National youth Volunteers
Open in Telegram
Ministry of peace, youth volunteers channel #ይህ ቻናል የተዘጋጀው ለብሔራዊ በጎ ፈቃደኞች መረጃን በቀላሉ ለማድረስ ነው
Show more1 087
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Notice:
የአንድ ማአከል አገልግሎት የሚገኘው በተመረጡ ወረዳዎች ሲሆን የሚገኙትም በወረዳ የሥራ ኢንተርፕራይዝ: ኢንዱስትሪ ቢሮ ነዉ::
ለምሳሌ አዲስአበባ አካባቢ የምትገኙ ቦሌ ክ/ከተማ (ወረዳ 3(ቦሌ አትላስ አካባቢ) ~5(ገርጂ አካባቢ)~6(ቦሌ ክ /ከተማ ጀርባ )~11) የሥራ ኢንተርፕራይዝ: ኢንዱስትሪ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን በምዝገባ ወቅት የተሰጣችሁን የማረጋገጫ ቁጥር ብቻ በመያዝ biometrics መረጃ መስጠት ይቻላል::
አዲስአበባ በተጨማሪ የካ~ቃሊቲ~አዲስከተማና ኮልፌ ክ/ከተማ ላይ በተመረጡ ወረዳዎች አገልግሎቱ ይሰጣል::
ስለዚህ የተመረጡ ወረዳዎችን ለማወቅ ክ/ከተሞች ላይ ሥራ ኢንተርፕራይዝ: ኢንዱስትሪ ቢሮ በመግባት information መጠየቅ ይቻላል :: ሌሎች የተዘረዘሩ ክልሎችም ላይ በተመሳሳይ ገብቶ መጠየቅ ይቻላል::
ትክክለኛ አድራሻ ሄዳችሁ ያረጋገጣችሁ በዉስጥ መስመር ብታሳውቁን ሌሎች እንዳይቸገሩ post የምናረግላችሁ ይሆናል::
መልካም እድል 🙏🙏🙏
ሰላም👏
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ባስተላለፈው የምዝገባ ጥሪ መሰረት በድረ-ገጽ (በኦን ላይን) ተመዝግበው የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች በሚገኙ የተመረጡ 400 ለሚሆኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ሥርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በመሆኑም የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ
👉በኦሮሚያ ክልል
(በአምቦ፣ በሻሸመኔ፣ በአዳማ፣ በአሰላ፣ በቡራዩ፣ በምስራቅ ሃረርጌ፣ በመትሃራ፣ በፉሪ፣ በጉደር እና በጅማ)
👉በአዲስ አበባ
(በቦሌ፣ በየካ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ እና በኮልፌ ክፍለ ከተሞች)
👉በሲዳማ ክልል
(በሃዋሳ፣ ባንሳ፣ አለታ ወንዶ እና በወንዶ ገነት)
👉በደበብ ምዕራብ
(በቴፒና ሌሎች ከተማ)
በሚገኙ የተወሰኑ አንድ ማዕከላት አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል።
ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱትና በሚቀርባቸው የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ተገኝተው አስፈልጊውን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ::
ሌሎች ቦታዎች ላይ በቀጣይ የሚዳረስ ይሆናል::
Adama ላይ ስልጠና ሳይሆን የእውቅና እና ሽልማት program ነው ያለው, በሰላም ሚኒስቴር(ከ 1ኛ -5ኛ ዙር )
መቼስ እንደምታዉቁት ሁሉንም እንሸልም ቢሉ ስለማይችሉ በየክልሉ የተወሰኑ ልጆችን select አድርገዉ ነዉ የጠሩ ,
ለምን እኔ አልተመረጥኩም ብለን መከራከር ከኛ አይጠበቅም በጎ ሥራን ለእዉቅና እና ለሽልማት ብለን ስላልሰራን ::
ባይሆን አብረዉን ከሰሩ ልጆች ተመርጦ acknowledge ከተደረጉ እኛም ተመሰገንን ማለት ነዉ😊:: ይህ ደግሞ ሊያስደስትን እንጂ ሊያናድደን አይገባም!!
