cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Esat_tv_News

World news ትኩስ እውነተኛ ወቅታዊ ሀገራዊ ዜናዎች ከፈለጉ join ይበሉ ይቀላቀሉን👈🇪🇹 በቻናላችን አለማችን🌐🌎 ላይ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ join በማለት ይታደሙ🌎🌐 ሃሳብ አስተያየት ካአልዎት -👇⬇⬇⬇⬇⬇🔽 [💌📩📤💬inbox @riz_one123

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
196
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር በፎቶ
Show all...
በለንደን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ************************** “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መሪ ቃል በለንደን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ፡፡ ገንዘቡ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከdefend Ethiopia የዩናይትድ ኪንግደም ግብረሃይል ጋር በመተባበር ባካሄዱት የገቢ ማሰባሰቢያ መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር የተካሄደውን የገቢ ማሰባሰቢያ በማስመልከት ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በዚሁ ወቅት በስኬት የተጠናቀቀው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ኢትዮጵያውያን ከውስጥም ከውጪም የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለመፈታተን የሚሞክሩ ሀይሎችን በጋራ የመመከት የቆየ ታሪካቸውን ይበልጥ አጎልብተው የመጡበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል እና አንድነታቸውን ለመሸርሸር የሚፍጨረጨሩትን በንቃትና በትጋት መታገል ይገባል ያሉት አምባሳደር ተፈሪ አጀንዳችን ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያን ማበልጸግ ነው ብለዋል፡፡ ማህበረሰቡን በዘር እና በጎሳ ለመከፋፈል የተደረገውን ያልተሳካ ጥረት አሸንፈው የወጡት በዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እያደረጉት ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰቡት ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ (91 ሺህ 34 ፓውንድ ከ25 አምስት ሳንቲም) ከኤምባሲው በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ወቅቱ አዲሱና በህዝብ ይሁንታ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍትሃዊና ግልጽ በሆነ ምርጫ የተመረጠው መንግስት የሚቋቋምበት በመሆኑ በዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የdefend Ethiopia የዩናይትድ ኪንግደም ግብረሃይል አስተባባሪ አቶ ዘላለም ተሰማ በበኩላችው የሀገሪቱን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በመንግስት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለመደገፍ የሚደረገውን ጥረት ግብረ ሀይሉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ ሀገርን ለማፍረስ ሲኦልም ቢሆን እንወርዳለን ያለውን አሸባሪ ቡድን በወረደበት ሲኦል እንዲቀር የማድረግ የኢትዮጵያውያን ግዴታ በመሆኑ ማንኛውንም አስተዋጽኦ ለማድረግ ግብረሀይሉ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጪው ኦክቶበር 9 ቀን 2021 በሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት መላው በዩናይትድ ኪንግደም እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪ ማቅረባቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
በትናንቱ ምርጫ የተሳተፉ መራጮች የተረጋገጠ የምርጫ ውጤት በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስኪገለፅ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ተጠየቀ ************************* ትናንት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የተሳተፉ መራጮች በቦርዱ የተረጋገጠ የምርጫ ውጤት በቦርዱ ብቻ እስከሚገለፅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አቀረበ፡፡ መራጮች ከሌሎች ምንጮች የሚገለጹ ማናቸውንም የምርጫ ውጤትና የውጤት ትንበያ ከመቀበልና ለሌሎች ከማጋራት እንዲቆጠቡ ቦርዱ ጠይቋል፡፡ መራጮች በምርጫው ሂደት ያሳዩትን በትዕግስትና በጨዋነት የተሞላ ተሳትፎም ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድንቋል፡፡
Show all...
ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ ይጠየቃል‼️ 🗣 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሳሰበ፡፡ የሀገሪቱን ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው መሆኑን የጠቀሰው ተቋሙ አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል፡፡ እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስጠንቅቋል። @Esat_t_news
Show all...
የአማራ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬን አፈ-ጉባዔ አድርጎ ሾመ‼️ የአማራ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፍዬን አፈጉባዔእንዲሁም አቶ አማረ ሠጤን ም/አፈ-ጉባኤ በማድረግ መርጧል። አፈ-ጉባዔዎቹ ሀቅና ህግን በማስቀደም የወከላቸውን ህዝብ ለማገልገል ቃለ መሀላ ፈፅመዋል። @Esat_t_news
Show all...
. "ውበት እንደ እንደ ሳባ. . . ሁሉም የሚመኛት ማንም ያላገኛት፣ በአፈጣጠር ቅኔ፣ለኔው የተቀኛት፣ ውበት ላይ ስብዕና. . . በሱ ላይ አዕምሮ፣ የጥበቡ ዋቢ፣ሰንደቅ የተፈጥሮ! ስወድቅ ምርኩዜ ናት፣ ስነሣ ማጌጫ፤ እሷ ማለት ለኔ የዘላለም ምርጫ! አግኝቼ አልጠግብሽ፣ ኖረሺኝ አላጣሁ፣ ካወቅኩሽ ጀምሮ ከሐሴቴ አልወጣሁ፣ በቁንጽል ሣቋ ላይ. . . እናቴን ዐያለሁ. ... ሐገሬን ዐያለሁ እህቴን አያለሁ ኢትዮጵያን🙏🙏🙏🙏 አያለሁ . . ." . . . . By Girma🙈🙈
Show all...
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቀጣይ አምስት አመታት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እንዲመሩ ተመረጠዋል‼️ እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የምክር ቤት ምስረታ ስነ-ስርአት ላይ በቀጣይ አምስት ዓመታት ከተማ ከንቲባ እንዲመሩ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል። @Esat_t_news
Show all...
ወ/ሮ ፋይዛ መሀመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ ጉባኤ በመሆን ተመርጠዋል‼️ 35 ዓመታቸው ሲሆን የመጀመሪያ በኢኮኖሚክስ እና ቢዝነስ አድምኒስትሬሽን ዲግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱ ሲሂን እንግሊዝና ዴንማርክ በተለያዩ ስራዎች ላይ አገልግለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ በመሆን አሁንም ድረስ በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ በሀገር ውስጥና በውጪ የያዙትን ልምድ በመጠቀም ለአዲስ አበባ ህዝብ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን 138 ድምፁ ፀድቆ አሁንም በምክትል አፈ ጉባኤነት ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡ @Esat_t_news
Show all...
ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በበርሊን ማራቶን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ ‼️ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በዛሬው ዕለት በጀርመን በተካሄደው የቢኤምደብልዩ በርሊን ማራቶን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። አትሌት ጎይቶም ገብረሥላሴ በውድድሩ 2:20.09 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፋለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሕይወት ገብረኪዳን 2:21.23 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት ሔለን ቶላ 2:23.05 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ወጥታለች። @Esat_t_zena
Show all...
ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ግድያ እና መፈናቀል መኖሩን አስታወቀ *************** የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ግድያ እና መፈናቀል መኖሩን ከነዋሪዎች መረጃ የደረሰው መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደኅንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚያሳስብ መሆኑን ነው ብሏል። በዚሁ ወረዳ፣ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም በደረሱ ሦስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም በውልማይ ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ አሳውቀዋል። በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ፣ በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለወራት አስቸኳይ ሰብአዊ ዕርዳታ እና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬ እና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አረጋግጡን ገልጿል። የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ላለው የፀጥታ ስጋት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ኢሰመኮ አሳስቧል።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.