cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሻሸመኔ ደ/አርያም ቅ/አርሴማ እና ቅ/መርቆርዮስ ሰ/ት/ቤት

✟✟✟

Show more
Advertising posts
1 508Subscribers
No data24 hours
-107 days
-7130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🍁🍁የሲኦል እና የገሀነመ እሳት ልዩነት በአጭሩ 🍁🍁🍁ሲኦል ÷ የነፍስ ጊዜአዊ ማቆያ ነው ። የዓለም ፍፃሜ እስኪሆን ድረስ በምድር ላይ ከ ሕገ እግዚአብሔር ርቀው ፣ በሐጥያት እና በበደል ያሳለፉ ሰዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ስጋቸው ወደ መቃብር ነፍሳቸው በሲኦል ትቀመጣለች ፣ ትቀጣለች ። 🍁🍁🍁ገሀነመ_እሳት ደግሞ ÷ ከምፅአት( ከፍርድ ቀን) በኃላ በበደል ያሳለፈች ነፍስ እስከ በሌለው ፍርድ ለዘላለም የምትቀጣበት አስፈሪ ስፍራ ነው ። አሁን ሰው በሞተ ስጋ ሲለይ በሐጥያት አሳልፎ ከሆነ ነፍሱ እስከ እለተ ምፅአት ( የፍርድ ቀን) ድረስ እየተቀጣች የምትቀመጠው በሲኦል ነው ። ገሀነመ እሳት ፍርድ ቀን የሚመጣ ነው ። ከምፅአት ( ከፍርድ ቀን) በኃላ ግን የተበተነው ፣ የበሰበሰው ስጋ ተነስቶ ወንድ የ30 ሴት የ15 ዓመት ሆነው በሲኦል የነበረችው ነፍስ ከተነሳው ስጋ ጋር ተዋህዷ ነፍስም ስጋም አንድ ላይ በዘላለም ፍርድ በእሳት ቅጣት የሰው ልጅ ይኖራል ። ሁሉን ማስተካከል የሚቻለው በምድር እያለን በሞተ ስጋ ከዚህ ዓለም ሳንሔድ ብቻ እና ብቻ ነው ። የገሀነመ እሳት ሁኔታ ምን ይመስላል ÷ እሳቱ የማይጠፋ ፣ ትሉ የማያንቀላፋ በቁማችን የሚበላን ፣ ሰይጣን እና መልዕክተኞቹ የሚሰለጥኑብን ( የፈለጉትን የሚያደርጉብን) ......... ይሆናል ልዑል እግዚአብሔር ይህን ስፍራ እንዳናይ ይርዳን አሜን።
Show all...
👍 1
🍁🍁የሲኦል እና የገሀነመ እሳት ልዩነት በአጭሩ 🍁🍁🍁ሲኦል ÷ የነፍስ ጊዜአዊ ማቆያ ነው ። የዓለም ፍፃሜ እስኪሆን ድረስ በምድር ላይ ከ ሕገ እግዚአብሔር ርቀው ፣ በሐጥያት እና በበደል ያሳለፉ ሰዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ስጋቸው ወደ መቃብር ነፍሳቸው በሲኦል ትቀመጣለች ፣ ትቀጣለች ። 🍁🍁🍁ገሀነመ_እሳት ደግሞ ÷ ከምፅአት( ከፍርድ ቀን) በኃላ በበደል ያሳለፈች ነፍስ እስከ በሌለው ፍርድ ለዘላለም የምትቀጣበት አስፈሪ ስፍራ ነው ። አሁን ሰው በሞተ ስጋ ሲለይ በሐጥያት አሳልፎ ከሆነ ነፍሱ እስከ እለተ ምፅአት ( የፍርድ ቀን) ድረስ እየተቀጣች የምትቀመጠው በሲኦል ነው ። ገሀነመ እሳት ፍርድ ቀን የሚመጣ ነው ። ከምፅአት ( ከፍርድ ቀን) በኃላ ግን የተበተነው ፣ የበሰበሰው ስጋ ተነስቶ ወንድ የ30 ሴት የ15 ዓመት ሆነው በሲኦል የነበረችው ነፍስ ከተነሳው ስጋ ጋር ተዋህዷ ነፍስም ስጋም አንድ ላይ በዘላለም ፍርድ በእሳት ቅጣት የሰው ልጅ ይኖራል ። ሁሉን ማስተካከል የሚቻለው በምድር እያለን በሞተ ስጋ ከዚህ ዓለም ሳንሔድ ብቻ እና ብቻ ነው ። የገሀነመ እሳት ሁኔታ ምን ይመስላል ÷ እሳቱ የማይጠፋ ፣ ትሉ የማያንቀላፋ በቁማችን የሚበላን ፣ ሰይጣን እና መልዕክተኞቹ የሚሰለጥኑብን ( የፈለጉትን የሚያደርጉብን) ......... ይሆናል ልዑል እግዚአብሔር ይህን ስፍራ እንዳናይ ይርዳን አሜን።
Show all...
☝️☝️☝️☝️☝️ #አውደ_መጻሕፍት 👇👇👇👇👇
Show all...
🛑የሰላሳ አመታት /30/ የሰማዕትነት ጉዞ። ▪ለታሪክም አስቀምጡት። 🛑አንብቡት ይጠቅማችኋል በምን አይነት መከራዎች ውስጥ አልፈን እኛ እና ቤተክርስቲያን ለዛሬ እንደበቃን ትቃኙበታላችሁ።
Show all...
Repost from National Lottery et
✔️እንኳንንንን ደስስስስ አላችሁ👇👇👇 ብሄራዊ ሎተሪ ለባለ ዕድለኞች አስደሳች ዜና ይዞ መጥቷል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ የማህበረሰቡን የቤት እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ከEthio Telecom ጋር በመተባበር፣ #100_ሚሊዮን_ብር በመመደብ #ሚያዚያ 27/2016 በፋሲካ እለት የሚጠናቀቅ ልዪ የሆነ "ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ " ፕሮግራም አዘጋጅቷል። የኢትዮ ቴሌኮምና ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በወሰነው መሰረት  ድርጅታችን በቴሌቪዢንና በሬድዮ ለማስታወቂያ ይመድበው የነበረውን በጣም ከፍተኛ ገንዘብ በመቀነስ የቴሌግራም ቻናል በመክፈት ራሱን እያስተዋወቀ ይገኛል!! ቴሌግራም ገፃችንን ብዙ ተከታይ እንዲያገኝ (ሼር) ላደረጉ ተከታዮቻችን 1ኛ እጣ ባለ 3 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 2ኛ እጣ ባለ 2 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 3ኛ እጣ ባለ 1 መኝታ ለ 50 ዕድለኞች እና ቀጥሎ ላሉ 200 እድለኞች የ1 አመት ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት ይኖረዋል፡፡ አሁንስ ምን ይጠብቃሉ ሊንኩን ተጭነው ከገቡ በኃላ፣ ይህን ፅሁፍ ለ40 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ወዳጅ ጓደኛችዎና ግሩፓች ላይ ሼር ፎርዋርድ ሲያደርጉ፣ የመሸለም እድሎ የሰፋ ነው። ይህን የማይገኝ አጋጣሚ በከንቱ እንዳያሳልፉ አሁኑኑ ሼር ፎርዋርድ ያድርጉ ፡፡ ከ40 በላይ ሼር ማረጋችሁ የመሸለም እድላችሁን ያሰፋዋል ልብ ይበሉ ❗️ ሼር አድርገው ሲጨርሱ ከታች ባለው ቦት ላይ 👇👇            @Abs_Ethiopiabot          @Abs_Ethiopiabot     Start በማለት የሽልማቱን ቀን ይጠባበቁ በኮምፒውተር እጣ አወጣጥ መሠረት #ሚያዝያ 27/2016 በትንሣኤው እለት ተሸላሚ ባለ ዕድለኛዎችን በ ቴሌግራም ቻናላችን የምንገልፅ ይሆናል መልካም እድል ከ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር @NATIONAL_LOTTERYET @NATIONAL_LOTTERYET ♻️ ሼር ሲያረጉ እኛ ደሞ እንሸልሞታለን!!
Show all...
