cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአማራ ተማሪዎች ማህበር /አተማ/

አተማ የአማራ ትውልድ ተቋም አማራነት በክዋክብት ልጆቹ ይደምቃል ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
201Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ውድ የዚህ ቻናል ተከታዮች ከዚህ በፊት ስንጠቀምበት የነበረውን ይህንን ቻናል በማቆም በተደራጀ መልኩ ፈጣን እና አመርቂ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከታች ባለው ሊንክ በመጠቀም አዲሱን ቻናል እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። አተማ:የአማራ ትውልድ ተቋም!!! https://t.me/ASAabcd
Show all...
የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ)/Amhara Studentes Association(ASA)

👉ይህ ቻናል የአማራ ተማሪዎች ማህበር ከ9ኛ-3ኛ ድግሪ ያሉ አባላቱንና ደጋፊዎቹን ያሰባሰበ ቻናል ነው። 🔰ስለማህበሩ መረጃ የሚዳሰስበት 🔰ወቅታዊ ሁነቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው። 👉 ለበለጠ መረጃ 🌐 WWW.Amhara students Association.Com 📩 Fb:facebok Com/ASA የሞባይል 📲 +251918388838 💪 አተማ፡ የአማራ ትዉልድ ተቋም!!!

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በ12 ኛ ክፍል የአማራ ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ምሁራዊ የዘር ፍጅት(Intellectual Genocide) እና በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መንግሥታዊ የዘር ፍጅት ፤ የአማራ ሕዝብ ትውልድ ዘለል እሴታችን " ፋኖ" ላይ መንግሥት የሚያደረገውን ያልተገባ እርምጃና ፍረጃ ፤በአማራ ልዩ ሃይል ላይ የተያዘውን የማፍረስና የማዳከም እንቅስቃሴ የሚያወግዝ እና ለሁለንተናዊ ትግሉ መጀመሪያ የሚሆን ቀጣይነት ያለው ፤በደረጃ የተቀመጠ (ዝርዝር አፈጻጸሙን በቅርቡ የምናሳውቀው) ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና ሕዝባዊ እምቢተኝነት የፊታችን እሁድ መጋቢት 18 2014 ዓ. ም በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች ስለሚካሄድ ሁሉም አማራ ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። ዋና አስተባባሪዎች ፦ 1).የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) 2). የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አጋር/ተባባሪ አካላት ፦ 1).በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የመምህራን ማህበራት 2).በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የምሁራን መማክርት ጉባኤ አባላት 3).በአማራ ስም የተደራጁ ሁሉም የሲቪክ ማህበራት 4).ሁሉም የሙያ ማህበራት እንዲሁም የአማራ ሕዝብ ጉዳዩ ጉዳዬ ነው የሚሉ ሁሉም ተቆርቋሪ አካላት ወዘተ ......ናቸው ። ዝርዝር አፈጻጸሙን በቅርቡ እናሳውቃለን ። አማራ በጸኑ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል !!! መጋቢት 14 2014 ዓ.ም
Show all...
ማህበሩ የተመሠረተበት ዓላማ እንደመሆኑ መጠን በድኅረ-ፈተና በክልሉ የሚገኙ በአብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ላይ ቅኝት አድርጓል። በቅኝቱም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሂደቱ ላይ ጊዜዉን ያላገናዘበ ውሳኔዎችን እንደወሰነ ለመመልከት ችሏል። በተለይ በጦርነት ውስጥ ያለፉ እኳን የሚያነቡበት ጊዜ እና ቦታ ይቅርና የትምህርት ተቋሙ ወደ ፍርስራሽና ዐመድነት የተቀየረባቸዉ መሆኑን የዘነጋም ይመስላል። አብዛኛዎቹ የክልሉ ትምህርት ቤቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጦርነቱ ሰለባ መሆናቸዉን ጭምር። ከላይ ከተጠቀሰዉ በተጨማሪ ሀገሪቱ ከፍተኛ በጀት በጅታ ስለደከመችባቸዉ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጅ ፣መምህራን፣ርዕሳነ መምህራንና ማህበረሰቡ ለ12 ዓመት እና ከዚያ በላይ የደከመባቸዉ ልጆች መዳረሻቸዉ የት እንደሆነ በግልጽ የተቀመጠ ነገር አለመኖሩን ተመልክቷል። በተለይም በመንግሥት ዩኒቨርሲቲም ፣ በግል ዩኒቨርሲቲም መማር የማይችሉ ተብለዉ ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ የተፈረደባቸው ተማሪዎች ጉዳይ ማህበሩን ብቻም ሳይሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በእጅጉ የሚያሳስበዉ ሆኗል። በመጨረሻም፦ ማህበሩ ከላይ በቅደመ-ፈተና፣ በፈተና ወቅት፣ ድኅረ-ፈተና ወቅት የነበረዉን ድከመት ለመግለፅ ሞክሯል።ትምህርት ሚኒስቴር በጦር ቀጠና ውስጥ ያለፉትን ልጆች ቢያንስ ከታዳጊ ክልሎች ጋር እንኳን እኩል ማየት አለመቻሉ ሲያሳዝነን የፈተና እርማቱ ፍጹም ስሕተት ከመሆኑም በላይ ሆን ተብሎ የተደረገና የሴራ ፖለቲካው ማስፈጸሚያ አንዱ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴርና መንግሥት በድኅረ-ፈተና ወቅት የታየዉ የተማሪዎች የዉጤት ማሽቆልቆል እና የተንሸዋረረ ውሳኔ በድጋሜ እንዲያጤኑት በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ማህበሩ በተለይም በጦርነት ቀጠና የነበሩ እና በጦርነቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጎጂ የሆኑ ተማሪዎች ጉዳይ በእጅጉ የሚያሳስበው በመሆኑ በወቅቱ ተማሪዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ውሳኔ እንደገና እንዲወሰን እና ተማሪዎች ለነገ የሀገራችን ሰላምና ዕድገት የበኩላቸዉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ውሳኔ እንዲወሰን ጽኑ መልክእቱን እያስተላለፈ መንግሥት ውሳኔውን የማያስተካክል ከሆነ ጉዳዩ የአማራን ሕዝብ በቀጣይ ምሁር አልባ የማድረግ (Elite Genocide) ተልዕኮ መሆኑን ተገንዝቦ ማህበሩ የራሱን ሰላማዊ ትግል የሚጀምር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
Show all...
ከአማራ ተማሪዎች ማህበር የተሰጠ መግለጫ ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤትን እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብን አስመልክቶ የተወሰነውን ውሳኔ እውነታውን ለመገንዘብ የሚያግዝ ከዝግጅት ጀምሮ እስከ ድኅረ ፈተና በተማሪዎች በኩል የነበረውን ድባብ የሚገልጽ በጥናት ላይ የተመሠረተ ሰነድ በማቅረብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመልክተው በአፋጣኝ አስፈላጊውን ማሰተካከያ እንዲያደርጉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴርንና ሀገር ዓቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጀንሲን ጠይቋል፡፡ ተቋማቱ ጥያቄውን ካቀረብንበት ሰዓት ጀምሮ በሚቀጥሉት 30 ሰዓታት ውስጥ አወንታዊ ምላሽ ካልሰጡ ማህበሩ የራሱን ሰላማዊ ትግል የሚጀምር መሆኑን እየገለጽን ለዚህም ተማሪዎች፣መምህራን፣ወጣቶች፣የጤና ባለሙያዎች፣የሲቢክ ማህበራት፣የማህበረሰብ አንቂዎች እና መላው የአማራ ሕዝብ ጉዳዩ በሥራ አጋጣሚ የተፈጠረ ስሕተት ሳይሆን ለዘመናት ዝግጅት የተደረገበት የአማራን ሕዝብ ምሁር አልባ የማድረግ ወይም የምሁራን ዘር ማጥፋት(Elite Genocide) እና ሁለንተናዊ ዐቅም የማሳጣት ስልታዊ አካሄድ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከጎናችን እንድትቆሙና ለምናደርገው ጥሪም እንድትዘጋጁ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ በሰነዱ የተነሳው ዝርዝር ሐሳብ ከዚህ በታች ቀርቧል፡- የ12ኛ ክፍል ውጤት መቁረጫ ነጥብ በተመለከተ መንግሥት ውሳኔውን በድጋሜ ሊያጤነዉ ይገባል!!! በአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተዘጋጀ መጋቢት 9/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ መግቢያ፦ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሀገር በቀል የሲቪክ ማህበር ሲሆን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሕጋዊ ሰዉነት የተሰጠዉ ማህበር ነዉ። ማህበሩ በተማሪዎች ሁለተናዊ መብት ይከበር ዘንድ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ተማሪዎች በእውቀት ፣ በክህሎት ፣ በፈጠራ ችሎታ በአህጉር ዓቀፍ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑም እየሠራ ይገኛል። ማህበሩ በዚህ በአሰፈረዉ አጭር ጽሑፍ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በተመለከተ በቅድመ-ፈተና፣ ከፈተና ወቅት እስከ ድኅረ ፈተና ደረስ ሲከታተል መቆየቱን እንዲሁም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ መንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብን በተመለከተ ሀገሪቱ የነበረችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ተማሪዎች ፣የተማሪ ወላጆች፣ ርዕሳነ መምህራን እና መምህራን የደረሰባቸዉን የስነ-ልቦና ጫናን በአጭሩ ለመግለፅ ሞክሯል። ይህ ብቻም ሳይሆን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት ማሽቆልቆል ተከትሎ በሀገሪቱ እና በማኅበረሰቡ እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ሊደርስ የሚችለዉ ሁለንተናዊ ቀውስ በአጭሩ ተገልጿል። 1. ቅድመ-ፈተና ዝግጅት እንደሚታወቀዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት(3) ዓመታት እና ከዚያ በላይ በርካታ ሁነቶችን አስተናግዳለች። በመጀመሪያ ሀገሪቱ በተፋለሰ እና መዳረሻዉን በዉል ባለዬ የትምህርት ሥርዓት ትውልድ ለመቅረጽ ጥረት ስታደርግ እንደቆየች እናምናለን። ይህን ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ምዕራፍ ተሻገሩ። ብዙም ሳይቆይ ኮቭድ -19 ተከሰተ። በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርትን ጨምሮ በርካታ ዕቅዶች ተፋለሱ። በዚህ ሳይቆም የሀገሪቱ ዳር ድንበር ጠባቂ የሆነዉ የሀገሪቱ ትልቁ ተቋም የሆነው መከላከያ ሠራዊት ራሱን የትግራይ ነፃ አዉጭ ነኝ ብሎ በሚጠራዉ ወራሪ ሀይል ከጀርባ ተመታ። በመቀጠል ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በሰላም እጦት፣ በጦርነት ለበርካታ ወራት የመከራ ቀንበርን ተሸክመው ቆይተዋል። ጦርነቱን ተከትሎም በርካታ የሀገሪቱ መሰረተ ልማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ የጤና ተቋማት፣ የእምነት ተቋማት ከጥቅም ውጭ መሆናቸዉን እና የወታደራዊ ካምፕ ሁነዉ መቆየታቸዉ ይታወቃል። በዚህም ተማሪዎች ብቻም ሳይሆኑ በርካታ የሀገሪቱ ሕዝቦች ለሁለተናዊ የመብት ጥሰት፣ ስደትና ሞት ተጋላጭ ሆነዉ ቆይተዋል። በተለይ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የነበሩት የክልላችን ተማሪዎች መሳሪያ አንግበው ሀገርን ለማዳን ጠላት ጋር ሲፋለሙ የቆዩና ሀገር እንድትቀጥል ብዙዎች ተማሪዎች የአካልና የሕይወት መሥዋእትነት ሲከፍሉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ሰበብ ተማሪዎች መጽሐፍ ገልጠዉ ሊያነቡ ይቅርና መኖር በራሱ በጠላት እጅ በችሮታ የሚሰጥበት ሀገራዊ ዐውድ ውስጥ ቆይተዋል። በአጠቃላይ በቅደመ-ፈተና ዝግጅት ወቅት ሀገር በጭንቅ ውስጥ ነበረች። በተለይም በጦርነት ቀጠና የነበሩ ተማሪዎች ከሁሉም በከፋ ችግር ውስጥ ነበሩ። ሀገሪቱም እንደ ሀገር በገጠማት የሰላም እጦት ወይንም ጦርነት ምክንያት ፈተናዎችን በሁለት (2) ዙር እንድትሰጥ ተገዳም ነበር ። ማህበራችንም የ12ኛ ክፍል ቅደመ ፈተና ዝግጅት በብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁኖ የተሰጠ ፈተና መሆኑን በርካቶች ከሚናገሩት ሀቅ በተጨማሪ በቅጡ ይገነዘባል። ተማሪዎችም እንዲሁ በአስቸጋሪ የስነ-ልቦና ስብራት ውስጥ እንደነበሩ እና ለሁለንተናዊ የመብት ጥሰት ተጋላጭ እንደሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ወላጆች ፣ መምህራን ፣ ርