cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማህተቤን አልበጥስም

መንፈሳዊ ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ፣የየዕለቱን ስንክሳር፣ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ፣መንፈሳዊ ፊልሞች ፣መንፈሳዊ ትረካዎች እና ትምህርቶች... ሁሉንም በአንድ ማግኘት ይፈልጋሉ? ታዲያ ምን ይጠብቃሉ በፍጥነት ወደዚህ ቻናል ይቀላቀላሉ ከማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ስልክ ላይ ሊጠፋ የማይገባው ቻናል ነው።የኦርቶዶ ሃይማኖት ተከታይ ነክ ታዲያ ምን ትጠብቃለ በፍጥነወደዚህ ቻናል ተቀላቀል ተቀላቀሉ

Show more
Ethiopia10 380The language is not specifiedReligion & Spirituality88 996
Advertising posts
286
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

2.54 MB
2.94 MB
1.43 MB
ነበር፡፡ አባታችንም ከገዳም ወጥቶ መሄድ በፈለገ ጊዜ አንበሶችን እንደ ፈረስና በቅሎ ይጋልባቸዋል፣ መጻሕፍቶቹንም ይጭንባቸዋል፤ መንታ የወለደች አንበሳም ብትኖር ልጆቿን እየታቀፈ በየተራ ያጠባቸው ነበር፡፡ ወደ ደብረ ዋሊም በሄደ ጊዜ ጌታችን ተገልጦለት በዕለቱ የእመቤታችን በዓል ስለነበር እንዲቀድስ ነግሮት ከሰማይ ኅብስትና ጽዋ መጥቶለት ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኝ በግራ እየተራዱት ሲቀድስ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ኅብስቱንና ጽዋውን ጋርዶታል፡፡ ጌታችንም ቦታዋንና በዚያ ያሉትን መነኮሳት ሁሉ ልጆቹ ይሆኑ ዘንድ አስራት አድርጎ ሰጠው፡፡ ዋልድባ የተመሠረተው በቀደምት ጥንታዊያን አበው ቢሆንም አባ ሳሙኤል ሲገቡበት ምድረ በዳ ሆኖ ጠፍቶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኞች መፈልፈያ ሆኖ ነበር፡፡ አባታችን ግን የተበታተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተውና አድሰው አቀኑት፡፡ የተባሕትዎ ኑሮንም አጠናከሩበትና ገዳሙን የመናንያን አበው መሰብሰቢያ አደረጉት፡፡ አባታችን ዋልድባን እንደ ሞሰብ አንስተው አስባርከዋታል፡፡ አባ ሳሙኤል ጊዜው ደርሶ ከማረፉ በፊት ቅዱስ ሚካኤል ነሐሴ 16 ቀን ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ ከዕረፍቱ በኋላ ከልጆቹ ጋር የሚኖርበትን ሥፍራ አሳይቶታል፡፡ በገነት ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ካሳየው በኋላ በእግዚአብሔርም ዙፋን ፊት ቀርቦ ምስጋናና ቃልኪዳንን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ተመልሶ ታኅሣሥ 12 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፎ ነፍሱን ጌታችን በእጆቹ ተቀብሏታል፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- ‹‹መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ በዚያ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ መኖሪያቸውንና ክብራቸውን አሳየኝ፡፡ ‹እነሆ የተጋድሎህን ሥራ ፈጽመሃልና አንተም ወደተዘጋጀችልህ ትመጣ ዘንድ ጊዜህ ቀርቧል› ብሎ ጌታዬ የሰጠኝን መኖሪያዬን አሳየኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ልዑል ዙፋን ወደ አርያም አደረሰኝ፡፡ በዚያም በክብሩ ዙፋን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ተወዳጅ ወልድን አየሁት፡፡ በዚያም እመቤታችን ማርያምን ከተወዳጅ ልጁዋ ቀኝ አየኋት፡፡ የብዙ ብዙ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ በየወገናቸው ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የክብር ምስጋና ሰማያትንና ምድርን መላ› እያሉ በፊቱ ይዘምሩ ያመሰግኑ ነበር፡እኔም በአምላኬ ፊት ሰገድኩ፡፡ ተወዳጅ ወልድም ተናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፡- ‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፣ ደስ ይበልህ፡፡ በጥቂቱ የታመንህ ባሪያዬ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ፡፡ እኔን በመውደድ ብዙ ደክመሃልና የመስቀሌንም መከራ በመሸከም እኔን መስለሃልና እኔም በመንግሥቴ መልካም የሆነውን የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ፡፡ እነሆ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የተካከለ መቀመጫህንና አክሊልህን አዘጋጀሁልህ፣ ዕድል ዕጣህም ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያቶቼ ጋር ነው፡፡ አፅምህ በተቀበረበት፣ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት፣ መታሰቢያህ በተደረገበት፣ ሥፍራ ሁሉ ምሕረትና ድኅነት ይሁን፡፡ በጸሎትህ የሚታመነውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ ለአንተ አሥራት ሰጥቼሃለሁ፡፡ ስለ እኔ የተቀበልከውን ድካም ሁሉ ዛሬ ያገኘኸውን የአንዲት ቀን የደስታ ልክ አይሆንም፡፡›› ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሰማዕታቱ_ቅዱስ_አንቂጦስ_እና_ቅዱ_ፎጢኖስ ዳግመኛም በዚህች ቀን ወንድማማቾቹ ቅዱሳን አንቂጦስ እና ቅዱስ ፎጢኖስ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ መእመናንን የሚያሠቃይባቸውን የማሠቃያ መሣሪያዎች ለሕዝቡ እያሳየ ሲያስፈራራ የጸኑንም ሲገድል ቅዱስ አንቂጦስ በሕዝቡ መሐል ቆመና ንጉሡን ስለከንቱ እምነቱ ዘለፈው፡፡ ንጉሡም ይዞ ብዙ ካሠቃየው በኋላ በሕዝቡ ፊት ለተራበ አንበሳ ሰጠው፡፡ ነገር ግን አንበሳው ቅዱስ አንቂጦስን ፊቱን አሻስቶ ሲተወው በማየቱ ንጉሡ ሰይፉን መዞ ሊሰይፈው ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ ተሳነው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰውነትን ቆራርጦ ወደሚጥል መንኮራኩር ውስጥ ከተተው ነገር ግን ሰማዕቱን ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡ ንጉሡ ዳግመኛ ቅዱስ አንቂጦስ እርሳስ ካፈሉበት ትልቅ ጋን ውስጥ ቢጨምረውም የታዘ መልአክ ከጋኑ ውስጥ ነጥቆ አውጥቶ በንጉሡ ፊት አቆመው፡፡ ይህን ጊዜም ወንድሙ ፎጢኖስን አንጢቆስን አቅፎ ካሳመው በኋላ ንጉሡን ‹‹አንተ ከዳተኛና ጎስቋላ ንጉሥ ወንድሜን ታሸንፈው ዘንድ አይቻልህም አምላኩ ይጠብቀዋልና›› አለው፡፡ ንጉሡም የሚያደርግባቸውን ነገር እስኪያስብ ድረስ ቅዱሳኑን ወንድማማቾቹን እጅና እግራቸውን አሳሥሮ ወህኒ ቤት ጨመራቸው፡፡ በማግሥቱም አውጥቶ ሰውነታቸውን ጥፍር ባለው ብረት ሰነጣጠቃቸው፡፡ ወደ አደባባይም አውጥቶ በድንጋይ አስወገራቸው፡፡ ከብዙ ግርፋትም በኋላ በቁስላቸው ላይ ጨው ጨምሮ ካሠቃያቸው በኋላ እሳት ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ነገር ግን አሁንም እሳቱ እንደቀዝቃዛ ጠል ሆነላቸው፡፡ ንጉሡም ይህን ባየ ጊዜ ነበልባሉ ከፍ ብሎ እስኪታይ ድረስ እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ቅዱሳኑም ከእሳቱ ውስጥ ሆነው በመስቀል ምልክት አማትበው ረጅም ጸሎት ካደረጉ በኋላ ቅድስት ነፍሳቸውን ለእግዘኢብሔር አሳልፈው ሰጡ፡፡ የሥጋቸውም በድን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ከእሳቱ ፍሕም ላይ ነበር ነገር ግን የራሳቸው ፀጉር እንኳን አልተቃጠለችም ነበር፡፡ ምእመናንም ቅዱስ ሥጋቸውን ወስደው በክብር አስቀመጡት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ አስደናቂ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ዳግማዊ_ቂርቆስ (የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ) በዚህችም ቀን ዳግማዊ ቂርቆስ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ ብሔረ ብፁዓን የገባበት ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡- ብፅዕት ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ‹‹ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡
Show all...