👍 2
“ ኑሮ ከብዷት ነው ! ” ኑሮ ከብዷቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ትልቁ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ የወጡ አንዲት እናት በሕይወት ተረፉ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጫው ካሬ ቀበሌ ወይሶ ሰፈር ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት  ወ/ሮ ሂሩት በቀለ “ራሳቸውን ለማጥፋት” ረጅሙ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ ላይ ወጥተው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወረዳው ባለስልጣን ማረጋገጥ ችሏል። ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት በክልሉ ወላይታ ሶዶ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አስራት ፣ “ ማክሰኞ ዕለት (ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም) የመብራት ፖል ጫፍ ላይ ወጥታ፣ አውቶማቲክ ስለሆነ በራሱ ጊዜ ዘጋና ጠቆማ ሰጠን (ሰው ወደ ላይ እየወጣ እንደሆነ)፣ ከዚያ ከወረዳ ቲም ተዋቅሮ ፓሊስ፣ የወረዳው አመራርና የቀበሌ አመራር አንድ ላይ በመሆን ወደ ስፍራው ደርሰው ሴትዮዋ ጋ ሲደርሱ ጫፍ  ላይ ወጥታ ነበር ” ብለዋል። “ አንድ ላይ በመሆን እንድትወርድ ሰዎች ለምነው ነበረ፣ ‘አልወርድም’ ብላ በጣም አስቸግራ ነበር” ያሉት አቶ ተመስገን፣ “ሌሎቹ ሰዎች ተደብቀው ፓሊስ፣ የሴትዮዋ እናትና አባት አንድ ላይ ሆነው በመለመን ወረደች ” ሲሉ አስረድተዋል። ወ/ሮ ሂሩት እንዲህ ያደረጉት ለምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ተመስገን፣ “ ኑሮ ከብዷት ነው። የሁለት ልጆች እናት ናት። ኑሮ ከብዷት ከባለቤቷ ሁሉ ተጣልታ ከቤተሰቦቿ ጋ ነች። እናትና አባቷ ጋ ሆና ነው ይሄ ክስተት የተፈጠረው ” ብለዋል። ሴትዮዋ ሕመምተኛ ስለሆኑ ከወረዱ በኋላም ሶዶ ኦተና ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል። መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው ለጊዜው በወላይታ ሶዶ የሚገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው። @tikvahethiopia
Show all...
ይድረስ እንደኔ ለተሸወዱ መፅሀፍ ቅዱስ የማያቃቸው እነሱ ግን በግድ አውቀዋለው የሚሉ ሴት ፓስተሪቶች ሴት ልጅ ባደባባይ ትሰብ ዘንድ መፅሀፍ ቅዱስ በፍፁም አይፈቅድም የሴት ፓስተርነት ይህ ፍፁም ኢ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው ራሷን ሳትሸፍን እንደወንድ ሱሪ ታጥቀው ሲሰብኩ ሳይ እስቃለው ራስዋን ሳትሸፍን ሳትሸፍን ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራሷን ታዋርዳለች !! እንደተላጨች ያህል ነውና 1ኛ ቆሮ 11_5 ይሄ ጥቅስ የሻራችሁት የብሉይ ጥቅስ አይደለም 🤭 ዳሩ ግን ማንንም ሊከራከር ቢፈቅድ እኛ እግዚአብሄር አብያተ ክርስትያናት እንዲ ያለ ልምድ የለም 1ኛ ቆሮ 11_16 ሴት እህቶቻይን የምትሰብኩት እንዲ ይላል ማቴዎስ 7:21-23 “በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም። በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል። በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ።🤭ጉድ ፈላ እሺ የእግዚአብሄር ፍቃድ ምንድነው 👇👇 ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አንፈቅድም 1ኛ ጢሞ 2_11_12 እና ምን እያልኩ ነው ሲስተር አንቺ አውቀዋለው ብለሽ የምትሰብኪው ኢየሱስ እሱ አያቅሽም ሼር እያደረጋችሁ አስመልጡ ምእመናን https://t.me/debre_aryam_kidest_arsema
Show all...
