cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍኖተ ሠላም ሰንበት ትምህርት ቤት

ይህ በኢ/ኣ/ተ/ቤ/ክ በፉሪ ደወለ አይነ ከርም ቅድስት ኪዳነ ምኅረት እና ቅ/አማኑ ቤ/ክ ወይም በተለምዶ ሠፈራ ኪዳነ ምኅረት ቤ/ክ በመባል የሚታወቀው የሰፈራ ኪዳነ ምኅረት ልጆች አንድነት የቴሌግራም አውታር ነው። መንፈሳዊ ጹሁፎችን፥ስለ ቤ/ክን ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚግልጹ መረጃዎች እንዲሁም ማስታወቂያ ጹሁፎችን በዚህ ገጽ ለአባላቱ በሙሉ ያስተላልፋል መልክት አስታየት ጥቆማ ካሎት 0941064928

Show more
Advertising posts
196
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሴቶች_በቤተ_ክርስቲያን_ዝም_ይበሉ!_አዲስ_ስብከት_በዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ_deacon_yordanos.mp354.93 MB
እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ መደንገል በሀገራችን የድንግልና ሕይወት ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የተከበረና በማንኛውም ሰው ዘንድ ዋጋ ያለው ነገር ነበር፡፡ እስከሚያገባ (ታገባ) ድረስ በድንግልና መቆየት ግዴታው (ዋ) ነበር ነውም፡፡ ይህንንም ለማድረግ ሴቷና ወንዱ እንዳይተያዩ፣ እንዳይገናኙ እርስ በርሳቸው ስሕተት እንዳይሰሩ በማለት በልዩ ልዩ ዘዴ ይጠብቁ ነበር፡፡ ቶሎ እንዲያገቡም ይደረግ ነበር፡፡ ባሁኑ ጊዜ ደግሞ እጅግ በዛ እንጂ በሁሉም ረገድ እስኪደራጁ ድረስ ሳያገቡ መዘግየት መልካም ሆኖ ሳለ ስለ ንጽሕናቸው አጠባበቅ ደግሞ ምንም የተወሰደ እርምጃ ስለሌለ የድንግልና ሕይወት እየቀለለና ዋጋ እያጣ መጥቷል፡፡በጨቅላ እድሜያቸው ያገቡ ልጆች ጋብቻቸውን እንዳይጸናና ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ሁሉ ሳያገቡ ድንግልናቸውን የሚያጡ ስድ የለመዱ የዛሬ ተጋቢዎችም ራሳቸውን ገትቶ መያዝ ስለማይሆንላቸው ከትዳር በኋላ ስያዝኑና ሲያለቅሱ ማየት የዘወትር ክስተት ሆኗል፡፡ ለእስራኤላውያን ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው በሕግ ተስጥቷቸዋል፡፡ ይህም ድንግልናውን የሚያጠፋ ሁሉ በድንጋይ ተወግሮ፣ በእሳት ተቃጥሎ ይገደል ነበር፡፡ ዛሬ በገጠራችን አከባቢዎች አንድ ሰው የትዳር አግኝቶ እስከሚያገባ ድረስ ድንግልናውን ጠብቆ ይኖር ነበር፡፡ ከትዳር በኋላ ወንድ ድንግልናውን በከበረ ስጦታነት በረቂቅ መንገድ ለሚስቱ ሲያስረክብ ሴቲቱ ደግሞ ሕጓን ሊታወቅ በሚችል መልኩ (በግዘፍ) ለባሏ ትሰጣለች፡፡ ይህ ሲሆን በባልና በሚስት መካከል ጥልቅ የሆነ መከባበር፣ መተሳሰብ፣ መተማመንና መፋቀር ይጎልብታል፡፡ ከዚህ ውጭ የሆነ ጋብቻ ግን እንደው መቻቻል እንጂ መፋቀር የጎደለው ይሆናል፡፡ በእናንተ አከባቢ ያለ ድንግልና ከተጋቡ ሰዎች ምን አነበባችሁ? እናንተስ? ጋብቻ በደናግላን ያምራል፡፡ የብዙ ቅዱሳን ወላጆችም በድንግልና ኖረው በቅዱስ ጋብቻ የተወሰኑ ናቸው፡፡ድንግልናን እስከ ጋብቻ ድረስ ጠብቆ ማቆየት ለሰው ልጅ በሙሉ የተሰጠ ችሎታ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በውዴታ መደረግ ያለበት ነገር ብቻ አይደለም፡፡ በሀገራችን እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ድንግልናዋ የጠፋ ሴትን ማንም አያገባትም ይልቁንም ድንግልናዋን የወሰደ ሰው በግድ እንዲያገባት ይደረግ ነበር፡፡ እሷም ባያገባት እንኳን ተመልሳ ትዳርን አታስብ፤ ያለ ድንግልና የሆነ ጋብቻ ጣዕም የለውምና፡፡ ስለዚህ ወጣቶች ራሳችንን ጠብቀን ከኛ በታች ያሉ ታዳጊዎችንም አስተምረን የቀደመው ባህላችንን እንመልስ እላለሁ፡፡
Show all...
3
ደናግላንና አለባበሳቸው ለዐቅመ ሔዋን የደረሱና ያልደረሱ ደናግላን የሆኑና ያልሆኑ ሴቶች ተለይተው የሚታወቁበት የፀጉር አሠራር፣ አለጫጨትና የአለባበስ ሁኔታ በየሀገሩ ይገኛል፡፡ ጥንቱን የሀጋራችንንም ብሔር ብሔረሰቦች ባህል ወደ ኋላ መለስ በሉና አስቡ፤ የዛሬው ግን....፡፡ ድሮ እስራኤላውያን ደናግል ለፍሬ አልደረስንም ሲሉ ወርቅ እንደ አበባ የፈነዳበት ነጭ ሐር ለብሰው ይታዩ ነበር፡፡ ደናግላን የተለየ አለባበስ አንደ ነበራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ትዕማር ድንግል በነበረች ጊዜ ብዙ ኅብር ያለውን ልብስ ለብሳ ነበር እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱት ነበርና፡፡ ነገር ግን በተደፈረችና ክብሯን ባጣች ጊዜ ‹‹ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ተርትራ እየጮኸች ሄደች›› 2ሳሙ. 13፡18-19፡፡ ዛሬስ ሴቶች እህቶች ቀሚሳቸውን ቀድደው፣ አጭር ጣል የተደረገች ቀሚስ መሳይ ልብስ፣ የተወጣጠረች ቲሸርት፣ ዳሌ የምታሳይ አጭር ነጠላ፣ የውስጥ ሰውነት የሚያሳይ ስስ ቀሚስ፣ ሰይጣን አምላኪዎች የሚያደርጉት የፀጉር አሠራር ምንን ያሳያል? አንዲት ሴት ድንግል ሆና እያለች የተቀደደ ቀሚስ፣ አጭር ቀሚስለብሳ ብትሄድ ሌላ መልእክት የለውም ‹‹እኔ ድንግል አይደለሁም፣ እኔ ዘማ ነኝ፣ ተዋርጃለሁ፣ ሕጋዊ ትዳር መያዝ አልፈልግም...›› ማለት ነውና ራሳችንን እንጠብቅ፤ እኛ ክርስቲያኖች አለባበሳችን አስተማሪ መሆን አለበት፣ ምሳሌ እንኳን ባይሆን ለሌሎች መሰናክል መሆን የለብንም፡፡
Show all...
አንዳንድ ወገኖች (በተለይም ወጣቶች) በምዕራባውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የሚደረገውን በማየትና የቤተክርስቲያንንም ሥርዓት ካለመጠንቀቅ (በተገቢው ደረጃ ካለመረዳት) የተነሳ “ለሴቶች ለምን ክህነት (ዲቁና፣ ቅስና እና ጵጵስና) አይሰጣቸውም?” የሚል ጥያቄን ያነሳሉ። አልፎ አልፎም ቤተክርስቲያን ለሴቶች ክህነት አለመስጠቷ ለወንዶች ስለምታደላ (ሴቶችን ስለምታገል) ነው ሲሉም ይሰማሉ። በአጠቃላይም የክርስትና አስተምህሮ፣ ታሪክ፣ አገልግሎትና ሥርዓት ወንዶች ላይ ያተኮረና ሴቶችን ያላሳተፈ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ
Show all...
