cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EKREA ኢቅራዕ ኢስላሚክ መፅሀፍት እና አፕሊኬሽን🕋Amharic Islamic books&applications

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ አስተያየታችሁን በ @ABC_1_XYZ መናገርም ትችላላችሁ

Show more
Advertising posts
376
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
ንቁ niqu - Apps on Google Play

This book is all about the facts and biblical contradictions in Christianity.

Please join blachu like adrgu yhen design https://t.me/+hb-_ea3KQ9Y4MDJk
Show all...
Civil Department half life 2016

This is Civil engineering's halflife stuff. Join this group to known about the events concerning the halflife.

Repost from Yusuf App™
📲 ❏ አዲስ አፕ ተለቀቀ
ሸርሑ ሱንና | شرح السنة للإمام البربهاري | ሙሉ ደርስ Offline ያለኔት
➩🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዞሁሏህ-
◇ ➩📚 ከክፍል 01-45 ሙሉ ደርስ ◈
➩📥 ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! #share በማደረግ ለብዙሃን ይደረሰ ዘንድ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ያድርጉ!
◇ 📮 መሰል ጠቃሚ 📲አፖችን ማሰራት የምትፈልጉ ከስር ባለው አድራሻችን ይነግሩን! ❑በቴሌግራም-@Yusufapp_developer ▢App developer:- Yusuf App ኢስላማዊ እውቀት ከሁሉም በፊት! http://t.me/Yusuf_App1
Show all...
ቴሌግራም መጠቀም ላቆም ስለሆነ ነው ልባችሁን እንዳልሰቅል ብዬ ታሪኩን አሳጥሬ ሁሉንም በአንዴ የለቀኩት እና መልካም ንባብ ብያለው ቻው
Show all...
#እርዕስ_ያረፈደ_ተዉበት #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_ሃያ_ሁለት #የመጨረሻዉ_ክፍል "የሱፌ የኔ ፍቅር ታዉቃለህ አንተ ስለኔ ያላወከዉ አንድ ነገር አለ ሀኒ ወይም ሀናን የሀይዲ ፍቅረኛ የኔ የስጋ እህቴ ናት እናም የሱፌ ሀኒ በኔ ምክንያት ነዉ ወደዚ ሂወት የመጣችዉ ሀናንን ያገኘሁዋት ካደገች ቡሀላ ስለሆ በጣም እንደ ጓደኛ ነበር የማያት ከጊዜ ቡሀላ ግን አንደ እህቴ መቀበል ስለነበረብኝ ተቀብያት መኖር ጀመርኩ ሀናን ልጅ ሆነን የወሰዷት ሰዎች በጣም አንቀባረዉና በጥሩ ኢማን ነበር ያሳደጉዋት ነገር ግን እነሱ ከእናቴ ነጥቀዉ ወደ ኸይር ሲያመሯት እኔ እህቷ ደሞ ወደ ለራም አቀናሁዋት እናም ሀኒ ያን የመሰለ ሂወት ትታ ወደኛ ቤት ወይም አንተ ወደ መጣህበት ቤት መጥታ እንደኔ ሆነች እኔም ካለሷ መኖር መሞት መሰለኝ እናም አንድ ቀን ግን እኔም ወደ ሀራም ከተትኳት እናም ሁለታችንም ከመቆጨት በስተቀር አልተለወጥንም ነበር ብቻ የኔ ፍቅር ከባድ ጊዜ አሳልፈን አንድ ቀን ከዚ ሀራም እንደምንወጣ ተነጋግረን ነበር ወደ አዳማ የሄድ ነዉ እዛ ሄደን ስንመለስ ግን ሀራሙን ወደሃላል ለመቀየር ነበር የተማከርነዉ እናም ግን ያሰብነዉ ሳይሆን ያላሰብነዉ ነበር የገጠመን እኔም እሷን እንዳጣሁ ሁሉም ነገር ከበደኝ የግድ አንተን ከኔ ሌላ ሰዉ እንድትለምድ ነበር የተኮሳተርኩት እናም የሱፌ ከምነግርህ በላይ ከአንተ ጋር አንድ ቤት ሆኜ አላህን መገዛት እፈልግ ነበር ነገር ግን ምን ያረጋል ከረፈደ ወደሱጁድ ብወርድም ግን ቫይረሱ አልቀረልኝም በመድሀኒት ተቃጠልኩ አላህን ሳምፀዉ ያላነባቡትን እንባ ሲቃ ሲገጥመኝ አነባሁ መስራት ባለብህ ሰአት ካልሰራህ መሳቅ ባለብህ ሰአት ታለቅሳል አይደል የሚባለዉ እኔም የሱፌ ተዉበቴ ከረፈደ መሰለኝ ዛሬ ይህን ደብዳቤ ስፅፍልህ እየተሰናበትኩህ ነዉ አንተን ወደ ገደል ስለጠቆምኩህ ግን አፉ በለኝ እናም በቃ የሱፌ የራስህን ሂወት ለኔ ስትል ጀምር እናም የመጀመሪያ ልጅህን ደሞ ሀናን በልልኝ እቴን በጣም ስለምወዳት ነዉ እንደዛ ያልኩህ የሱፌ ለሁሉም ስህተቶቻችን አላህን ምህረት ጠይቀዉ አንተም በጊዜ ህክምና ጀምር እሺ ደሞ የሱፌ እናትና ወንድሜን አደራ ለአንተ ሰጥቼሀለዉ እናም በሳምንት አንዴ ቀብሬን መጥተህ ጎብኘዉ ቦታዉን ደሞ ወንድሜ ያሳይሀል ደና ሁንልኝ የኔ ዉድ መልካም ሂወት ላንተ ብዬሀለዉ። {የአንተ አፍቃሪ ሲሀም} ይላል ሲሁ ደብዳቤዋን አንብቤ እንደጨረስኩ በእንባ እየታጠብኩ ነበር  ሲሁን እንዳጣሁ የግድ ማመን ነበረብኝናም እራሴን ወደ አላህ ለማዞርና በስህተትም ወደ ሴት ላልዞር ለራሴ ቃል ገባሁ ተነስቼ ተጣጥቤ ወደ መስጂድ አቀናሁ እዛ ሆኜ ከልቤ ተፀፅቼ አለቀስኩ አመፄን አንድ በአንድ አስታዉሼ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ አላህ መሀሪም አዛኝም ነዉና ከላዬ ላይ የሆነ ነገር ቀለለኝ ሱና ሰግጄ እስከ አስር ቁረአን ቀራሁና አስር ሰአት ሲደርስ ሰግጄ ወደ ሀይዲ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ እናም ሰፈራቸዉ ስደርስ ደዉዬለት እንዲወጣ ጠየኩት እናም እሱም ሰዉ ልክልሀለዉ ቤት ና አለኝ እንዲወጣ ብለምነዉ አይሆንም ና ያላየህዉና ማየት ያለብህ አንድ ነገር አለ አለኝ እኔም እሺ ብዬዉ ሰዉ እንዲልክልኝ ነግሬዉ ስጠባበቅ አንዲት ሴት መጥታ አሰላም ከለይክ የሱፍ አንተ ነህ አለችኝ ማንነቷን እንኳን ቀና ብዬ ሳላይ አዎ አልኳት ሀይዲ ልኮኝ ነዉ ተከተለኝ ብላ ቀድማኝ መራመድ ጀመረች ከአንድ ትልቅ ጊቢ ደረስን እናም አንኳኩቷ ገባች እናም ወደ ዉስጥ ተከተለኝ እያለችኝ ከአንድ ክፍል ግባ ብላኝ ሄደች እኔም እየፈራሁ ገባሁ ሀይዲ ከእንቅልፉ አልተነሳም መሰለኝ እኔን ሲመለከተኝ ተነስቶ ተቀመጠ ከአልጋዉ ግን አልወረደም እኔም ሀይዲ አልተሻለህምንዴ ስለዉ አልሀምዱሊላህ አሁን ደናነኝ ግን ሰሞኑን ለምን ጠፋህ አለኝ የተፈጠረዉን በሙሉ ነገርኩት እሱም ደንግጦ እንባዉ በላዩ ላይ እስኪርስ አለቀሰ ሀኒና ሲሁ እህት መሆናቸዉ አስደነገጠዉ ነገር ግን ሰብር ለማድረግ ሞከረ አላህን አላማረረዉም በጣም ደስ አለኝ ሀይዲ ሰብር ማድረጉን ቀጠለ እናም አልሀምዱሊላህ ብሎ በእጁ አንድ ነገር ላይ ጠቆመኝ ስዞር ግን የምር ደነገጥኩ ሀይዲ ሽባ ሆኗል ከወገብ በታች ብዙም አይንቀሳቀስም የመትረፍ እድል ቢኖረዉም ግን ጊዜ ይፈጃል በጣም ደነገጥኩ ለምን ሳትነግረኝ ቆየህ ስለዉ የዛን ቀን የምትመለስ ስለመሰለኝ ነበር አለኝ። "እኔም ወደድሮዬ ተመልሼ ሀይዲን እንደወንድም መንከባከቤን ቀጠልኩ ሀይዲን ከትምርት መልስ ሁሌ ቁረአን ከአሊፍ አስጀምሬ አስቀራዉ ጀመር አሁን ከሁሉም ጋር ተለየን አፊያ የት እንዳለች አናዉቅም እናም ህክምና ጀምረን የኤች አይቪ መድሀኒት እየተከታተልን እንወስዳለን የኔም ቤተሰቦቼ የደረሰብኝንና የነበርኩበትን ሂወት ከጊዜ ቡሀላ ደርሰዉበት ቢያዝኑም ቢበሳጩም ግን ለጊዜዉ በሰብር አልፈዉት ከጎኔ ሆነዉ እየተረዱኝ ነዉ አልሀምዱሊላህ አላህን ካለ ፍርሀቻ ሳምፅ ግን እሱ እዝነተ ሰፊ ነዉና በቀላሉ አስተምሮ ምሮኛል አልሀምዱሊላህ ታሪኬን በዚሁ አበቃሁ። {ተፈፀመ} #የፀሀፊ_ፎዚያ_መልእክት "በመጀመሪያ ተከታትላቹ ስላነበባቹ አመሰግናለሁ በመቀጠል ደሞ ሁላችሁም ወጣቶች ተመከሩ ሁላችንም እንመከር ወላሂ በሀራም የተጀመረ ፍቅር አላህ ካላዘነልን በስተቀር መጨረሻዉ አያምርም እኔ እህታቹ ይህን ስፅፍ የተሻልኩኝ ሆኜ አይደለም ነገር ግን መጥፎ ነገርን መቅረብ ስለሚያስፈራኝና ብዙ የተቀጣ ሰዉ ሰዉ ስላየሁኝ ነዉ እናም ሀሳቤን ለመግለፅ የምፈልገዉ ነገር ቁረአን ስናከትም በጥሩ ስንሰራ ብቻ እንጂ ጥሩ ሂወት የምንኖረዉ ቀርተን ካመፅን አወዳደቃችን መጥፎ ነዉ አንድን ወንጀል ሰርተን ነገ ቶብታለዉ ማለት ደሞ በጣም ከባድ ነዉ ምክንያቱም መሞቻችንን ብናዉቅ ነበር እንደዛ ማለት የምንችለዉ እናም መሞቻችንን ስለማናዉቅ ተዉበትን ለነገ ቀጠሮ መስጠት አያስፈልግም ሀራም ላይ ገብቶ ለመዉጣት ሰዉን ማስፈቀድ አይጠበቅብንም ወደ ሀራም ለመግባት ደሞ አስበን አይደለም ግን ደሞ ሀጂ ነብይን ስንጨብጥና ሀያችን እስኪጠፋ ስንመለከት ልንፈራ ይገባል ወላሂ መፍራት አለብን ወደ ሀራም ለመግባት እነተንደረደርን ነዉ ማለት ነዉ እህት ወንድሞቼ በዚ ግዜ ማወቅ መስሎን አጉል ላይፍ ፍቅረኛ ብለን ከምንጃጃል አንዴዉኑ ቶሎ መዘወጅ ወይም ኒካህ ማሰር ነዉ ያለብን ይህም ብዙዎቹ ጓደኛ ሳንይዝ እንዴት እናስራለን የሚል ነገር በጭንቅላታቹሁ ይመጣል እናም አሁን በደንብ ስሙኝ አንድ ሰዉ ለሀላል ከፈለገን ብቻ ለብቻ እንገናኝ አይለንም ፍቅር እንጀምር አይለንም ምክንያቱም ሀራም ካልፈለገ ላገባሽ እፈልጋለዉ ብሎ ኒካህ አስሮ ጓደኝነት መጀመር ይችላል ሀራም ስለማይሆን እናም በዚ ሀሳብ ካስቀየምኳቹ ለአላህ ብላቹ አፉ በሉኝ እኔ ፎዚያ&ዮሚፍ ነበርኩ ደና ሁኑ ወሰላም አለይክ ወረህ መቱላህ ወበረካቱሁ ይቀላቀሉን👇                                         ይቀላቀሉን👇
Show all...
#እርዕስ_ያረፈደ_ተዉበት #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_ሃያ_አንድ "ያለችኝ ቦታ እየሄድኩኝ በመንገድ አንድ ከሰዉ ገንዘብ የሚለምኑ ትልቅ ሰዉዬ ልጄ ብለዉ ጠሩኝ እኔም አቤት ብዬ አጠገባቸዉ ስሄድ ሀይዲ ደወለልኝ እሳቸዉ መቆማቸዉን እረስቼዉ ስልኩነሰ አንስቼ ወዬ እያልኩ ስሄድ ሽማገሌዉ ተናደዉብኝ ያሰብከዉ መና ይቅር ብለዉ ረገሙኝ የእሳቸዉ እርግማን ቢያስደነግጠኝም ተመልሼ ግን አፉታ ለመጠየቅ አልቻልኩም ምክንያቱም ሀይዲ የደወለልኝ የሆነ መረጃ ሊሰጠኝ ነበር የመሰለኝ ብቻ ለመመለስ ብፈልግም አልቻልኩም ብቻ እንደምንም ብዬ ስልኩን እያወራሁ ከሲሁ ሰፈር ደረስኩ በቃ ደና ሁን ብዬ ስልኩን ዘግቼዉ ወደ ሰፈሩ ገባሁኝ ልጆችን ስጠይቅ ቤታቸዉን አሳዩኝ ቤቱ የቀበሌ ነዉ መሰለኝ ያረጀ ይመስላል እኔም ፈገግ ብዬ ወደ በራፉ እየተጠጋሁ ኢንሻአላህ ከሲሁ ጋር እናድሰዋለን እያልኩኝ እያሰብኩ በሩን አንኳኳሁኝ አቤት የሚል ድምፅ ይሰማኛል አሁንም ሳንኳኳ ግቡ የሚል የሴት ድምፅ ሰማሁ አሰላም አለይኩም ብዬ ወደ ዉስጥ ገባሁ ወአሌይኩም ወሰላም መርሀባ ብላኝ አንዲት ከወጣትነት በቲኒሹ እየወጣች ያለች አንዲት እናት እንድቀመጥ ጋበዘችኝ  እኔም ሄጄ ካለማንገራገር ተቀመጥኩ <እኔ ምለዉ ምን ፈልገህ ነዉ ልጄ <<እኔ የሲሀም የቅርብ ጓደኛ ነኝ <ምን ብለዉ ማልቀስ ጀመሩ በጣም ደነገጥኩ ምን እንደምል ጠፋኝ <<ማዘር እባኮትን አያልቅሱ እኔ በጣም ነዉ የምወዳት አሁን የመጣሁት እሷ የኔ ሀላል እንድትሆን  ላስፈቅዳትና ላበስራት