የሻሸመኔ ደ/አርያም ቅ/አርሴማ እና ቅ/መርቆርዮስ ሰ/ት/ቤት

✟✟✟

👍 2 2🥰 1👏 1
ይሁን ብለን ብንጠቀምበት ስህተቱ ምን ይሆን? ጥያቄ3፡- የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እስኪሠራ ድረስ በእርግጥ ታቦቱ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘዋወር ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ ግን ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ስለመውጣታቸው መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም፡፡ ታዲያ ዛሬ ክርስቶስ ደሙን ካፈሰሰ በኋላ፤ በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መመሪያ ሳይኖር፤ ከየት አምጥታችሁ ነው ታቦትን በየጊዜው በማውጣት የክርስቲያኖች ህሊና ሁሉ ወደተሰቀለው ክርስቶስ መሆኑ ቀርቶ ወደ ታቦቱ የሆነው? መልስ፡- በብሉይ ኪዳን እንኳን አይወጣም ነበር ማለት አንችልም ምክንያቱም በችግራቸው ጊዜ ለችግራቸው መፍትሔ ያገኙ ዘንድ ከነበረበት ከድንኳኑም ቢሆን ያወጡት ነበርና ለምሳሌ፦ 1. በሙሴ ምትክ የተመረጠ ኢያሱ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ወደ ምድረ ርስት ሲሄድ ድንገት የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ባገኘው ጊዜ ወንዙን ከፍሎ አሕዛብን ለማሻገር ከእግዚአብሔር በተነገረው መሠረት ካህናቱ ታቦቱን ከነበረበት ቦታ ተሸክመው ወደ ወንዙ በመሄድ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት እግር ወንዙን ሲረግጥ ወንዙ ተከፍሎ ሕዝቡ ሁሉ በሰላም መሻገራቸውን እናገኛለን፡፡ ኢያሱ 3፥1-17፡፡ 2. እስራኤል ምድረ ርስት በደረሱ ጊዜ ምድረ ርስት (ኢያሪካ) በጠላት እጅ በጽኑዕ ግንብ ታጥራ አገኟት፡፡ በዚህም ጊዜ ይህን የጠላት የግንብ አጥር ለማፍረስና ርስታቸውን በእጃቸው ለማድረግ እግዚአብሔር የገለጠላቸው ጥበብ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ሕዝቡም እየተከተሉ ሰባት ጊዜ ግንቡን እንዲዞሩት ነው፡፡ የታዘዙትን አደረጉ ግንቡም ፈረሰላቸው፡፡ ኢያሱ 6፥1-17፡፡ 3. እስራኤል ጠላት በበረታባቸው ጊዜ ጠላትን ለማሸነፍ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ይወጡ ነበር፡፡ 1ሳሙ 5፥1-ፍ፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ካህናቱ ታቦቱን ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ካልሆነ በቀር ለሚፈልጉት ዓላማ ታቦቱን ካለት ቦታ ተሸክመው አያወጡትም ነበር ማለት አንችልም፡፡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ካስገባው በኋላ ቢሆንም ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው እንዳያወጡ የሚል ሕግም የለም፡፡ እግዚአብሔር የሠራው ሥራ በብሉይ ኪዳን የተፈጸመው አገልግሎት ሁሉ ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ያልተጻፈ ብዙ ነገር እንዳለ እናምናለን ከዚህ በመነሳት ነው እኛ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ተሸክመን የምናወጣው፤ በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር ቸርነት (ትእዛዝ) ካህናቱ ታቦታቱን ተሸክመው እንዲወጡ ተደርጎ ካህናቱም ታቦታቱን ተሸክመው በመውጣት በታቦቱ ያደረ ኃይለ እግዚአብሔር ለሕዝበ እስራኤል ያደረገው ድንቅ ሥራ ለማሰብና እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው፡፡ዛሬም ለሥጋና ለደሙ የክብር ዙፋን የሆነውን ቅዱስ ስሙም የተጻፈበትን ቅዱስ ታቦት በምናወጣበት ጊዜ በደሙ የባረከን መድኅነ ዓለም ክርስቶስ አሁንም የሥጋውና የደሙ ዙፋን በሆነው በታቦቱ ረቂቅ ኃይሎች በማስተላለፍ በረከቱን ያበዛልናል ብለን በማመን ነው፡፡ የተሰቀለው አምላክ መክበሩና መንገሡ ቀርቶ በየጊዜው ታቦት ወጣ እየተባለ ታቦቱ ብቻ ነገሠ ከበረ ሕዝቡም ወደ አምልኮ ባዕድ ኮበለለ ስለሚለው ግን አንድ ሕዝብ የንጉሡን ዙፋን ሲያከብርና ሲፈራ ንጉሡን ማክበሩና መፍራቱ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ እኛ የምናምነው ቅዱስ ስሙ የተጻፈበትን የክርስቶስ ሥጋና ደም የክብር ዙፋን የሆነውን ታቦት ማክበራችን በኪሩቤል ዙፋን የሚቀመጥ መድኅነ ዓለም ክርስቶስን ማክበራችን መሆኑን ነው፡፡ በታቦቱ ፊት መስገዳችንም በታቦቱ ለተጻፈው ለቅዱስ ስሙ ነው፡፡ በታቦት ፊት ለእግዚአብሔር ስም ይሰግዱ የነበሩ ኢያሱና የእስራኤል ሽማግሌዎች በረከት አገኙበት እንጂ አልተጎዱበትምና ነው፡፡ ኢያ 7፥6፣ ዘዳ 33፥10፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ‹‹ድል ለነሣው ስውር መናን እሰጠዋለሁ፤ የብርሃን መጽሐፍንም እሰጠዋለሁ፤ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎበታል›› ራእ 217፡፡ ለዚህ ስም ደግሞ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ይህም በሰማይና በምድር በቀላያትና ከምድርም በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው። አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው›› ፊልጵ 2፥10-11፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት ከነጭ ድንጋይ (ከዕምነ በረድ፣ከእንጨት) በተሠራው በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ምናልባት ስለታቦት፣ ስለጽላት ባለማወቅ ባጠቃቀሙ በኩል የሚሳሳቱ አባቶችን፤ እናቶችን ወንድሞችንና እህቶችን በተገቢው መንገድ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ስለ ታቦት ከቤተ መቅደስ መውጣትና አለመውጣት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ብዙዎች በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቃወም በኤር 3፥16፡፡ የተጻፈውን ጠቅሰው “በዚያ ዘመን ፦የ እስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት እነኋት እያሉም በአፋቸውም አይጠሯትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሿትም።” ተብሏልና ታቦት አያስፈልግም በማለት ያስተምራሉ፡፡ እንደተባለው ታቦት ብሎ መጥራት ካላስፈለገ በኤርምያስ 31፥34፤ ደግሞ “እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም” ተብሎ ስለተጻፈ እንግዲህ ሰው ሁሉ በየዘመኑ እግዚአብሔርን እንዲያውቅ ማስተማር አያስፈልግም ማለት ነዋ! ደግሞም ጌታችን በማቴ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ” ብሎ መናገሩ ስህተት መሆኑ ነዋ! በአጠቃላይ እንዲህ ነው ብሎ ከመናገር አስቀድሞ በመጽሐፍ የተጻፈው ነገር ለምንና እንዴት ባለ ሁኔታና ጊዜ መጻፉን ማጥናትና መልእክቱን (ምስጢሩን) መመርመር ይገባል እንላለን፡፡ በመጨረሻ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶኮክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማርያም፣ የቅዱሳን፣የሰማዕታት፣ የመላዕክት ወዘተ…. ታቦት እየተባለ የተሰየመበት ምክንያቱና የዚህ ስያሜ ከየት ነው የመጣው ምንድን ነው የሚሉ ጥያቄዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እርግጥ ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ መሠየሙ በትንቢተ ኢሳይያስ 56፥46 በተገለጸው መሠረት የእግዚአብሔርን ሰንበቱን ለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘውንም ለሚመርጡ ቃል ኪዳኑንም ለሚይዙ ጃንደረቦች (ስለእግዚአብሔር መንግሥት ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ቅዱሳን) ማቴ 19፥12 በእግዚአብሔር ቤትና በቅጥሩ የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሚደረግላቸው የተገለጠ በመሆኑ ይህን አብነት በማድረግ ጌታ ሥጋው፣ ደሙ የሚከብርበት ሆኖ ለቅዱሳኑም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፡፡ /መዝ 111፥7/ እንዲሁም የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነውና ምሳ 10፥7፡፡ በዚህ ምክንያት እንጂ በታቦታቱ የሚከብረው መድኃኒተ ዓለም ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን። /ምንጭ፦ ሐመር መጽሔት ሚያዝያ 1985 ዓ.ም/
Show all...
