Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል
Open in Telegram
💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2
Show more1 862
Subscribers
-224 hours
-167 days
-6030 days
Posts Archive
አግራሞቴን በብዕር
▮ ብዙ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይሰማል....
❝እለፋለሁ እደክማለሁ ነገር ግን ሊሳካልኝ አልቻለም፤ አሁንስ በቃ ሰለቸኝ የኔ እድል ጠማማ ነው❞!! ይላሉ።
አዎ ብዙዎቻችን በተለያዩ ምክንያቶች የልፋታችን ላናገኝ ወይም ላይሳካልን ይችላል። አንዳንዶቻችን የራሳችን ጥፋት ሆኖ ለስኬቶቻችን እንቅፋት እንሆናለን።
አንዳዶቻችን ደግሞ በተፈጥሮ ምክንያት ወደኋላ የቀረን ወይም ያልተሳካልንም ሊመስለን ይችላል። ወንድምና እህቶቼ እኛ ያልተረዳነው፣ ከእንቅልፍ ያልባነንበት ነገር ቢኖር አንድ ነገር ነው እሱም 🎯 ዓላማ 🎯 ነው።
ያለ 🎯 ዓላማ እንጥራለን፣ እንደክማለን ነገር ግን ድካማችን ፍሬ አያፈራም ምክንያቱም 🎯 ዓላማ ስለሌለን ነው። ለምን እየለፋን፣ እየደከምን እንዳለ አናውቅም፤ እኛ የምናውቀው ነገር ቢኖር አንድ ነገር ነው እሱም እየሰራን ያለነው በቃ ለመኖር እንደሆነ።
▮ ለመኖር ብቻ ብለን እየደክምን ያለነው ጥረታችንና ድካማችን መሠረት የሌለው ቤት መነሻና መድረሻ የሌለው መንገድ ሲሆን ትኩረታችን ደግሞ በየተመቸው አቅጣጫ የሚነፍስ ንፋስ ነው ማለት ነው።
እናም ድካማችንና ጥረታችን ጠንካራና ሊናድ የማይችል መሠረት ያለው ቤት እንዲሆንና ትኩረታችን ደግሞ በፈጣሪ እርዳታ ስኬት ያሰመረችልን መሥመር እንዲሆን 🎯 ዓላማ ሊኖረን ይገባል።
🎯 ዓላማ ካለን በአምላካችን እዝነትና እርዳታ የፈለግንበት ቦታ እንደርሳለን፣ ወንድምና እህቶቻችንም የስኬት ማማን እንዲጎናፀፉ ምክንያት ልንሆን እንችላለን።
🎯 ዓላማ ካለንና የምንደክምለትን ነገር ለምን እየደከምንለት እንደሆነ ካወቅነው ያለ ምንም ጥርጥር በፈጣሪ እዝነትና እገዛ ይሳካልናል።
እህ እንዳለ ሆኖ ሳለ 🎯 ዓላማ ኖሮንም ደክመንም በአንዴ ስኬትን አልተጎናፀፍኩም ብለን ልንሰላችም አይገባም።
🎯 ዓላማ ያለው ጥረታችንና ድካማችን ቀጣይነት ሊኖረው ግድ ይላል።
ስለዚህ ወንድምና እህቶች ለምናደርገው ነገር 🎯 ዓላማ ይኑረን። 🎯 ዓላማ ኖሮን የምንለፋው ልፋትም መሰለቸት የሌለበት ቀጣይነት ይኑረው‼️
በናተው ወንድም በረሻድ ሙዘሚል
t.me/SharpSwords
ለጥንታዊ የሥነ-ጽሁፍ ቅርሶች ጥበቃ መፍትሔ የሆነው ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸውን አስራ ሁለት ጥንታዊ መዛግብት ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ሰነዶች ይገኛሉ፡፡
ሆኖም እነዚህን በቁም ጽሕፈት (Calligraphy) የተከተቡ ጥንታዊ መዛግብት ለጥናት እና ምርምር ሥራዎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ለትውልድ ጠብቆ ለማቆየት ሰነዶቹን ከኮምፒዩተር ጋር ማወዳጀት ለነገ የሚባል አይደለም፡፡
ይህን ለማድረግ ከሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንደኛው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት እየተሰራበት የሚገኘው #OpticalCharacterRecognition (OCR) ተብሎ ይታወቃል፡፡
ቴክኖሎጂውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በማጣመር በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና በሕትመት መልክ የሚገኙ መዛግብትን ስካን በማድረግ አሊያም ፎቶ በማንሳት በቀላሉ ኮምፒውተር ወደሚረዳው እንዲሁም የአርትኦት ሥራን ለማከናወን ወደሚያስችል የጽሁፍ አይነት (ቴክስት) መቀየር የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡
በሀገራችን የሚገኙ ጥንታዊ መዛግብቶች ለትውልድ የሚኖራቸውን አበርክቶ የተረዳው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም የቁም ጽሁፎች፣ የቆዩ የሕትመት ውጤቶች እና በእጅ የተጻፉ ሰነዶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይህን ቴክኖሎጂ ለትግበራ ለማብቃት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ሥፍራዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡
መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ማሳቹሴትስ ያደረገው ኢቮልቭ የተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም ትምህርት ቤቶች፣ ስቴዲየሞች እና ሰዎች በብዛት የሚገኙባቸውን መሰል ሥፍራዎች ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጥቅም ላይ አውሏል፡፡
በእነዚህ ሥፍራዎች ለመገልገል የሚመጡ ሰዎች በተለመደው የፍተሻ አይነት ማለፍ አይጠበቅባቸውም፡፡ ይልቁንም በግራ እና ቀኝ በቆሙ ሁለት ሰሌዳዎች መካከል ያለምንም ንክኪ፣ ሰልፍ እና እንግልት በማለፍ ይስተናገዳሉ፡፡
ቴክኖሎጂው የሚሰራው እጅግ የተራቀቁ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቆሚያዎችን (ሴንሰር) ከካሜራዎች ጋር በማቀናጀት እንደሆነ ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በዚህም ምንም አይነት ጉዳት የሌላቸውን ብረት ነክ ቁሳቁሶች ከሽጉጥ፣ ከስለት እና ተቀጣጣይ መሣሪያዎች በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ የማንቂያ መልዕክት ይልካል፡፡
ይህም በብዙ ሥፍራዎች የሚገኙትን የብረት ነክ ቁሳቁሶችን በአጠቃላይ እንደ አደገኛ መሣሪያ በመቁጠር የፍተሻ አገልግሎት ከሚሰጡ መሣሪያዎች በእጅጉ እንዲለይ አስችሎታል፡፡
ተቋሙ ከአውሮፓውያኑ 2019 ጀምሮ በስፖርት ውድድር መታደሚያ ሥፍራዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና መሰል ስፍራዎች ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ በማድረግ ሦስት መቶ ሚሊዮን ሰዎች መፈተሸ መቻሉን አስታውቋል፡፡
ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ስለእርስዎ ብዙ መረጃዎችን ሊይዝ ይችላል፤ ይህም እጅግ ግላዊ የሆኑና ሌሎች
ሰዎች እንዲያዩዋቸው የማይፈልጓቸው መልእክቶች፣ የይለፍ ቃሎችና አድራሻዎችን ያካትታል።
ስለዚህ ስልክዎ መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) ካወቁ ወዲያውኑ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን
አብዛኛዎቻችን ስልኮቻችን እንደተጠለፉ እንኳን ላናውቅ እንችላለን።
ጥሩ ዜና ግን አለ። ይህንን ለማወቅ የግድ የቴክኖሎጂ እውቀትዎ ከፍ ያለ መሆን የለበትም። እነዚህን
ምልክቶችን በተንቀሳቃሽ ስልክዎት ላይ ካስተዋሉ፤ የመጠለፉ እድል ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።
1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ
ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ
ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።
እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን
ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።
ነገር ግን ብዙ መተግበሪያዎች በስልክዎት ላይ ካሉም ፍጥነት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ
ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ
አልያም ባለሙያ ያማክሩ።
ይህ የሚሆነው አላስፈላጊና የሆኑና ተመሳስለው የገቡ ቫይረሶች እርስዎ ያላዘዙትን ሥራ እያከናወኑ ናቸው
ማለት ነው።
3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ
ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።
ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል
ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።
4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ
ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል
ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።
ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች
ይበዟቸዋል።
ወዲያው እርምጃዎ መሆን ያለብዎት ታዲያ መልዕክቱን ከመክፈትዎት በፊት ማጥፋት ነው
5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች
ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ
መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።
መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት
ይውጡ።
6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች
አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ
ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።
የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ
አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።
ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች
እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
7. ያልተለመዱ ድምጾች
የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን
ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም
ሊሆን ይችላል።
መፍትሄዎች
• የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት
• እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት
• ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም
• ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት
• ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን
• ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ
• የስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ
❶. #RAM (Random Access Memory)
ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::
❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot)
ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::
❸. #Heat_sinker
ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
#Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::
❹.#Fan
ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::
❺ #CPU
#CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::
#CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::
ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::
#CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
▫️3. #Regster
ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::
ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::
❻ #Port (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው::
መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::
የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::
❼ #Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል)
power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው::
የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::
❽#ሞደም (Modem):-
ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::
:
❾#ኪቦርድ Keybord:-
መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::
#ረሻድ_ሙዘሚል
t.me/TechnologyMasterPage
Repost from Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል
ርዕስ:- ከቴክኖሎጂ ማህደር
Page:- 77
MB Size:- 2.38MB
#Format:- Signed PDF
#ጥንቅር እና ዝግጅት: #በረሻድ_ሙዘሚል
t.me/TechnologyMasterPage
#የናተው ወንድም:- #ረሻድ_ሙዘሚል
Repost from Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል
አስደሳች ዜና!