እናንተ የተመሰገናችሁት ያኔ በጎ ፈቃድ ሰርታችሁ የሰዉን ስራ ስታቀሉ, የተቸገሩን ስትረዱ, በናንተ ምክንያት ሰዎች ሲደሰቱ እና ከድካም ሲያርፉ ነዉ:: ስለዚህ እዉነተኛ በጎ ፈቃድን ከልቡ የሰራ ሰው ህሊናዉን ንፁህ ያደረገ እና ሽልማትን የማይፈልግ ነዉ ::
በዛ ልክ ደሞ ቤታቸው ሆነው ሲከፈላቸው የነበሩ ; tshirt ለብሶ ማህበራዊ አገልግሎትን ማድረግ ሲፀየፉ የነበሩ እና አብሮ ተሳትፎ ባለመስራት የሚታወቁ ልጆች አብረዉን ነበሩ, ግን ከምርቃት በሁላ ሁላችንም እኩል ነን::
so, ዋናው ነገር የህሊና እርካታ ነዉ እና እናንተ የተመሰገናችሁት ያኔ ነዉ ልላችሁ እወዳለሁ🙏🙏🙏
ይሄንን ርእስ እዚህ ላይ እናቁምና..
በ ሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር በኩል አዲስ ነገር እስኪኖር እየጠበቅን ነው::
ከዛ ዉጭ ግን በያላችሁበት ክልል በራሳቹ ተንቀሳቅሳችሁ ስራዎችን የጀመራችሁ በጎ ፈቃደኞች ሌሎች የስራ እድሎች በምታዩበት ጊዜ በዉስጥ መስመር or comment ላይ ብታሳዉቁን አውነተኛነቱን አያረጋገጥን post የምናረግላችሁ ይሆናል::
Volunteer to volunteers👏🤝🤝 ከተረዳዳን እና ለመጠቃቀም ከወሰንን ከበጎ ፈቃደኛ ዉጭ ለበጎፈቃደኛ የሚያስብለት/ላት አይኖርም 😊
መልካም ምሽት🙏
@MOPAddis1st
Join this channel!!
ሰላም :
ከሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር ጋር በተያያዘ አዲስ ነገር የለም ; አሻራ መስጫ ቀን ወይም ሌሎች መረጃዎች በሚገለፁ ጊዜ በዚህ page የምናሳዉቃቹ ይሆናል🙏
@MOPAddis1st
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
መልካም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችን ነዉ፡፡
ዒድ ሙባረክ!
ሰላም,
በአሻራ እና ቀጣይ steps ዙሪያ ጠይቀን የተሰጠን ምላሽ ገና እንደሆነ እና በሚጀምር ሰአት በሚዲያ እንደሚያሳውቁ ነው:: የሚሰጥበት ቦታም በየክልሉ በሚገኙ የመንግስት ቢሮዎች ወይም ጊዜያዊ ጣቢያዎች apply ካረግን በሁላ የተሰጠንን Id ቁጥር በመያዝ ነው የሚሆነዉ ተብሎአል ::
Stay calm and check new things upto then!!
Have a good day!!
ሰላም :
ለ 1ኛ እና ለ 2ኛ ዙር የተላለፈው የምዝገባ ጥሪ በዚህ 2 ቀን ዉስጥ ሊያበቃ ስለሚችል, ያልሞላችሁ ቶሎ ብትሞሉ ጥሩ ነው ::
https://www.lmis.gov.et
ሌላው በተለያየ ምክንያት መሙላት ያልቻሉ አብረዋችሁ በጎ ፈቃድን ሲያገለግሉ የነበሩ ጉአደኞቻችሁን apply ማድረጉ ላይ ብታግዟቸዉ እና መስማት ያልቻሉትን እንዲሰሙ ብናደርግ ጥሩ ነዉ::
Biometric data መስጫ ቀን እስካሁን አልተነገረም, ምናልባትም ምዝገባ ካለቀ በሁላ ሊጀምር ይችላል, anyways, በሚነገር ሰአት immediately እናሳዉቃችሁለን ::
በዚህ ጉዳይ ሌላ የሰማችሁት ነገር ካለም comment, ላይ ብትነግሩን ደስ ይለናል!
ምዝገባ ላይ የተሳሳታቹት ነገር ብዙ ካልሆነ እዛው biometric data በሚቀበሏችሁ ጊዜ ያስተካክሉላችሁአል ብለን እናስባለን... It is known that no one is perfect adel!!!!!!!
Byzway, መመዝገብ ግዴታ አይደለም; አለመመዝገብም ይቻላል : ስለዚህ ማትመዘገቡ ልጆች ትክክለኛ አይደለም የተረጋገጠ አይደለም በሚል ሌሎች ይህን እድል መጠቀም የሚፈልጉ ልጆችን እንዳይመዘገቡ ባናደርግ ጥሩ ነዉ ::
ቀጣይ ብዙ process ሊኖር ስለሚችል please be active and alert to check for new informations regarding to the next steps!
Join this channel for more informations!!!
@MOPAddis1st
መልካም ቀን 🙏
ማንኛውም ጥያቄ ወይም ግራ የገባችሁ ነገር ካለ screenshot እያደረጋችሁ ' Leave comment' ሚለውን በመጫን መጠየቅ ይቻላል..
መልካም ቀን 🙏
ከዛ ወደ 6 steps አሉት next, እያረጋችሁ ሁሉንም መሙላት አለባችሁ... ለመመዝገብ ከናንተ ሚጠበቀው
* ፎቶ
* የትምህርት ማስረጃ
*የሰላም ሚኒስቴር ሰርተፊኬት
በማዘጋጀት አያንዳንዱ ሚጠይቃችሁን ጥያቄ በትክክል በመመለስ መጨረሻ ላይ ሚሰጣችሁን ቁጥር(Biometrics ID) በመያዝ ቀጣይ steps ( Biometrics መረጃ) ማእከላት ላይ ስጡ ተብሎ ማስታወቂያ ላይ እስኪነገር ወይም እስኪተላለፍ ቁጥሩን ይዞ መጠበቅ ነው; እኛም እናሳዉቃችሁለን 🙏
መልካም እድል!!
Join this channel for more informations!!
@MOPAddis1st
ከዛ email, ስልካችሁን እና password(×2) ካስገባችሁ በሁአላ sign up ሚለዉን ተጫኑ ::
ፓሥዎርድአችሁ capital letter, ቁጥር እና character መኖር አለበት...
ለምሳሌ ስማችሁ... Biniyam ከሆነ : (Bini@123) ማድረግ ይቻላል::
ሰላም :
1ኛ እና 2ኛ ዙር ምዝገባ ምታደርጉት online በተሰጠዉ ድህረ ገፅ (link) ነው::
https://www.lmis.gov.et
ይህንን ሊንክ በስልካችሁ google chrome ላይ copy paste አርጋችሁ ወይም ቀጥታ በመክፈት መመዝገብ ትችላላችሁ ::
Join this channel for more informations!!
@MOPAddis1st
ለሚመለከታችሁ የበጎነት ለአብሮነት ብሔራዊ አገልግሎት 1ኛ እና 2ኛ ዙር ተሳታፊዎች
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ያሉ የስራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ካለው ከፍተኛ ስራ አንፃር እስካሁን ለብዙ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል።
በመሆኑም የበጎነት ለአብሮነት ብሔራዊ አገልግሎት 1ኛ እና 2ኛ ዙር ተሳታፊዎች ሆናቹ በአሁን ጊዜ ስራ ፈላጊ የሆናቹ እና በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሚኖሩ የስራ ዕድሎች ላይ ለመሰማራት ፍቃደኛ የሆናቹ ወጣቶች የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የስራ ዕድሎችን ለማመቻቸት እየሰራ የሚገኝ ስለሆነ የዕድሎቹ ተጠቃሚ ለመሆን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያስችል ዘንድ ፍላጎቱ ያላቹ ሚንስትር መስሪያቤቱ ባለማው የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ደህረ-ገጽ ላይ ገብታቹ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ስትመዘገቡም ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የባዮሜትሪክስ ቁጥር በመያዝ (Biometrics-ID) በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ የባዮሜትሪክስ መረጃ የሚሰጥባቸው ከ2200 በላይ አንድ ማዕከላት በመኖራቸው በአቅራቢያቹ በሚገኝ አንድ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በማድረግ የሰራተኛ ቁጥር (Labor ID) የሚሰጣቹ መሆኑን እናሳውቃለን።
ከቀናት በኋላ የሚከናወነውን የባዮሜትሪክስ መረጃ ምዝገባ የሚጀምርበትን ቀን በወቅቱ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
የመመዝገቢያ ድህረ-ገጹ አድርሻ https://www.lmis.gov.et
መልካም ዕድል
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት !
