cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dn Henok Haile

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመር እጅግ ጥልቅ ናት! #henokhaile #eotc #mahibere_kidus #tewahdomedio #orthodoxmezmur #ኦርቶዶክስ #Janderebaw_media #የአዕላፋት_ዝማሬ

Show more
Advertising posts
619
Subscribers
+324 hours
+147 days
+5730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🔴 ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ , ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ። 👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ! ዛሬ ይዘንባል እያሉ , ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስት ሞልተዋል። 👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ , ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም። በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል። 👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም። በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ , እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል። 👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙር , አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም። ከረቫትና ሱፉን ለብሰው የሚንጎራደዱ ሞልተዋል። 👉የልብሱ ቁራጭ አጋንንትን ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም። የግብፅ ነገስታት አፅማቸው በክብር ይቀመጣል። 👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም። በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል። 👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ , በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም። ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ, ዛሬ ብዙዎቹ አድንቀውታል። 👉 እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም። ጥበብን ለቅዱሳን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን #join
Show all...
🥰 3 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
11
+ የሚሮጥ ዲያቆን + የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዲበ ሠረገላ ሰማይ ለኢጃት ዲያቆናት ሲመት ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.
Show all...
🙏 4
+ ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበላችሁ! + በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ +++++ ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4፡4 ላይ ‘‘ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ’’ ካለ በኋላ መልሶ ‘ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ አንዴ ደስ ይበላችሁ ካለ ቢበቃም በዛው ዓረፍተ ነገር ድጋሚ ‘ደስ ይበላችሁ’ ማለት ለምን አስፈለገው? ለነገሩ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ላይ ደስ ይበላችሁ ያለው እዚህ ዓረፍተ ነገር ላይ ብቻ አልነበረም፡፡ በጣም አጭር በሆነው ባለ አራት ምዕራፉ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ 16 ጊዜ ደስ ይበላችሁ ፣ ደስ ብሎኛል ፣ ደስ ይበለን ፣ ደስታዬ ተፈጸመ ፣ ደስ አለኝ ፣ ደስታ ፣ ደስ ፣ ደስ ብሏል፡፡ በዚም ምክንያት የፊልጵስዩስ መልእክት የደስታ መልእክት ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህን የምታነቡ ሁሉ እኔም ከሐዋርያው ጋር ልላችሁ እወዳለሁ ፤ ደስ ይበላችሁ! +++++ ምናልባት በዚህ ሰዓት በከባድ የመንፈስ ጭንቀትና ችግር ውስጥ ወይም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለ ሰው ይህንን የቅዱስ ጳውሎስ ‘ደስ ይበላችሁ’ ጥሪ ሲያነብ ‘አንተ ደልቶሃል ወዳጄ እኔ እንኳን ደስ ሊለኝ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶብኛል’ ማለቱ አይቀርም፡፡ የሚገርመው ግን ጳውሎስ ይንን ዐሥራ ስድስቴ ደስ ይበላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፈው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ እግሩ በሚቀዘቅዝ ጉድጓድ ውስጥ በሚከረክር ብረት ታስሮ ፣ እጆቹ ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጣብቀው እያለ ፣ ከታሠረ ሦስት ዓመት ሊሞላው ሲል በፈገግታ ተሞልቶ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፡፡ +++++ እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ደብዳቤ እንዲጽፍ ዕድል ቢሠጠው ምን ብሎ የሚጽፍ ይመስልሃል? ‘የእስር ቤቱ አበሳ’ ‘የቂሊንጦ ምሥጢሮች’ ‘ገራፊዎቼና ጭካኔያቸው’ ‘የግርፋቴ ጠባሳዎች’ የሚል ዓይነት የደረሰበትን ሥቃይ የሚገልጹ መጻሕፍት አይጽፍ ይሆን? ያም ባይሆን ለቤተሰቦቹ ሲጽፍ ‘ኸረ ቁንጫውን አልቻልሁትም! ምግቡ አልተስማማኝም ፣ እገሌ ምነው አልጠየቀችኝም ደህና አይደለችም? ፣ እነ እንቶኔ ግን የማይጠይቁኝ ለምን ይሆን? እኔ ለእነርሱ እንዲህ ነበርሁ? ነግ በኔ አይሉም ወይ? ‘ያስተዛዝበናል ይኼም ቀን ያልፍና’ የሚል ይዘት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ +++++ ይህም ባይሆን እንኳን ከእስር ቤት ውስጥ ሆኖ 16 ጊዜ ‘ደስ ይበላችሁ’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለቤተሰቡ የሚልክ ሰው አይኖርም፡፡ እንደዚያ ብሎ ቢጽፍ እንኳን ቤተሰቦቹ ‘አእምሮው እየተነካ ነው! እነዚህ ሰዎችማ የሆነ ነገር ሳይወጉት አይቀሩም! ራሱን ሊያጠፋ ይሆን?’ ብለው ይጨነቃሉ እንጂ የእስር ቤቱን እንኳን ደስ አላችሁ ከቁም ነገር ቆጥረው ‘እንኳን አብሮ ደስ አለን’ አይሉም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን ደብዳቤ ግን ቤተ ክርስቲያን ከማንበብ አልፋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አካተተችው፡፡ ጳውሎስ ደስ ያለው በእስር ቤቱ ፣ በሥቃዩ አልነበረም፡፡ ደስ ይበላችሁ ያለው በጌታ ነው! ከሚደርስበት መከራ በላይ የደረሰለት ፈጣሪ በልጦበት ውስጡ በደስታ ተሞልቶ ስለፈሰሰ ከታሰሩት አልፎ ውጪ ላሉት ደስታ እስከመመኘት ደረሰ፡፡ ጭንቅ ጥብብ ብሎህ ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ጳውሎስም እንዳንተ ጭንቅ ላይ ሆኖ ‘በጌታ ደስ ይበልህ’ እያለ ነው፡፡ +++++ እግዚአብሔርን ስታስብ መከራህ ሁሉ ትንሽ ይሆናል፡፡ ጳውሎስን በቀዝቃዛው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ደስታ ያሰጠመው ፈጣሪውን አስቦ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር ውጪ ላሉት ክርስቲያኖች ‘በደስታ እጸልያለሁ’ አለ ፣ እሱ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ወንጌል የሚሰብኩ ሰባኪያን በመብዛታቸው ‘ክርስቶስ ይሰበካልና ደስ ብሎኛል’ አለ፡፡ እስር ቤት መጥተው ላልጠየቁት ሰዎችም ‘አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር’ እያለ በደብዳቤው አጽናንቶአቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ደስታ ምንጩ ግን ከመከራው በላይ እግዚአብሔርን ማየቱ ነበር፡፡ ++++++ እምነት እንዲህ ነው ፤ ጳውሎስ እግር ከወርች ከመታሰሩ በላይ ያየው ጌታውን ነበር፡፡ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር ሲተኛ ያየው የአንበሶቹን ጥርስ ሳይሆን ፈጣሪውን ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ድንጋይ ሲወርድበት ገለባ የመሰለው ጠላቶቹ በቀኝ እጃቸው ከያዙት ትልቅ ድንጋይ ይልቅ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ያለውን እየተመለከተ ስለነበር ነው፡፡ ወዳጄ ምናልባት በሕይወትህ የተጫነህ ድንጋይ ፣ ሊውጥህ የቀረበ አንበሳ አይጠፋም ፤ ጳውሎስና እርሱን መሳይ ቅዱሳን ግን ጥሪ ያቀርቡልሃል ፡፡ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበልህ! +++++ ክርስትና የመጨነቅ የመጨፍገግ ሳይሆን የደስታ ሃይማኖት ነው፡፡ የተፈጠርነው ለደስታ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ማንም የማይነጥቀው ደስታ የሚሠጥ አምላክ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ‘በደስታ ተገዙ’ ተብለናል፡፡ /መዝ.100፡2/ ወንጌል የምሥራች ነው፡፡ ወንጌል የሚጀምረው ድንግሊቱን ደስ ይበልሽ ፣ እረኞችንም ደስ ይበላችሁ በማለት ነበር፡፡ ጥምቀቱንም ‘’በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ’ የሚል ምስክርነት አለበት፡፡ክርስቶስ መከራን ሲቀበልም ‘ነውርን ንቆ በፊቱ ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ’ ነበር፡፡ /ዕብ 12፡2/ በክርስቶስ የማመን የመጨረሻው ግብም ‘ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ የሚለውን የሕይወት ቃል መስማት ነው፡፡ /ማቴ 25፡21/ +++++++ ጳውሎስ ‘’በጌታ ደስ ይበላችሁ’ አለ፡፡ ቅዱስ እንጦንስ የጳውሎስን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል ፦ በጌታ ደስ ይበላችሁ በዓለም አይደለም፡፡ በእውነት ደስ ይበላችሁ በዓመፅ አይደለም፡፡ በዘላለም ተስፋ ደስ ይበላችሁ በሚረግፉ አበቦች አይደለም፡፡ ደስታ ማለት ይህ ነው ፤ የቱንም ያህል በምድር ላይ ብትቆዩ እግዚአብሔር ቅርብ ነውና አትጨነቁ!’’ ++++ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ዓይነት ደስታ አለበት ፤ ወዳጄ አንተ አንዱን መርጠህ ደስ ይበልህ፡፡ +++++ ዳዊትን ተመልከተው ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ይልሃል፡፡ ልብ አድርግ ‘’ጎልያድን ግንባሩን ብዬ ስጥለው ደስ አለኝ’ አላለም፡፡ ንጉሥ ሆኜ የተቀባሁ ቀን ደስ አለኝ አላለም፡፡ እሱ ደስ ያለው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ያሉት ቀን ነበር፡፡ ‘እኔ እኮ ንጉሥ ነኝ ሥራ ይበዛብኛል ባይሆን እናንተ ሒዱ እኔ በገንዘብ ልርዳችሁ’ አላለም ፤ መሔጃ ያላጣው ባለጸጋ ንጉሥ ወደ ድንኳንዋ የእግዚአብሔር ቤት እንሒድ ሲሉት ደስ አለው፡፡ እዚያ ሔዶ ዙፋኑን አስዘርግቶ መንግሥትን በመወከል ‘መንግሥት ለእምነት ተቋማት ትኩረት ይሠጣል’ የሚል እግዚአብሔር ላይ የሚመጻደቅ ቅብርር ያለ ንግግር ሊያደርግ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እርሱ የፈለገው እግዚአብሔር ሥር ለመውደቅ ነበር፡፡ ‘ከአእላፋት ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች ፤ በኃጢአተኞች በድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ’ አለ፡፡ /መዝ. 84፡10/ ++++++ የዕንባቆምን ደስታ ተመልከተው ‘ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ’ ይልሃል፡፡ ኑሮው ምስቅልቅል ቢልም ፣ ችግር ቢያስጨንቀውም በእግዚአብሔር ደስ ብሎት ነበር፡፡ /ዕን 3፡17፡18/+++++
Show all...
ሳሙኤል ተመስገን ዘመሰረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት

ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

👍 3 2
ያቺን የደስታ መፍሰሻ ፤ የደስታችንም እናት እመ ብርሃንን ተመልከታት ፤ ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ ትልሃለች፡፡ ጨንቆህ እንደሆነ በጸነሰችው ደስታ እንደ ኤልሳቤጥ ደስ ታሰኝሃለች:: ደስታን በውስጥዋ ይዛ እንደ ዮሐንስ በደስታ ታዘልልሃለች:: እመነኝ ከዚያ በኁላ ደስ ይበልሽ ባልካት ቁጥር ደስ እያለህ "ተፈስሒ ማርያም" (ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ) ስትል ትውላለህ! +++++ ሐዋርያትን እያቸው አርባ አርባ ጅራፍ ተገርፈው ሲወጡ ጮማ እንደ ቆረጠ ጠጅ እንደጠጣ ሰው ‘ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ ስለተገባቸው ደስ እያላቸው’ ከሸንጎ ሲወጡ እያቸው፡፡ +++++ አዎ ምንም ደስ የማይል ዘመን ላይ ነን ፤ የምናየው የምንሰማው የምናነበው የምንጽፈው ሁሉ ደስ አይልም ፤ ከሟርትና ክፉ ዜና በቀር ደስ የሚል ነገር የለም፡፡ አዎ ልክ ነው፡፡ ሁሉ ነገር ቅፍፍ ምርር ብሎናል፡፡ በዚህ ወቅት የምንደበቀው በሚያበረታን የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብቻ ነው:: እኔ እንኳን ይህንን ስለጻፍሁ እንዴት ደስ አለኝ መሰላችሁ! ደስ ብሏችሁ ዋሉ ደስ ብሏችሁ እደሩ! ጭንቀት ሁሉ ከእናንተ ይራቅ! +++ ቃሉ ደጋግሞ እንዲህ ይላል:- ++++ ‘’ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ’ +++++ #join
Show all...
3🙏 2👏 1
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ + የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው:: ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል:: እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን:: ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው:: በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ:: ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም:: ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም:: የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው:: ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም? ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም? እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ:: አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው:: ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :- "ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
Show all...
11
✍ የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው ____ እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሴት የተወለደ ልጁን ሊልክ የዘመኑ ፍጻሜ ቀረበ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር። ቀድመው ልጅ ቢወልዱ ኖሮ ይህችን የፍጥረት ደስታ የሆነች ልጅ አይወልዱም ነበር:: የእርስዋ የልደት ቀን የፍጥረት ደስታ ቀን ነው:: 📌 ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው። 📌 ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው። 📌 ክርስቶስ መድኃኒት ከሆነ ዛሬ የመድኃኒቱ ሙዳይ የተገኘችበት ዕለት ነው:: ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል። እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። " አድባር ነውኃት ዚአኹ ውእቱ እስመ መሠረታቲ ውስተ አድባር ቅዱሳን " የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው! 📌 ግንቦት ልደታ ብሔራዊ በዓል ይሁን! 📌 ግንቦት ልደታ የአደባባይ በዓል ነው! #join
Show all...
🙏 8 5👍 2
የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ። ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው። "ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር" ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን? እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!! #join
Show all...
2
የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ። ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው። "ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር" ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን? እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!! #join
Show all...
Dn Abel Kassahun Mekuria

