cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

️ናታን❤_️Tube

እንኳን ወደ ቻናላችን በደህና መጡ ለበሌጠ መረጃ የቻናሉ ዋና አላማ #0925502446 ✔️የዱሮ የሆኑ ዝማረዎች🎶 ✔️የተለያዩ ታርኮች📁 ✔️ስነ-ፁሁፍ እና📃 ✔️አስተማር vedoዎች🎬 @Olankaman @olankaman @olankaman @olankaman

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
መንፈሳዊ ዕድገት የምመጣ ሰፍ በሆነው አገልግሎት ፕሮግራም በመኖር ሳይሆን ሰፍ የሆነ የቃልና የፀሎት ጊዜ በመኖር ነው 👉 መንፈሳዊ ዕድገት በመደርክ አገልግሎት ሳይሆን በግል ሕይወት በቤታችን ክርስቶስ ጋር ባለን ህብረት ይወስኖል። 👉 በመንፈሳዊ ሕይወት ለማደግ ጠንካራ የህብረት መፍጠር መቻል አለብን 👉 መንፈሳዊ ዕድገት የምመጣ እና የምኖርን ነገር ሳይሆን የምሆነው ነገር ነው። የኮንፍራንሱ ቀን፦20/8/2014 ሰላማቹ ይብዛ #Nagesa du ነኝ ቸር ሰንበት🙏🙏🙏 @Natanbh @Natanbh @"Natanbh @Natanbh
Show all...
እግር አጣቢው ንጉሥ! .*** ሳምንቱ ሰሙነ ሕማማት ሲኾን፥ ዛሬ ጸሎተ ሐሙስ ነው። ምሴተ ሐሙስም ይባላል። ጌታችን የመጨረሻውን ራት በላይኛው ደርብ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በላ። የጌታ ራት (ቅዱስ ቍርባን) መሠረቱን ያገኘው በዚያ ነው። በተጨማሪም፥ ጌታ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡም (ሕጽበተ-እግር) ይታሰብበታል። … ይህ ኹሉ የተከናወነ ከ2000 ዓመታት በፊት በአንድ በማናውቀው ሰው ቤት ላይኛ ክፍል ውስጥ ነው። . ኹሉን የያዘና የሰውን ሕይወት ዕርቃን በጸጋው የሚሸፍን የሕይወት ራስ፥ ሰውን ፍለጋ በመጣ ጊዜ ዓለም ለእርሱ ቦታ አልነበራትም። ይመጣ ዘንድ በተስፋ ቃል የተነገረለትና ሕዝቡ የጠበቀው መሲሕ (የተቀባው ንጉሥ) ከገመቱትና ከጠበቁበት መንገድ የተለየ ኾነባቸው። . በንጉሥ አደባባይ ሳይኾን እናቱ ማደሪያ እንኳ ባላገኘችበት ምሽትና ትንሽ ከተማ በቤተ ልሔም ተወለደ። በንጉሥ እልፍኝ ሳይኾን በግርግም አስተኛችው። የሰው ልጅ ለጌታ ውለታ በተገላቢጦሽ ምላሽ ሰጠ። ሕይወታችንን በሚመስል ምጸት ዓለም ለኢየሱስ ያቀረበችለት ቦታ በረትና ግርግም ብቻ ነበር (ሉቃ. 2፥7፡ 12፡ 16)፤ የተውሶ ግርግም። ለማስተማር ታንኳ ተውሶ ነበር (ሉቃ. 5፥3)፤ ንጉሣዊ አገባቡን የሚመሰክረው የኢየሩሳሌም ጕዞው የተደረገው በተውሶ አህያ ጀርባ በመቀመጥ ነበር (ማቴ 22፥ 1-16)። የመጨረሻውን የፋሲካ ራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በተውሶ ቤት በላ (ሉቃ. 22፥7-12)። . በወደዳቸው ተገፋ (ሉቃ. 20፥17)። በገዛ ወገኖቹም ተጣለ (1ጴጥ. 2፥7፤ ዮሐ. 1፥11)። ክፉው የሰው ልብ ታላቁን ስጦታ በደስታ መቀበል አልቻለም። ቅዱሱን የእግዚአብሔር መሲሕ በጭካኔ ሰቀለ። ሊቤዠው የወረደለትን ገደለ፤ በተውሶ መቃብር ቀበረ (ማቴ. 27፥60)። . የመጨረሻውን ራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበሉ በኋላ አፈፍ ብሎ በመነሣት እግራቸውን አጠበ። እግር ማጠብ በዘመኑ የመጨረሻው ታችኛ ደረጃ ያለ ባሪያ የሚያከናውነው ሥራ ነበር። ቀደም ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ነገራቸው፥ የእርሱ አመጣጥ አገልጋይ ንጉሥነት ነበር። “በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ” (ሉቃ. 22፥27)። አዳኛችን በፈቃዱ ለአባቱ በመታዘዝ እንደ ሎሌ አገለገለው (ኢሳ. 42፥1-7፤ 49፥1-6፤ 50፤4-9፤ 53፥1-13)። ሕይወቱም በትሕትና የደመቀ (ፊል. 2፥5-10)። ሎሌው ንጉሥ (Servant-King! . የምድር አገልግሎቱም በመከራ የተሞላ ነበር። ሕይወቱና አገልግሎቱ መከራና እንግልት ያልተለየው ስለ ነበር “ሥቍይ ሎሌ” ተብሎ ታወቀ። ድኅነትን እንዲያስገኝልንም ተሰቀሎ ሞተ። ስለዚህ የተሰቀለው መሲሕ ተብሎ ተጠራ (ማቴ. 26፥1-27፥56)። ሥቁሉ መሲሕ (the Suffering Servant)! አገልጋዩ ንጉሥ የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበው በማግስቱ በመስቀል ለመሞት ተዘጋጅቶ ሳለ ነበር። . ከእግር አጠባው ክሥተት በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠው ትምህርት እናንተም እንዲሁ አድርጉ የሚል ነበር። . ጌታ ኢየሱስ ካስተማራቸው ነገሮች አንዱ ሌሎችን ማገልገል እንዳለብን ነው። የኹሉ ጌታ የኾነው ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠብ የትንሹን አገልጋይ ሥራ ለመሥራት ራሱን ዝቅ ለማድረግ ከመረጠ ዘወትር ሌሎችን ለማገልገል ፈቃደኞች መኾን አለብን። ጌታችን ኢየሱስ ምሳሌውን እንድንከተል ተናግሯል። እኛም እንዲሁ እናድርግ። . Photo Credit: Edelfelt, A. G. Aristides: Nationalmuseum, Stockholm ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን @natanbh
Show all...
መስቀል መንገድ ነው! ኢየሱስ ስለ በደላችን የደቀቀበት መስቀል ዘላለማዊ መዳናችን የታወጀበት ሥፍራ ነው፡፡ ሥፍራ ብቻ ግን አይደለም፤ መንገድም ነው! ደቀ መዛሙርቱ የሆንን እኛ መምህራችንን ከምንመስልባቸው መንገዶች አንዱ፣ “በመከራው” ነው፡፡ ይህ የጥሪያችን አካል ነው፡፡ “ስለ እርሱ መከራ እንድትቀበሉ ይህ ጸጋ ተሰጥቶአችኋልና” (ፊልጵ. 1፡29) ተብለናል፡፡ የኢየሱስ የመስቀል ላይ ምጥ፣ ከሞት ኀይል የሚድኑትን ብቻ ሳይሆን በሞቱ የሚመስሉትንም ጭምር የመውለድ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ሥነ መለኮታችን፣ ወደ አንድ ጽንፍ ያጋደለ በመሆኑ አብዝቶ ስለ “ክብር” ያቀነቅናል፡፡ በእርግጥ ነገ ከክርስቶስ ጋር በምንገለጥበት ጊዜ የሚጠብቀን ክብር አለ፡፡ ወደዚያ ክብር መድረስ የምንችለው ግን ወደ ክብሩ በሚወስደው መንገድ መጓዝ እስከቻልን ድረስ ብቻ ነው፡፡ ያ መንገድ የመስቀል መንገድ ይባላል! የዕብራውያን ጸሐፊ፣ ኢየሱስ “የመስቀልን መከራ ታግሦ” በአባቱ ቀኝ እንደከበረ ከነገረን በኋላ፣ “እናንተም በመስቀል የታገሠውን ጌታ ተመልከቱ” የሚል ጥሪ ያቀርብልናል (ዕብ. 12፡1-2)፡፡ የክርስቶስ የሆኑት ሁሉ፣ ነገ ከሚጠብቃቸው ክብር በፊት፣ በትዕግሥት የመስቀልን መንገድ እንዲጓዙ ተጠርተዋል፡፡ “ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው” (1 ጴጥ. 2፡21) መባሉ፣ ጥሪያችን በክብሩ ብቻ ሳይሆን በመከራውም የመካፈል መሆኑን ያሳያል፡፡ አዎን መስቀል ዕለት ዕለት የምንኼድበት ጎዳና ነው፡፡ የአኗኗር ዘዬ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን በሕይወታችን የሚገጥመን መከራ ሁሉ በመስቀሉ መንገድ ላይ ለመሆናችን ዋስትና ነው ማለት አይደለም፡፡ እንዲያ እንዲሆን መከራችን የኢየሱስን መምሰል አለበት፡፡ ይህም ማለት፣ እርሱ ኀጢአትና ተንኮል ሳይገኝበት ንጽህ ሆኖ ሳለ እንደተጠላና እንደሞተ የእኛም መከራ ክፉ በማድረጋችን የምንቀበለው ሳይሆን መልካም በማድረጋችን ብቻ የሚደርስብን ሊሆን ይገባዋል፡- “በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ” የሚቀበሉት ዓይነት መከራ (2 ጢሞ. 3፡12)፡፡ በእርግጥ የመስቀል መንገድ የሕመምና የውርደት መንገድ በመሆኑ እንደ ሰው ይጎረብጣል፡፡ ክርስቶስን ለመከተል ራሱን ለካደ ደቀ መዝሙር ግን አማራጭ የሌለው መንገዱ ነው! ዓለም የምትነግረው የአኗኗር ዘዬ በየትኛውም መንገድ መከራን በመቀነስና ከተቻለም በማስወገድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የአማኞች መንገድ ግን ክርስቶስን በመከተል ውስጥ መከራ እንዳለ በማወቅ፣ ከመከራ በስቲያ ያለውን ክብር እያዩ፣ ወገብን ታጥቆ ወደ ፊት መጓዝ ነው፡፡ ዓለም ኖሮ መሞትን ስትሰብክ፣ አማኝ ሞቶ የመኖርን (የመስቀል መንገድ) ይመርጣል፡፡ ዓለም “ዘላለም አይኖር!” በማለት በዛሬው ሕይወት መንገስን ስትሠብክ፣ አማኝ ግን “የለም ዘላለም ይኖራል!” በሚል በአሁኑ ሕይወት ነፍሱን እንደማትከበር ይቆጥራል፤ የነገውን ንግሥና ትኩር ብሎ ይመለከታል፡፡ የዓለምንም ትርፍ ሁሉ እንደ ረብ የለሽ ቆጥሮ በጌታው መንገድ ይጓዛል፡፡ መስቀል መንገዱ ነው፤ የመንገዱ መርህ ደግሞ ይህ ነው፡- “ሕይወቱን የሚወድ ያጣታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል” (ዮሐ 12፡25) የሚል፡፡ በመንገዳችን እንጓዝ! መስቀል መንገዳችን ነው! ክብር ደግሞ መድረሻችን! አሳየኸኝ ለገሠ @natanbh
Show all...
08:18
Video unavailableShow in Telegram
˙ የክብር ዳርቻ ፓስተር ካሳሁን ለማ new protestant mezmur Share & join @natanbh @natanbh
Show all...
አዲስ_ዝማሬ_የክብር_ዳርቻ_ፓስተር_ካሳሁን_ለማ_new_protestant_mezmur_pas_lq3shdjLm1o.mp428.29 MB
˙ የክብር ዳርቻ ፓስተር ካሳሁን ለማ new protestant mezmur Share & join @natanbh @natanbh
Show all...
አዲስ_ዝማሬ_የክብር_ዳርቻ_ፓስተር_ካሳሁን_ለማ_new_protestant_mezmur_pastor.mp34.54 MB
Photo unavailableShow in Telegram
"ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለመወደዴ ማስረጃው ከእልፍ አእላፋት ምስክሮች በላይ ገዝፎ ቆሟል። መድኅኔ ፍቅሩን ለመግለጥ በመስቀል ላይ በደሙ ቀለም ጽፎ ደብዳቤውን (ክቡር እሱነቱን) በችንካር ላይ ለጥፎታል (1ዮሐ. 3፥16)። . ዓለሙን የወደደው ቸሩ እግዚአብሔር የአልማዝ ፈርጥ ሳይኾን ሕይወቱን በልጁ ሰጠን። እኔ ችንካር እርሱ ፍቅር ኾነ። በወጋሁት እጁ አቀፈኝ። ባፈሰስሁት ደሙ ከኀጢአቴ ዐጥቦ አነጻኝ። ያቈሰልሁት ዐመፀኛው ችንካር እኔ ብኾንም፥ በቍስሉ ግን አከመኝ። እናንተንም በፍቅሩ ያክማችኋልና ወደ እርሱ፥ ኑ።" ከ "የዱባ ጥጋብ፥ ገጽ 410፥ የተወሰደ @natanbh @natanbh
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንደ ተናገረው ተነስቷል! መቃብሩ ባዶ ነው። እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! @natanbh
Show all...
የምትወደው ይሁን ባለበት ጊዜ እግዚአብሔር ይወደው የነበረው ልጁን አሳልፎ የሰጠበት ምክንያት እኔና አንቺን ማዳን ስለነበረ ያ ቃል ይፈፀም ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋውን ተቀበለ። (ማርቆስ ወንጌል 14 : 32 - 36) ያንብቡ!
Show all...
˙ ኃጥያአት ተወገደ Mesfine Gutu የትንሳኤ መዝሙር መልካም በዓል! @natanbh @batanbh Share በማድረግ ለሌሎች ይጋብዙ
Show all...
Mesfen Gutu 07 04.mp36.21 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#Picture “ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ” — ዮሐንስ 15፥13 Graphics by ቤki SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY
Show all...