cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ ግጥም

ሰላም ውድ የቤተ ግጥም ቤተሰቦች በዚህ ቻናል የተለያዩ ግጥሞች📝 አነሳሽ ጽሑፎች📝 የታዋቂ ሰዎች አባባሎች📝 ሀገራዊ ለዛ ያላቸው ጽሑፎች📝 እንዲሁም📚 አማርኛ መፃህፍት በpdf📚 ታገኙበታላችሁ። for more join 👇👇👇👇 @home_of_poems ጥበብ ከጥንካሬ ይበልጣል። Leave ከማለቶ በፊት አስተያየቶን በዚህ ያጋሩን @Mishayemishaye

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
212
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ነይ አንቺው ጨርሺኝ በማስመሰል ዓለም በማጭበርበር ኑሮ፣ ህሊናዬን ስቼ ቅስሜ ተሰባብሮ፣ በሽንፈት ወድቄ ያኔ አግኝተሺኝ፣ አዲስ ዓለም ፈጥረሽ በተስፋ ያኖርሺኝ፣ በህይወት ሸራ ላይ በፍቅርሽ እርሳስ ደስታን የቀባሺኝ፣ ድንገት ባጋጣሚ ስትርቂ ከጎኔ፣ ምን ይዋጠኝ እኔ?…… ግና…………… አሁንም ፍቅርዬትመጫለሽ ብዬ ቆሚያለሁ ባቆምሺኝ፣ ሰዓሊ ፍለጋ ወዴትም አልሄድም አንችው እንደጀመርሽ ነይ አንቺው ጨርሺኝ። @Abelaaaaam @Abelaaaaam
Show all...
እያነቡ እስክስታ ========== (በረከት ሞላ)✍ በብዙዎች ምኞት፡ አይኖቹ ተጋርደው፤ የገዘፈ ፍቅሬን ፡ማየት ከተሳነው፤ ከአላቂው እውነት፡ ይጥገብ ከምኞቱ፤ ለኔ ግን ከንቱ ነው፡ ለሱ መቆየቱ። ስለዚህ ሄጃለሁ፡እዚያ የለሁ እኔ፤ ቃሌን አጣጥፌ፡ ሳልፈራ ኩነኔ። ምክኒያቱ ደግሞ፡ የትግስቴ ማለቅ፦ ከመኖር በስቃይ፡ተስፋ በመናፈቅ፤ እንዳትመጣ እያወኩ፡ አንተን ከመጠበቅ፤ የአለሙን ሰሪ ፡ትዕዛዝ ከመናቅ፤ ከልቤ አቻ ጋር፡በፍቅር ልራቀቅ፤ ለዓለም ሰው ልለግስ፡ እየሳትኩኝ ልጽደቅ። እናማ እስቃለሁ፡ ካንተ በመሄዴ፤ ላንተ ባዶ ሚዛን ፡ከሆነ መውደዴ፤ ደግሞ አለቅሳለሁ፡እስኪርድ አካሌ፤ "እጠብቅሃለሁ" ሲል፡ላረፈደው ቃሌ። አየህልኝ ውዴ ይህ ነው ሰውነቴ ስነኜን በስንኝ ላፈርስ መነሳቴ "አፈቅርሃለሁኝ"፡የሚለውን ግጥም "ሄጃለሁኝ" በሚል አዲስ ርዕስ ሳትም። አንተ የማታውቀው፡ መውደዴም ሻገተ፤ መጠበቄም አልቆ ፡መጓዝ መሄድ ሻተ፤ በእንባና ሳቆት ፡ውስጤ ተራኮተ፤ እያነቡ እስክስታ ፡ይህ ልቤም ዋተተ። @home_of_poems https://t.me/joinchat/CEgwJDu68dUxYTc0
Show all...
ቤተ ግጥም

ሰላም ውድ የቤተ ግጥም ቤተሰቦች በዚህ ቻናል የተለያዩ ግጥሞች📝 አነሳሽ ጽሑፎች📝 የታዋቂ ሰዎች አባባሎች📝 ሀገራዊ ለዛ ያላቸው ጽሑፎች📝 እንዲሁም📚 አማርኛ መፃህፍት በpdf📚 ታገኙበታላችሁ። for more join 👇👇👇👇 @home_of_poems ጥበብ ከጥንካሬ ይበልጣል። Leave ከማለቶ በፊት አስተያየቶን በዚህ ያጋሩን @Mishayemishaye

Kipa: 🌿ወጣትነት ማለት... ____ ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! . . ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም! . . ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም... . . ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው። . . ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...። . . ምንጭ ፦ "ኤጭ...!" መጽሐፍ -- ከገጽ 170-172 የተቀነጨበ --
Show all...
2.08 KB
Girls If he make you laugh, if he make you feel ur at home, if you feel like u gonna smile everyday if u live with him....DON'T LET HIM GO!!!
Show all...
BOYS If she makes you happy, if you like her, if you feel like you know her............... DON'T LET HER GO🚶‍♀
Show all...
Show all...
ምርጥ ግጥሞች✍️

