አብረኸን ማደግ ከፈለግክ አሁኑኑ በውስጥ መስመር "ዝግጁ ነኝ" ብለህ ላክልን፦👉 [ @RadiantEphrem ]
