cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hope

if you are patient, you will find that everything is going well. The food of life is hope! So hopefully as long as we breathe Don't cut it! If you have hope, if you are strong and patient,respect your religion, be patriotic, human for cross @variopa

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
188
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጠቃሚ-ምክር በህይወት ጉዞ ላይ አንዳንድ ያላሠብካቸዉ ነገሮች ሊገጥሙ ይችላሉ። ቢያጋጥሙህም ግን እሩጫህን እንዲያደናቅፍብህ አትፈቀድላቸዉ። እንደዉም ለሀይል ና ብርታት እንደሚጨምርልህ አርገህ ቁጠረው። *ምን ግዜም "ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ"የሚለዉን የመፀሀፈ ቅዱስ ቃል አስብ።ይሄን እዉነት መተግበር ስጀምር ምንም አይነት ነገር በህይወትህ ላይ ቢገጥሙህ፤የብረታት እንጂ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትን ከህይወትህ ላይ ጠረገህ ታጠፈለህ። ስለዚህ ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብለህ አስብ። ፡ ራስህን አትጣል የሚያነሣህ የለምና፤ ጥንካሬህንና አቋምህን አስተካክል በዙሪያህ ዉድቀትህን የሚመኙ አይጠፉምና፤ ለራስህ ቦታ ስጠዉ ያንተዉ ነህና፤ ለራስህ ክብር ስሰጥ ነዉ የሌሎች ክብር የሚገባህ። : በህይወትህ ዘመን ታላቅ ሠዉ መሆን ከፈለክ ሞራልህን ጠብቅ ሞራልህን ሊያሣጣህ የሚችሉትን የአሉታዊ ሰዋች ንግግር አታዳምጥ አንተ የምቶድቀዉ ገንዘብ ሣይኖርህ ሲቀር ሣይሆን ሞራልህ ሲወድቅ ነዉና ሞራልህን ሣታስነካ ጠብቅ።ሞራልህ የወደቀ ቀን ጉልበት ይከዳሀል፣ማገናዘብ ይሣንሀል፣ መራመድ ያቅትሀል በመጨረሻም ትወድቃለህ። : አስተዉል👉አንዳንዴ ችግሮች ለመጣል ወይም ወድቀን እንድንቀር ብቻ ሣይሆን ያላየነዉን የስኬት ጉዞ ሊያሣየን፤ከድክመት ይልቅ ጥንካሬን ሊያስተምሩን ነዉና ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እራሣችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ። ፡ ♦️ፍፃሜህ እንዲያምር ራስህን አታመፃድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመማር ፍቃደኛ ሁን ጥፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሠልህ። ፡ ሰንደል ሢያቃጥሉት ነዉ ሚሸተዉ ስለዚህ አንተም እኔም አንቺም በችግር ብንፈተንም ያ ማለፊያችን ነዉና ታግሰን እናሳልፈዉ ከዛ ጥንካሪያችንን አጠንክረን ወደ ፊት እንጓዝ ያኔ እራያችን እዉን ይሆንና መአዛችን አለምን ያዉዳል። ፡ አስተዉል👉 ህይወት እንዲ ነዉ ፤በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም! ንፈስን አባሮ እንደ መያዝ ነዉና ሁሉም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር ። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላዉ ምእራፍ እንደሚያሸጋግረህም ፈጣሪህም ታመን ።ከዛም በአምላክህ ደስ ይበልህ በእምነት ኑር!!! መልካም ጊዜ ወዳጆቼ♥️ join @brokenochu
Show all...
ያንተ ጥንካሬ! አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ። ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው! ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
Show all...
መጥፎ ልማዶቻችንን ትተን ለሰውነታችን ግዜ እንስጥ! ሰውነታችን ከፈጣሪ የተሰጠን ውዱ ስጦታችን ነው ስለዚህ በደንብ ልናከብረው ፣ ልንንከባከበውና ልንጠብቀው ይገባናል ! በምን? ስፖርት መስራት ለሰው ልጅ ሰውነት ማማር ብቻ ሳይሆን ጤናን በሚገባ ለመጠበቅና የአእምሮ ስራ ሂደትንም በጣም ከፍ ለማድረግ እጅግ ይረዳናል ወደ ውስጣችንም የምናስገባውን እያንዳንዱን ነገር የምንበላው ፣ የምናነበው ፣ የምናየውን ሁሉ በሚገባ ልንጠነቀቅለት ይገባል! ፈጣሪ አክብሮ በአምሳሉ ሰርቶናል ስለዚህ በየዕለት እንቅስቃሴያችን የምናደርጋቸውን አላስፈላጊ ነገሮች አስወግደን የሚጠቅመንን ተግባራት ለማከናወን ለራሳችን እድል እንስጠው ያኔ ሁሉ ነገራችን ሰላም እና መልካም ይሆናል!
Show all...