ነዉ ኡሚ አታስቢ ሀቋን ጠብቄ ነዉ የማስተዳድራት "ይባስ ብለዉ በጣም ተንሰቅስቀዉ አለቀሱ እኔም በጣም ግራ ተጋብቼ ምነዉ ቤት ተሳሳትኩኝ መሰለኝ  ብዬ ልወጣ ስል ዩሱፍ ማለት አንተ ነህ? <<አዎ እኔ ነኝ ዩሱፍ ማለት <ልጄ ብለዉ በተረጋጋ ድምፅ ፈገግ ብለዉ አዩኝ <<ምነዉ ኡሚ ችግር አለንዴ <አዎ ልጄ ይወልህ ምን መሰለህ  ሁሉም ያአላህ ነዉ ወደ አላህም ተመላሽ ነዉ። "አላህ እኛን ሲፈጥረን ለፈተና ነዉ የኔ ልጅ በሂወትህ ስትኖር ማንም ምንም ነገር ላይ ሀብት ላይ ትዳር ላይ እዉቀትና እዉቅና ላይ ቢቀድሙህ አትዘን አንተ አላህን በመፍራት መቅደም ስለሚጠበቅብህ። <<ኡሚ እሱስ ልክ ነዉ ግን ሲሀምን ከገባሁ እስካሁን አላየሁአትም ምነዉ እሷ የለችምንዴ <አዎ ልጄ አረፈድክ ልጄ ሲሁ ልጄ ወደ አኼራ ከሄደች ወራቶች አስቆጥራለች <<ምን ሲሁ ሞተች እኔን ትታኝ ሄደች <ልጄ ሁሉም ነፍስኮ ሞትን ቀማሽ ናት <<ኡሚሚሚሚሚ እያልኩ እራሴን አዞረኝ "ስነቃ ግን ከነ ሲሁ ቤት አልወጣሁም ጭራሽ ፍራሽ ላይ ተኝቼ ነበር አጠገቤ አንድ አነስ ያለ ልጅ አለ እናትየዋ ቁጭ ብለዉ ሙስፓ እየቆጠሩ ነዉ ግራ ገባኝ ተነስቼ ልወጣ ስል <ልጄ <<አቤት ኡሚ <አንድ መልክት ነበረህ ብለዉ አንድ የተጣጠፈ ወረቀት ሰጡኝ ምንድ ነዉ ስላቸዉ አንዴ ቁጭ በል እስቲ ብለዉ በሀሳብ ትክዝ አሉ እኔም የሚሉትን ለመስማት እያየሁ ዝም አልኳቸዉ "ሲሀሜ እህቷን ካጣች ቡሀላ ሰብር ማድረግ አቅቷት ነበር <<እንዴ እህቷን ማለት የጠፋችዉን ለማለት ፈልገዉ ነዉ ብዬ ለራሴ ጠይቄ ዝም አልኩ>> <እናም ልጄ በጣም ብቸኝነት ተሰምቷትም ነበር ታድያ በለቅሶ ጊዜ ስለተጎዳች በዛ የተነሳ ትታመም ጀመር ልክ በታመመች በሳምንቱ ሀኪም ቤት ይዘናት ለመሄድ ስነሳ እሷ አይሆንም ለብቻዬ እሄዳለዉ ብላኝ ለብቻዋ ሄደች ስትመለስ ግን በጥቁር ፌስታል በጣም የተፈለቀቀ ክኒን ይዛ መጣች የምን ክኒን ነዉ ብለን የበሽታዋን አይነት ስንጠይቃት አትነግረንም እሷ ስትፈጠርም ክኒን የሚባል ነገር መዉሰድ አትወድም እናም በጣም እየታመመች መጣች በባዶ ሆዳ ነበር ብዙ ጊዜ መድሀኒቱን የምትዉጠዉ እናም እማዬ ተቃጠልኩልሽኮ እያለች አንዳንዴም ታለቅሳለች እኔም አብሬአት አለቅሳለዉ እናም አንድ ቀን ይሄን ወረቀት እኔን ፈልጎ የሚመጣ የሱፌ የሚባል ልጅ ይመጣል  እናም ለሱ ስጭልኝ ግን እሱን እንደምትይዉ እኔን ስትፈልግ ዱአ አድርግልኝ በይዉ ብላኝ እኔን  አቅፋ ታለቅስ ጀመር እኔም አባብያት ምን ትበያለሽ ስላት እሷም ከሱቅ ጁስ እንዳመጣላት ጠየቀችኝ እኔም እሺ ብዬ ላመጣላት ወጣሁ በመሀል እዛዉ ቆይቼ ስመጣ የኔ ሲሁ በዚ በምታየዉ ቤት ዉስጥ ብለዉ የጣራዉን አንድ የተጋደመ እንጨት አሳዩኝ ። እናም በዚ ቤት እራሷን አንቃ ሩሁዋ ወጥቷ አገኘዋት ልጄ ተቃጥላ ሞተች ልጄ በራሷ እጅ ካለ ርህራሄ ነፍሷ ላይ ጨከነች ብለዉኝ እሳቸዉ ሰብር ማድረግ እስኪያቅታቸዉ ያለቅሱ ጀመር እኔም እንባዬን እያፈሰስኩ ወረቀቱን እንደጨመኩ ይዤ ወጣሁ። "ከነሲሁ ቤት ከተመለስኩ አንድ ሳምንት ሆነኝ ያለፉት ቀናቶች ፈታኝ ነበሩ ሀይዲንም አላገኘሁትም እንደምንም ብዬ አሁን እየተፅናናዉ ነዉ የሲሁን ደብዳቤ ለማንበብ ከፈትኩት!! ~የሱፌ የኔ ፍቅር~ <<ብላ ጀመረች>> የሱፌ የኔ ፍቅር ታዉቃለህ አንተ ስለኔ ያላወከዉ አንድ ነገር አለ ሀኒ ወይም ሀናን የሀይዲ ፍቅረኛ የኔ የስጋ እህቴ ናት... #ክፍል_ሃያ_ሁለት_ይቀጥላል ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን ይቀላቀሉን👇                                         ይቀላቀሉን👇
Show all...
