cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰርካለም ያለው የተለያዩ መንፈሳዊ ታሪኮች፣ወረቦች፣ጽሕፋቶች፣ትምህርቶች፣ትረካዎች በድምፅእናሌሎችም ኪነ ጥበባዊ ግጥሞች፣ቅዱሳን ስዕሎች በምስል

ይህ በተለያዬ ጊዜ በሰንበት ትምህርት ቤታችን ያጠናናቸው ወረቦች፣ጽሕፋቶች፣ዝማሜዎች፣የተማርናቸውን ትምህርቶች በድምፅ የሚያገኙበት እንዲሁም ሌሎችም ኦርቶዶክሳዊ ጉዳዮች የምንቃኝበት ቻናል ነው።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
184
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🕊 💖 🕊 [ ሥራህን ሥራ ! ] 🕊 " ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነዉ። ቢቻለዉ እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ። በእርግጥ ሥራዉን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ ፥ ሄሮድስ ፥ ሀናንያ ፥ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በፀና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኽኝን ስራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።" [ ሥራህን ሥራ ! ] 🕊 [ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ] 🕊 [ 1933 ዓ.ም - ሐምሌ 22/ 1982 ዓ.ም ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊 💖 🕊
Show all...
🕊 † እንኳን ለሰማዕታት አበው አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ : ቅዱስ መቃርስ እና ቅዱስ ለውንትዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊 † ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ † 🕊 † ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ምንም እንኳ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያን ያህል ዋጋ ቢከፍሉም ትውልዱም : መንግስቱም : ራሷ ቤተ ክርስቲያናችንም ተገቢውን ክብር ሰጥተው እያሰቧቸው አይደለም:: እስኪ እንዲያው ቢያንስ እንደ ክርስቲያን : አንድም እንደ ኢትዮጵያዊ እነዚህ ነገሮቻቸውን እናስብ:: ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ከልጅነታቸው ጀምረው ትምሕርት : ትሕርምትና ደግነት ወዳጅ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት የምትሻበት ጊዜ ነበርና በፈቃደ እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ የሃገራችን አራት አባቶች ጵጵስናን ተሾሙ:: እነርሱም ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እና አበው አባ ሚካኤል: አባ አብርሃም እና አባ ይስሐቅ ናቸው:: የተሾሙትም ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስ ከተሾሙ በኋላ በሐዋርያዊ አገልግሎትና በጸሎት ተግተው ኑረዋል:: በ፲፱፻፳፰/1928 ዓ/ም ፋሺስት ጣልያን ሃገራችንን በወረረች ጊዜ ቆራጡ ጳጳስ በዱር በገደል ለመሔድ ተነሱ:: በየበርሃው እየሔዱ አርበኞችን ሲያጽናኑ : ሲናዝዙ : ሲባርኩም ቆይተዋል:: ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ረሃብ : ጥም : እንግልትን ታግሰዋል:: በተያዙባት በዚያች ሌሊትም በጣልያኖች ለሮም እምነትና ለአገዛዙ እንዲያጐበድዱ ተጠየቁ:: ቆራጡ ሰው ግን እንቢ ቢሉ የሚደርስባቸውን እያወቁ "አይደረግም" አሉ:: በማግስቱ በአደባባይ መትረየስ ተደግኖባቸው አሁንም ጥያቄ ቀረበላቸው:: አቡነ ጴጥሮስ አፋቸውን ከፍተው ሊናገሩ ጀመሩ:- "የሃገሬ ሕዝብ ሆይ! ለሃገርህ : ለሃይማኖትህ ባትጋደል ትውልድ ይፋረድህ:: ለጣልያን ግን እንኳን ሰው ዛፍ ቅጠሉ መሬቱ እንዳይገዛለት አውግዣለሁ" አሉ:: በደቂቃዎች ልዩነት በግራዚያኒ ትዕዛዝ የመትረየስ ጥይት ዘነበባቸው:: አካላቸው ተበሳስቶ በሰንሰለት እንደ ታሠሩ መሬት ላይ ወደቁ:: አንዱ ወታደር ቀርቦ ቢመለከት ትንሽ ትንፋሽ ነበረቻቸው:: "ይሔ ቄስ አልሞተም" ብሎ ጭንቅላታቸው ላይ ተኮሰባቸው:: አቡነ ጴጥሮስ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ተሠው:: ነገሩ በአርበኞች ዘንድ ሲሰማ ትግሉ ተቀጣጠለ:: ይሄ የተደረገው ሐምሌ ፳፪ [22] ቀን በ፲፱፻፳፰/1928 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስም በተ/መ/ድ [UN] የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት [MARTYR OF THE MILLENIUM] በመባል ይታወቃሉ:: 🕊 † ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት † 🕊 † ሰማዕቱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ [ሶርያ] በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ እና የቅድስት ሶፍያ ልጅ ነው:: ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ከወላጆቹ ፍቅረ ክርስቶስን : ንጽሕናንና ደግነትን ወርሷል:: በተለይ ነዳያንን ሰብስቦ ዕለት ዕለት ያበላ ነበር:: [መቃርስ ማለት በልሳነ ዮናኒ ብጹዕ : ንዑድ : ክቡር ማለት ነው::] ቅዱሱ ያ የመከራ ዘመን ሲመጣ ሁሉም ቤተሰብ ስለ ክርስቶስ መሞትን በመምረጡ እርሱም ደስ እያለው የመከራው ተካፋይ ሆኗል:: ያን የመሰለ የቤተ መንግስት ክብር ስለ ክርስትና ናቀው:: ተገረፈ:: ተሰቃየ:: በእሳትም ተቃጠለ:: አንድ ጊዜም በአደባባይ የሞተ ሰው በጸሎቱ አስነስቶ "መስክር" አለው:: ከሞት የተነሳውም የክርስቶስን አምላክነት በመመስከሩ በአደባባይ የነበሩ ብዙ አሕዛብ በክርስትና አምነው ተሰይፈዋል:: ቅዱስ መቃርስን ግን ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን አንገቱን ቆርጠውታል:: ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አጽሙን አፍልሶ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጾለታል:: 🕊 † ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት † 🕊 † ቅዱሱ የተወለደው በተመሳሳይ ዘመን [በቅዱስ መቃርስ] ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል : ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው:: እርሱ ግን ምንም ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው : ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል:: የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት : ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር:: በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: † እግዚአብሔር ዐጽመ ሰማዕታትን ይጠብቅልን:: ከሰማዕታቱ ጽናትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: 🕊 † ሐምሌ ፳፪ [22] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩. አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት [ኢትዮጵያዊ] ፪. ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት [የፋሲለደስ ልጅ] ፫. ቅዱስ ለውንትዮስ [ክቡር ሰማዕት] ፬. አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት [ቅዳሴ ቤታቸው] ፭. ቅዱስ መርካሎስ † ወርኀዊ በዓላት ፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ] ፬. አባ ጳውሊ የዋህ † "እንግዲህ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ::" † [ማቴ. ፲፥፳፮] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: /የቅዱሳንን ዜና [ታሪክ] እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊 💖 🕊
Show all...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
እንኳን አደረሳችሁ! ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዑራኤል የሚለው ስም `ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ፣ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መጽ/ሄኖክ 6÷2 ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መጽ/ሄኖክ 28÷13 • ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤ • ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤ •እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤ • አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመልአኩ አማላጅነት ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ሕይወትን ስላጠጣቸው ነው፣ • በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፤ የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓላት በዓመት 3 ናቸው። • ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣ • መጋቢት 27 የጌታ ደሙን ለዓለም የረጨበት፣ • ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እሩህሩህ መልአክ ነው። የቅዱስ ዑራኤል አማላጂነት አይለየን፤ ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡ መልካም በዓል!!!🌹🌹🌹 🌸ሐምሌ ፳፩/ ፲፩/ ፳፻፲፬ ዓ.ም🌸🌸
Show all...
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
እንኳን አደረሳችሁ! ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዑራኤል የሚለው ስም `ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ፣ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መጽ/ሄኖክ 6÷2 ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መጽ/ሄኖክ 28÷13 • ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤ • ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤ •እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤ • አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመልአኩ አማላጅነት ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ሕይወትን ስላጠጣቸው ነው፣ • በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፤ የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓላት በዓመት 3 ናቸው። • ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣ • መጋቢት 27 የጌታ ደሙን ለዓለም የረጨበት፣ • ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እሩህሩህ መልአክ ነው። የቅዱስ ዑራኤል አማላጂነት አይለየን፤ ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡
Show all...