ውድ የ Ethio Worldwide Students እና Technology Master Page የቴሌግራም አባሎች!
ቃል በገባነላችሁ መሰረት፤ በጣም ብዙ ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ መፅሐፍ ይዘን መጣን!!
#ርዕስ:- ከቴክኖሎጂ ማህደር
#Page:- 77
#MB Size: 2.38MB
#Format:- Signed PDF
#ጥንቅር እና ዝግጅት: #በረሻድ_ሙዘሚል
t.me/TechnologyMasterPage
ስለመፅሐፉ አስታየት መስጠት ከፈለጋችሁ
telegram: @ReshadMuzemil
ስልክ: 0919728324
Email: reshadmuzemil@yahoo.com
የናተው ወንድም:- ረሻድ ሙዘሚል
📌 SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?
✅ SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።
✅ HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው።
ኤችዲዲ መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው።
✅ መረጃውን ለመድረስ በክንድ ላይ የተነበበ/የፃፈ ጭንቅላት ከተሽከረከረው ሳህን በላይ ይንሳፈፋል።
ሳህኑን ለማሽከርከር እና ክንዱን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግል ሞተርን ያካትታል።
✅ ለHDD ላፕቶፖች 2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን ለዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች 3.5 ኢንች ነው።
HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።
✅ SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።
✅ ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም።
✅ SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።
✅ እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ።
✅ አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።
✅ HDD ከSSD ርካሽ ነው
✅ HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው
✅ HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል
✅ HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል
✅ HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው
✅ HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል
⚠️ ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ Enter ይጫኑ.
Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።
#ረሻድ_ሙዘሚለ
t.me/TechnologyMasterPage
✳️ላፕቶፓችን ያለኛ ፍቃድ ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት እንደ ሚቻል ላሳያችሁ።
⚡️ፍላሽ ዲሰክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰውማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ላማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡
⚡️ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲሰክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡
⚡️ከኛ ፍቃድም ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡
⚡️ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡
1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣
2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣
3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access
4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣
5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣
6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡
⚡️አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡
⚡️ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣
5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣
6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡
════❁✿❁ ═══════
📣የ Technology ቻናላችንን ለመቀላቀል👇👇
t.me/TechnologyMasterPage
ስልኮቻችንን ከጥቃት ለመከላከል የሚረዱ 10 መንገዶች
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ❖❖
በስማርት ስልኮች ላይ እየደረሰ ያለው የመረጃ ጥቃት ከቀን ቀን እያደገ ይገኛል፡፡
ይህን የላላ ደህንነት ክፍተት በመጠቀም የመረጃ በርባሪዎች በስልካችን ውስጥ ያሉትን እንደ ኢ-ሜይል
፣ማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እና የባንክ አካውንታችንን በቀላሉ እንደሚመዘብሩ ጥሩ አጋጣሚን
ይፈጥራል፡፡
ሊያደርሱብን የሚችሉትን የመረጃ ጥቃቶች ለመከላከል እንዲያግዘን እነዚህን መንገዶች ብንጠቀም
