cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጥበብ ኃሰሳ

ሰው ሰውነቱ የሚገለጠው በሰዋዊነት ነው!! ሰዋዊነት መገለጫው ለሰው በመኖር ነው ለሰው ፣ስለሰው ፣ እንደሰው እንኑር እስከኖርኩ እፅፋለሁ ፣ እየፃፍኩ እኖራለሁ

Show more
Advertising posts
216
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

I AM BACK .... ሀይማኖት ወ ስነ-ምግባር “If God did not exist, it would be necessary to invent him.” Voltaire በ17ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ተወልዶ እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በፈረንሳይ የኖረው ኢ-አማኝ (atheist) ፈላስፋ፣ ደራሲ እና የታሪክ ተመራማሪ የሆነው ቮልቴር በህይወተ ዘመኑ ሀይማኖትን እና ሀይማኖተኞቹን በተለያየ ፅሑፉ ሲወርፍ፣ ሲተች እና ሲያጣጥል ባጅቷል፡፡ ከቮልቴር ሹፈት ንግግሮች ውስጥ “God is a comedian playing to an audience that is to afriaid to laugh.” የሚለው ንግግሩ በሰፊው ይታወቃል፡፡ ሀይማኖትን/ በፈጣሪ ማመንን እንዲህ አምርሮ የሚቃወመው ቮልቴር በአንድ ወቅት እንዲህ አለ “በእርግጥ ፈጣሪ ብሎ ነገር የለም! ግን እባካቹ ለሰራተኛዬ እንዳትነግሯት ስተኛ ጠብቃ እንዳትገለኝ ምክንያቱ ፈጣሪ ነው” ይህን አባባሉን ቮልቴር በአንድ ወቅት  “ሰዎች ኢ-አማኝ እንዲሆኑ ትመክራለህ?” ተብሎ በተጠየቀው ላይ እንዲህ ሲል አብራርቶታል “በእርግጥ ኢ-አማኝነት ከ ምክንያታዊነት (reasoning) ጋር ሲቀዳጅ አብርሆት ነው! ነገር ግን ኢ-አማኝነት ከ ኢ-ምክንያታዊነት ጋር ከተገናኘ ቀጥሎ የምናገኛት ዓለም የጫካ ህዝቦች (barbaric society) መፈንጫ ሆና ነው” ለዚህም ነው ከላይ ሀሳባችንን የጀመርንበትን ንግግር ኢ-አማኙ ፈላስፋ (ቮልቴር) የተናገረው “እግዚያብሔር ባይኖር እንኳ ልንፈጥረው ግድ ነው፡፡” ስነ-ምግባር የሚለው ቃል በስርወ-ቃሉ (ethimology) ከግሪኩ ቃል ethos ጋር የሚዛመድ ሲሆን ትርጉሙም ልምድ ወይም ባህሪ ማለት ነው፡፡ ይህም ቃል በውስጡ ብዙ የተጠየቅ ጣጣዎችን የተሸከመ ሲሆን እንዴት መኖር ይገባናል? ጥሩ ምንድነው? መጥፎስ? ምን ማድረግ ይገባናል? ለምን ግብረ-ገባዊ እንሆናለን? የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ብዙዎች ምሁራን እንደሚስማሙት የስነ-ምግባራዊ ጥያቄዎችን መመለስ ፈታኝ ቢሆንም ቅሉ በሰው ልጅ የእለት ከእለት ኑሮ ውስጥ ግን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው እሙን ነው፡፡ ይህ የስነ-ምግባር ጥያቄ በሳይንስ፣ በፍልስፍና እንዲሁም በሐይማኖት የተለያዩ አንድምታዎች ሲኖሩት፤ ከሶስቱ አንድምታዎች ግን ሁለቱ ማለትም ፍልስፍና እና ሳይንስ ከተፈጥሮአቸው (essence) አንፃር ለስነ-ምግባር ጥያቄ ግልጽ መልስ አያስቀምጡም፤ ወይም እርስ በእርሳቸው ይጋጫሉ፡፡ ነገር ግን የስውን ልጅ ለረጅም ዘመናት ጨርሶውኑ ከመጠፋፋት ያዳነው በውስጡ የያዘው ሀይማኖት እና የስነ-ምግባር መመሪያዎቹ እንደሆኑ እሙን ነው፡፡ የሀይማኖቶችን ትክክልነት እና ስህተት እንዲሁም ከፍልስፍና እና ከሳይንስ የሚነሱበትን የተጠየቅ ጣጣዎች ወደጎን አድርገን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ላበረከተው የስነ-ምግባር መመሪያ ግን ክብር ይገባቸዋል፡፡ “ለራስህ የምትጠላውን በሌላው ላይ ታደርገው ዘንድ አትውደድ፡፡ ራስህ የተደሰትክበት ለሌላ ሲደረግ አይተህ ተደሰትበት፡፡ አንተ የማትወደውን ለራስህ የማታደርገው ከሆነ ለሌላም አታድርገው፡፡" (ሮሜ ፯፡፲፭፡፳፩።)
Show all...