🕊 † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም : ቅዱስ ዑራኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊 † ድንግል እመቤታችን እና ቅዱስ ዑራኤል † 🕊 † በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል :- ፩. ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ፪. ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል:: ፫. ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል:: ፬. ለብዙ ቅዱሳን [አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ] ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል:: 🕊 † አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ † 🕊 † ወላጆቻቸው ማርቆስ እና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: ተአምራትን ገና ከእናታቸው ማኅጸን ጀምሮ ይሠሩ የነበሩት ጻድቁ በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው መንነዋል:: በስብከተ ወንጌልም ትግራይና አካባቢውን አድርሰዋል:: በነዚህም ጊዜያት ብዙ አርድእትን አፍርተዋል:: በጋስጫ ገዳም መስርተው የወንድና የሴት ብለውም ለይተዋል:: ሲጸልዩም ሆነ ሲያስተምሩ ተደሞ ይመጣባቸው የነበረ ሲሆን አንድ ቀን እባቡን ዓሣ አድርገው ደቀ መዛሙርትን አስደንቀዋል:: ከጾም: ከጸሎትና ከስግደት ባሻገር ከወቅቱ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን መከራ በመቀበላቸው እንደ ሰማዕትም ይቆጠራሉ:: ከብዙ የገድል ዓመታት በኋላም በ1330 ዓ/ም በዚህች ቀን ትግራይ ውስጥ ዐርፈዋል:: በቆይታ ግን ወደ ጋስጫ ዐጽማቸው ፈልሷል:: 🕊 † ቅዱስ ላዕከ ማርያም ኢትዮጵያዊ † 🕊 ††† ቅዱሱ የአፄ ናዖድ የልጅ ልጅ : የቅድስት ሮማነ ወርቅ ልጅ : የልብነ ድንግል የእህት ልጅና የገላውዴዎስ አጐት ነው:: በግራኝ አህመድ ዘመን ተማርኮ ወደ የመን : ከዛም ቱርክ ተወስዷል:: ሃይማኖቴን አልክድም ስላለ ብዙ አሰቃይተው : አባለ ዘሩን ቆርጠው ጃንደረባ አደረጉት:: በድንቅ ተአምር ግን ወደ ሃገሩ ተመለሰ:: እስከ ዕለተ ሞቱም ነዳያንን ሲያበላ ኑሮ ዛሬ ዐርፏል:: 🕊 † ቅዱስ ሱስንዮስ † 🕊 በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የኤፌሶን ሰው ሲሆን ጃንደረባም ነበር:: በ431 ዓ/ም ሁለት መቶውን የጉባዔ ኤፌሶን ሊቃውንት አገልግሎ በዛው ዓመት አርፏል:: ቅዱስ ቄርሎስ ገንዞ ቀብሮታል:: 🕊 † ብጹዕ አወ ክርስቶስ † 🕊 ከተባረከች ሚስቱ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ : ግን ደግሞ በድንግልና ኑረዋል:: ቀን ቀን እንግዳ ሲቀበሉ: ነዳያንን ሲያበሉ ውለው ሌሊት ሲገሰግዱና ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: ጌታችን ከሰማይ መስክሮላቸው ዛሬ ዐርፈዋል:: 🕊 † ቅዱስ ዮራኖስ † 🕊 በሉቃስ ወንጌል ላይ [ሉቃ.፳፫፥፵፯] የምናገኘው የመቶ አለቃው ሲሆን በጌታችን ትንሣኤ ቀን የጠፋች ዓይኑ በርታለት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል:: † ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን : ከቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከትን እግዚአብሔር ያድለን:: 🕊 † ሐምሌ ፳፩ [21] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩. ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ ፪. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ፫. አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ [ኢትዮጵያዊ] ፬. ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር [ኢትዮጵያዊ] ፭. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ [ኢትዮጵያዊ] ልደታቸው ፮. ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ [ጻድቃን] ፯. ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ ፰. ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን [የመቶ አለቃው] † ወርኀዊ በዓላት ፩. አበው ጎርጎርዮሳት ፪. አቡነ ምዕመነ ድንግል ፫. አቡነ አምደ ሥላሴ ፬. አባ አሮን ሶርያዊ ፭. አባ መርትያኖስ ጻድቅ † "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ:: . . ." † [ዕብ.፲፩፥፴፪] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: /የቅዱሳንን ዜና [ታሪክ] እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊 💖 🕊
Show all...
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ " #ቅዱስነታቸው_ቤተክርስቲያን_ይወክላሉ!!! #እሳቸው_ባሉበት_ኹሉ_ቤተክርስቲያን_አለች!!! #እሳቸውን_የሚናገር_እየተደፋፈረ_ያለው_ቤተክርስቲያንን_ነው!!! " የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጡ። የሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል። በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል። ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች። የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል። ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል። መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.