en
Feedback
የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

Open in Telegram

*ጥቃቅን ለውጦች- አስደናቂ ውጤት!!! ** የእለት ከእለት ልማዶችን በመጠቀም የላቀ ሕይወት መምራት *** ራስን የመቆጣጠር ምስጥር **** የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ኃይል ***** ዘላቂ ውጤቶችን የማምጣት ምስጢር

Show more
945
Subscribers
+124 hours
+47 days
+430 days
Posts Archive
#መኖር ማለት #አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ #እየኖረ ነው ። ግን መኖር ማለት #እራስን መሆን ፤ ለዓላማ መቆም ፤ #ህሊናን አለመዘንጋት ፣ ፍርድን አለማጓደል ፤ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን #መስዋዕት ማድረግ ብሎም #አርዓያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን #በህይወት ያለነው ?

በጣም አሪፍ አሪፍ የ ድሮ ሙዚቃወች ስብስብ https://t.me/ethiopianoldiessong

እልም ባለ ጨለማ ውስጥ ብርሀን የሚያይ ሰው ከምንም ነገር ይወጣል፤ "ማየት ማመን ነው" ሲባል እንሰማለን ግን አንድ ነገር ካየኸውማ ማረጋገጥ ነው የሚባለው። ማመን ያለብህ ገና ያላየኸውን ነው፤ ገና እጅህ ውስጥ እንዲገባ የምትፈልገውን ደስታ፣ ሀብትና መንፈሳዊ እርካታ ገና ከመሳካቱ በፊት እንደሚሳካ እርገጠኛ መሆን ነው ማመን ማለት። ወዳጄ እምነት እንዳለው ሰው ሀያል የለም፤ አስፈሪ የሚመስሉ ሁኔታዎችና ነገሮች ሁሉ በእምነትህ ፊት ቁጫጭ ናቸው!

የምታደርገውን ነገር ለምን እንደምታደርገው ቆም ብለህ ራስህን ጠይቀው ። 📖📖📖 የተለያዩ ስሜቶችህ የሚመጡት አንተ ስትጠራቸው ሳይሆን በፈለጉበት ሰዓት ነው ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት በስሜትህ ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ሁኔታዎች ዘርፈ-ብዙ በመሆናቸው ነው ። ይህ ሁኔታ በቀላሉ ለመገንዘብ የሚያዳግተን የተወሳሰበ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ስሜትህ፣ የትናንት ልምምድህ፣ የምታሰላስላቸው ሃሳቦች፣ የሰውነት "የሆርሞን" ለውጦችና የመሳሰሉት ከአንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ጥርቅም ነው። ወደ አንተ የሚመጡትን ሁኔታዎች ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ባትችልም፣ ለእነዚህ ነገሮች የምትሰጠውን ምላሽ ግን መቆጣጠር ትችላለህ ። ፧ ለምሳሌ፣ በጥዋት መነሳትና መሄድ ያለብህ ቦታ መሄድ ሲገባህ ከአልጋህ ሳትወጣ ተደብተህ የቆየህበትንና፣ ከተነሳህም በኋላ ራስህን ጥለህ ከቤት ሳትወጣ የዋልክበትን ምክንያት "ለምን?" ብለህ ጠይቅና ተጋፈጠው። ይህንን አትዘንጋ፣ የእለቱ ስሜትህ ነው ተግባርህን የሚወስንልህ። ስለዚህ፣ "ይህንን ነገር የማደርገው ለምንድን ነው? " ብለህ ራስህን መጠየቅ ስትጀምር መንስኤውን ታገኘዋለህ። ይህንን እውነታ መለማመድ ስትጀምር ስሜትህ አንተን መምራቱ እየቀነሰ ይሄድና አንተው አውጥተህና አውርደህ ሚዛናዊ እውነታ ላይ በመድረስ መምራት ትጀምራለህ ። 📖📖📖 ምንጭ ፦ የስሜት ብልህነት(Emotional Intelligence)...ገጽ 41 ✍ ዶክተር ኢዮብ ማሞ

ስኬታማ መሆን ማለት አሁን የቱ ጋር እንዳለህ ማወቅ፤ ከዛ ወደ ምትፈልግበት ጫፍ ለመድረስ የሚጠበቅብህንና ያመንክበትን እያደረክ ከሆነ ነው። አየህ ሁሌም ቀኑ አልፎ ማታ ልተተኛ ስትል እና ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ያመንክበትን ነገር እየሰራህ፣ የሚያስደስትህን ኑሮ እየኖርክ እንደሆነ አስበህ ደስተኛ ከሆንክ ስኬታማ ነህ። ወዳጄ የስኬት ጥግ ደስተኛ መሆን ነው! ደስተኛ ህይወት ተመኘውላችሁ🙏