❗🔷#ግንቦት_21 #ደብረ_ምጥማቅ  ❗ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 🔴👉 የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሰራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ላይ ተቀምጣ ለተከታታይ ቀናት የተገለፀችበት ነው።  🔵👉 ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: 🔴👉 ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ በዛ በስደቱ ወራት ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር በስሟ ቤተ ክርስቲያን እንደሚታነፅም አስቀድሞ ትንቢት ተናግሮ ነበር :: 🔶👉 ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::   🔴👉 በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን7 ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::  🔵👉 እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::  የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ❗👉 ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: 🔷👉 እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::  እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት          ❗#እንኳን_አደረሳችሁ ❗ ፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨ ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።። ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።    🙏⏩ሼር አድርጉ አይከፈልበትም     
Show all...
ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፤ ዘለፋን የሚጠላ ግን ደንቆሮ ነው። 2 ደኅና ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ሰው ግን ይቀሥፈዋል። 3 ሰውን ዓመፃ አያጸናውም፤ የጻድቃን ሥር ግን አይንቀሳቀስም። 4 ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት። 5 የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ የኃጥኣን ምክር ግን ተንኰል ነው። 6 የኃጥኣን ቃል ደምን ለማፍሰስ ትሸምቃለች፤ የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል። 7 ኀጥኣን ይገለበጣሉ፥ ደግሞም አይገኙም፤ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል። 8 ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል። 9 ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል። 10 ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው። 11 ምድሩን የሚሠራ ሰው እንጀራ ይጠግባል፤ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን አእምሮ የጐደለው ነው። 12 የኅጥኣን ፈቃድ የክፉዎች ወጥመድ ናት፤ የጻድቃን ሥር ግን ፍሬን ያፈራል። 13 ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል። 14 የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል። 15 የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል። 16 የሰነፍ ቍጣ ቶሎ ይታወቃል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል። 17 እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፤ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። 18 እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፤ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው። 19 የእውነት ከንፈር ለዘላለም ትቆማለች፤ ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው። 20 ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ፤ በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው። 21 ጻድቅን መከራ አያገኘውም፤ ኀጥኣን ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው። 22 ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። 23 ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፤ የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል። 24 የትጉ እጅ ትገዛለች፤ የታካች እጅ ግን ትገብራለች። 25 ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል። 26 ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል፤ የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች። 27 ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፤ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው። 28 በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም።
Show all...
👍 1
የሴቶች አገልግሎት 👇👇👇 የቤተክርስቲያን አልባሳትንና የተለያዩ ንዋየ ቅድሳትን በእጃቸው ሠርተው በማዘጋጀት፣ ቅፅረ ቤተክርስቲያንን በማፅዳት፣ መገበሪያውን መርጠው በማዘጋጀት፣ የአብነት ተማሪዎችን እና ካህናቱን በመመገብ፣ በእንግዶች መስተንግዶ፣ በአስተዳደር ሥራዎችና በመሳሰሉት ዘርፎችም ሴቶች የሚያበረክቷቸው አገልግሎቶች ታላቅ ዋጋ እንዳላቸውና ሰማያዊ ክብርን እንደሚያሰጧቸውም ማስተዋል ያስፈልጋል። በበጎ አድራጎት ዘርፍም ገዳማትን፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመርዳት ሴቶች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ታላቅ ነው። ይህም ሊበረታታ ይገባዋል። ሴቶች (እናቶች) የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጀምሮ እስካላንበት ዘመን ድረስ ተነግሮ የማያልቅ ድንቅና ታላላቅ መንፈሳዊ አገልግሎትን ሲፈጽሙ ኖረዋል። በዚህም ለራሳቸው የጽድቅ አክሊልን አግኝተዋል፣ ለትውልድም አርአያ የሚሆን የተጋድሎ ታሪክን አቆይተዋል። በዚህ ዘመንም በዓለምና በገዳም ሃይማኖትን በመጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ወሳኝ የሆነ የመንፈሳዊ አገልግሎት ድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ስለዚህም ቅዱሳት መጻሕፍትና የቤተክርስቲያን የታሪክ መዛግብት ያሰፈሩትን የእናትነት አገልግሎት በዘመናችን ላለው ትውልድ በበቂ ሁኔታ ማስተማርና ጽፎም ማሰራጨት ያስፈልጋል። በዘመናችን ላሉት ሴቶች እህቶቻችን አብነት ይሆን ዘንድ የቤተክርስቲያን አውደምሕረትም አሁን ከሚደረገው በበለጠ የእነዚህ ቅዱሳት አንስት ተጋድሎ የሚሰበክበት፣ ስለእነርሱም የሚዘመርበት፣ ገድላቸው የሚነበበት ሊሆን ይገባል እንላለን። የእነዚህ ደጋግ ቅዱሳን እናቶች በረከታቸው ይደርብን እመለስበታለሁ
Show all...
