en
Feedback
የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

የልማድ አስደናቂ ኃይል/ Atomic Habits

Open in Telegram

*ጥቃቅን ለውጦች- አስደናቂ ውጤት!!! ** የእለት ከእለት ልማዶችን በመጠቀም የላቀ ሕይወት መምራት *** ራስን የመቆጣጠር ምስጥር **** የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ኃይል ***** ዘላቂ ውጤቶችን የማምጣት ምስጢር

Show more
945
Subscribers
+124 hours
+47 days
+430 days
Posts Archive
🌀24ቱ የምንጊዜም የህይወት ህጎች🌀 🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺 ✅ከመናገርህ በፊት→አስብ፣ ✅ከመፈረምህ በፊት→አንብብ፣ ✅ከማስተማርህ በፊት→ተማር፣ ✅ከመምከርህ በፊት→ተግብር፣ ✅ከመቁረጥህ በፊት→ለካ፣ ✅ከማጉደልህ በፊት→ተካ፣ ✅ከመዋጥህ በፊት→አላምጥ፣ ✅ከመገንዘብህ በፊት→አድምጥ፣ 🌀ከማመንህ በፊት→አረጋግጥ፣ 🌀ከመረከብህ በፊት→ቁጠር፣ 🌀ከመወሰንህ በፊት→መርምር፣ 🌀ከመስራትህ በፊት→አቅድ፣ 🌀በትጋት ሳይሆን በብልሃት ስራ፣ 🌀ከመተኮስህ በፊት→አልም፣ 🌀ከመተቸትህ በፊት→አጣራ፣ 🌀ከመብላትህ በፊት→ስራ፣ ✴ከመሞትህ በፊት→ነሰሃ ግባ፣ ✴ከመሄድህ በፊት→ተስፋ ሰንቅ፣ ✴ስትወያይ→ሁን አስተዋይ፣ ✴ስትናደድ→ቶሎ ብረድ፣ ✴ስትናገር→በቁምነገር፣ ✴ስትቸገር→መላ ፍጠር፣ ✴ስትቀመጥ→ቦታ ምረጥ፣ ✴ስትወስን→ቆራጥ ሁን!! ═════════❁✿❁ ═════════ 💪💯 አንብባችሁ #ሼር #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇 https://t.me/atomichabity

#ጠቃሚ_ምክሮች 1. ከአላስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች መራቅ። 2. ራሳችንን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች እናርቅ። ምክንያቱም እኛን ራሱ ሳንፈልገዉ እንደነሱ እንድናስብ እንድንገደድ ስለሚያረጉን፡፡ 3. መቀበል የምንፈልገውን እንስጥ። 4. ገንቢ ያልሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት መቆጠብ። 5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑረን። 6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አንበል፣ የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና። 7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻው መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል.... ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኋላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ:: #መልካም_ቀን_ይሁንላችሁ!

ለማሸነፍ ራሳችንን መሆን ነው ያለብን! ሴት እና ወንድ እኩል ናቸው የፈለጉትን የማድረግ ችሎታውም መብቱም አላቸው ፣ የመሳሰሉትን ነገሮች እናውቃለን ነገር ግን ይሄ ማለት ምንም የሚያለያያቸው ነገር የለም አንዳቸው የሚችሉትን በሙሉ ሌላኛቸውም ይችሉታል ወይ መቻል አለባቸው ማለት አይደለም ! እንደዛማ ቢሆን የተለያየ ፆታ መኖር አያስፈልገንም ነበር ሴት ልጅ የራሷ የሆነ የማሸነፍያ ጥበብ ተሰጥቷቷል ለማሸነፍ ለማሳካት ድል ለማድረግ ወንድን መሆን አይጠበቅባትም እህቴ ከበቂ በላይ ብልሀት እና ጥበብ በውስጥሽ አለ ስለዚህ ባለሽ ነገር ማሸነፍ ትችያለሽ ወንድሜ አንተም ሞገስ ተሰጥቶሀል አቅም አለህ ስለዚህ እንደራስህ ሆነህ አሸንፍ! የተሰጠንን ሆነን ስንኖር ትዳራችንም ቤታችንም ይሰምራል! የተባረከ ቀን ተመኘው 🙏

ለመስነፍ አልተፈጠርክም! የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ! ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወዳጄ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው። ግሩም ምሽት ተመኘውላችሁ🙏

ነገ ትልቁ ቦታ የሚያስቀምጥህ አሁን ትኩረት ያደረክበት ነገር ነው፤ አሁን ጊዜህን የሚሻማው ጊዜያዊና የማይጠቅም ከሆነ ዋጋ ትከፍላለህ ራስህን መቼም አትችልም ሁሌም የገንዘብ ጉዳይ ያሳስብሀል፤ ለምትወዳቸው አትደርስም! ትኩረትህ ግን የሆነ ነገህን የሚያሳምር፣ አሁን የሚያለፋ ነገ ግን የሚያሳርፍህ ነገር ላይ ከሆነ ወጥረህ ትሰራለህ፣ ገንዘብ ታስቀምጣለህ፣ ሁሌም ራስህን ታሳድጋለህ፣ ጊዜያዊ ደስታን ትንቃለህ። ወዳጄ ለሚጠቅምህ ነገር ብቻ ዋጋ ከከፈልክ ደስተኛ ሆነው ህይወትን ከሚመሩ ጥቂት ሰዎች አንዱ ትሆናለህ! ሰናይ ረቡዕ ተመኘውላችሁ🙏

"ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ ካላወክ የትኛውም መንገድ የሚወስድህ ይመስልሀል" የሚል አባባል አለ።የምትሰራው ስራ የት እንደሚያደርስህ ማወቅ አለብህ፤ እሱን ካላወክ እግረ መንገድህን ነው የምትኖረው ማለት ነው። ህልም ያስፈልግሀል፤ የአላማ ሰው መሆን አለብህ! እርግጠኛ ነኝ ሁሌም የአይምሮ ሰላም እየተሰማህ መኖር ትፈልጋለህ፤ ወዳጄ አንድ ነገር አርግ 'አጥብቀህ የምትፈልገውን የህይወትህን መድረሻ አሁን እወቀው!' ከዛ ወደሱ መጓዝ ጀምር። ግሩም ሰኞ ተመኘንላችሁ🙏

ብዙ ነገር ልትፈራ ትችላለህ፤ ተሰፋ ልትቆርጥ ስትል ግን ፈጣሪን አስብ፤ ፈጣሪ ማለት በሱ ላይ አምፀህ በሩን የዘጋህ ጊዜ የምትተነፍሰውን አየር በበሩ ስር የሚያስገባልህ ነው፤ ለፍርሀትህ አሳልፎ የሚሰጥህ ይመስልሀል? እንዳይመስልህ ወዳጄ! የእምነት ህይወት ተመኘንላችሁ🙏

ለሰዎች መምከርማ እንችልበታለን! ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል ከነሱ በላይ እኛ እናውቃለን፤ ችግሩ እሱ አይደለም "ለራሴስ እንዴት ልወቅበት?" ነው ጨዋታው። አንድ የማከብረው ሰው "አገሬን እቀይራለው ብዬ ተነሳው ብዙም ሳልቆይ እንደማይሆን ገባኝ፣ አይ መቀየር ያለብኝ ከተማዬን ነው አልኩ እሱም እንደማይሳካ ሲገባኝ ሰፈሬን አልኩ፣ ከዛ ቤተሰቦቼን አልኩ....በመጨረሻ የገባኝ ነገር መጀመሪያ ራሴን መቀየር እንዳለብኝ ነው" ይለናል። ጣፋጭ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

እውነተኛ መውደድ የሚገለፀው መጀመሪያ ራስን በመውደድ ነው፤ ሰዎች አንተን ከማክበራቸው በፊት አንተ ራስህን አክብረው። እነሱ ሁኔታህን አይተው ነው የሚለዋወጡት። የአንድን ዕቃ ዋጋ የሚያወጣው ሻጩ ነው ካላዋጣው እኮ መቼም አይሸጥም፤ የራስህን ዋጋ የምታወጣው አንተ ነህ! ራስህን ከምንም ነገር በላይ አክብረው ወዳጄ! ተመልሰናል ቤተሰቦች💪 ውብ አዳር ይሁንላችሁ🙏

ጥረት በጣም ወሳኝ ነው፤ ከሱ በላይ ግን ጠንቅቀህ ማወቅ ያለብህ የቱ ጋር መጣር እንዳለብህ ነው። ትልቁ ቦታ የምትደርሰው ጠንካራ ጎንህ ላይ ይበልጥ ከጠነከርክ ብቻ ነው! ጠንክረህ እንደምትሰራው "ምንድነው የምሆነው? የት ነው የምደርሰው?" ብለህ ጠንክረህ አስብ። አቦ ሸማኔ እንዲሮጥ እንጂ እንዲዋኝ አልተፈጠረም፤ ወዳጄ አንተም የቱ ጋር ማተኮር እንዳለብህ ስታውቅ ተዓምረኛ እንደሆንክ ታየዋለህ! አስጠራም ዕለተ ሰንበት ተመኘውላችሁ🙏

ለዛሬ መድረስ ቀላል አይደለም፤ ያበላሸኸውን እንድታስተካክል እድል ተሰቶሀል፤ ደስተኛ ሆነህ በእርካታ እንድትኖር አንድ ቀን ተጨምሮልሀል። ዛሬ የመጨረሻ ቀንህ ቢሆን እንዴት ነው ምትጠቀምበት? የሚባክን ይመስልሀል? እርግጠኛ ነኝ ከምትወዳቸው ጋር ምርጥ ጊዜ ታሳልፋልህ፤ ወደ ፈጣሪህ ይበልጥ ትቀርባለህ፤ ያስጨነቁህ ነገሮች ሁሉ ካንተ እንደማይበልጡ ስለሚገባህ ፍርሀቶችህ ሁሉ ተነው ይጠፋሉ። ወዳጄ ዛሬ የተሰጠህ እንትጨነቅበት አይደለም አመስግነህ እንድትጠቀምበት ነው! አስገራሚ ማክሰኞ ተመኘውላችሁ🙏

የምትፈልገው ጥግ ድረስ መሄድ የምትፈልግ ከሆነ መቼም የማይቆሙ ልማዶች ያስፈልጉሀል፤ እነዚሆኖ ልማዶች ለማስኬድ ደግሞ ዲስፕሊን ወሳኝ ነው! ዲስፕሊን ማለት ቢመችህም ባይመችህም፤ ደስ ቢልህም ቢከፋህም በቀን ውስጥ ማድረግ ያለብህን ሁሉ ማድረግ ነው። ፀባይህ እንዲህ ከሆነ ከምታስበው በላይ ስኬታማ ትሆናለህ! የተባረከ ዓርብ ተመኘውላችሁ

ይሄ ቀን ለኔ ነው በል! እንዴ ላንተ ባይሆንማ በተኛህበት ትቀር ነበር፤ ስንቶች በተኙበት ቀሩ? ስንቶች በዚህ ለሊት ከመሬት በታች በመቃብር አደሩ? ለምን መሰለህ? ቀናቸው እንዲሆን ፈጣሪ አልፈቀደማ! እኛ ግን ተፈቅዶልናል ዛሬ የኛ ነው! መልካም ማክሰኞ ተመኘውላችሁ🙏

[ Photo ] #Daily_Tips በራስ መተማመንን እንዴት ልገንባ? በራስ መተማመን( self confidence) ስንወለድ ጀምሮ የሚሰጠን ነገር አደለም አንዳንዴም በቀላሉ ለመገንባት ሊከብድ ይችላል
[ Photo ] #Daily_Tips በራስ መተማመንን እንዴት ልገንባ? በራስ መተማመን( self confidence) ስንወለድ ጀምሮ የሚሰጠን ነገር አደለም አንዳንዴም በቀላሉ ለመገንባት ሊከብድ ይችላል የአኗኗር ዘያችን አስተዳደጋችን በራስ መተማመንን የማያስገነባ ሊሆን ይችላል ብዙዎች በሰዎች ፊት ቀርቦ ማውራት ሀሳብ መናገርን ይፈራሉ ምክንያቱም በተልምዶ እንግዳ ወይም አዲስ ሰው ሲመጣ ልጅ ወደጓዳ የሚባል ነገር አለ ለታላቅ መልስ አይሰጥም በማለት ልጆች ፍርሀትን እንዲለማመዱ ያደርጋል። ታድያ እንዴት እንገባው 🔷 ከዚ በፊት ህይወታችን ላይ ስላሳካናቸው ትልቅም ትንሽም ነገር ማሰብ ማስተዋል እራስን መገምገም 🔷 እራሳችንን ምን ላይ ጎበዝ እንደሆንን ማስተዋል 🔷 ግብ ማስቀመጥ ልናሳካው ምንፈልገውንና የምንችለውን ነገር 🔷 ከራሳችን ጋር ያለንን ንግግር መልካም (positive) ማድረግ እንደምንችል እንደምናደትገው ማመን ተደጋግሞ በራስ መተማመን የሚለውን ቃል ስለምናደምጠው ያወቅነው የተላበስነው ይመስለናል።

10 አነቃቂ ጥቅሶች፡- 1. አልበርት አንስታይን - "ስህተት ያልሰራ ሰው, አዲስ ነገር ሞክሮ አያውቅም." 2. ስቲቭ jobs - "ጊዜህ የተገደበ ነው, ስለዚህ የሌላ ሰውን ህይወት በመምራት አታባክን." 3. ቢል ጌትስ - "ስኬትን ማክበር ጥሩ ነው, ነገር ግን የውድቀት ትምህርቶችን መከተል የበለጠ አስፈላጊ ነው." 4. ዋረን ባፌት - "ታማኝነት በጣም ውድ ስጦታ ነው, ከርካሽ ሰዎች አትጠብቅ." 5. ብሩስ ሊ - "ስህተቶች ሁል ጊዜ ይቅር ይባላሉ, አንድ ሰው እነሱን ለመቀበል ድፍረት ካለው." 6. አልበርት ሁባርድ - "አንድ ማሽን የሃምሳ ተራ ሰዎች ስራ ሊሠራ ይችላል, የትኛውም ማሽን የአንድ ያልተለመደ ሰው ስራ አይሰራም." 7. ሮበርት ኪዮሶኪ - "ሽንፈት ተሸናፊዎችን ያሸንፋል, ነገር ግን አሸናፊዎችን ያነሳሳል." 8. አብርሃም ሊንከን - "የወደፊቱን ለመተንበይ ምርጡ መንገድ መፍጠር ነው." 9. Audrey Hepburn - "ምንም የማይቻል ነገር የለም, ቃሉ ራሱ "እችላለሁ" ይላል. 10. ማያ አንጀሉ - "ሰዎች የተናገርከውን እንደሚረሱ, ሰዎች ያደረጋችሁትን እንደሚረሱ, ነገር ግን ሰዎች እንዴት ደስተኛ እንዳደረጋችሁ አይረሱም."

አይምሯችን መሬት ነው፤ የተዘራበትን ማብቀል ነው ስራው። መልካም ነገር ከነገርነው፣ መልካም ነገር ካየ የህይወት መንገዳችን ያማረና ደስተኛ እንሆናለን። ለሆዳችን እኮ በጣም ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በፍፁም የቆሸሸ ምግብ አንበላም። ታዲያ የነገ መድረሻችንን ለሚወስነው አይምሯችን ምንድነው የምንመግበው? መጥፎ ዜና ነው ወይስ መንፈሳዊ ሀሳብ? ስለ ሰው አሉባልታ ነው የምናስበው ወይስ ስለ ነገ መድረሻችን? ምርጫው የኛ ነው!

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም። በራስህ ለውጥ
የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም። በራስህ ለውጥ ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ። ወዳጄ አይንህን ከሌሎች ላይ ነቅለህ ወደ ራስህ ባየህ ቁጥር እድገትህ ፈጣን ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአይምሮ ሰላም አለህ! ሰላማዊ ሰኞ ተመኘዉላችሁ🙏

አንዳንዴ ማድረግ የሚገቡንን ነገራቶች ሳንከውናቸው እንቀራለን፤ ለዛ ነገር ያለመሆን ምክኒያት ብለን ደግሞ ዝርዝር እናወጣለን! በሥህተት ላይ ስህተት ማለት ይሔ ነው። ሲጀምር ያን ነገር በተግባር ከመግለጻችን በፊት በአይምሮዓችን ላይ ስራውን ሰርተን መጨረስ ይገባናል! ያ ከሆነ ስራችን በእጅጉን ይቀላል!!! ሲቀጥል ስላልፈጸምነው ነገር ምክንያት ከመደርደር ይልቅ ሃላፊነቱን ወስደን ለማስተካከል መሞከር ለውጥ የሚያመጣና መነሳሳትን ሊፈጥር የሚችል ነው!!! ማንኛውንም ስራ መሬት ከማውረዳችን በፊት እኛ ውስጥ ሰርተን መጨረሱ ጥሩ ስራ በተግባር እንዲገለጽልን ይረዳናል!!!

🧤እንደ ፈጣሪ ያለ ማንም የለም! ለሱ ታመን፤ እሱ ካከበረህ ማንም ቢንቅህ ቢሰድብህ እንዳትደነግጥ! እንዳትከፋ! የምትኖርበት ቤት ያለ ግድግዳና ምሰሶ ይደረመሳል፤ ሰማይ ግን ምሰሶ የለውም፣ ግድግዳ የለውም ብቻውን ነው የቆመው! እሱን ብቻ ፍራ! ማንም አያቆምህም! እምነት የሞላው ህይወት ተመኘውላችሁ🙏

ራስህን ለመለወጥ ብትሞክርም ባትሞክርም ጊዜው እንደሆነ መሄዱ አይቀርም፤ ታዲያ ራስህ ላይ ሰርተህ የዛሬ አመት ቢመጣ አይሻልም? ህይወትን በዘፈቀደ ሳይሆን በእቅድ ለመኖር ምርጫው ያንተ ነው! ልዩ ረዕቡ ተመኘውላችሁ🙏