en
Feedback
የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

Open in Telegram

*ጥቃቅን ለውጦች- አስደናቂ ውጤት!!! ** የእለት ከእለት ልማዶችን በመጠቀም የላቀ ሕይወት መምራት *** ራስን የመቆጣጠር ምስጥር **** የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ኃይል ***** ዘላቂ ውጤቶችን የማምጣት ምስጢር

Show more
945
Subscribers
+124 hours
+47 days
+430 days
Posts Archive
ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በስራ፣ በሀብት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ። ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! ደማቅ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

ፈጣሪ ሆይ 'መቀየር የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል እርዳኝ፤ መቀየር የምችላቸውን እንድቀይር ድፍረቱን ስጠኝ ከሁሉ በፊት ግን ሁለቱን መለየት እንድችል ማስተዋሉን ስጠኝ።' እርካታ የሞላው ህይወት ለመኖር ወሳኝ ፀሎት ነው። የሚያረካ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏 @yikdem

የፈጣሪ እምቢ ማለት አያስደንግጥህ እዚ አለም ላይ እምቢ የተባሉ ናቸው ትልቅ ነገር ያሳኩት። ፈጣሪ ለአንተ የሚገባውን ትልቁን ሊሰጥህ ሲል ትንሹን ነገር ብትፈልግም ፣ ብትለፋበትም ፣ አለቅም ብትልም በግድ ያስለቅቅሃል። ሁሉም ነገር ለበጎ ነው። ድንቅ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ህይወቴ ባዶ ናት፣ ትርጉም የላትም፣ እንደበረሀ ደርቃለች ብለህ ተስፋ ልትቆርጥ ስትል አንጀት የሚያርስ መልስ የሚሰጥህ ፈጣሪህ አለ። ወዳጄ የዘገየ ይመስልሀል እንጂ እሱን የሚቀድመው የለም! አንተ ብቻ ታገስ! የሚያምር ቅዳሜ ተመኘዉላችሁ🙏

🛑 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው 1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ ጊዜው ሲገፋ በዘፈቀደ የሚኖር ከንቱ ሰው እንደሆንክ ማሰብህ አይቀርም፤ 2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤ 3. በፈጣሪህ ታመን ከዛ ልበሙሉነት ፀባይህ ይሆናል ግን ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን! ጣፋጭ ምሽት ተመኘው🙏

የሆነ ነገር ማድረግ ፈልገህ ሰዎች ምን ይሉኛል ወይ ደግሞ ፍርሀት ሲሰማህ እንዲህ ብለህ ለራስህ ንገረው "አንድ አይን ያለው በአይን አይቀልድም፤ አንድ ህይወት አለኝ ያመንኩበትን አደርጋለሁ!" ሁሉም የሚኖረው አንተ ስትኖር ነው፤ ታዲያ አንተ የምትፈልገውን ካላደረክ፣ አንተ ራስህን ካልሆንክ ሌላ ማን እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ? ወዳጄ እንዲ የሚያስቡ ሁሉ የተሻለ የአይምሮ ሰላም አላቸው፤ ውስጥህ እየወቀሰህ እስከመቼ ትኖራለህ? አንተም እኮ ይሄ የአይምሮ ሰላም ይገባሀል! ሰላማዊ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም። ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም። የደስታ ምሽት ተመኘው🙏

ህልም ያለ ስራ ሕልም ብቻ ነው! እቅድ ኖሮህ ሕልም አልመህ በደምብ ካልሰራህ ለምን አልተሳካልኝም ማለቱ ጥቅም አይኖረውም! የስኬት ጫፍ ላይ እስክትደርስ ድረስ በደምብ መስራት አለብህ! አንዳንዴ አንተን መርዳት የሚችለው ብቸኛው ሰው አንተው ራስህ ነህ! የልምድ አስደናቂ ኃይል ለተሻለ ነገ! 🦋

እስካሁን ከደረሳችሁበት ደረጃ የላቀ ደረጃ ባለመድረሳችሁ ከሚሰማችሁ የቅሬታ ስሜት በበለጠ ሁኔታ እንዲያውም ያሳለፋችሁትን ሁሉ ትግል አልፋችሁ እዚህ ደረጃ መድረስ በመቻላችሁ ያላችሁ ደስታ ሚዛን ካልደፋ የወደፊታችሁ ሊያሳስባችሁ ይገባል፡፡ የወቅቱን የአለም ሁኔታ፣ በሃገራችን ያለውን የመሰናክል ብዛት፣ የሰዎችን አስመሳይነትና አስቸጋሪነት፣ የራሳችሁን የስሜት ውጣ ውረድ፣ ብዙውን ነገር ካለምንም ደጋፊ ለብቻችሁ የመጋፈጣችሁን ሁኔታ . . . አልፋችሁ አሁን ያላችሁበት ደረጃ መድረሳችሁ በራሱ አስገራሚ ሰው የመሆናችሁ ማስረጃ ነው፡፡ እናንተ ባለፋችሁበት ሁኔታ ቢያልፉና ተጋፍጣችሁ የመጣችኋቸውን ነገሮች ቢጋፈጡ ኖሮ እናንተ አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለመድረስ ቀርቶ የህልውናቸው ጉዳይ እንኳን የሚያጠራጥር አይነት ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ እናንተ ግን ብዙ ታግላችሁ ሳትበገሩ፣ ወላውላችሁ ተስፋ ሳትቆርጡ፣ ወድቃችሁ ውዳቂ ሆናችሁ ሳትቀሩ . . . እዚህ ደርሳችኋል፡፡ አስገራሚ ሰዎች ናችሁና በዚሁ ግፉበት!

በቅድሚያ ልማዶቻችንን እኛ እንሰራቸዋለን፤ በመቀጠል እነርሱ ይሰሩናል። /ከጆን ድራይደን አንደበት/ የልማድን ግሩም ሃይል ለማወቅ ዛሬ ያለንበትን ደረጃ መመልከት በቂ ነው። ዛሬያችን የትናንት ልማዶቻችንን ውጤት መሆኑ ግልፅ ነው። ዋናው ጉዳይ ጠቃሚ ተግባሮች ልማድ እስኪሆኑ የሚያስከፍሉት ዋጋ ከባድ መሆኑ ነው። በእርግጥ አንድ ድርጊት ልማድ ከሆነ እርሱን ማቆሙና በሌላ መቀየሩ በጣም ከባድ ነው። ጥልቅ ጥንካሬን ይጠይቃል፤ ቆራጥነትን ይፈልጋል፤ ጉዳቱን ደጋግሞ ማሰብ ያስፈልጋል፤ እስከ ዛሬ ሲደረግ ቢቆይም ምን እንደጨመረልን፣ ምን እንዳሳጣን ማሰቡ ተገቢ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ምንያህሉ ልምዶችህ ሰርተውሃል? ምንያህሉስ እያጠፉህ ይገኛሉ? እራስህን ለመፈተሽ አትስነፍ። እራስህን ሳታገኝ የምትሻገረው ደልድይ፣ የምትደርስበት መዳረሻም አይኖርም። አዎ! የሚገነቡህም ልማዶችህ ስለፈቀድክላቸው እየገነቡህ፣ እየሰሩህ፣ ከፍ እያደረጉህ ይገኛሉ። የሚያጠፉህ፣ የሚያሳፍሩህ፣ የሚያሸማቅቁህ ልማዶችህም እንዲሁ ስለፈቀድክላቸው እርሱን ያደርጋሉ። በእራስህ ጉዳይ ፈቃጁም ከልካዩም አንተ ነህና እንዲወዳጁህ የምትፈቅድላቸውን ልማዶች ለይ፤ የምትከለክላቸውን፣ ማራቅ ያለብህንም በጊዜ አቁም፤ በጊዜ ተዋቸው፤ መንፈስህን አድስ፤ ውስጥህን አሳርፍ። የልምድ አስደናቂ ኃይል ለተሻለ ነገ! 🦋

በዚህ አለም ትልቁ እርካታ ምንድነው? ሁላችንም መንፈሳዊ እርካታ የሚሰጠን ፈጣሪን ማምለክና ማመስገን እንደሆነ እናውቃለን፤ አለማዊ እርካታ ለማግኘት ግን በሙሉ አቅም መስራትና መደሰት ግዴታ ነው። (Doing our best) ስራህን ስትሰራ ጥግ ድረስ መስራት፣ ስትደሰት ጥግ ድረስ መደሰት፣ ፍቅር ስትሰጥ ጥግ ድረስ መስጠት፣ ጊዜህን ጥግ ድረስ መጠቀም...ወዳጄ ሁላችንም ከዚህ አለም ስንሰናበት ምንም ነገር ይዘን አንሄድም፤ አየህ በህይወትህ የምትረካው ፈጣሪ የሰጠህን ሁሉ አሟጠህ ስትጠቀም ብቻ ነው! የሚያረካ ህይወት ተመኘውላችሁ🙏

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን ተመኝ፤ መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት! ማራኪ ዕለተ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

ወተቱ ለረጅም ጊዜ ተቀምጦ "የሚጠጣኝ ጠፋ እኮ!" ብሎ ተስፋ ሊቆርጥ ሲል አንጀት የሚያርስ እርጎ ሆነ። ነገሮች በፈለከው መንገድ አልሄዱልኝም ብለህ የጀመርከውን እንዳታቆም! ወዳጄ ልብህን የሚያሞቅ እርካታ ከፈለክ ትንሽ ታገስ። ትዕግስተኛ መሆን ማለት አንድን ነገር መተው፣ ማቆም እየቻልክ ወይ ቸኩለህ መወሰን እየቻልክ ትልቁን ነገር አስበህ ራስህን አሳምነህ አሁን ዋጋ ከፍለህ ነገ በብዙ እጥፍ ማትረፍ ነው። የሚገርም ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