እህቶቻችን ሆይ ማስተዋልን ትላበሱ ዘንድ እንለምናችኋለን መሰልጠንና መሰይጠንም ትለዩ ዘንድ ይሁን ሰውነትሽ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነውና ሁሉን በአግባብና በሥርዓት አድርጊለት፡፡ ደግሞም ክርስትና ራስ ወዳድነትን አብዝታ ትጠላለች ምንም ነገር ስናደርግ ስለ ሌላው ሰው ልናስብ ያስፈልገናል እኛስ ሰውን ወደ ዝሙት ሊያመራው ስለሚችል አለባበሳችን እጅግ ተጨነቅን ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ወንድማችንን ስለማሰናከል ምን አለ “መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም፡፡” (1ኛ.ቆሮ 8፡13) እንግዲህ ክርስትና እዚህ ድረስ ነው ስለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ወንድሞችና እህቶቻችን የምናስብባት ለእነሱም መሰናከያ እንዳንሆን እየተጠነቀቅን ሁሉን በአግባብና በሥርዓት የምናደርግባት፤ እምነታችንን በምግባር የምንገልጽባት ናት፡፡ “በእውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን፡፡ (ትን.ኤር. 13፡27) እህቴ ሆይ አንቺም ኤርምያስ እንዳለው ኢትዮጵያዊነትሽን ጠብቂ የምዕራባውያን በዓል ከሆነው አለባበስም ሆነ የምንዝር ጌጥ ራስሽን አርቀሽ በሚያኮራው ኢትየጵያዊ ባህላችን ትዋቢ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡ ስለእውነት አሁን ማን ነው ተጠያቂ የጡት ካንሰር ቢይዘን?? ኦረ እንዲያው ለመሆኑ ስንቶቻችን የጡት ካነሰር፣ የዲስክ መንሸራተት፣ የማህፀን ካንሰር እንዲሁም ሌሎች የበሽታ ጠንቆች የሚመጡብን በዚህ አለባበሳችን እንደሆን አስበነው እናውቅ ይሆን?? እስኪ በአሁኑ ዘመን ከጤነኛው አወላለድ (normal birthing) ውጭ የሚወልዱ እናቶች ብዛት ስንት ፐርሰንት እንደሆነ አገናዝበን እናውቅ ይሆን ይህስ በምን የመጣ መሆኑን አስበን እናውቅ ይሆን?? እስቲ እንመካከርበት እግዚአብሔር ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡
Show all...
👍 1
የበረታ የጸሎት ህይወት ይኑርህ! ✅ተደርጎልህ እንደሆነ የምታመሰግነው በጸሎት ነው የሌሎች ጉዳት አስጨንቆህ ከሆነ የምትማልደው በጸሎት ነው ኃጢአትህ ከብዶህ ከሆነ ንስሐ የምትገባው በጸሎት ነው አጥተህ ከሆነ የምትለምነው በጸሎት ነው ጸሎት ለንጉሥ አቤት ማለት ነው ጸሎት  ለዳኛ ይግባኝ ማለት ነው ጸሎት ለሰጪው ጌታ እጅን መዘርጋት ነው  ጸሎት ለቤትህ ራስ ጉድለትህን ነግረህ መተኛት ነው ጸሎት ምግበ ሥጋ ምግበ ነፍስን የምንጠይቅበት ነው ጸሎት የሃይማኖት መሣሪያ ነው ጸሎት ሀልወተ እግዚአብሔርን የምንመሰክርበት ነው ስታገኝም ጸልይ ባለህ ነገር ትረካለህ ስታጣም ጸልይ ተስፋን ይዘህ ትነሣለህ ስታለቅስም ጸልይ ከኀዘን ሸለቆ ያወጣሃል ። ✅በአገርህ ስትሆን ጸልይ ከወገን ጠላት ይጋርድሃል በሰው አገር ስትሆንም ጸልይ ባዕዱን ዘመድ ያደርግልሃል ። ✅ስፍራና ጊዜ ለይተህ በማለዳና በምሽት ጸልይ ከበረታህ በሃያ አራት ሰዓት ሰባት ጊዜ ጸልይ ከቤትህ ስትወጣ የመንገድ ጸሎት ስትመገብ የማዕድ ጸሎት አትርሳ ወደ ወዳጅህ ቤት ስትሄድ ደግሞም ስልክ ስትደውል ጸልይ የእግርህ ኮቴ እንዲናፍቀው ያደርጋል ወደ ሥራ ስትገባና ሥራህን ስትጀምር ጸልይ ሐኪም ሆነህ እንደሆነ ሳትጸልይ በሽተኛ አትንካ እውቀቱን የሰጡህ ፈረንጆች ቀዶ ጥገና ከማድረጋቸው በፊት ተንበርክከው ይጸልያሉ “አንተም በእምነትህ ጸልይ” ብለው በሽተኛውን ይጠይቃሉ በማለዳ አፍህን በጸሎት ሳታሟሽ ከሚስትህም ጋር ቢሆን አትነጋገር ላንተ ማንጋት አልረሳምና በማለዳ ተነሥተህ አመስግን ታርፍ ዘንድ ላንተ ማስመሸት አልረሳምና ሲመሽ ጸልይ ። ✅ከጸሎት ሁሉ አውራው “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ - አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን” የሚለው ነው ያለማቋረጥ ይህን ጸሎት ጸልይ ፈተናና ትግሉ ሲበዛ መዝሙር 22ን እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ ደግሞም ጸሎተ ማርያምን ታዐብዮ ነፍስዬን- ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ (ሉቃ. 1፡47-55) የመቍጠሪያ ጸሎት እጅግ ጠቃሚ ነው ከመዝሙረ ዳዊትም በጸሎትህ ደባልቅበት ። ✅የአጋንንት ፍላጻ ሲበዛ መዝሙር 90ን ደጋግመህ ጸልይ “በልዑል መጠጊያ የሚኖር…” የሚለውን ማለቴ ነው አባቶችን ስታገኝ ጸሎት ተቀበል አንተም ትባረካለህ እነርሱንም ታተጋለህ በማለዳ ጸሎትህ ላይ ውኃ በብርጭቆ አድርገህ ጸልይ ራስህንና ቤተሰብህን በተባረከው ውኃ ቀድስ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ስላገኘህም ጸልይ የሚፈልጉትን የማያውቁና የሚፈልጉትን ያጡ በዓለም ላይ አሉ የሚያድናቸው ጸሎት ብቻ ነው። ✅ወደ ወዳጅህ ቤት ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርስ ወደ ጉባዔ ስትሄድ በቃሉ እንዲናገርህ ጸሎት አድርስ በታላቅ መከራ ውስጥ ስትሆን ዝም ብለህ ጸልይ ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ ጸልዮአልና እባክህ ጸልይ ። "ምክርን የሚጠላ ሰው ኃጢአተኞችን ይመስላቸዋል እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ግን በመከሩት ጊዜ ልቡናውን ከኃጢአት ይመልሳል"(ሲራክ 21:6)
Show all...
ወንድማችን ዲያቆን እንኳን ደስስስ አለህ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.