#ታኅሣሥ_12 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐስራ ሁለት #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐረፉ፣ #ቅዱሳን_አንቂጦስ እና #ቅዱስ_ፎጢኖስ በሰማዕትነት ዐረፉ፣ #ዳግማዊ_ቂርቆስ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ ብሔረ ብፁዓን የገባበት ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ታኅሣሥ ዐስራ ሁለት በዚህች ዕለት ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ዋሊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በአክሱም ጽዮን ነው፡፡ ነገዳቸው የአክሱም ገበዝ ከነበረው ከጌድዮን ነው፡፡ የአባታቸው እስጢፋኖስና እናታቸው አመተ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ትሩፋት ተጋድሏቸው የሰመረ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገና በ12 ዓመቱ ማይ ሹም በተባለው ባሕር ገብቶ ሲጸልይ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር፡፡ ከባሕሩም ወጥቶ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ እያለቀሰና እያዘነ ሲጸልይ ካህናቱ ‹‹ይህ ሕፃን የእኛ ኃጢአት እየታየው? ወይስ ምን ኃጢአት ኖሮበት ነው እንዲህ የሚያዝነውና የሚያለቅሰው?›› እያሉ ያደንቁና ይገረሙ ነበር፡፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ እናቱ አመተ ማርያም ቤተሰቧንና ቤት ንብረቷን ትታ ከመነኮሰች በኋላ እርሱም ካልመነኮስኩ በማለት አባቱ እስጢፋኖስን ቢለምነውም እምቢ ስላለው በራሱ ፈቃድ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ወደ አባ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደብረ በንኰል ገብቶ መነኮሰ፡፡ በዚያም ነፍሱን ‹‹ነፍሴ ሆይ! እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ፣ የቅዱሳንን ቀንበር እንሆ ተሸከምሽ፣ የመላእክትን ንጽሕና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ሁሉ ፊት ቃልኪዳን ገባሽ፣ ቃልኪዳንሽን ብትጠብቂ መላእክት ይደሰቱብሻል፣ ባትጠብቂ ግን አጋንንት ይዘባበቱብሻል…›› እያለ ብዙ መከራን በራሱ ላይ በማብዛት ሰባት ዓመት በዚያች ገዳም ኖረ፡፡ እህልም አይቀምስም ነበር ይልቁንም የሚሰጡትን እንጀራ ለሕጻናትና ለውሾች እየሰጠ አሠር ይመገብ ነበር፡፡ ዳግመኛም በሌላ ጊዜ ቅጠልን እየቀቀለ እስከ አምስት ቀን ከድኖ ያስቀምጠዋል፣ እስከሚተላም ድረስ ይጠብቀውና ያን ይመገባል፡፡ ኩስይ የምትባል ከሣር ሁሉ የምትመርን ሣር ምግቡ አደረገ፡፡ በኋላም አባቱም ልጁን ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ እርሱ መጥቶ በአባ እጅ መነኮሰ፡፡ ለአባቱም መምህር ሆኖት እያገለገለው ያስተምረው ነበር፡፡ በሌላም ጊዜ 17 ዓመት ከተቀመጠባት ወይና በምትባል ቦታ ሲኖር ከውኃ በቀር ምንም ሳይቀምስ 12 ዓመት ተቀምጧል፡፡ ለ50 ዓመትም ያህል ሣር፣ ቅጠል፣ የዛፍ ሥርና ፍሬን እነዚህንና የመሳሰሉትን እየበላ ኖረ እንጂ እህል የሚባል አልበላም፡፡ ወጥቶም ወደ ዋሻ እየገባ ብዙ ጊዜ 40 ቀንና 40 ሌሊት በጾም በጸሎት እየኖረ እንቅልፍም እንዳያሸንፈው እስከሚነጋ ድረስ ሳይቆም ሳይተኛ እንደቆመ በጽኑ ተጋድሎ ተቀመጠ፡፡ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ በውስጡ እየገባ ሳይቀመጥ ሳይተኛ ሰውነቱ እንደ እንጨት እስኪደርቅ ድረስ በጾም በጸሎት በእጅጉ ይተጋ ነበር፣ በዚህም ወቅት ጌታችን ተገልጦለት ሰውነቱን በሙሉ ምራቁን ስለቀባለትና አውራ ጣቱን ስላጠባው ከዚህ ጊዜ በኋላ ርሀብና ጥሙ ጠፍቶለት ሰውነቱም ታድሶለታል፡፡ ዳግመኛም በአፉም ድንጋይ ጎርሶ፣ እግሩንም ታስሮና ማቅ ለብሶ ወደ ባሕር እየገባ ይጸልይ ነበር፡፡ አባታችን አባ ሳሙኤል በሕይወተ ሥጋ ሳለ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን አድርጓል፡፡ እንደሙሴ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ፤ በልዑልም ዙፋን ፊት እየቀረበ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚያመሰግንበት ጊዜ አለ፣ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ጋር ሆኖ የሚያጥንበት ጊዜ አለ፤ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ከሁሉ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ጋር በአንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፤ በእጆቹ የያዛቸው መጻሕፍቶቹ ምንም ሳይርሱ ትልቅ ወንዝን በውስጡ እያቋረጠ የሚሻገርበት ጊዜ አለ፤ እመቤታችንንም ሲያመሰግናት ከምድር ወደ ላይ አንድ ክንድ ያህል ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፤ በቤትም ውስጥ ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሠረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ፤ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ክንፍ እየወሰደው ወደተለያዩ ገዳማት ያደርሰውና ሥጋ ወደሙን እንዲቀበል ያደርገው ነበር፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም የሁልጊዜ ጠባቂው ነውና በሁሉ ነገር ይራዳውና እንደ ጓደኛም ያማክረው ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም በጎዳና ሲጓዝ ወንዝ መልቶበት አገኘው፡፡ አባታችንም መጻሕፍቶቻቸውንና እሳት በእጃቸው እንደያዙ በወንዙ ውስጥ ለውስጥ ውኃውን አቋርጠው ሲሻገሩ መጻሕፍቶቻቸው አልራሱም በእጃቸው የነበረው እሳትም አልጠፋም ነበር፡፡ አባታችን ሊያስቀድሱ ወደ በተ መቅደስ በሚገቡ ጊዜ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ይወርድላቸው ነበር፡፡ የእመቤታችንንም ውዳሴዋን ሲደግሙ ክንድ ከስንዝር ያህል ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ እመቤታችንም እየተገለጠች ንጹሕ ዕጣንንና የሚያበራ እንቁን ሰጥታቸዋለች፡፡ ቅዱስ አባታችን ለክቡር ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያን አስቀድሰው ሁሉም ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲወጡ ከአራቱ መነኮሳት ውስጥ አንዱ አስታወከ፣ በቤተክርስቲያንም ዳርቻ ተፋው፡፡ ያዩትም ሁሉ ደንግጠው ቆሙ፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ብፁዕ ሳሙኤል ግን ሁሉንም በአፉ ተቀበለው፣ በምላሱም መሬቱን ላሰው፡፡ ይህን ጊዜ ከሰማይም ‹ሳሙኤል ሳሙኤል› የሚልን ድምጽ ሰማና ወደላይ ባንጋጠጠ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተው አየ፡፡ ከላይ ያለው ያ ቃልም መለሰ፡- ‹በሰው ፊት እንዳመሰገንኸኝና ፈጽሞም እንዳከበርከኝ የባልንጀራህን ትውኪያ ትቀበል ዘንድ እንዳላፈርህ እኔም እንዲሁ አከብርሃለሁ፤ በሰማያት ባለው በአባቴም ፊት በመላእክት ማኅበር አመሰግንሃለሁ› አለው፡፡›› ሌሎቹም ቅዱሳን እነ አቡነ ተክለሐዋርያትም እንዲሁ ለሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ የቆረበ ሰው ሲያስመልሰው የዚያን ሰው ትውኪያ ይጠጡት እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለክርስቶስ ያላቸው ክብር እስከዚህ ድረስ ነው፡፡ አንድ ቀን አባታችን በገዳም ውስጥ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይጎበኘው ዘንድ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ከእርሱም ጋር ተቀምጦ ‹ወዳጄ ሆይ! ሰላምታ ይገባሃል፡፡ አንተ ግን ከትንሽነትህ ጀምሮ አገለገልኸኝ፣ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?› አለው፡፡ ትሑት ሳሙኤልም ‹የነፍሴ ወዳጅ ጌታዬና አለቃዬ ሆይ! መልካም ሀብት ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ምሕረትህንና ብሩህ ፊትህን ታሳየኝ ዘንድ እሻለሁ› አለ፡፡ ጌታችንም ‹አገልጋዬ ወዳጄ ሆይ! የፈለግኸውን እሰጥሃለሁ፣ ዳግመኛም ያልፈለግኸውንም እጨምርልሃለሁ› አለው፡፡ አባ ሳሙኤልም ‹ጌታዬ ሆይ! አንዲት ልመናን እለምንሃለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃጢአቴን አይ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ የሌላውን ኃጢአት ግን አታሳየኝ› አለው፡፡ አባ ሳሙኤልን የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዙለት ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ዘንዶ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ቶራህ፣ ዝሆን፣ አንበሳና ሌሎችም የዱር አራዊት ሁሉ እየመጡ እግሩን እየላሱት ወደ ቦታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ አንበሶቹንም እሾህም በወጋቸውና እግራቸው መግል በያዘ ጊዜ በመርፌ እያነቆረ ያድናቸው ነበር፡፡ ስንጥርም ሲወጋቸው ወደ እርሱ እየመጡ ያሳዩትና ያወጣላቸው ነበር፡፡ አንበሳም አጋዘንን ገድሎ ሲበላ ሲያየው ‹‹አንዴ ዞር በልልኝ ቆዳዋን ለልብሴ እፈልገዋለሁ›› ባለው ጊዜ ይለቅለት ነበር፡፡ እንዲሁም አንበሳው ለአባታችን ምግብም ትሆነው ዘንድ ጅግራን እየያዘ በሕይወት ሳለች ያመጣለት
Show all...
