cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🇪🇹 TURN ENTERTAINMENT 7 📲0️⃣9️⃣6️⃣6️⃣7️⃣7️⃣4️⃣2️⃣8️⃣0️⃣ 🇪🇹

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
215
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Forgot password is my password! (አሌክስ አብርሃም) አሜሪካ ኑሮው ከባድ ነው፣ብቸኝነቱ ከባድ ነው፣ አየሩ ከባድ ነው ፣ ይሄ ከባድ ነው …ያ ከባድ ነው ይላሉ እንጅ እኔ እስከአሁን የከበደኝ ሁለት ነገር ብቻ ነው! አንዱ ፓስወርድ ማስታወስ ! ፓስወርድ የሌለውን ነገር ጠይቁኝ …. ፓስወርድ በጣም ከመብዛቱ የተነሳ ዝም ብሎ በተራ ቁልፍ የሚከፈት ነገር ላይ ሁሉ ጣቴን አሾላለሁ! ዋሌቴን የሞላውን ካርድ አውጥቸ ብበውዘው …. በየመንገዱ እየዞርኩ በመጫዎቻ ካርድ ማጅክ ምናምን የምሰራ ሰው ያስመስለኛል !እዚች አገር ትንሽ ከቆየሁ እንደጋሽ ስብሃት ካርዴን በፌስታል መያዜ የማይቀር ነው! እንግዲህ ይሄ ሁሉ ካርድ ፓስወርድ አለው! እንዴት እንደሚሰለች የደረሰበት ያውቀዋል! እና አንድ ወዳጀ forgot password is your password ይለኛል ! ሁለተኛው ችግሬ … በጣም የሚበዙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ስቀላቀል ልክ እንደቻይና ኮሪያ ምናምን አንድ አይነት ይሆኑብኛል ! መለየት በጣም ነው የሚከብደኝ ! በምሳሌ ላስረዳ! አሁን በቅርቡ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሳ ጠሩኝ …ምክንያት? ከኢትዮጵያ እህታቸው ስለመጣች! ....ስደርስ ያለምንም ግነት ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ አንድ አይነት ሴቶች ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይላሉ …የሌላውን እንግዳ ብዛት ደግሞ ተውት …ሁሉም አንድ አይነት የባህል ልብስ ለብሰዋል …ሁሉም ሹሩባ ተሰርተዋል …ሁሉም በሜካፕ አብደዋል …ሁሉም አይፎን ስልክ ይዘዋል … እና ሁሉም ጥርሳቸው ብሬስ …በእርግጥ ሁሉም ቆንጆዎች ነበሩ ! እና ምሳ የጠራችኝ አክስታቸው እያስተዋወቀችኝ ነው … እሷ ቲጅ ናት ባለፈው ዳኒን አግብታ የመጣችው …ያው ዳኒ ግን የአጎቷ ልጅ ነው …ለፕሮሰስ ነው እንጅ እሷ አላገባችም ሲንግል ነች ሂሂሂ(ምን ሂሂሂ ያስብላል) !ትክ ብየ አየኋት በስማም ቁንጅና ….ሌሎቹ ጋር አንድ አይነት !ይሄ የተረገመ ሹርባ እንዴት ነው ሰው የሚያመሳስለው! …ይችኛዋ ኪያ ነች ….የዛሬ አመት አሴን አግብታ የመጣችው …አሴን ታውቀው የለ የኔ ትልቁ ልጅ የሩታ ባል …ለፕሮሰስ ነው እንጅ ትክክለኛ ባሏ ዳጊ ነው ! ያች (ነይ አንች ሰላም በይው ) ፍልቅልቅ እያለች መጣች ! ይች ሩሃማ ነች … ለቫኬሽን መጥታ በአሳይለም የቀረችው … ፖለቲከኛ ነች ጋዜጠኛ?