ይመከራል፡-
1. ➳➳ሁልጌዜ ስማርት ስልኩን ሶፍትዌር ማሻሻል፡- የሶፍትዌር ማሻሻዎች ለስልኮች በሚለቀቁበት ጊዜ
በወቅቱ ማሻሻያውን ኢንስቶል( install) ማድረግና፡፡
2.➳➳ ስማርት ስልኩን በይለፍ-ቃል( passcode) መቆለፍ
3.➳➳ በስማርት ስልኩ በህዝብ ዋይፋይ( Wi-Fi) ኔትዎርክ ከመጠቀም መቆጠብ
4. ➳➳ሁልጊዜ ብልቱዙ( Bluetooth) መዘጋቱን ማረጋገጥ እና መዝጋት
5.➳➳ ስልኩ ላይ የተለየ ነገር ሲከሰት የሚያሳውቅ ማሳወቂያ ማስቀመጥ፡- ይህ ሁኔታም ስልኩ
በሶስተኛ ወገን እጅ መግባቱን የሚጠቁም ሲሆን በአስቸኳይ ስልኩ ውስጥ ያሉትን ኢ-ሜይል ፣ማህበራዊ
ሚዲያ አካውንቶች እና የባንክ አካውንታችንን ለመሰወር ያግዛል፡፡
6.➳➳ ህጋዊ እና ደህንነታቸው ከተጠበቁ ሶፍትዌር አቅራቢዎች ብቻ አፕሊኬሽኖችን ኢንስቶል( Install)
ማድረግ፡፡ ለምሳሌ ከጉግል እና አፕል ስቶር
7.➳➳ ሁልጊዜ የኦንላይን አገልግሎቱ የተቆለፈ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ
8.➳➳ እያንዳንዱን በስልካችን ውስጥ ያሉትን አፕሊኬሽኖችን በይለፍ-ቃል መቆለፍ
9.➳➳ በስውር ከእኛ እውቅና ውጪ በስልካችን ውስጥ አጥፊ ሶፍትዌሮች ዳውንሎድ(download)
መሆናቸውን መፈተሸ እና ማስወገድ
10.➳➳ በስልኮቻችን ውስጥ ያሉ እና ኢንስቶል ያደረግናቸውን አፕሊኬሽኖችን መፈተሸ እና መሻሻል
ያለባቸውን ማሻሻል፡፡
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
ይህን ኹጥባ ሳንለቅ ማሳደር አልቻልንም!
--------------
ፕሮፌሰር ሸይኽ ከማል አልጀዛኢሪ ዛሬ የቁርአን ውድድሩ ላይ ስለ ሀበሻ ምድር ያደረጉት ኹጥባ እጅግ ድንቅ ነበር! ሀቂቃ ለመናገር ታሪካዊ ኹጥባ ነበር!! ስለ ሀበሻ በሌሎች አንደበት እንዲህ መስማት ያስደስታል!
እነሆ እናነተም ትመለከቱትና ታጣጥሙት ዘንድ ለቀነዋል!!!
خطبة الشيخ البروفيسور كمال الجزائري في حفل المسابقة لحفظ القرأن الكريم شارك فيها الحفاظ من دول متنوعة في العالم
تم القاؤه في نادي اديس ابابا في الدولة اثيوبيا يونيو 13 عام 2022
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ
ቴሌግራም 👇
t.me/huda4eth
ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth
ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia
ሳተላይቶች ወደ ህዋ ሲመጥቁ ዋንኛ ተግባራቸው የምድር ሁኔታ የሚያሳዩ እጅግ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን በማንሳት መላክ ነው፡፡ የዛሬው ጥንቅር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግኝት ሳተለያቶች እንዲያስቡ ያደረገ በፈጣን መንገድም የመረጃ መላላኩን በቅጽበት እንዲካሄድ ያደረገ ነው፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
የርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?
● 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> properties -> system type የሚለውን ይመልከቱ!
#እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ።
▮ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
➝ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን፤ የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡
➨ 32 ቢት ፕሮሰሰር 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
➘ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
➘32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን፤ ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
➨64 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም፤ እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም።
➘በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ። ▮በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡
➨ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
➽ ማስታወሻ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን፤
➽ ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)።
▮ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን፣ አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን፤ 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡
➽ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡
➽ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን፤ 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን.....
➘ 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡.
● በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው።
t.me/TechnologyMasterPage