እውቀትህ ከማንም ይለይሃል፤ ፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨ ታነባለህ? በጣም አሪፍ! ብዙ አምብበሃል? ብዙ አውቀሃል? በጣም ግሩም ደስ ይላል። በማንበብህ፣ በማወቅህ እርግጠኛ እንደሆንከው፣ እውቀትህን በመኖርህ፣ ንባብህን በመተግበርህ ምንያህል እርግጠኛ ነህ? እውቀት ሲበስል ደስ ይላል፤ ፍሬው ይጣፍጣል። ብዙ ማንበብህ ምናልባት አዕምሮህን ለተግባር ሊያዘጋጀው ይችላል፣ የተሻልክ ሰው ያደርግሃል፣ ልዩነት ፈጣሪ ልዩ ሰው ያደርግሃል። ንባብህን፣ እውቀትህን ስትጠቀመው ግን ሙሉ አዋቂ፣ አድረጊ፣ የተግባር ሰው፣ ግሩም ተምሳሌት ሰው ያደርግሃል። አዎ! ጀግናዬ..! እውቀትህ ከማንም ይለይሃል፤ ተግባርህ ግን ከሁሉም ያስበልጥሃል። የጊዜ ችግር እውቀት ብቻ አይደለም፣ ንባብ ብቻ አይደለም ያወቁትን መኖር፣ መተግበር፣ በገሃድ አለም ማሳየት፣ መፈፀም ነው። በማንበብህ የተሻልክ ሰው ነህ፣ በተግባርህ ግን እጅግ አስገራሚ፣ አስደማሚ ተዓምረኛ ሰው መሆን ትችላለህ። አስበው እውቀትህ በተግባር ቢታገዝ፣ በምግባር ቢሞላ የት ትደርሳለህ፣ ምን ስታደርግ ነበር፣ ከማን ጋር ነበርክ። ያወከውን ለማካፈልም ሆነ ለመኖር ድፍረት ያስፈልግሃል፣ ቆራጥነት ወሳኝ ነው። ለእውቀት ባዳ የሆነ ሰው እንደ አዋቂ በሚቆጠርበት፣ በማይመለከተው በሚገባበት፣ አላዋቂነቱን በሃሳቦቹ፣ በተገባሩ በሚያስመሰክርበት በዚህ ጊዜ ያንተ እውቀትህን መሸሸግህ፣ አበርክቶትህን፣ እርዳታህን ማጉደለህ አንተንም ሆነ በዙሪያህ ያሉትን እንዲሁም ሃገርህን ብዙ ያሳጠችኋል። ክብራችሁን፣ የሚገባችሁን ስፍራ፣ የሚገባችህን፣ የሚመጥናችህን ስጦታ ያሳጣችኋል። አዎ! ጀግናዬ..! አዋቂ የተግባር ሰው ሁን፣ የድርሻህን ተወጣ፤ እራስህን አሳርፍ፣ ቤተሰብህን ደግፍ፣ ሃገርህን አበርታ። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 የልማድ አስደናቅ ኃይል ለተሻለ ነገ! 🦋

🧠 የስነ-አዕምሮ እና ስነ-ልቦና ችግሮች መረጃ ይፈልጋሉ? ✅ይህ ቻናል በዋናነት በአዕምሮ ጤና ላይ ያተኩራል:: ✅ስለ አዕምሮ ህመም አይነቶች ግንዛቤ እንዲኖርዎ ያስጨብጣል; https://t.me/joinchat/UTa8HjtdRDcRVbEa

በህይወት ውስጥ ትልቁ ፈተና የልብህን እውነት ሰዎች እንዲረዱህ ማድረግ ነው። ቤተሰብ፣ ወዳጅ የልቤ የምትለው ጓደኛ ላይረዳህ ሁሉ ይችላል፤ የሚሻለው መተው ነው። እነሱ እንዲረዱህ የምታባክነውን ጉልበትና ልፋት ራስህን ለማሳደግ ብታውለው ብዙ ርቀት ትጓዛለህ። በህይወትህ ላይ ልዩነት የምትፈጥረው ራስህ ላይ ስትሰራ ብቻ ነው!

#እንዴት_ድንበርህን_ማካለል_ትችላለህ? #ሕይወትህን_አንተ_በምትፈልገው መንገድ መምራት የሚያስችሉ ጤናማ ድንበሮችን አብጅ። #ዋጋ_የምትሰጣቸውን ነገሮች፣ የምታምንባቸውን መርሆዎች እና ቅድሚያ የምትሰ
#እንዴት_ድንበርህን_ማካለል_ትችላለህ? #ሕይወትህን_አንተ_በምትፈልገው መንገድ መምራት የሚያስችሉ ጤናማ ድንበሮችን አብጅ። #ዋጋ_የምትሰጣቸውን ነገሮች፣ የምታምንባቸውን መርሆዎች እና ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ነገሮች ለይ። #ድንበርህን_ከሚያልፉ ሰዎች ጋር ተቀምጠህ ተወያይ። ላንተም ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ነግረህ ድንበር እንዳያልፉ ንገራቸው። #በውይይቱም_ሊቀልዱብህ_ወይም ሊሳለቁብህ ይችላሉ፤ ነገር ግን የምርህን እንደሆነ አስረግጠህ ንገራቸው። #ድንበርህንም_ባለፉት_ቅጽበት፣ ድንበር እያለፉ እንደሆነ ንገራቸው። ስትነግራቸውም መጥፎ ምላሽ ወይም ስድብን ከመለሱልህ ከእነሱ ጋር አፍ እላፊ አትግጠም - ትተሃቸው ሂድ። #ክብርህን_ለሚጠብቁ እና ድንበርህን ለማያልፉ ሰዎች በምላሹ እነሱ የሚወዱትን ነገር አክብርላቸው። አመስግናቸው ወይም የሚያደርጉት ነገር እንደሚያስደስትህ ምልክት ስጣቸው። #አንተም_በተቻለህ_አቅም የሰዎችን ድንበር ላለመጣስ ሞክር። ክብርን ስትሰጥ ክብርን ታገኛለህ። #አምባገነን_ለመሆን_አትሞክር። አንዳንዴ ከሁኔታዎች አንጻር እና በአንዳንድ አሳማኝ ምክንያቶች ድንበሮችህ ሊጣሱ ይችላሉ። እናም ድንበሮችህን መቼ መዝጋት እና መክፈት እንዳለብህ እወቅ። #ታጋሽ_ሁን። ድንበሮችህን አስምረህ የማታውቅና ይሄ የመጀመሪያህ ከሆነ፣ ሰዎች ድንበሮችህን ለማስተዋል እና ለማክበር ጊዜ ይፈጅባቸዋል። እንደውም አንተ እራስህ ድንበሮችህን ለማስከበር እርግጠኛ ላትሆን ወይም ልታፍር ትችላለህ። እናም ቀስ በቀስ ድንበሮችህን አስምር። #በራስህ_ተማመን። ለራስህ ክብር ስትሰጥ እና እራስህን ስትወድ ድንበርህን ማስከበር ቀላል ይሆንልሃል። ማንምም እንዲያስከፋህ አትፈቅድለትም። #ጭንቅላትህን_አጽዳ መፅሐፍ

አይታችሁ ከሆነ አርፍደን ከተነሳን ወይ ማስቀመጥ ያለብንን ገንዘብ ካጠፋን፣ እሰራለው ወይ አነባለው ብለን ሳናደርግ ከቀረን ውስጣችን ይወቅሰናል፣ ሰላም ይነሳናል፤ ይህ ስሜት ሲደጋገም የሰነፎችን እጣ ፋንታ ይሰጠናል። ወዳጄ ሙሉ አቅምህን ተጠቅመህ ጥግ ድረስ መማር ወይ ወጥረህ መስራት ያለብህ ስኬታማ ለመሆን ብቻ አይደለም፤ የአይምሮ ሰላምህን ለማግኘትም ነው! ሰላማዊ ማክሰኞ ተመኘውላችሁ🙏

ራስህን ለመለወጥ የሚያስገድድህ ቀን እስኪመጣ ለምን ትጠብቃለህ? አሁን ነቃ ብለህ ራስህን ጠይቀው 1. ነገ ምንድነው የምሆነው? 2. ምን አይነት አለማዊና መንፈሳዊ ህይወት ነው የሚኖረኝ? 3. ከማን ጋር ነው የምኖረው? 4. ደስተኛ የምሆነው ምን ባሳካ ነው? ብለህ ጠይቅ፤ ፈጣሪ በአንድም ይሁን በሌላ መልስ ይሰጥሀል። መልሱ ግልፅ እስኪሆን ግን ነገን አስበህ ራስህን ሁሌም አሳድግ፤ ገንዘቡን አስቀምጥ፣ መፅሀፉን አንብብ፣ ተማር፣ ገቢህን ለማሳደግ የሚጠበቅብህን አድርግ! ወዳጄ ስንፍናህን ቆፍረህ ቅበረው፤ የዚህ አለም ስኬት ለተኙ አይደለም ለነቁ ነው፤ ለፈዘዙ አይደለም ለባነኑ ነው! ጣፋጭ ምሽት ተመኘውላችሁ🙏