#እርዕስ_ያረፈደ_ተዉበት #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_ሀያ "ወደ ሀይዲ ጋር ሄድኩኝ ሀይዲ ኮማ ዉስጥ ገብቷል ቤተሰቦቹ እሱ ክፍል ከዉጪ በኩል ሆነዉ ወደዉስጥ ያዩታል እኔ ስሄድ ግን ወደኔ ዞራ እህቱ ታለቅስ ጀመር የሀይዲ ሁኔታ አስጊ ሆነ መሰለኝ ሊነቃ አልቻለም እንደምንም ብዬ እሱ እስኪነቃ መጠበቅ ጀመርኩ ቤተሰቦቹ የሱ ጓደኛ መሆኔን ሲረዱ እነሱ ቤት ሄደዉ እንዲያርፉ ለመንኳቸዉና ሄዱ እኔ ሀይዲ ጋር ቁጭ ብዬ አስብ ጀመር እናም ብቻዬን ለማዉራት ይቃጣኝ ጀመር ብቻ በዝምታ ካሰብኩ ቡሀላ ሀይዲ አጠገብ ገብቼ ተቀመጥኩኝና ማዉራቴን ጀመርኩ <<ሀይዲ ታዉቃለህ በጣም ልበ ንፁ ነህ ቆሻሻዉ እኔዉ ነኝ በአገኘሁት አጋጣሚ አዉርቼህና ተረድቼህ ቢሆን ኖሮ ይሄ ክስተት በጥሩ ያልፍ ነበር አላህ ግን እኔን ለምን በቲኒሹ ብቻ ቀጣኝ ለምን ሀይዲዬ ታዉቃለህ እንደ ወንድሜኮ እወድህ ነበር የምር በተለይ የመጀመሪያ ቀን ስለ ሀኒ ልጠይቅህ ካፌ ያገኘሁህ ቀንኮ በጣም ወድጄህና ወንድሜ ሆነህ ነበር የመጣህዉ ሀይዲዬ አፉ በለኝ በአላህ ስለ ዲን እያወኩኝ እዉቀትን ነፍጌህ አንተን ለመጥፎ ደረጃ ዳረኩህ አፉ በለኝ እያልኩ እንባዬን መቆጣጠር ስለከበደኝ እሱ እጅ ላይ ተደፍቼ መንሰቅሰቅ ጀመርኩ በዚ መሀል ግን አንዲት ዶክተር ገብታ አሰላም አለይክ ወንድሜ እባክህ ቀና በል አላህን በለቅሶ አታማረዉ ሁሉም የአላህ ዉሳኔ ነዉ ብላ አባነነችኝ ቀና ብዬ ወደሷ ስመለከት እሷ ያደረገችዉ ሙሉ ጅልባብ ነበር እናም እኔ ወደሷ ስመለከት እሷ አይኗን ሰበረች በጣም ነበር የደነገጥኩት የምር የድሮዉን የሱፌን ነበር ያስታወሰችኝ ያአሏህ ምን እየተካሄደ ነዉ ደሞስ ስለምን አዉቃ ነዉ ሁሉም የአላህ ዉሳኔ ነዉ ያለችኝ ከሀይዲ መተኛት ዉጪ የምታዉቀዉ ነገር ይኖር ይሆንዴ በማለት እያሰብኩ ከአጠገቧ ወጣሁና ደጅ ላይ ቁጭ ብዬ እሷ እስከምትወጣ መጠባበቅ ጀመርኩ እሷም ወጣችና ወደኔ ሳትዞር ወደ ቢሮዋ አመራች እኔም ወደ ሀይዲ ጋር ተነስቼ ገባሁ>> "ቀናቱ እየነጎደ እኔም አልፎ አልፎ ወደቤት እየሄድኩኝ እንደምንም 2 ወር ሆነኝ እናም ሀይዲ ጋር አንድ ቀን ሁሉንም ሸኝቼአቸዉ ተቀመጥኩኝ እናም ሀይዲ ጋር እንደተለመደዉ ተደፍቼ አፉ በለኝ እያልኩ እጁ ጋር ስደፋ ዲንገት ጭንቅላቴን የሆነ ሰዉ ነካ አደረገዉ ደንግጬ ቀና ስል ሀይዲ ነቅቶ እንባዉ እየፈሰሰ ነበር እኔ ወንድሜ ብዬ ተነስቼ ፊቱን ተመለከትኩ ፊቱ በጣም ዉብ ሆኗል የታመም አይመስልም እኔም ሁኔታዉ እየገረመኝ በቃ ይደክምሀል ተኛ አልኩት እሱም አይ አይደክመኝም አለኝ <<እንዴ ሀይዲ ምን ማለትህ ነዉ ዛሬኮ ነዉ የነቃህዉ እናም ተኛ ይደክምሀል <አይ የሱፌ እኔኮ የሚፈጠረዉን እያንዳንዱ ነገር አቀዋለዉ እያየሁ ነበር እናንተ ግን የነቃሁ ስላልመሰላቹ ነዉ  ያላስተዋላቹሁኝ ግን አሁን አልሀምዱሊላህ ደናነኝ <<ግን እራስህንኮ ስተህ አታዉቅም ነበር እንዴት ደሞ የድካም ምልክት እንኳን አይታይብህም <የሱፌ ትዝ ይልሀል የመጀመሪያ ጊዜ እዚ ገብተህ ቤተሰቦቼን ወደቤት ሸኝተህ እኔ ጋር ተደፍተህ አፉታ እየጠየከኝ ነበር አስታወስክ <<አዎ እንዴት እረሳዋለዉ ብለህ ነዉ <የዛን ቀን የመጣችዉን ዶክተርስ አስታወስካት <<አዎ ኢማን ያላት ትመስላለች ማሻአላህ አይኔን እንኳንኮ አላየችዉም <እሷ መንታ እህቴ ናት ነፊሳ ትባላለች እኔ የነቃሁት በገባሁ በ5 ቀኔ ነበር ነገር ግን መነሳቱ ከበደኝና የሀኒንም ሞት መሄዱ አስፈርቶኝ ሁሉም ጨለማ ሲሆንብኝ እሷ ሁሌም ከምግብ ቡሀላ የእንቅልፍ መድሀኒት እየሰጠችኝ ነበር የምተኛዉ አንተ መመላለስ ስትጀምር ግን መድሀኒቴን አቁሜ እንዳልነቃ ሰዉ ሆኜ የአንተን ሁኔታ መከታተል ጀመርኩ አንተ ግን እንደወንድም ሁሌም እራስህን ስትወቅስና በኔ ጥፋት መልሰህ እኔኑ አፉታ ስትጠይቀኝ እየተፀፀትኩኝ ነበር እናም ከአጠገቤ ሳትርቅ አብረህኝ ስለታመምክ  አመሰግናለዉ እናም የሱፌ አፉ በለኝ ወንድሜ ብሎ ሀይዲ ተንሰቅስቆ ያለቅስ ጀመር እኔም ተነስቼ አቅፌዉ ከለቀስኩና በመሀላችን ያለዉ እርቀት ፈርሶ ወንድሟሟችነትን አየሁ በዚ መሀል ነፊሳ ገብታ ይበቃቹሀል ተላቀቁ ብላን ሳቀች እኔም ፈገግ ብዬ <<እኔ ምልህ ሀይዲ <ወዬ ወንድሜ <<ስለ ሲሁ ላወራህ ነበር <የሱፌ ስለ ሲሁ ምን << ያዉ ሀይዲ ስለሁለታችን ያላወከዉ ነገር የለም ግን ብዬ እሷ ያለችኝን እያንዳንዱን ነገር ነገእርኩት <በጣም ተገርሞ ሲሁ ለሶስት ወር አስችሏት አንገናኝም አለችህ <<አዎ ሀይዲ እኔም ገርሞኛል <እና ምን አሰብክ መቼስ እንደ በፊቱ ለተራ ጊዜ እንደማይሆን አስባለዉ <<ሀይዲ አሁን ሳገኛት መቼ ለኒክሀ ሽማግሌ እንደምልክና እሷን ሚስቴ ላደርጋት እፈልጋለሁ በቃ ሀራሙን ወደ ሀላል መቀየር አለብኝ ግን ምን እንደምላት እራሱ ግራ ገባኝ <የሱፌ አትፍራ አሁን ሶስት ወር ሞላህ ከተናገረችህ <<አዎ እንደዉም አንተ ጋር ከመጣሁ ቡሀላ 10 ቀን አለፈኝና ሶስት ወር ከአስር ቀን ሆነኝ የተባባልነዉን ነገር  አንተን ማማከር ስላለብኝ ነዉ ግን ሲሁ እሺ የምትለኝ ይመስልሀል <እንዴ የሱፌ ትጠራጠራለህንዴ በቃ ለማንኛዉም ለሰርጉ ቆሜ ባላጅብህም ቁጭ ብዬ ግን አይሀለዉ <<እንዴ ወንድሜ አንተማ የግድ መቆም አለብህ ብቻ አሁን ልሂድ <የሱፌ <<ወዬ ወንድሜ <ስትመለስ ግን እኔ እፈልግሀለዉ ከዚ አልወጣም <<ወንድሜ መጀመሪያ ደስታዬን ለአንተ ለመናገር እመጣለሁ <ደና ሁን ወሰላም አለይኩም ወረህ መቱላሂ ወበረካቱሁ የሱፌ የኔ የዋህ ና አዛኝ ጓደኛዬ አላህ ኸይሩን ይምረጥልህ እኔ አላህ የእጄን ነዉ የሰጠኝ አንተ ግን በኛ ሰበብ ተሰቃየህ ደና ሁን መልካሙን ሁሉ አላህ ይምረጥልን> "እህቴ ለምን አትሰሚኝም የማገባትኮ ስንት ነገር አብራኝ የሆነችዉን ፍቅረኛዬን ነዉ <የሱፌ ለምን ድርቅ ትላለህ <<እሺ ምን አድርግ ነዉ የምትይኝ ደሞ ቶሎ ቶሎ በይ ስልኬ ካርድ ሊዘጋ ነዉ <የሱፌ በጣም ተቀይረሀል ይህዉ አሁን ለኔ እራሱ እንደድሮ አይደለህም እሺ እሱን ተወዉ ማንን ነዉ የምታገባዉ ኢማኗስእንዴት ናት ቤተሰብ ያዉቃታል ቤተሰቦቿስ <<ደና ሁኚ እህቴ በቃ ከኔ ጋር ማዉራቱ ከደበረሽ ተይዉ እኔ ላገባት ከፈለኩስ ደሞኮ እየጠበቀችኝ ነዉ አሁን ለቤተሰብ ትነግሪልኛለሽ ወይስ በራሴ ሄጄ ላግባት <የሱፌ እንዳታረገዉ እንደዛማ ሀራም ነዉ። እሺ በቃ አሁን ለአባዬ ደዉዬ ሽማግሌዎቹን እንዲያዘጋጅና አንተ እንድታገባ እነግረዋለዉ ግን በምን ልታስተዳድራት ነዉ <<የኔ ዉድ እህት አመሰግናለዉ የምንተዳደረዉ የቀን ስራ እየሰራን ማታ እየተማርን ነዉ በቃ አሁን ሄጄ ልንገራት ደና ሁኚልኝ "አሁን አልሀምዱሊላህ ሁሉም ነገር ተስተካክሏል ብዬ ወደ ሲሁ ስጓዝ አባባ ከአጎቴ ጋር ደዉሎ የኔጎረምሳ ለካ አድገህልኛል በል እናትህንም እንድትዘጋጅ ብር ሰጥቼ እኔም ከወንድሜ ጋር ይሀዉ እየተማከርኩ ነዉ አንተ እስክትመለስ ድረስ እኔ ሽማግሌዎችን ሰብስቤ እጠብቅሀለዉ ብቻ ቶሎ የልጅቷን ነገር አሳዉቀን ብሎኝ በደስታ ስልኩን ዘጋዉ>> "እኔ ሲሁ ከዚ ቀደም እኔን ታገኘኛለህ ብላ ያለችኝ ቦታ እየሄድኩኝ በመንገድ አንድ ከሰዉ ገንዘብ የሚለምኑ ትልቅ ሰዉዬ ልጄ ብለዉ ጠሩኝ እኔም አቤት ብዬ አጠገባቸዉ ስሄድ ሀይዲ ደወለልኝ እሳቸዉ መቆማቸዉን እረስቼዉ ስልኩነሰ አንስቼ ወዬ እያልኩ ስሄድ ሽማገሌዉ ተናደዉብኝ ያሰብከዉ መና ይቅር ብለዉ ረገሙኝ.... #ክፍል_ሃያ_አንድ_ይቀጥላል ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን
Show all...
👍 1
#እርዕስ_ያረፈደ_ተዉበት #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ "እንቀስቅሳቸዉ ብያት ወደዉስጥ ይዣት ገባሁ ነገር ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ ሀናንና ዳጊ ሀይዲ ወድቀዋል እንደምንም ብዬ ያመጣንን ሹፌር ደዉዬ ጠራሁት የተፈጠረዉን ነገርኩት እሱም ፖሊስ ይዞ መጣ እኔ ሲሁ እያለቀሰች ስለነበር ከቤቱ አስወጥቻት እያባበልኳት ዉጪ ሹፌራችን ቆሞ እንድይዛት አደረኩና እኔ ወደ ፖሊሶቹ ተመለስኩ" ሀይዲ በሂወት አለ አልሀምዱሊላህ አልሞተም ሀኒና ዳጊ ግን ተገድለዋል ሀይዲ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ተወሰደ። "ሲሁ ግን አሁንም ታለቅስና ዲንገት ፍዝዝዝ ትል ጀመር እኔ ነገሩ ሁሉ ቢያስደነግጠኝም ዉስጤ መጀመሪያም በአፊያ በሽታ ስለተደናገጥኩ አሁንም ድንጋጤዉ ቢሰማኝም ግን የኔ ተራ መች ነዉ እያልኩ በዉስጤ አወራ ጀመር ብቻ ፖሊሶች የሀኒንም የዳጊንም አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ሸኝተዉ አፊያን መፈለግ ጀመሩ አፊያ ደሞ ከጓሮ በኩል ተደብቃ እነሱን ስታይና ድምፃቸዉን ስትሰማ እየሮጠች መጥቴ እኔ ላይ ተጠመጠመች ሲሁ ግን እሷ እንደዚ ሁሉ እኔ ላይ ስትሆን አይታ እንዳላየ ሆና ዝም አለች ፖሊሶች ሶስታችንንም ለምርመራ ይዘዉን ሄዱ ከቦታዉ እየወጣን እኔ ወደ መኪናዉ መስኮት ስዞር❌ ይሄንን የኤክስ ምልክት አስታወስኩት ቆይ ብዬ ጮኬ መኪናዉን አስቆምኩትና ወርደን ወደ ❌ ምልክቱ ጋር መጠጋት ጀመርን ፖሊሶችም አብረዉን ተጠጉ ❌ከዚ ምልክት ጀርባ ግን 3 ወረቀቶች አሉ አንዱ ፖሊስ በጓንት አነሳዉና አንዱን ከፈተዉ  በወረቀቱ ላይም  የተፃፈዉ እንዲህ ይላል [በድንበሬ በቤቴ ሰላሜን አጊንቼ በተቀመጥኩበት መጣቹሁብኝ በሂወት መመለስ ከፈለጋቹ በገባቹሁት እግራቹ ዉጡ ይላል] ሁለተኛዉንም ከፈተዉ [ከተበታተናቹሁበት ተሰብሰቡና ዉጡ የሚል ነበር] ሶስተኛዉንም ሲከፍተዉ ግን [ነግሬአቹ ነበር ደብዳቤዬን እንኳን አላስተዋላቹሁትም ፅፌ ጠረፔዛዉ ላይ ትቼ ላቹ ነበር አሁን አንድ በአንድ ማለቅ ስለሚኖርባቹ የትም ብትገቡ አታመልጡኝም