cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ- ማርያም የተዋህዶ ልጆች /ንስሐ እንግባ/✝✝✝Bete-Mariam Yete Wahdo Lijoch Nisha Engba በ ቴሌግራም ይከታተሉ❤️❤️❤️❤️✝✝✝✝

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች , ወቅታዊ የቤተክረርስቲያን መልክቶች, ሥለ-ንስሀ ሂዎት, የየእለቱ ቅዱሳን ገድል መጽሀፈ ስንክሳር እና መዝሙሮች የሚተላለፉበት።ሸር አና forwared በማድረግ ለማንኛውም ኦርቶዶክስ እህትና ወንድማችሁ አዳርሱ view ሚለውን በመጫን የቅዱሳንን ዜና ገድል ይወቁ ይማሩ።

Show more
Advertising posts
201
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። (ሙሉ መግለጫው ከታች እልክላቹኃለሁኝ) Credit : EOTC TV ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE @MoaeTewahedoB
Show all...
ዋና ዋና ነጥቦች ●ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል። በዚህም ከመንግስት ጋር፦ ● የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ  አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤ ● አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል። ●መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ለነገ እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። ●በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ  ምሕረት ላይ  ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። ●ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ የተደረገው የአቋም ለውጥ ተደርጎ አለመሆን በመግለፅ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያኗ በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት በማሳየቱ ምክንያት መሆኑን አስገንዝቧል። ●ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል። tikvahethiopia ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE @MoaeTewahedoB
Show all...
Show all...
ደስ እያላቸው ወጡ ! አዲስ ስብከት በዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ( deacon yordanos abebe )

Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UCaNn...

የቅዱሳንን ዜና (ታሪክ) እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን " " አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ " ትምህርቱን ለሌሎች ያዳርሱ #ZETEWAHEDO-ዘተዋህዶ

https://t.me/zikirekdusn/8180 ሰማዕታተ አሪንጎ የካቲት 4
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

✝እንኳን አደረሳችሁ✝ 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/ ☞በአፄ ሱስንዮስ ዘመን (ከ1595-1624)፡ በዚች ዕለት (የካቲት 4)፡ በአሪንጎ (ከደብረ ታቦር 10 ኪሎ ሜትር) 85 ቅዱሳን መነኮሳት ስለቀናችው እምነት (ተዋሕዶ) ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ ☞ንጉሡና ጀሌዎቻቸው በእሳት ፈተኗቸው፡ እሳቱን አጠፉ፡፡ አናብስትን ላኩባቸው አሰገዷቸው፡፡ አንገታቸው ሲቆረጥ ክንፍ አውጥተው 150 መዝሙረ ቅዱስ ዳዊትን ደግመው ተሠውረዋል፡፡ ☞እነዚህም የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስና የቅዱሱ ሰማዕት ባለቤቷ የዘርዓ ክርስቶስ ማኅበር ናቸው፡፡ "" ከሰማዕታተ አሪንጎ በረከትን ይክፈለን፡፡ "" Dn Yordanos Abebe ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

https://t.me/zikirekdusn

'

✝እንኳን አደረሳችሁ✝ "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/ ማኅደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኵልነ ኀበ ማርያም እምነ። ሰላም ለክሙ እንጦንስ ወመቃርስ፤ አቢብ ሲኖዳ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤ ለባርኮትነ ንዑ ውስተ ጽርሐ ዛቲ መቅደስ፤ ተክለሃይማኖት አኖሬዎስ ኤዎስጣቴዎስ፤ ሳሙኤል ተክለ አልፋ በብኑዳ ኪሮስ፡፡ ነብያት ወሐዋርያት ጻድቃን ወሰማዕት ደናግል ወመነኮሳት አዕሩግ ወሕጻናት ገዳማውያን ወሊቃውንት ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት። ሰአሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን . . . ከዋክብት ብሩሃን . . . ማኅትዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ~የቤተ ክርስቲያን መብራቶች:: ~የንጋት ኮከቦች የተባላችሁ:: ~ስለ ቀናች እምነት የተጋደላችሁ አእላፋት ሰማዕታት ሆይ! ~ትለምኑልን ዘንድ ለእኛ ይገባል !!! "" አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም "" "" ሰማዕታት የዚህን ዓለም ክብር በእውነት ናቁ ""   ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!! " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::        አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Show all...
†✝† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ ††† ††† ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት (በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ) በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: (ሐዋ. 11:27) በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው (መቃብሩ) ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች:: ††† የአባታችን በረከት ይደርብን:: የ††† ካቲት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት 2.አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ††† "በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ:: ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ:: እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" ††† (ሐዋ. ፲፩፥፳፯) ††† "ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን::" ††† (ዕብ. ፲፫፥፲፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† Dn Yordanos Abebe
Show all...
ዛሬ የምነግርህ ነገር በልብህ ውስጥ ይቀመጥ✝                           Size 16MB Length 46:01   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ http://t.me/abagebrekidan http://t.me/abagebrekidan
Show all...