"ከሚከፈልህ በላይ ስትሰራ ከምትሰራው በላይ ይከፈልሀል" ይለናል ታላቁ የስኬት ደራሲ ናፖሊዮን ሂል። አሁን የምታገኘውን ገቢ አይተህ ልፋትህን አትቀንስ፤ ነገ የምትደርስበት ነው ወሳኙ። ስለዚህ ለምን አቅምህን ትሰስታለህ? በሙሉ አቅምህ ስራ ተማር ከዛ በህይወትህ ላይ ተዓምሩን ታየዋለህ! ውብ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

✅✅✍ የውሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም ፡፡😒 ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም! አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸውን ቀስረው ይስቁብሃል ፡፡ 😏የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸው ።🤷‍♀ ✅✅✍ ገንዘብ ያለውና ፀዳ ብሎ የሚመላለሰውን ሰው ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡😟 የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳው ታየዋለህ ።☹️ ✅✅✍ ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነው ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪው ነገር ነው ፡፡😩 አንዳንዴ ሰውን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል ፡፡😐 ✅✅✍ አንድ ውሸታም ጓደኛህ ከ100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል ፡፡ 😫ጠላቶችህን ተከታተላቸው ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸው ። ✅✅✍ ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል ፡፡ 🙄ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለው ፡፡😢 ✅✅✍ ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም ፡፡🙎‍♂ አንዳንዴ ሰው ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ ፡፡🤷‍♂ ✅✅✍ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ውሰደው ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም ፡፡🙅 ✅✅✍ የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል ፡፡🙄 ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸው አንተነትህ ላይ የሚያመጣው ነገር የለም ፡፡😳 ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትውጣ ፡፡😵 የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ ።🤷‍♀ ✅✅✍ ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነው ፡፡🙍 በአጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት ።🤦‍♀ ✅✅✍ ሰዎች ስለ ደስታ አጋነው ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል ፡፡🤔 በአጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነው ፡፡🙂 ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ ፡፡😟 ብቻ ህይወት እኩል አይደለችም ። 😞በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰው አለ... 🌷በፍቅር እንኑር 🌷

በየቀኑ የምትወስናቸው ትናንሽ ውሳኔዎች የነገ መድረሻህን ይወስኑታል። ማንበብ ውሳኔ ነው፤ ስፖርት መስራት ውሳኔ ነው፤ በጠዋት መነሳት ውሳኔ ነው፤ ለህይወትህ ከሚጠቅሙህ ሰዎች ጋር መዋልም ውሳኔ ነው። ተኝቶ መዋልም ውሳኔ ነው፤ ብር ማጥፋትም ውሳኔ ነው፤ ቲቪ በማየት፣ ፊልም በማሳደድና ስልክ ላይ በመጣድ ሰፊ ጊዜ ማጥፋትም ውሳኔ ነው። ወዳጄ እጅህን ወደ ውሀው ወይ ወደ እሳቱ መስደድ ያንተ ምርጫ ነው! ግን አስብና የሚጠቅምህን ወስን! 🙏🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼

ሙሉ ሰውነትህ ቢወፍር የተለመደ ነው፤ አንድ እጅህ ተነጥሎ ቢወፍር ግን እንግዳ ነገር ነው። አየህ መዝናናትና ፈታ ማለት ላይ ምርጥ ሆነህ ነገር ግን ስራህ ላይ፣ መንፈሳዊ ህይወት ላይ፣ የቤተሰብ ወይ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፈዘዝክ ይሄን ምሳሌ አስታውስ። ወዳጄ የሁሉንም ነገር ሚዛን ማስጠበቅ አለብህ። የተባረከ እለተ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