ይላል] "ፖሊሶቹ መልሱን ያገኙት መሰለኝ ምክንያቱም ወደኛ ዞረዉ አትፍሩ ብለዉ ያረጋጉንና አዲስ አበባ ይዘዉን እንደሚመለሱ ነገሩን ሲሁ ግን አትናገር አትጋገር ዝምታን መርጣለች እኔ አጠገቧ ሄጄ ተቀመጥኩ እሷ ደሞ ትሸሸኝ ጀመር የሲሁ ሁኔታ ግራ ቢያጋባኝም አፊያ ግን አጠገቤ ስላለች ልናገራት አልፈለኩም ዝም እንደተባባልነሰ አዲስ አበባ ተመልሰን ገባን ሁላችን የዳጊና የሀኒን አስክሬን እንዲጠብቁን ስለተደረገ ለቤተሰቦቻቸዉ ተደዉሎ የተፈጠረዉ ነገር ቢያስደነግጣቸዉም ሲሁም አብራቸዉ ከሀናን ቤተሰቦች ጋር ሄደች አጠገቧ ሲደርሱም አንቺ ነሽ የሷ ገዳይ ብለዉ ተጠምጥማ አንዲት ትልቅ ሴት ተጠምጥማባት ታለቅስ ጀመር እኔም ሁኔታቸዉ ቢገርመኝም የጓደኛዋ እናት ስለሆኑ ነዉ ብዬ ዝም አልኩ እሳቸዉም አቅፈዋት ይዘዋት ሊሄዱ ሲሉ እኔን አይታ ወደ ሁዋአላዋ ተመለሰችና" <ዩሱፍ <<ወዬ የኔ ፍቅር <ስለሁሉም ነገር ይቅር በለኝ <<እንዴ ሲሁ አንቺ ደሞ ምን አደረግሽኝ <በኔ የተነሳ ነዉ እዚ ሁሉ ማጥ ዉስጥ የገባህዉ እናም እናም በቃ ከዛሬ ቡሀላ ይብቃን <<ምኑ ነዉ የሚበቃን ሲሁ <ሁሉም ነገር <<ቆይ በኔ ጨከንሽ በቃ እኔ አንቺን ካላየሁ መዋል እንደማልችል ታዉቂ የለንዴ አሁን ምን ተገኝቶ ነዉ በአንድ ለሊት ሀሳብሽን የቀየርሽዉ <ዩሱፍ እባክህ መገናኘት የለብንም ቢኖርብን እንኳን ከሶስት ወር ቡሀላ ከሆነ ብቻ ነዉ <<እሺ ቢያንስ ዛሬ የሀኒን ለቅሶ እንኳን አብረን እንዋል <የሱፌ ሰፈር አድርሰህኝ ብቻ ከተመለስክ ነዉ አለበለዚያ ግን በቃ አትምጣ <<እሺ አላወራም ግን ሰፈራቹ  አስካደረስሽ ቢያንስ ነይ አጠገቤ ሁኚ <ዩሱፍ <<ወዬ ሲሁ <አላህን ፍራ አትቀልድ <<ይሄ ቃል ከሷ አንደበት መዉጣቱ አስደነገጠኝ ሲሁን ላለማጣት ዝም ብዬ ወደሷ ሳልዞር ለነሱ ወደመጣዉ መኪና ገብቼ ተቀመጥኩ ሲሁም አብራኝ ወጥታ መጣች አፊያም ከዳጊ ቤተሰቦች ጋር ሄደች እኔም ከነ ሲሁ ጋር መጓዝ ጀመርኩ እናም ከሆነ ሰፈር ስንደርስ አስቁማዉ ይዛኝ ወረደች የሱፌ እዚ ድረስ ከመጣህ ይበቃል እኔን ፍለጋ ከመጣህ ከሶስት ወር ቡሀላ እዚ ታገኘኛለህ አሁን የጓደኛዬ ሀዘን ላይ ስለሆንኩ በቃ ደና ሁን ብላ አንገቴ ስር ተጠምጥማ ይቅርታ ብላ ተንሰቅስቃ አለቀሰች እኔ ወንድነቴ ስለያዘኝ በመንገድ ማልቀሱ ከብዶኝ ወደመኪናዋ ሸኘዋትና እኔ ወደቤቴ ተመለስኩ ከሶስት ወር ሳይሞላኝ ግን እሷን ፍለጋ ለመሄድ በጣም ተጨነኩ እሚገርመዉ በተለያየን በ15ተኛዉ ቀን የሆነ ሀይለኛ ጭንቀት ላይ ነበርኩ ነገር ግን የቫይረሱ ስሜት መስሎኝ ዝም ብዬ አለፍኩት እናም ሀይዲ ከ1 ወር ቡሀላ  ስልክ ተደወለልኝ አንስቼ ሄለዉ ስል ሴት ነበረች ሲመስለኝ የሀይዲ እህት ናት እናም ሆስፒታል እንድመጣ አድራሻ ሰጥታኝ ወደ ሀይዲ ጋር ሄድኩኝ ሀይዲ ኮማ ዉስጥ ገብቷል ቤተሰቦቹ እሱ ክፍል ከዉጪ በኩል ሆነዉ ወደዉስጥ ያዩታል እኔ ስሄድ ግን ወደኔ ዞራ እህቱ ታለቅስ ጀመር...... #ክፍል_ሀያ_ይቀጥላል ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን ይቀላቀሉን👇                                         ይቀላቀሉን👇 https://t.me/Ekrea https://t.me/Ekrea
Show all...