👍 1
በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛ ቆሮ 3፥1-3፤ በዕብ 8፥8-13፡፡ የእኛ አካልና ልቡና የእርሱ ታቦትና ጽላት አልሆነም ወይ? በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ የሚሉ አሉ፡፡ የክርስቲያኖች አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለን፡፡ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፤ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደባልጀራ ያነጋገረበት፣ የክብሩ ዙፋን ሆኖ ጽላቱ በውስጡ ለታቦቱ ማደሪያ በመሆኑ፤ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኅኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው፡፡ ጥያቄ2፡- በዘዳ 31፣18፣32፣15፣134፣1-5፡፡2ኛዜና 5፣10 ያሉትን ጥቅሶች በመጥቀስ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ሁለት ጽላቶችን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህን እልፍ አእላፋት ጽላቶች ከየት አመጣቻቸው? አራብታችሁ ቅረጹ የሚል አለ ወይ? መልስ፡- በዘዳ 32፥19፡፡ ስንመለከት እግዚአብሔር ራሱ አዘጋጅቶ ለሙሴ የሰጠውን ሁለቱን ጽላቶች እሥራኤል ጣዖት ሲያመልኩ ስላገኛቸው ሙሴ ተበሳጭቶ ሰብሯቸዋል፡፡ነገር ግን ቸርነቱ ለዘለዓለም የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴ የመጀመሪያዎቹን አስመስሎ እንዲሰራ ነገረው፤ ሙሴም አስመስሎ ሠራ፡፡ ዘዳ 34፥1-5 መሥራት ብቻ ሳይሆን ዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃላትም በጽላቶቹ ላይ እንዲጽፍ ሙሉ ሥልጣን ከእግዚአብሔር ተሰጠው፡፡ ሙሴም ተፈቅዶለታልና አሥሩን ቃላት በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፡፡ ዘዳ 34፥27-28 ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጽላትንም ሆነ ታቦትን እያስመሰሉ ለመሥራት ሙሉ ሥልጣንን አግኝተናል፡፡ ይህን በተመለከተ አንዳንድ አባቶች እንዲህ ይላሉ፤ ‹‹አዳም እንኳን በደለ አዳም ባይበድል ኖሮ አምላክ ሰው ሆኖ በቀራንዮ ስለእኛ የመሰቀሉን፤ ስለኛ የመሞቱን የፍቅር ምስጢር አናውቀውም ነበር፡፡›› እስራኤልም በጥጃ ምስል ጣኦት አምልከው እንኳን በደሉ እሥራኤል ባይበድሉ ሙሴ በእግዚአብሔር የተዘጋጁት ሁለቱ ጽላቶች’ የሰው ልጅም እግዚአብሔር የሠራቸውን የፊተኞቹን አስመስሎ ለመሥራት ስልጣን ባልኖረውም ቢሠራም ለምን ሠራህ ለሚለው መረጃ ባላቀረበም ነበር›› ይላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ጽላትን አስመስለን፤ አባዝተን፤ አራብተን ለመሥራት መሠረታችን ሥልጣኑ ለኛ ለልጆቹ የተላለፈልን ከአባታችን ከሙሴ ነው፡፡›› ሙሴ የተሰበሩትን አስመስለህ ሁለት ጽላቶች ቅረጽ ከሚል በቀር ጽላቶችን አብዝታችሁ፤ አራብታችሁ ተጠቀሙ የሚል ቀጥተኛ ቃል አምጡ ለሚለው ግን ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የጽላትም ሆነ የቤተ መቅደስ ሥርዐት፤ የመስዋዕቱ የዕጣኑ አገልግሎት፤ በኢየሩሳሌም ብቻ ስለነበረና፤ የሌላውም አገር ሕዝብ የሚከተለው የጣዖትን ሥርዓት እንጂ የሙሴን ሥርዐት ባለመሆኑ ጽላቱ ተባዝቶ ተራብቶ ለሌላው አገር ሕዝብ አልተሰጠም፡፡ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ውጭ አልፈቀደም የተቀደሰውን ጣዖታውያኑ አሕዛብ ያረክሱታልና ስለዚህ ስግደቱም የቤተመቅደስ ሥርዐቱም በኢየሩሰሳሌም ብቻ ነበር። /ዮሐ 4፥18-24/ በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ አሕዝቦችም ሠሎሞን ያሠራው ታላቁ ቤተ መቅደስና ሁለቱ ጽላቶች አንሰውናል፤ በርቀት የምንገኝ እኛ የመንገድ ድካም በዝቶብናልና፡፡ ስለዚህ በያለንበት ቤተ መቅደስ ሠርተን ጽላቱን አክብረን መገልገል እንፈልጋለንና ይፈቀድልን ብለው ሙሴም ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ሌላ አልተፈቀደም ብሎ መልስ የሰጠበት ቦታ የለም፡፡ ያም ሆነ ይህ በሐዲስ ኪዳንም በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በአብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው ፤ሁለተኛ የድኅነት ልደት ተወልደው የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣን ሰጣቸው። ለክርስቲያኖችም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ እንደሚበዙና በአዲስ ኪዳን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንጹሕ የሆነውን ቁርባን ከኢየሩሳሌም ውጭ በየቦታው ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡፡ 1. ‹‹ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ይከበራልና፤ በየስፍራው ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፤ ንጹሕንም ቁርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር›› ሚል 1፥11፡፡ 2. ‹‹ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎ የለምን? እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ አስተማራቸው›› ማር11፥17፤ ኢሳ 56 ፥ 7፤ ኤር 7፥11 ፡፡ ይህ ትንቢት በቀጥታ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስም ሆነ የዕጣን፤ የቁርባን አገልግሎት እንኳን ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ላሉ አሕዛብ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በቀር ለእስራኤል ጎረቤት አገሮች እንኳ አልተፈቀደምና፡፡ ነቢዩ ሚልክያስ ንጹሕ ዕጣን ያለው በማቴ 2፥11፡፡ ወንጌል እንደተናገረው ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰብአ ሰገል በቤተልሔም ዋሻ ለክርስቶስ ካቀረቡት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ለክርስቶስ የምናቀርበው ቅዱስ ዕጣን ነው፡፡ ንጹሕ ቁርባን የሚለውንም በማቴ 26፥26፤ ጌታ ኅብስቱን አንሥቶ ነገ የሚቆረሰው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ወይኑንም አንሥቶ ነገ ስለብዙዎች ሀጢአት የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሎ ለሐዋርያት የሰጣቸው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ ንጹሕ የተባለው እርሱ በባሕርዩ ንጹሕ ሆኖ የእኛን የኃጢአት እድፍ ስለሚያነጻ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በኢየሩሳሌም ብቻ መሆን የሚገባቸው ቤተ መቅደሱ፤ ዕጣኑ፣ ቁርባኑ፣ በክርስቶስ ደም በአዲስ ሕይወት፣ በአዲስ ተፈጥሮ፤ በአዲስ ሥርዓት፣ ክርስቲያኖች ለሆንን ለዓለም ሕዝቦች በየሥፍራው (በያለንበት) እንድንጠቀምባቸው ከተፈቀዱልን በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሁለቱ ጽላቶች ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ተባዝተው በዓለም ያለን ክርስቲያኖች በያለንበት በየቤተ መቅደሳችን ለሥጋውና ለደሙ የክብር ዙፋንነት ብንገለገልባቸውና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ብናከብርባቸው ምን የሚጎዳ ነገር ተገኘ? የሚያስደነግጠውስ ምኑ ነው? ስህተቱስ የቱ ላይ ነው? እንዲሁም ዐሠርቱ ትእዛዛት የተጻፉባቸው ሁለቱ ጽላቶች መባዛት መራባት የለባቸውም ከተባለ በጽላቶቹ ላይ የተጻፉት ዐሠርቱ ትእዛዛት መባዛት የለባቸውም፡፡ ከኢየሩሳሌምም መውጣት የለባቸውም ማለት አይደለም? ትእዛዛቱም ተከለከሉ ማለት ነውና፡፡ በጽላቶች ላይ የተጻፉት ትእዛዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ በፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በሚገኙ ክርስቲያኖች እጅ ገብተዋል፡፡ ይህም ያስደስታል እንጂ አያሳዝንም፡፡ ይህ ከሆነ ለሥጋውና ለደሙ (ለክርስቶስ) ክብር ሲባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ጽላቶች ምን በደል አስከተሉ፥ እግዚአብሔር ለቀደሙ አባቶቻችን በታቦቱ አድሮ የሠራላቸውን ድንቅ ሥራ እያስታወስን እግዚአብሔርን ከማመስገን ውጭ ደግሞም ጌታ ስለ ጸሎት ሲያስተምረን ‹‹አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ውስጥ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን›› በሉ ብሏል፡፡ በዚህ መሠረት በዮሐንስ ራዕይ 11፥19 ላይ ታቦቱን በሰማይ አሳይቶናል፡፡ ስለዚህ የሙሴ የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰማይ እንዲገኝ፤ በሰማይ እንዲሆን፤ በሰማይ እንዲታይ ፈቃዱ ከሆነ፤ በምድርም እንዲሆን ፈቃድህ
Show all...
👍 2