ቀጭን ሴቶች ዝምብዬ ሳያቹ የፑል ቤት stick ነው ምመስሉኝ🥶
Show all...
ህይወት በመበላላት የተሞላ ነው...ተፈጥሮ መቼም ፍፁም ሆኖ አያቅም...ይህ ከሆነ ተፈጥሮን ስለ ፈጠረ ፈጣሪ ፍፅምናም ምንም አይገባኝም  ከእግዘብሔር በፊት እራሴን ፈራለው...የኔ የጥበብ መጀመሪያ ያ ነው...ጥገኛም አይደለሁም ለክፋቴ ማሳበቢያ ሰይጣንን አልፈጥርም...ለጥፋቴ ማስፈራሪያም እግዚአብሔርን አልፈጥርም...አለም ሁሌም ጎዶሎ ነች...የሰውም ልጅ ከፍጥረት ሁሉ ራሱን በፈጣሪው አምሳያ መስታወት ላይ የሳለ ቅዠታምና እርጉም ነው....የሰው ዘር በሙሉ ይቀፈኛል...ግን አንዲት ሴት እፈልጋለሁ...አለምን በሙሉ ስለኔ የምትተው....እኔም ከሰው ዘር በሙሉ ብቻዋን የማፈቅራት....ቢያንስ ከአዕላፍ ራስ ወዳድ ፍጡር....ሁለት ራስ ወዳድ ነፍሶች በብዙ ይሻላሉ...ምክንያቱም ፍፁም ፍቅርም ፍፁም አለምም የለም...አለም ሁሌም ጎዶሎ ነው...ልክ እንደ ኑሮ!..ሁሉም ሰው ህይወቱ ውስጥ የሚፈልገው አንድ ሁነኛ የልብ ሰው...መልኩን በመስታወት እንደመፈለግ ያለ ነው።....እኔም ያቺን ሴት ያገኘው ይመስለኛል...ራሴን እሷ ውስጥ የማይበት...አይኖቿ እንደ ህፃን ያባብሉኛል አይኖቼን በስስት ስለሚያዩ...
Show all...
እስቲ አማኞች እቺን ጥያቄ ለመከራከር ሳይሆን ሳታንዛዙ ለማሳመን መመለስ ሞክሩ ፈጣሪ አዳምን በገነት እያለ እቺን ዛፍ ብሉ እቺን ደግሞ አትብሉ ብሎ የፈተነው ለምንድነው? ፈጣሪ አዳምን የፈተነው አዳም ይታዘዛል?  ወይስ አይታዘዝም የሚለውን ስለማያውቅ ፈትኖ ለማረጋገጥ ብሎ ነው ወይስ? አዳም ተፈትኖ እንደሚወድቅ ስለሚያውቅ አዳምን በገነት ከሚኖርበት ለማፈናቀል ነው የፈተነው? ወይስ ለምንድነው?
Show all...
የሆነ ሰው ሀይማኖት ባይኖር አለማችን ሰላም ታጣ ነበር የሀይማኖት መኖር ነው ህዝብ ለህዝብ በጭካኔ እንዳይተላለቅ ያረገው አለኝ😂 ብራዘር ጎግል ማድረግ ከቻልክ 75% የአለማችን ጦርነቶች የተነሱት ፍልስጤም እና እስራኤልን ጨምሮ በሀይማኖት ምክንያት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሀይማኖተኛ ነን ባዮች እንኳን ጠላትህን እንደራስህ ውደድ ሚለውኝ አስተምህሯቸውን ረስተው እርስ በእርስ ለመገዳደል ሰከንድ አላሰቡም። እንደውም አለማችንን ሰላም ያሳጣው ሀይማኖት ነው እመነኝ የመንግስት ህግ አስከባሪ ባይኖር በቅርቡ ዮናታን ተብዬውና ምህረተአብ ተብዬው የጀመሩት ክርክር እንኳን ኦርቶዶክስ እና ጴንጤ ነን ባዮችን ወደእርስ በእርስ መገዳደል ያመራ ነበር። ሀይማኖተኛ ማለት ጨካኝ አረመኔ ለሰው ልጅ ማይራራ ነው።
Show all...
በሾፐናውር እምነት የማናቸው ነገሮች ምንነት (ኢሴንስ) ፣ ሰዎችንም ጨምሮ፣ እውቀታቸው፣ ምክንያታዊነታቸው ወይምን መንፈሳቸው ሳይሆን ፈቃዳቸው ነው ይል ነበር። ፈቃድሲል ማናቸውንም ነገሮች፣ ከአለቶች ጀምሮ እስከ ሰው ልጅ ኅልው እንዲሆኑ የሚገፋቸውን ጉልበት ነው። ይህ ጉልበት ምንም ምክንያት የለውም፣ ኅልው ለመሆኑም ምክንያት የለውም፣ ስለሆነም የሰው ልጅ ስቃይ ከዚህ ምክንያት የለሽ እውር ጉልበት ይመነጫል ብሎ ሾፐናውር ያስተምር ነበር። «የሰው ልጅ የሚፈልገውን ማድረግ ይችላል ነገር ግን የሚፈልገውን መፈለግ አይችልም» ሾፐናውር ለዚህ ስቃይ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የዘየደው ፈውስ ሰዎች የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዲኖራቸው መምከር ነበር የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዴት ይገኛል ለሚለው የእርሱ መልስ የሰው ልጅ ፍላጎቱን ማሟላትን እንዲክድ፣ ጊዜ ሰውቶ እራሱን እንዲመረምርና ምን ቢሰራ ስቃዩን እንደሚያመልጥ በማሰብ ነው። ለስቃዩ ማምለጫ ከአዘዘው ውስጥ የኪነት ስራወችን መስራትና የተሰሩትን ማድነቅ፣ በተለይ ሙዚቃን ያጠቅሳል። ሙዚቃ፣ በሾፐናውር አስተሳሰብ፣ ለሰው ልጆች ኅልው መሆን (መኖር) አንዱ ምክንያት ነው ሾፐናውር ለሪቻርድ ዋግነር፣ ፍሬደሪክ ኒሺ፣ ሉድዊግ ዋይንስታይን፣ ሲግመንድ ፍሮይድ፣ ሊዮ ቶልስቶይ፣ ካርል ጀንግ እና ሌሎች ብዙ የምዕራቡ አለም የኪነትና ፈጠራ ሰወች ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ፈላስፋ ነበር ! HE IS GENIUS FOR ME ! 🔥❤️
Show all...
"ከሁሉም እንደ አቅሙ ፣ ለሁሉም እንደ ፍላጎቱ!"                                ለኢትዮጵያም ለኢትዮጵያውያንም  መፍትሔው ይህ ማርክሲዝም ርዕዮተዓለም ነው    የካርል ማርክስ ኮሚኒዝም በኮሚኒዝም ፍልስፍና መሰረት ማንኛውም ቁስ-ሀብት እናም የሀይል ምንጭ ነው። ሀብትን በቁጥጥሩ ስር ያዋለ ማንኛውም አካል የሰፊውን ህዝብ ባህል፣ እሴት፣ አስተሳሰብ፣ ሀይማኖት፣ ትምህርትና ጥበብ ይቆጣጠራል። የመገናኛ ብዙሀንን የተቆጣጠሩ አካላት የህዝቡን አመለካከትና የፖለቲካ ምህዳር ይቀይሳሉ። የሙዚቃውን ኢንደስትሪ የተቆጣጠሩ ሀይሎች በማህበረሰቡ የሙዚቃ ምርጫና ጥበብ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ - የማንኛውም ትውልድ እምነትና አመለካካት በገዥው መደብ የተጣለበት ውርስ ነው። በመሆኑም ሀብትና ንብረት የሀይል ምንጭ እንደመሆኑ በሰፊው ህዝብ ቁጥጥር ስር መዋል ይኖርበታል። ኮሚኒዝም በብዙ መልኩ ሊገለጽ ቢችልም በዋነኝነት የሀብት ህዝባዊ ባለቤትነት ወይንም ግላዊ ባለሀብትነትን የማስወገድ ርእዮተ አለም ነው። በዚህ ርዕዮተ አለም መሰረት ማንኛውም ግለሰብ ወይም አናሳ - መደብ የተወሰነ ንብረት ከመሰብሰብ ባለፈ ሀብትን በበላይነት መቆጣጠር ወይም ማከማቸት አይችልም። ሀብት የጋራ እንደመሆኑ የሰፊው ህዝብ ንብረት እንጂ የግለሰቦች ወይም የመደቦች ግላዊ መገልገያ አይደለም። ሀብት በግለሰቦች ቁጥጥር ስር