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ

https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube

https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram

https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW

ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባሉት ዕለታት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዓት ኾኖ ይከናወናል፡፡ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታትም ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ ይጠራሉ፤ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤ ሰኞ የትንሣኤው ማግሥት ዕለተ ሰኞ ‹ፀአተ ሲኦል› ወይም ‹ማዕዶት› ትባላለች፡፡ ይህቺውም ጌታችን በትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ናት (ዮሐ. ፲፱፥፲፰፤ ሮሜ. ፭፥፲-፲፯)፡፡ ማክሰኞ ይህቺ ዕለት፣ ለሐዋርያው ቶማስ መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቶማስ› ተብላ ትጠራለች፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ በመጣ ጊዜ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት ‹‹ሳላይ አላምንም›› ብሎ ነበር፡፡ በሳምንቱ እርሱ በተገኘበት ጌታችን በድጋሜ ለሐዋርያት ተገለጸ፡፡ ስለዚህም ይህቺ ዕለት በሐዋርያው ቶማስ ስም ተሰይማለች (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ረቡዕ ጌታችን ከሞተና ከተቀበረ ከአራት ቀናት በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላስነሣው ለአልዓዛር መታሰቢያ ናት፡፡ በክርስቶስ ሥልጣን የአልዓዛርን ከሞት መነሣት አይተው ብዙ ሕዝብ በጌታችን ስለ አመኑ ዕለቲቱ (ረቡዕ) ‹አልዓዛር› ተብላ ትታሰባለች (ዮሐ. ፲፩፥፴፰-፵፮)፡፡ ኀሙስ ይህቺ ዕለት ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ፤›› ተብሎ ቃል የተገባለት የአዳም ተስፋው ተፈጽሞ ከነልጅ ልጆቹ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ኾና ‹የአዳም ኀሙስ› ወይም ‹አዳም› ተብላ ትከበራለች (ሉቃ. ፳፬፥፳፭-፵፱)፡፡ ዐርብ የትንሣኤ እሑድ ስድስተኛዋ ዐርብ ደግሞ በክርስቶስ ደም ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቤተ ክርስቲያን› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ ሐዋ. ፳፥፳፰)፡፡ ቀዳሚት ሰንበት በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበያይባት ‹የቁራ ገበያ፣ የገበያ ጥፊያ› ተብላ ትጠራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጕልበታቸው ላገለገሉት፤ በስቅለቱ ጊዜ እስከ ቀራንዮ ድረስ ለተከተሉት፤ በትንሣኤው ዕለት በሌሊት ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው ለገሰገሱት፤ በትንሣኤውም ጌታችንን ከዅሉ ቀድሞ ለማየት ለበቁት ሴቶች መታሰቢያ ትኾን ዘንድ ‹ቅዱሳት አንስት› ተብላ ትጠራለች (ማቴ. ፳፭፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፫፥፳፯-፴፫፤ ፳፬፥፩-፲)፡፡ እሑድ ሰንበት በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ከላይ እንደ ተጠቀሰው ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Show all...
🙏 6 3👍 2