አሸናፊነትን እንገንባ ፣ አሸናፊነት ይገንባን! አሸናፊ ሰው ያለውን ሁሉ ይሰጣል ። አስፈላጊ ከሆነ እስከ ደሙ ጠብታ ይታገላል ፤ ትግል መገለጫው ነው ፤ ስሜቶቹ እንዲያሸንፋት አይፈቅድም ፤ ፍራቻን አያስበውም ፣ ዋናው አላማው ማሸነፍ ያለበትን ጥሎ ወደ ሌላው አሸናፊነት በፅናት ፣ በታታሪነት መገስገስ ነው ። ከብረት የጠነከረ ስብዕና አለው፤ በቀላሉ አይበገርም ። አዎ! ትንሽ ነገር ባገኘ ቁጥር በፈንጠዝያ ግዜውን አያባክንም ፣ እርሱ ህልሙ ትልቅ ነው ፣ የእርካታው ጥግ ሩቅ ነው ፤ ሁሌም አሸናፊ ሆኖ መኖር የህይወት ግቡ ነው ። ይህ ሁሉ ግን ቅድሚያ ከየት ይጀምራል? እራስን ከማሸነፍ ፣ አትችልም ሰነፍ ነህ የሚለውን አሉታዊ አስተሳሰብ ድል ከማድረግ ፣ በአዕምሮ ውስጥ ያለውን የማይመች መንገድ በመጥረግ በማፅዳት ። አዎ! ጀግናዬ...! በየቀኑ እራስን ድል ማድረግ ፣ እራስን ማሸነፍ የትልቁ አሸናፊነት መሰረት ነው ። አሸናፊነትን እንገንባ ፣ አሸናፊነት ይገንባን! አሸናፊነትን እንኑር ፣ አሸናፊነት ይግለፀን! የአሸናፊነት ቀን ይሁንልን !!

ምሳሌ ሁን ሁሌም አንድ ነገር አስተውል ሰዎች አላማ እንዲኖራቸው ፣ በእቅድ እንዲመሩ ፣ ጠንካራ እንዲሆኑ ምክርህን ከመሥጠትህ በፊት ፤ እነሱ አይሰሙኝም ቢሰሙኝ እኮ የት ይደርሳሉ ከማለትህ በፊት መጀመርያ ለራስህ እወቅበት ራስህን እስከ ጥግ ድረስ ቀይር እና ምሳሌ ሁናቸው። መልካም ምሽት🙏

ምን አይነት ነገሮችን ታዘወትራለህ? በዕለት ዕለት እንቅስቃሴያችን የምናዘወትራቸው ብዙ ተግባሮች ፣ ሀሳቦች ፣ የምናገኛቸው ሰዎችም እንዲሁ አሉን ። ከነዚህ መሀከል አንተስ ጀግናዬ በቅለቱና በክብደቱ ልኬት ዛሬ አብዝተህ የምታዘወትረው የትኛውን ነው ? ቅላሉን ተግባር ፣ አሁን ላይ ምቾት የሚሰጥህን ፣ የሚያደላድልህን ፣ እረፍቱ የበዛውን ፣ የተለመደውን ሀሳብ ወይንስ ጌዜዓዊ ምቾትህን የሚነሳህን ተግባርና ሀሳብ ፣ ረፍት የሚያሳጣህን ተግባርና ሀሳብ ፣ ምናልባትም ከሰው የሚለይህን ተግበርና ምልከታ ? አዎ! ይህ ነው ያንት ማንነት መለኪያ ፣ ይህ ነው የነገው ህይወትህ መመዘኛ ። ዛሬ ተመችቶህ ፣ ተደላድለህ ተኝተህ የፈለከውን እያደረክ መኖርህ ለነገው ህይወትህ ትርጉም አልባ ነው ፣ ዋስትና የለውም ። እርግጥ ነው ምቾትን የሚጠላ የለም ነገር ግን ዘላቂውንና መሠረታዊውን ምቾት ለማግኘት ብዙ አለመመቸትን ፣ ብዙ ፈተናን ፣ ብዙ ሰውን መቻልና ማለፍ መቋቋም ይኖርብሃል ። መበልፀግን የሚጠላ አንድ ሰው ላታገኝ ትችላለህ ፣ ለመበልፀግ ፣ ህይወቱን ለመቀየር ጠንክሮ ዛሬውን የሚሰራ ፣ የሚለፋ ፣ የሚታትር ብዙ አታገኝም ። ዛሬን ሰይሰሩ ነገን እበለፅጋለሁ ፣ አድጋለሁ ፣ እቀየራለሁ ብሎ ማሰብ ግን ሞኝነት ነው። ሁሉም የተሻለ ነገር የሚመጥነውና የሚገባው ዋጋ አለው ። አዎ! ጀግናዬ... ! ዋጋው ዛሬን መልፋት ነው ። ዋጋው ዛሬን መታገል ነው ። ዋጋው ዛሬን እንቅልፍ ማጣት ፣ የሞላሀውን Alarm Snooze ማድረግ ሳይሆን ፤ በቀጠርከው ሰዓት መነሳት ነው ። በድካምህ ጊዜ ከመታገል ፣ በጉብዝናህ ጊዜ አለመመቻቸትን ፣ መታገልን ምረጥ ። ዛሬን ጠንክር ነገን በብዙ ታርፋለህና ። ሰናይ ቀን ይሁንልን!!