ሲውል 'ብዙሀኑ በአናሳው ይመዘበራል' የመደብ ትግልና የኮሚኒስቶች አብዮት የካርል ማርክስ የኮሚኒዝም ፍልስፍና መሰረታዊ እሳቤ በሁለት ፈጽሞ ሊታረቁ በማይችሉ ተጻራሪ መደቦች መካከል ያለው የመደብ ትግል ነው። የመጀመሪያው መደብ የባለሀብቱ የቡርዡዋው መደብ ሲሆን ሌላኛው የላብ አደሩ ወይም የፕሮሊታሪያቱ መደብ ነው። የሁለቱ መደቦች ፍላጎት ፍጹም ተቃራኒ ከመሆኑም ባሻገር እርስ በርሱ የሚጋጭም ጭምር ነው። በመሆኑም ይህንን የመደብ ግጭት ለመፍታት ብቸኛው መፍትሄ አንዱን መደብ - ቡርዡዋውን ማጥፋት ይሆናል። ምክንያቱም የቡርዡዋው መደብ ለማህበረሰቡ ምንም ፋይዳ ሳያበረክት በማህበረሰቡ ላይ ተጣብቆ የሚበዘብዝ ጥገኛ መደብ ነው። በኮሚኒስት ማህበረሰብ ውስጥ ደግሞ ሁሉም የድርሻውን ማበርከት ይጠበቅበታል- "ከሁሉም እንደየአቅሙ ፤ ለሁሉም እንደየፍላጎቱ።" በማርክዝ አስተሳሰብ በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚታየው ማህበራዊ ቀውስ ግምባር ቀደም ተጠያቂና ተወቃሽ የቡርዡዋው፤ ባለሀብት መደብ ነው። የቡርዡዋው መደብ ያለ ላቡ ሀብትን የሚያጋብስ ከመሆኑም ባለፈ ላብ አደሩ ከሚያመርተውና ከሚገባው በታች በመስጠት የሰራተኛውን መደብ ያላግባብ ይመዘብራል የባለ ሀብቱ መደብ በፈጠረው ስርአት ለሁሉም ነገር ዋጋ ሰፍሮ ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ክቡር ሰብአዊ እሴቶች ሳይቀሩ የገበያ ሸቀጥ ተደርገዋል ባለሀብቱ በፈጠረው በዝባዥ ስርአት የላብአደሩ ሰብአዊ ማንነት ተገፎ እንደ ሸቀጥ በሰው ሀይል ገበያ ዋጋው ይተመናል። በጥረቱና በውጤቱ ሳይሆን በገበያ ዋጋ ከላቡ በታች ይከፈለዋል። ስለሆነም ማህበረሰቡ ሰላምና እፎይታ ያገኝ ዘንድ ለማንኛውም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ መንስኤ የሆነውን የቡርዥዋ መደብ ከነስሩ መመንገል አማራጭ የማይገኝለት መፍትሄ ይሆናል። ከሁለቱ ተጻራሪ መደቦች ውስጥ በዝባዡን በማጥፋት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንድ መደብ መፍጠር በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ያለ ላቡ ተንደላቆ የሚኖረው የቡርዥዋው መደብ ተወግዶ አእምሮውን ወይንም ጉልበቱን በማፍሰስ የሚያድረው ብቸኛው የሰራተኛ መደብ ሲቀር በሰፊው ህዝብ ውስጥ በመደብ ያልተከፋፈለ መደብ አልባ ማህበረሰብ ይፈጠራል። ከሁለቱ ተጻራሪ መደቦች መካከል የባለሀብቱ መደብ ሲወገድ የሚቀረው ብቸኛው የሰራተኛ መደብ የሰው ሀይል አስተዳደርና ቁጥጥርን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት የመንግስት አመራር ይረከባል። ለግዛቱ ህልውና ከሚያበረክተው ፋይዳ አንጻር የገዢነቱ ስልጣን የሚገባው በላቡ ለሚያድረው የሰራተኛ መደብ ብቻ ነው። ስለሆነም መንግስት በሰራተኛው መደብ የበላይነት የሚመራ መሆን ይኖርበታል። በመደብ ባልተከፋፈለው ማህበረሰብ ውስጥ የሰራተኛው መደብ እራሱን በራሱ ያስተዳድራል። በካርል ማርክስ አስተሳሰብ የታሪክ መዘውር የሚወሰነዉ በኢኮኖሚያዊ እውነታዎች አማካኝነት በመሆኑ መላው አለም ወደ ኮሚኒስታዊ ሶሻሊዝም ማምራቱ አይቀሬ ነው። ሀገራት ወደዚህ መዳረሻ ቢያመሩም ባያመሩም፣ ፈጠነም ዘገየ ይህ ለውጥ እውን ይሆናል። እያንዳንዱ ማህበረሰብ የየራሱን አጥፊ ጀርም በጉያው በመሰብሰቡ ኮሚኒዝም በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ ሊወገድ የማይችል እጣ ፈንታ ይሆናል። እነዛ ወደዚህ ፍጻሜ ተጉዘው የከሽፉ አብዮቶች ዛሬ የዘሩትን ነገ የሚያጭዱበት ትክክለኛው ቀን ይመጣል ። ይሁን እንጂ ገዢው መደብ ያካበተውን ሀብት፣ ንብረትና ስልጣን በፈቃዱ የሚለቅ ባለመሆኑ ሀይልን መጠቀም አስገዳች ከሆነም ጦር ማንሳት ግድ ይሆናል። የቡርዡዋው መደብ ሀብትና ስልጣን የሰራተኛው መደብ ላብና ጥሪት በመሆኑ ሰራተኛው ሀብቱን ቢያስመልስ በኢፍትሀዊነት አይኮነንም። «በመሆኑም ኮሚኒስቶች...ኣላማቸውን ከጫፍ ማድረስ የሚችሉት ነባራዊውን ስርአት በሀይልና በትግል ከስር መሰረቱ በመገርሰስ እንደሆነ አውቀው አቋማቸውን በግልጽ ማወጅ ይኖርባቸዋል..... በዝባዥ መደብ በኮሚኒስቶች አብዮት ይውደም.... የመላው አለም ላብ አደሮች ታጥቃችሁ ተነሱ...... ጠላቶቻችሁ ላይ አብሩ። ››  Karl Marx, Manifesto of the comminist party
Show all...
ሁለት ነገሮች ይገርሙኛል ህንዳውያን በባህላቸው ወግ አጥባቂዎች ናቸው። ይሄንን በቀላል ምሳሌ እንመልከት። ቦሊውድ የህንዳውያን የፊልም ማእከል ነው። ባህላቸውን ያስተዋውቁበታል። ቢሊየኖች ያተርፉበታል። እንደገና ቱሪዝሙን አፋፍቶ ተጨማሪ ፍራንካ ይሸቅሉበታል። ታድያ በፊልሞቻቸው በተአምር የወሲብ ትእይንት አይታይም። መሳሳም እንኳን የለም። እልል ያለ የፍቅር ታሪክ ቢሆን እንኳን ቃላት ከመለዋወጥ የዘለለ ግንኙነት በስክሪኑ ላይ አትመለከቱም። ህንዳውያን የሚኖሩት ልክ እንደ ፊልሞቻቸው ከሆነ The Big Bang Theory ላይ እንዳለው Sheldon Cooper የሚባዙት  asexually ነው ብላችሁ ልትጠረጥሩ ትችላለሁ። ከእለታት አንድ ቀን ግን አንዱ ዳይሬክተር የፍቅር ፊልም ሰራ። አጭር የመሳሳም ትእይንት አለበት። ህንዳውያን ፊልም ተመልካቾች ተቆጡ። የከተሞቻቸውን አውራጎዳናዎች አጥለቀለቁ። ተቃውሞዋቸውን አሰሙ። ወዲያውኑ ፊልሙ ታገደ። በመላው ህንድ እንዳይታይ ተከለከለ። አሁን ደግሞ ሌላ የህንድ ታሪክ ልንገራችሁ። ህንዳውያን ጥንታዊ መፅሀፍ አላቸው። ካማ ሱትራ ይባላል። የብዙ ሺህ አመት እድሜ ያለው መፅሀፍ ነው። መፅሀፉ በስእል የታገዘ የሴክስ ፖዚሽን መፅሀፍ ነው። እዚህ ጋር አበስ ገበርኩ ማለት ይቻላል። እነዚህ በፊልሞቻቸው ላይ መሳሳም እንኳን የማይፈቅዱ ህንዳውያን ጥንታዊ የወሲብ መፅሀፍ አላቸው። መታቀብን የሚያበረታቱ ሂንዱይዝም እና ቡድሂዝም ሃይማኖት መስራች ሕዝቦች ስለ ወሲብ በግልፅነት የሚያስተምር መፅሀፍ አላቸው። ቱባ መንፈሳዊ መፅሀፍት(Mahabharata and Ramayana) ያላቸው ህንዳውያን ቱባ የወሲብ መፅሀፍ አላቸው። በአደባባይ ፍቅራቸውን የማይገልፁት ህንዳውያን በግላጭ ስለ ወሲብ የሚያወሩበት መፅሀፍ አላቸው  This is paradox. በሀበሽኛ አያዎ(አይ+አዎ) እንለዋለን። ሁለተኛውን አስገራሚ ነገር ሌላ ግዜ እነግራችኋለሁ
Show all...