አሸንፈሀል ማለት ነው! የሞተን ውሻ ማንም አይደበድበውም! በህይወት እስካለን እና እስከሰራን ድረስ ሰዋች ሊወቅሱን ብዙ ትችቶችን ሊያደርሱብን እና በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ አስተያየት ሊያበዙብን ይችላሉ ፤ ለምን? አነሱ አይሰሩማ ስለስራችን ዋጋ እና ክብደት አያውቁም ፣ እና ደግሞ በጣምም ተበልጠዋል ፤ ታድያ መሸነፋቸውን በፀጋ መቀበል ስለሚያቅታቸው ሌላውን በመተቸት የማሸነፍ ጥማቸውን ያረካሉ ስለዚህ ሁሌም ቢሆን በስራችን ላይ ያለምክንያት የሚተች ከበዛብን በጣም ከፍ እያልን ነው ማለት ነዉ እና ደስ ይበለን !
Show all...
ድንቅ ነህ! ምን ያህል ጀግና እና እድለኛ እንደሆንክ ማወቅ ከፈለክ እስከዛሬ ያለፍካቸውን የህይወት ፈተናዎች አስብ፤ አንተ ባትሆን ኖሮ እነዛን ከባድ ጊዜያት ማን ያልፍ ነበር?! ስለዚህ ድንቅ ነህ ወዳጄ! አንቺም እኮ የማይታሰበውን ነው ያለፍሺው ስለዚህ እህቴ አንቺም ልዩ ነሽ!
Show all...
ትዕግስተኛ መሆን! አንዳንዴ እኮ ምንም ሳይጎድለን ትዕግስት ማጣት ብቻ ባለንበት ያስቀረናል። ይቺ አለም ትንፋሹን ዋጥ አርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሚያሸንፍባት መድረክ ናት። መጀመሪያ ለምትፈልገው ሳይሆን ለሚያስፈልግህ ቅድሚያ ስጥ! ለምሳሌ መዝናናት ፈታ ማለት እያማረህ ግን ቆይ እስኪ ዛሬ ይለፈኝ ማለት ከጀመርክና ያን ጊዜ ለሚጠቅምህ ነገር ከተጠቀምከው አትጠራጠር ወዳጄ ትክክለኛው መንገድ ላይ ነህ! ታጋሽ እንድትሆን ትልቁን የነገ መድረሻህ ማሰብ አለብህ፤ ለትልቁ ስትል ትናንሽ ደስታዎችን መተው ትችላለህ።
Show all...
የሚጠበቅብህን በሙሉ አድርግ ! እድሎች በየት በኩል ሊመጡ እንደሚችሉ አይታወቅም ፤ ዝም ብለህ አመስግነህ ማድረግ የሚገባህን ድብን አድርገህ ስራ ከዛ ታግሰህ ጠብቅ እመነኝ ካሰብካቸው በላይ የታሰበልህ ይበልጣል !
Show all...
ምስጋና እና ደስታ! ዕድሜያችን አጭር ናት፤ በዚህ ሰዓት የሚያሳዝኑህን የሚያናድዱህን ጉዳዮች ንገረኝ ብልህ ብዙ እንደምትዘረዝር አውቃለው። አስቂኙ ነገር የተሰጠህ ዕድሜ የሚያስደስቱህን ነገሮች እንኳን አጣጥመህ ለመጨረስ አይበቃም! ታዲያ ለምንድነው ለደስታ እንኳን የማይበቃ ጊዜህን በሀዘንና ጭንቀት የምታጣብበው? "ያንተን ወጣትነት እኮ የጨረጨሰ ንጉስም ይቀናበታል" ይለናል ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር። አንዳንድ ነገሮች እንደነበረህ ራሱ የምታውቀው ከእጅህ ሲያመልጥህ ነው፤ ወዳጄ አሁን ላንተ የሚመጥንም ምስጋና እና ደስታ ብቻ ነው! ደስታ የሞላበት ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
Show all...
ዛሬን መኖር ! ትላንት ላይመለስ ሄዷል ነገ ገና ስለመምጣቱ ተስፋ ብቻ ነው ያለን ዛሬ ግን የኛ ናት የትላንት ጥፋት የሚታረምባት ፣ ያፈራነው መልካም ፍሬም የሚሰበሰብባት ናት ፤ ለነገ ደግሞ ስንቅ ታዘጋጃለች! ስለዚህ በትዝታ ከመቆዘም ወይ ቢሆንስ በሚል ሀሳብ ውስጥ ከመዋለል ዛሬ የተሰጠችን ትልቅ ፀጋ ናት በደንብ አጣጥመን እንኑራት ፣ እንጠቀምባትም!
Show all...
3ቱ ወሳኝ ነገሮች! ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች ህይወትህን ይወስኑታል፤ አንዳንዴ ዝምብለህ ስለሮጥክ ወይ ስለለፋህ አይደለም፤ ወሳኝ ለሆነው ነገር ቅድሚያ ስጥ! 1. ወደ ፈጣሪህ በደምብ ቅረብ! 2. እጅህ ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ውደደው አጣጥመው! 3. ተረጋጋ እና ህይወቴን ወደምፈልገው ቦታ እንዴት ላድርሰው ብለህ በጥሞና አስብ፣ ካንተ የተሻሉ ሰዎችን አማክር፣ ስማ እና መፅሀፍ አንብብ! የሚያደምም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
Show all...