እንኳን ወደ ምርጥ ግጥሞች ደህና መጡ። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ ምርጥ ግጥሞች ቻናልን የምትወዱ የምርጥ ግጥሞች ተከታታዮች ለምትወዱት ሰው ቻናላችንን ሼር አድርጉልን። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ @Abelaaaaam @Abelaaaaam @Abelaaaaam

።።።።።። በጨዋው ልጫወት።።።።።። "ሆያ ሆዬ" ሲሉ ሙልሙል መስጠት ትቼ፣ ከድምፅ አውጪው ጋራ ብሄድ መንገድ ስቼ፤ ይቅር! ይቅር ብቻ በሉኝ የኔታ አይቆጡ፣ ለቀክፋት አይደለም ለ'አንድ ማታ አይምጡ። ምን መሰሎት አባ፦ ቡሄ አልፎ ክረምት፣ ዶሮም ጮሆ ለሊት፤ ስለማይደገም ግዜም እንደ ትውፊት፤ ዝም ይበሉኝ እና በጨዋው ልጫወት፣ እርሶም አይፈሩ እኔም ልወቅ ልኬት። ✍መክሊት የ16ቷ #የግጥም_ቃና 👇👇👇 @ilovvll @ilovvll 👈 🙌ቤተሰቦች🙌 ለኢትዮጲያዊያን ቤተሰብዎ ያጋሩ 💚💛❤ ሰናይ ግዜ
Show all...
ጃንቦ🍻 ደርድሮ የተነሳው ፎቶ ላይ "ያመነ የተጠመቀ💧 ይድናል" ብሎ ፖስቷል... #ማነህ_ወንድሜ በድራፍት የተጠመቀ ትቦ ውስጥ እንጂ መንግስተ ሰማያት አይገባም😉 😂😆🤣 Share👉 @weg_bicha
Show all...
ፍቅር የትም አለ ══════❁✿❁ ══════ 💞 ✍★★አንድ ብር ላይ ያለው ልጅ 10 ብር ላይ ላለችው ሞሰብ ለምትሰፋው ቺክ የፃፈው አሳዛኝ የፍቅር ደብዳቤ★★✍✍ ፡ ሀይ የኔ ፍቅር እንዴት ነሽ? እኔ በአንቺ ፍቅር ምክንያት ሰላሜን ካጣሁ ቆይቻለው፡፡ ሰው እየሳኩ ሲያየኝ የደላኝ ነው ሚመስለው፡፡ አንቺ ግን ደሀ ነው ብለሽ ነው አይደል ፍቅሬን የገፋሽው?? እዛ 5 ብር ላይ ካለው ሽማግሌ ሰውዬ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደጀመርሽ 50 ሳንቲም ላይ ያሉት ሰዎች ቡና እየጠጡ ሲያወሩ ሰምቼ ንዴቴን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ የዛን ቀን ማታ እራቴን እንኳን ሳልበላ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ስላንቺ እያሰብኩ አደርኩ፡፡ ጥዋት ላይ እንደውም ለምን አልሰድባትም ብዬ ወደ እናንተ ሰፈር ስመጣ በር ላይ ተቀምጠሽ ሰፌድ እየሰፋሽ አየሁሽ፡፡ የሰፌድ አሰፋፍሽን ሳየው ንዴቴ ቡን ብሎ ጠፋ፡ ውበትሽ አስደነገጠኝ፡፡ ስድቡን ትቼ በዝምታ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ ግን አንድ ነገር ልንገርሽ? ያ 5 ብር ላይ ያለውን ሼባ ካንቺ ጋር ያየሁት ቀን እግሩን ነው ምሰብርለት፡፡ አርፎ ቡናውን ቢለቅም ይሻለዋል፡፡ ደሞ እኮ በደንብ ሲያዩት ቡና እየለቀመ ሳይሆን ቡና ላይ የሆነ ምርምር ሚሰራ ነው ሚመስለው፡፡ የኔ ፍቅር ይሄን ደብዳቤ ላንቺ እየፃፍኩ የምጠብቃቸው ከብቶች ስንት ጊዜ የሰው ማሳ ውስጥ እየገቡ አስቸገሩኝ መሰለሽ፡፡ ሰሞኑን የሚመችሽ ከሆነ ሻይ ቡና እያልን እናወራለን፡፡ ለነገሩ ተይው 5 ብር ላይ ያለው ሼባ ሹገርዳዲ ቡና ሲለቅም ካየሁት በኋላ ቡና የሚባል ነገር አስጠልቶኛል፡፡ ♥ ♥ ሁሌም አፈቅርሻለው!!! ♥ 😏😏😏😏😚 🏵🏵🏵🏵🏵🏵 ┈┈••◉❖◉●••┈❀┈┈••◉❖ 🌸 @boznwa @boznwa
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.