cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🎀ሚፍታሁል ቀልብ🎀

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ቁርዓን እና ሀዲስ በሰለፎች አረዳድ

Show more
Advertising posts
264
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

_ለአንች ጥሩ ምሳሌና  አርአያ የሆነች ሴት ማን ነች ⁉️ ➀-) ነብዩ ﷺ መልእክተኛ  ከመሆናቸው ቀደም ብላ  የተወለደች ⓶-) ነብዩ ﷺ በጣም  የሚወዷት፣ ከሌሎች ልጆቻቸው በበለጠ መልኩ የሚቀርቧት፣ሚስጥራቸዉንም የሚያጋሯት ➂-) አላህን አመስጋኝ፣ በብዛት አምላኪ፣ቁጥብና ትጉህ  ሴት በመሆኗ  ነብዩ ﷺ ለቁጣዋ  የሚቆጡላት ⓸-) በአረማመዷ፣በአካሄዷ  እንድሁም በአወራሯ  ነብዩን ﷺ መሳይ ➄-) ከነብዩ  ቤት ስትገባ  ነብዩ ﷺ ተነስተው  ስመውና  እንኳን ሰላም መጣሽልኝ ብለው የሚቀበሏት።እርሷም ነብዩ  ከቤቷ  ሲመጡ  በተመሳሳይ የምትቀበል። ➅-) ነብዩ ﷺ በብዛት የሚቃለዷት።እሷ ማለትኮ የአካሌ ክፋይ ቁራጭ ሰውነቴ ነች እያሉ የሚያሞካሿት። ➆-) የዚች ኡማህ  ሴቶች ሁሉ አለቃ  ነች የሚል ማእረግን  የተጎናጸፈች ➇)- የጀነት ወጣቶች  አለቃ  መሆናቸው  ለተረጋገጠላቸው ልጆች እናት የሆነች  ➈-) በምድር ላይ ሙሉእነትን ከተጎናጸፉት አራት ምርጥ ሴቶች  መካከል  መመደቧ  የተረጋገጠላት ➉-) እሷም ይሁን  እህቶቿ  በሁለተኛነት ያልተገቡ ያልተገባባቸዉም ሴት ➀➀-) እሷን  ያስቸገረ  ነብዩን  እንዳስቸገረ  እንደሆነ  የተነገረላት ➀➁-) የአጎቷን  ልጅ ያንን  ምርጡን  ሰው  ከበድር ጦርነት በኋላ ያገባች ➀➂-) ስታገባ  ጥሎሽ ጠፍቶ  ጮኛዋ  ያለችውን የጦር ልብስ አውልቆ  የሰጣት ➀➃-) ወደባሏ  ዘንድ ስትሄድ አባቷ  ትራስን፣የዉሀ  እቃንና ፎጣ  መሳይ ልብስን ሰጥቶ  የሸኛት ➀➄-) ከባሏ  ቤት  ለሰርግ  የሚታረድ ስላልነበረ  ሰዕድ ቢን ዑባዳ  በግ  በማረድ፣ሌሎች አንሷሮች ደግሞ  እህልን በማመቻቸት የሰረጉላት ➀➅-) ያ  ጀግናው ባሏ ይዟት ወደ ቤቱ ሲሄድ፣ነብዩም  ﷺተከትለው ከቤት ገብተው   ( አላሁመ  ባሪክ ፊሂማ ወባረከ  ዐለይሂማ  ወባሪክ ፊነስሊሂማ ) ብለው ዱዐእ  ያደረጉላትና  ዱዐቸዉም  ተቀባይነትን  አግኝቶ  የምርጦች እናት ለመሆን የበቃች ➀➆-) የሀሰን  የሁሰይን፣የሙሀሲን፣የዘይነብ እና የኡሙ ኩልሱም  እናት ➀➇-) የነብዩ  ﷺ  የዘር ሀረግን  ያስተላለፈች ብቸኛዋ  ልጅ 💎ፋጢማ  ቢንት #ሙሀምድ رضي الله عنها وعن زوجها واولادها
Show all...
~አላህን ቀጥ ብሎ በመታዘዝ (ጧዐህ) እና በወንጀል መካከል ወዲህ ወዲያ እያሉ እያጣቀሱ የመኖር ጉዳቱ በየትኛው ላይ እያለህ የሞት መልኣክ እንደሚመጣብህ የማታውቅ መሆኑ ነው። ~ ለመገላገል ሳይሆን ለመታዘዝ ብለህ አላህን ታዘዝ። ~ ለመመፃደቅ ሳይሆን ወደ አላህ ይበልጥ ለመቃረብ ብለህ ከግዴታ አልፈህ ሱንና ነገሮችን ፈጽም። ~ የመታዘዝ ጥቅሙ ላንተው ነው፤ አላህ ካንተ አምልኮ የተብቃቃ ነው። ~ ሀሳብህን በሰዎች ዘንድ ለመወደድ አታድርገውሰው ዛሬ ቢወድህ ነገ ይጣላሃል። . ~የሁልጊዜ ሃሳብህ አላህ ዘንድ መወደድ ይሁን።
Show all...
☑️ ሊያሳስበን የሚገባዉ እስቲቃማ ላይ ቀጥ ማለታችን ነዉ قال العلامة الألباني رحمه الله : طريق الله طويل ونحن نمضي فيه كالسلحفاه، وليس الغايه أن نصل لنهاية الطريق، ولكن الغايه أن نموت على الطريق"ሼኽ አልባኒ አላህ ይዘንላቸዉና እንድህ ይላሉ። ~ ወደአላህ የሚያደርሠዉ መንገድ ረጅም ነዉ።እኛ በሱ ላይ እንደ ኤሊ ሆነን እንጓዛለን።አላማችን ግባችን የመንገዱ ፍፃሜ ላይ መድረስ አደለም።ነገረ ግን ግባችን አላማችን መንገዱ ላይ መሞታችን ነዉ። وقول ابن تيمية: أعظم كرامة لزوم الاستقامة ከከራማ ሁሉ በላጩ እስቲቃማን አጥብቆ መያዝ ነዉ።     t.me/https_Asselfya
Show all...
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