ቅድስት እናታችን ይዛው የተሰደደችውን የ3 ዓመቱ ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ አለቀሰ፡፡ በዚህም ጊዜ ከመነኮሳይያቱ አንዲቷ ‹‹ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር›› ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕፃኑን ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ እርሱም ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገብቷል፡፡ እጅግ አሳዛኝ ገድሉ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኛል፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት አና ጻድቃን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታህሣሥ እና #ከገድላት_አንደበት)
Show all...
❣† ስንክሳር ታህሳስ 3 †❣ እንኳን ለእግዝእትነ ማርያም (#በዓታ): አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ እና ቅዱስ ፋኑኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 🌿† በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም †🌿 ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) "ለጽንሰትኪ በከርሥ:: እንበለ አበሳ ወርኩስ:: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት፣ ኢሳ. 1:9) "ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::" "ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን)" የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) † የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,023 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለ3 ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ: ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ:: በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም:: ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር:: 3 ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ:: እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ:: ሕዝቡ: ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን: ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ:: ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ:: ግን መልአኩ ራቀ:: ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ: ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት:: በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል:: አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ:- "ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ:: ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ:: ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ" እንላለን:: (አርኬ)  ††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: ††† ታኅሣሥ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም 2.ብጹዓን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱሳን ካህናት ዘካርያስና ስምዖን 4.ቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት 5.አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል) 2.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 3.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት) ††† "ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም:: በቅድስናና በንጽሕና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ:: ድንግል ሆይ! ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ሕብስትን እንጂ:: ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጂ::" ††† (ቅዳሴ ማርያም) 🌹✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞🌹 (ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን)                🌹🌹🌹
Show all...
Show all...
