cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
191Subscribers
No data24 hours
+17 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ... ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው " - አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከቀናት በፊት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኃላ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በመግለጫው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ብዙ ውጤቶች እና እፎይታን ያስገኘ ቢሆንም አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር። ከነዚህ ቀሪ ስራዎች አንዱ የ ' ህወሓት ' ትጥቅ መፍታት እንደሆነ ጠቁሞ ፤ " በሰላም ስምምነቱ መሰረት ህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ፤ በብሄራዉ ተሃድሶ ኮሚሽን እቅድ መሰረት በፍጥነት መተግበር አለበት " ብሎ ነበር። በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ህወሓት በስምምነቱ መሰረት " ከኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ / የፌዴራል ጸጥታ ኃይል ውጭ ያለ ማንኛውም ኃይል ከትግራይ የአስተዳደር ወሰን እንዲወጡ መደረግ አለበት " ብሏል። የህወሓት ፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " ' ለዘላቂ ሰላም ትጥቅ መፍታት አለባቸው የሚለው ችግር የለውም ትክክል ነው። እንደ ትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻችን ከተመለሱልን ወደ ልማት እና ወደ የዴሞክራሲ ግንባታ ስራችን መሸጋገር እንፈልጋለን " ብለዋል። " ለሰላም ከማንም በላይ ጥብቅና እንቆማለን ስትራቴጃካዊ ፍላጎታችን ነው ግን ደግሞ ያ ሰላም ከጥያቄዎቻችን መመለስ ጋር በቀጥታ መያያዝ አለበት እንጂ ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ መብታችን ሳይከበር ዝም ብሎ ሰላም የሚመጣ ነገር አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል። " ለሰላም ብለን ቀደም ብለን ትጥቅ ማስፈታት ጀምረናል። የከባድ ማሳሪያም ርክክብም ከአመት በፊት አድርገናል፣ ከዛ አልፎ ከነበረን ሰራዊት በርካታውን demobilize አድርገናል ፤  " ሲሉ አክለዋል። " ትጥቅ #ሙሉ_በሙሉ_የማስፈታት_ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ከፌዴራል ኃይል ውጭ ያሉ የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ አሉ ህዝባችንን ለብዙ መከራ እየዳረጉ ያሉ በጸለምትም ፣ በደቡብ ትግራይም ስለዚህ አሁን ፌዴራል በጀመረው ነገር እነዚህን ኃይሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱና ወደ ሌላ ስራቸው እንዲሄዱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት " ብለዋል። ለDDR የሚያስፈልገው ሁሉ በጀትም መመደብ አለበት ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልጸዋል። @tikvahethiopia https://t.me//tamagnpress
Show all...
@T_PRESS

ኩሩ ኢትዮጽያዊ ነኝ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100088810264376

መረጃ‼️ ዛሬ በወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ህወሃት ተኩስ ከፍቶ ከ13 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መግደሉ ተሰምቷል ። በአከባቢው ሰወስት ሀይሎች ከፍተኛ ፍጥጫ ዉሰጥ ገብተዋል። ©ሪፖርተር ET ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me//tamagnpress
Show all...
ሪፖርተር ET

🔖 ይህ የሪፖርተር ET የቴሌግራም ገፅ ነው ®️ => በቻናሉ 📌 ፈጣን 📌 ትኩስ 📌 ወቅታዊ እና 📌 ወሳኝ መረጃዎችን እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !

አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው #FastMereja የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል። በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን  ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡ እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም  ከረፋዱ 5 ሰዓት  ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6  በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ  መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና  እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል። ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል። ዘገባው የፋና ነው። https://t.me//tamagnpress
Show all...
በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱኝ ነው - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን‼️ በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ የጥቆማ መቀበያ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ካደረገ በኃላ በርካታ ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡ የሚመጡ ጥቆማዎችን ተገቢነት በማጣራት ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የጥላቻ እና ሐሰተኛ ንግግሮች በአዋጁ መሰረት ከገንዘብ እስከ እስራት ቅጣት እንደሚያስከትሉ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡ ባለስልጣኑ የማህበራዊ የትስስር ገጽ አገልግሎት ሰጪዎች የኢትዮጵያን ሕግ እና ስርዓት አክብረው እንዲሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡ ህዝቡ ለሀገራዊ ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት ፀር የሆኑ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን ሲመለከት በ9192 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማዎችን እንዲሰጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡ https://t.me//tamagnpress
Show all...
@T_PRESS

ኩሩ ኢትዮጽያዊ ነኝ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100088810264376

ብልፅግና እና ህውሃት ዛሬ በአዲስ አበባ ተገናኝተው ምክክር ማድረግ መጀመራቸውን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።የምክክሩ ዝርዝር ሁኔታ በግልፅ አልተብራራም።
Show all...
በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ። በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ እንዳሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችና ግለሰቦች በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለባቸው የተባሉ ናቸው ብለዋል። በተለይም በመጋቢት 26/2016 ዓመተ ምህረት በጆር ወረዳ ለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለባቸው የተባሉ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና አምስት የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሆኑ ሰባት የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም በተለያዩ መድረኮች በጋምቤላ ከተማ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሞክር አንድ ግለሰብ ከአመራሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል። በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኮሚሽነር ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው @sheger_press https://t.me//tamagnpress
Show all...
@T_PRESS

ኩሩ ኢትዮጽያዊ ነኝ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100088810264376

👍 1
ሚኒስትሩ ከስልጣን ተነሱ‼️ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዉ የነበሩት አቶ ፀጋ አራጌ ከስልጣን መነሳታቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል። ጥቆማ❗❗👇 👉ፈጣን እና ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት፣ከስር ባለው ሊንክ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ https://t.me//tamagnpress
Show all...
በኖኖ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ፣ ባለፈው ሰኞ በተፈጸመ ጥቃት፣ 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁን የስልክ አምባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል። ለጥቃቱ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደረጉት ነዋሪዎቹ፣ 60 ቤቶች መቃጠላቸውንና ከመቶ በላይ ከብቶች መወሰዳቸውንም ተናግረዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ክሱን አስተባብሎ፤ “እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈፀመው በመንግሥት ነው” ብሏል። ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነውም ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በስልክ አምባ ከተማ ጥቃት የ11 ሰዎች ግድያ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። @ቪኦኤ
Show all...
ወደ ኦሮሚያና አዲስ አበባ የጉዞ ክልከላ…??    በተሽከርካሪ ሰርቶ አደሮች እንዳይቀሳቀሱ ማስፈራሪያና ዛቻ በሚዲያ ጭምር እየተገለፀ እየተሰማ ነው።ከወራት በፊት ወደ አዲስ አበባ ምርት እንዳይገባ እቀባ መጣሉ እና ለሳምት መተግበሩ ይታወሳል።ዛሬም አዲስ ጥሪ እየተላለፈ ተመልክተናል። ዝርዝሩን እዚህ👇 ያገኙታል Follow👇 https://vm.tiktok.com/ZMMQ11Sot/ https://vm.tiktok.com/ZMMQ11Sot/
Show all...