እብደትና የሮም ንጉስ ሮም በዓለም ገናና በነበረችበት ወቅት አንድ ነብይ ወደ ሮማው ንጉስ ይመጣና ፈጣሪ ከሰማይ ዝናብ እንደሚያዘንብ ያንን የዝናብ ውሀ የጠጣ ማንኛውም ሰው እንደሚያብድ ስለዚህም ሰው በሙሉ ቀድሞ ከወንዝ ወይም ከምንጭ ወርዶ ውሀ ቀድቶ እንዲጠቀም ይነግረዋል ፡፡ ለ 3 ቀናትም ዝናቡ ከነካው ከማንኛውም ውሀ እንዳይጠጡ ለህዝቡ ትእዛዝ እንዲያስተላልፍ እሱም ቀድሞ ውሃ ቀድቶ እንዲያስቀምጥና ለሶስት ቀናትም ቀድሞ ከተቀዳው ውሀ ብቻ እንዲጠጣ ይነግረዋል ፡፡ ንጉሱም ህዝቡን ሰብስቦ ይህንኑ ይነግራቸዋል  ከዛንም ለራሱ ውሀ ቀድቶ ያስቀምጣል ፡፡ ህዝቡ ግን ንጉሳቸው ያላቸውን በመናቅ ችላ ብለው ያልፋሉ ፡፡ ከዚያም ዝናቡ በተባለበት ቀን ይዘንብና የወንዙንም የምንጩንም ውሃ ይበክለዋል ፡፡ ህዝቡም ከወንዝም ከምንጭም ያገኝውን ውሃ ሲጠጣ ማበድ ይጀምራል ፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሁሉም ህዝብ ያብዳና ንጉሱ ብቻ ይቀራል ፡፡ ያ ያበደ ህዘብ ሀገሪቷን ሲያተራምስና ሲመሰቃቀል ንጉሱ ግን ጤነኛ ስለሆነ ይህንን ሊያስቆም ይሞክራል  ሕዝቡም ቆም ብለው ንጉሳቸውን ሲያዩ እሱ ከእነሱ የተለየ ይሆንባቸዋል ፡፡ ስለዚህ ህዘቡ ተሰብስቦ ንጉሳችን ስላበደ ከስልጣን ይውረድና እኛን በትክክልና በስርዓት የሚመራ ንጉስ እንሹም ብለው ግርግር ማንሳት ጀመሩ ፡፡ ንጉሱም እጅግ ብልህና አስተዋይ የነበረ በመሆኑ ካላበደ በስተቀር በትክክለኛው መንገድ ሊመራችው እንደማይችችል ሲገባው ከውሃው ጠጥቶ እሱም ያብዳል ፡፡ በዚህን ጊዜ ያበደው ህዝብ ተሰብስቦ ንጉሳችን ከእብደቱ ስለተሻለውና ስለዳነ አሁን እሱ ይምራን ብለው ተቀብለውት ይመራቸው ጀመር ፡፡ መቼም ቢሆን መሪ ለህዝብ ሲያስብ ህዝብ ትክክል ነው ማለት መቻል አለበት ፡፡ ህዝቡን ካልመሰሉ ህዝብን መምራት አይቻልምና ፡፡ ሀገር ብቻ ሳይሆን በየትኛው የአመራር ቦታ ያለ ሰው መጀመሪያ የሚመራውን ሰው መከተል ይገባዋል ፡፡ በሚመራው ሰው ጫማ ውስጥ ቆሞ ነው መሪው የሚፈልገውን ሀሳብ ለተመሪው መንገርና መምራት የሚችለው ፡፡ በአልበር ካሙ ተፃፈ ከእብዶች ዓለም ይቀጥላል
Show all...