አንድ ነገር ለማሳካት እሞክራለሁ የሚባል ነገር የለም፤ አደርገዋለው ማለት አለብህ! እሞክራለሁ ማለት ካልተሳካ አቆመዋለው ማለት ነው። አሁን ቁጭ ባልክበት ከኋላ አንድ ሰው መጥቶ አፍና አፍንጫህን እፍን ቢያደርግህ "ፈጣሪዬ ሆይ ነብሴን ተቀበላት ብለህ" ተስፋ ቆርጠህ ትቀመጣለህ? ወይስ ራስህን ለማዳን እስከምትችለው ድርስ ትንፈራገጣለህ? እርግጠኛ ነኝ ትንፋሽህን ለመመለስ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ትከፍላለህ። አየህ አንተም ማሳካት የምትፈልገውን ነገር እንደ አየሩ ያስፈልገኛል ካልክ ልፋትና ጥረትህን መቼም አታቆምም። ጣፋጭ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

"እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል" የሚባል አባባል አለ፤ መጀመሪያ ራስህን አድን፣ ራስህ ላይ አተኩር! እንዲህ ባደርግ ሰዎች ይደሰቱብኛል ማለቱን ተወውና 'እኔን ደስተኛ የሚያደርገኝ ምን ባደርግ ነው?' በል። አንተ ደስተኛ ስትሆን አለም አብራህ ትስቃለች፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አየህ ራስህ ላይ ስታተኩር ሰዎች ደግሞ አንተ ላይ ማተኮራቸው ግድ ነው። ወዳጄ ደስ የሚለኝ ነገር አንተ ደግሞ ለራስህ ደስታ አታንስም!

ዛሬ! የነገ መድረሻህን እና የመኖር አላማህን ጠንቅቀህ እወቀው፤ ከዛ ግን ትኩረት አርገህ መልፋት ያለብህ ግን ቀንህን ለማሸንፍ ነው። ነገህ ያማረ ሊሆን የሚችለው ዛሬ በሚገርም መንፈስ ካለፈ ብቻ ነው።

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል! ከጎደለህ ይልቅ የተደረገልህ ይበልጣል! ስለዚህ ተመስገን በል ወዳጄ! የምስጋና ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ጥበብ በህይወት ለምን የምፈልገው ነገር ራሱ አልተሰጠኝም ብለህ አትዘን፤ ግን የምፈልገውን የማገኝበትን ጥበብ ስጠኝ ብለህ ጠይቅ፤ ወዳጄ አትርሳ ከአሳው ይበልጥ ወሳኙ አሳ ማጥመዱ ነው! አስገራሚ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ደስታህን ከውጪ አትፈልገው! ከውጪ ባላቸው ነገር፣ በሰበሰቡት ሀብትና ስኬት የፈለጉት ሁሉ ያገኙት እየመሰላቸው ንፋስ እንደጨበጡ አውቀዋል። አንተም የሆነ ነገር ስታገኝ ደስተኛ የምትሆን እየመሰለህ ልክ ስታገኘው ግን ጊዜያዊ ደስታ ብቻ እንደተሰማህ እርግጠኛ ነኝ። ደስታ ከውስጥ ወደ ውጪ የሚወጣ ነገር ነው። የደስታ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

“❄️አትቁም_ወደ_ነገ_ሂድ… "እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል ። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል ። መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል ፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል ። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ ። ባለቀ ትናንት አትታሰር ፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን ፤ ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ ። ነገ ወዳ አንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ ። አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር ። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው ።" ⚜ምንጭ:- "የአዲስ አበባ ውሾች" በ #ዳንኤል_ክብረት ═══════❁✿❁ ═══════

ስሜት! ያለህበትን ሁኔታ ቀላልም ከባድም የሚያደርገው ስሜት ነው፤ አስበው እስኪ በጣም የሚያስደስት ሁኔታ ውስጥ ሆነህ የምታደርጋቸው ነገሮች እኮ ትርጉም ይሰጡሀል፤ ከባድ የሚባለውን ስራ ሳይደክምህ በሚገርም ሞራል ትሰራዋለህ። አየህ ብዙ ነገር ያሳኩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከላይ የነገርኩህ ስሜት ላይ ናቸው፤ ሁሌም የሚያበረታ ኃይል ከውስጥ ይገፋቸዋል። አንተም ውስጥ ያ ሀይል አለ! አሁን ራሱ ምንም አይነት ስሜት ውስጥ ብትሆን እስኪ ወደምትፈልገው ኑሮ፣ ሀብት፣ ደስታ እና የአይምሮ ሰላም እየተጓዝክ እንደሆነ አስብ...ስሜትህ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነኝ። አስደናቂ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