☑️ ኢማም ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- 👉ወደ በጎ ተግባር ከሚያመላክቱህ ጥሩ ሰዎች ጋር በመሆን አደራህን እንዳትዘናጋ ተጠንቀቅ። *በተሳሳትክ ጊዜ ያመላክቱሃል። *በረሳህ ጊዜ ያስታውሱሃል። *ዕውቀትን ባጣህ ጊዜ ያስተምሩሃል። *በጠመምክ ጊዜ የቅናቻ መንገድን ይጠቁሙሃልና።               📚شرح صحيح البخاري - ٦٢/١ ) ═════ ❁✿ ═
Show all...
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

 🫁  አዎ አንቺ አልሞትሽም እናቴ🫁 "እኔ ነኝ የሞትኩት ያንቺን ውለታ ሳልከፍልሽ የተቀበርኩልሽ፣    ከሰው ጋ እየሳኩ ኡሚ ረስቼሽ በቁም የሞትኩልሽ፣   አንቺማ ደና ነሽ ምድርን ተሰናበትሽ አንድ ቀን ሳላስቅሽ ሳልስምሽ፣ ለኔ መኖር ብለሽ እራስሽን ሰዋሽ፣ አንድ ቀን ሳለቅስ እንባዬን ጠርገሽ አመት እያለቀሽ፣ ለራስሽ ሳትበዪ የኔን ሆድ እየሞላሽ፣ ለኔ እድገት ብለሽ ቶሎ አረጀሽ፣ አረ ምን እብደት ነው ሚሰቀጥጥ እውነት፣ ክብር የሰው ልጅ ነብስ ይጠፋል በስሜት? አልቻልኩም ልናገር አይኔ ደም አነባ፣ ካንቺ መለየቱ አደረገኝ ገብጋባ ብዕሬ ደከመ አቅሙንም አጣ፣ ካንቺ መለየቱ አደረገኝ ፈጣጣ ብቻ ባለሽበት ሰለሙ ይብዛልሽ፣ የኔ ውድ እናት አላህ ይጠብቅሽ የቀብሩንም ቅጣት ቀለል ያድርግልሽ ያኬራውንም ፈተና ከፈፍ ያድርግልሽ ከጀነትም ጀነት ፊርዶስ ይወፍቅሽ።   ይሄ ነበር ልቤን በፀፀት ፤ ውስጤን በፍርሀት፤ አይኔን ደሞ በእንባ የሞላው :: የእናት ፍቅር ነው ::
Show all...
ቁርአንን በመሃፈዝ ታዋቂ የነበሩ ሶሓቦች 📌الشيخ عبد الكريم الخضير حفظه الله: ቁርአንን በመሃፈዝ በሶሓቦች ዘንድ ታዋቂ የነበሩ ታላላቃ ሶሓቦች —ዑስማን   — ዐሊይ   — ኡበይ ኢብኑ ካዕብ  — ዘይድ ኢብኑ ሣቢት  —ኢብኑ መስኡድ        —አቡ አደር ዳእ   —ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል        —ከአነስ ኢብኑ ማሊክ የአጎት ልጆጅ አንዱ የሆነው አቡ ዘይድ አል አንሷሪ  —አቡ ሁረይራህ   —ኢብኑ ዐባስ    እና  —ዐብደላህ ኢብኑ አስ ሳኢብ    رضي الله عنهم أجمعين. አንዳንዶቹ መልእክተኛው ﷺ በህይወት እንደነበሩ ነው ቁርአንን ሙሉ በሙሉ ያጠናቀቁት አንዳንዶች መልእክተኛው ﷺ ከሞቱ ቡሃላ ነው ያተናቀቁት 📚مصدر:شرح رسالة أصول في التفسير للسيوطي https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Show all...
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ

قال الإمام مالك ((لايصلح آخر هذه الأمة إلا بماصلح به أولها))

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል? አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356] 2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል? አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201] 3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል? አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ። 4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል? አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም] 5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል? አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9] 6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል? በፍፁም! ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ  ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው? የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ። በነገራችን ላይ ይሄ "የጌታ መውሊድ" ብለው የሚያከብሩት የገና በአል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ በቅድመ-ክርስትና ከነበረው የጣኦታውያን እምነት የተኮረጀ ነው። በዚያ ላይ ዛሬ የጎርጎሮሳዊውን አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት December 25ም ሆነ "የኢትዮጵያውን" አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት ታህሳስ 29ም በርግጠኝነት ዒሳ (እየሱስ) የተወለዱበት ቀን አይደለም። - መነሻ ሃሳቡ ዋትሳፕ ላይ ያገኘሁት 0ረብኛ ፅሁፍ ነው። == የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لقَدْ رَأَيْتُ رَجُلًا يَتَقَلَّبُ في الجَنَّةِ، في شَجَرَةٍ قَطَعَها مِن ظَهْرِ الطَّرِيقِ، كانَتْ تُؤْذِي النّاسَ﴾ “አንድን ሰው በመንገድ ላይ ሰዎችን ያስቸግር የነበረን ዛፍ ቆርጦ በማስወገዱ ምክንያት በጀነት ውስጥ ሲጣቀም አየሁት።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1914 https://t.me/Miftahul_Kelb
Show all...
🎀ሚፍታሁል ቀልብ🎀

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ቁርዓን እና ሀዲስ በሰለፎች አረዳድ

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “አላህ ዱኒያን ለሚወደውም ለሚጠላውም ይሰጣል ኢማንን ግን ለሚወደው እንጂ ለሌላ አይሰጥም።” 📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2714 አልኢማሙ ሰዓዲ እንዲህ ይላሉ፡‐ “ዱኒያዊ የሆነ ሲሳይን አማኝም ከሀዲም የሆነ ያገኛል። ነገር ግን የቀልብ ሲሳይ የሆኑትን እውቀትን፣ ኢማንን፣ አላህን መውደድ መፍራትና እሱን ተስፋ ማድረግና ሌሎቸም ለሚወደው እንጂ ለሌላ አይሰጥም።” 📚 «ተይሱሩል ከሪሙ ራህማን» (95/1) “አንዳችሁም አላመናችሁም ለራሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 13
Show all...
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِنَّمَا يَنْصُرُ اللَّهُ هَذِهِ الْأُمَّةَ بِضَعِيفِهَا، بِدَعْوَتِهِمْ وَصَلَاتِهِمْ وَإِخْلَاصِهِمْ﴾ “አላህ ይህንን ህዝበ ሙስሊም የሚረዳው በደካሞቻቸው ነው። በፀሎታቸው፣ በዱዓቸው በሶላታቸው እና በኢኽላሳቸው።” 📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2/409 https://t.me/Miftahul_Kelb
Show all...
🎀ሚፍታሁል ቀልብ🎀

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ቁርዓን እና ሀዲስ በሰለፎች አረዳድ