📝 መዝሙር ደብተሬ 📖
✝ ዘ ቅድስት ኪዳነምህረት ✝
💒 ንስሐ ግቡ 💒
✝ አማላጄ ማርያም ✝
✝ጸቃውዕ ሚዲያ ቤታ ለማርያም✝
✝ ሃይማኖት አበው ✝
✝ አማላጄ ነሽ እላታለሁ ✝
✝ ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ✝
📀 ተወዳጅ መዝሙሮች 📀
🎬 አዳዲስ ዝማሬዎች 🎬
💒 በ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ማ የማህበረ አቅሌሲያ ዘገርጂ ማርያም የቴሌግራም ቻናል(official) 💒
✝ ኢትኤላውያን 🇪🇹
🕊️ ሐመረ ኖህ የመዝሙር ግጥሞች 🕊️
💒 ሰአሊተ ምህረት 💒
✝ አይናችን ነሽ ማርያም ✝
✝ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን✝
📚ኑ በትንሳኤው እንመላለስ⛪️
✝ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ✝
✝ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ✝
✝ ድንግል ማርያም እናቴ ✝
🇪🇹 ቀደምት ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
✝ መዝሙረ ማህሌት ✝
🖼 ስዕለ አድህኖ ➕ የቅዱሳን ስዕሎች
✝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ✝
📚 መፅሐፈ ኩፋሌ 📚
✝ መንፈሳዊ ህይወት ✝
✝ ማህተቤን አልበጥስም ✝
✝ ትምህርተ ወንጌል ✝
✝ ኆህተ ሰማይ ✝
✝ የኦርቶዶክስ ልጆች ✝
✝ ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ✝
ዕሴተ ✞ያሬድ
ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች
🔔 የበገና መዝሙሮች 🔔
🛑"አዳዲስ መዝሙሮች
✝ EOTC ✝
✝ ኦርቶዶክስ እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ ✝
✝ ዮዳሄ (Yodahe) Tube ▶️
📖 የራፋቶኤል መጣጥፎች 📖
💒 ልሳነ ቅዱሳን አበው 💒
📝 ግጥም 📝
🎬 ፊልሞች 🎬
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
📖 🎚 ኑ‌ የ‌እ‌ግ‌ዚ‌አ‌ብ‌ሔ‌ር‌ን‌ ቃ‌ል‌ እ‌ና‌ን‌ብ‌ 🎚 📖
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆  ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
كل يوم قصة ✍️‏
Show all...
📝 መዝሙር ደብተሬ 📖
✝ ዘ ቅድስት ኪዳነምህረት ✝
💒 ንስሐ ግቡ 💒
✝ አማላጄ ማርያም ✝
✝ጸቃውዕ ሚዲያ ቤታ ለማርያም✝
✝ ሃይማኖት አበው ✝
✝ አማላጄ ነሽ እላታለሁ ✝
✝ ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ✝
📀 ተወዳጅ መዝሙሮች 📀
🎬 አዳዲስ ዝማሬዎች 🎬
💒 በ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ማ የማህበረ አቅሌሲያ ዘገርጂ ማርያም የቴሌግራም ቻናል(official) 💒
✝ ኢትኤላውያን 🇪🇹
🕊️ ሐመረ ኖህ የመዝሙር ግጥሞች 🕊️
💒 ሰአሊተ ምህረት 💒
✝ አይናችን ነሽ ማርያም ✝
✝ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን✝
📚ኑ በትንሳኤው እንመላለስ⛪️
✝ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ✝
✝ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ✝
✝ ድንግል ማርያም እናቴ ✝
🇪🇹 ቀደምት ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
✝ መዝሙረ ማህሌት ✝
🖼 ስዕለ አድህኖ ➕ የቅዱሳን ስዕሎች
✝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ✝
📚 መፅሐፈ ኩፋሌ 📚
✝ መንፈሳዊ ህይወት ✝
✝ ማህተቤን አልበጥስም ✝
✝ ትምህርተ ወንጌል ✝
✝ ኆህተ ሰማይ ✝
✝ የኦርቶዶክስ ልጆች ✝
✝ ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ✝
ዕሴተ ✞ያሬድ
ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች
🔔 የበገና መዝሙሮች 🔔
🛑"አዳዲስ መዝሙሮች
✝ EOTC ✝
✝ ኦርቶዶክስ እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ ✝
✝ ዮዳሄ (Yodahe) Tube ▶️
📖 የራፋቶኤል መጣጥፎች 📖
💒 ልሳነ ቅዱሳን አበው 💒
📝 ግጥም 📝
🎬 ፊልሞች 🎬
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
📖 🎚 ኑ‌ የ‌እ‌ግ‌ዚ‌አ‌ብ‌ሔ‌ር‌ን‌ ቃ‌ል‌ እ‌ና‌ን‌ብ‌ 🎚 📖
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆  ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
صارحني 💌
Show all...
📝 መዝሙር ደብተሬ 📖
✝ ዘ ቅድስት ኪዳነምህረት ✝
💒 ንስሐ ግቡ 💒
✝ አማላጄ ማርያም ✝
✝ጸቃውዕ ሚዲያ ቤታ ለማርያም✝
✝ ሃይማኖት አበው ✝
✝ አማላጄ ነሽ እላታለሁ ✝
✝ ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ✝
📀 ተወዳጅ መዝሙሮች 📀
🎬 አዳዲስ ዝማሬዎች 🎬
💒 በ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ማ የማህበረ አቅሌሲያ ዘገርጂ ማርያም የቴሌግራም ቻናል(official) 💒
✝ ኢትኤላውያን 🇪🇹
🕊️ ሐመረ ኖህ የመዝሙር ግጥሞች 🕊️
💒 ሰአሊተ ምህረት 💒
✝ አይናችን ነሽ ማርያም ✝
✝ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን✝
📚ኑ በትንሳኤው እንመላለስ⛪️
✝ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ✝
✝ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ✝
✝ ድንግል ማርያም እናቴ ✝
🇪🇹 ቀደምት ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
✝ መዝሙረ ማህሌት ✝
🖼 ስዕለ አድህኖ ➕ የቅዱሳን ስዕሎች
✝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ✝
📚 መፅሐፈ ኩፋሌ 📚
✝ መንፈሳዊ ህይወት ✝
✝ ማህተቤን አልበጥስም ✝
✝ ትምህርተ ወንጌል ✝
✝ ኆህተ ሰማይ ✝
✝ የኦርቶዶክስ ልጆች ✝
✝ ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ✝
ዕሴተ ✞ያሬድ
ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች
🔔 የበገና መዝሙሮች 🔔
🛑"አዳዲስ መዝሙሮች
✝ EOTC ✝
✝ ኦርቶዶክስ እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ ✝
✝ ዮዳሄ (Yodahe) Tube ▶️
📖 የራፋቶኤል መጣጥፎች 📖
💒 ልሳነ ቅዱሳን አበው 💒
📝 ግጥም 📝
🎬 ፊልሞች 🎬
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
📖 🎚 ኑ‌ የ‌እ‌ግ‌ዚ‌አ‌ብ‌ሔ‌ር‌ን‌ ቃ‌ል‌ እ‌ና‌ን‌ብ‌ 🎚 📖
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆  ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
صارحني 💌
Show all...
📝 መዝሙር ደብተሬ 📖
✝ ዘ ቅድስት ኪዳነምህረት ✝
💒 ንስሐ ግቡ 💒
✝ አማላጄ ማርያም ✝
✝ጸቃውዕ ሚዲያ ቤታ ለማርያም✝
✝ ሃይማኖት አበው ✝
✝ አማላጄ ነሽ እላታለሁ ✝
✝ ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ✝
📀 ተወዳጅ መዝሙሮች 📀
🎬 አዳዲስ ዝማሬዎች 🎬
💒 በ/ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ማ የማህበረ አቅሌሲያ ዘገርጂ ማርያም የቴሌግራም ቻናል(official) 💒
✝ ኢትኤላውያን 🇪🇹
🕊️ ሐመረ ኖህ የመዝሙር ግጥሞች 🕊️
💒 ሰአሊተ ምህረት 💒
✝ አይናችን ነሽ ማርያም ✝
✝ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን✝
📚ኑ በትንሳኤው እንመላለስ⛪️
✝ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ✝
✝ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ✝
✝ ድንግል ማርያም እናቴ ✝
🇪🇹 ቀደምት ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
✝ መዝሙረ ማህሌት ✝
🖼 ስዕለ አድህኖ ➕ የቅዱሳን ስዕሎች
✝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ✝
📚 መፅሐፈ ኩፋሌ 📚
✝ መንፈሳዊ ህይወት ✝
✝ ማህተቤን አልበጥስም ✝
✝ ትምህርተ ወንጌል ✝
✝ ኆህተ ሰማይ ✝
✝ የኦርቶዶክስ ልጆች ✝
✝ ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ✝
ዕሴተ ✞ያሬድ
ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች
🔔 የበገና መዝሙሮች 🔔
🛑"አዳዲስ መዝሙሮች
✝ EOTC ✝
✝ ኦርቶዶክስ እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ ✝
✝ ዮዳሄ (Yodahe) Tube ▶️
📖 የራፋቶኤል መጣጥፎች 📖
💒 ልሳነ ቅዱሳን አበው 💒
📝 ግጥም 📝
🎬 ፊልሞች 🎬
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
📖 🎚 ኑ‌ የ‌እ‌ግ‌ዚ‌አ‌ብ‌ሔ‌ር‌ን‌ ቃ‌ል‌ እ‌ና‌ን‌ብ‌ 🎚 📖
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆  ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
صارحني 💌