…አልኩ ….. ማን እሷ? አሁን ያለው ጠቅላይ ሚንስትር ማነው ብትላት አታውቀውም …ለፕሮሰስ ነው ! ያችኛዋ ናኒ ነች የፍሬው ሚስት …እና ደግሞ ይች ፊኖ የሽሜ ሚስት …ያች ….ኪራ ለፕሮሰስ ፍፄን አግብታ የመጣችው ናት …ፍፄን ታውቀው የለ የሲቲና ባል …. ዘወርወር ስላለብኝ …ከምግብ ቡፌው ላይ ሁለት ናብኪን አንስቸ ሰሃኑ ላይ ካነጠፍኩ በኋላ ቀይ ወጥ ጨመርኩበት …አልጫ ልጨምርበት ስል ነው እንጀራውን እንደረሳሁ ትዝ ያለኝ😐! ወደውስጥ ገብተው በተመለሱ ቁጥር አንዷ ከሌላኛዋ ይምታቱብኛል …ዋናው ነጥብ ሲንግል የተባለችውን ላለመርሳት መሞከር ነው እላለሁ ለራሴ…ለምልክት ቀሚሷን ቀይ ወጥ ላስነካው ይሆን ….! ግን ነገሩ ቀይዋን ያየ የሚሉት አይነት የካርታ ጨዋታ ነበር …ተበወዙብኝ …ውር ውር ውር ያገባች ያላገባች ፕሮሰስ አሳይለም! የቷ ናት ሲንግል ይለኛል አእምሮየ …ይች ነቻ እላለሁ …ተሳሳትክ ይች የፍሬው ሚስት ናት! ሲንግሏ ናት ብየ ያሰብኳትን ፈገግ አልኩላት ፈገግ አለች …ብሬስ ! እንዴት ነው ታዲያ አገሩን ለመድሽው … ኦ እኔ አይደለሁምኮ የመጣሁት …የት ሄደች ቲጅ ናት … ተሳሳቅን! ቆይቸ ቲጅን አገኘኋት ብየ ወሬ ስጀምር ቶማስ መጥቶ አብርሽ ተጫዎት ተዋወቃችሁ?…ናኒ ባለቤቴ ነች ! እንዲቹ እንደተምታታብኝ ‹‹የታለች ሲንግሏ ቲጅ ? መልሳችሁ.... ወደአገር ቤት ላካችኋት እንዴ ? ….›› ብየ ልጮህ ምንም አልቀረኝም በሰው አገር ሰንደል ፀጉሬ ላይ ሰክቸ ከመዞሬ በፊት ማሰቡትን ትቸ ሰሀኔ ላይ አቀረቀርኩ! ምናይነት ፊዚክስ የሆነ ቤተሰብ ነው?! ተሰናብቸ ስወጣ አክስታቸው …ከተል ብላኝ በቁም ነገር … ‹‹እኔ የምልህ አብርሽ …. ትንሽ አትጫዎትም ነበር? …. ‹‹ሌላ ቀን እመጣለሁ ›› ‹‹ መምጣትማ አለብህ ! አንግዳዋን እናተ ካላላመዳችኋት ማን ያላምዳታል?! …ካለች በኋላ ወደዋናው ነጥቧ ገባች! እየውልህ …ሰው በቁሙ ካልተጠቃቀመ መቸም በኋላ እየየ ምን ያደርጋል …አንድ ነገር አስቤኮ …አንድ እህታቸው ብቻ አገር ቤት ቀርታለች … ለፕሮሰስ ለማን ልዳራት ብየ ሳስብ አንተ ትዝ አልከኝ … ባይሆን ያንተን እህት ደግሞ አንዱ የኔ ልጅ አግብቶ ያመጣታል ! ሲንግል ናት …? አልኩ (እስቲምናገባኝ) ኧረ አግብታ ሁለት ወልዳለች …ባሏ በካቦ ቢጎትቱት ከዛ አገር የሚንቀሳቀስ አይነት አይደለም እንጅ ! እንዴት ያለች ቆንጆ መሰለችህ …መዓዚየ! ይች ሴትዮማ በአሳይሎም ቀርታ እንጅ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሳትሆን አትቀርም ! …ወደቤት ስመለስ መንገድ ላይ የትኛው መስመር የኔ የትኛው በተቃራኒ መስመር የሚመጣው መኪና እንደሆነ ብዥዥዥዥዥዥዥዥ …ጭራሽ የተሳሳተ ሰፈር ገብቸ አረፍኩ! ጂፒኤስ ለመጠቀም ስልኬን አወጣሁ…. ስልኬ በፓስወርድ ጥርቅም ተደርጎ ተዘግቷል ….ፓስወርዱን ምን ነበር ? ….አዎ forgot password is my password!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.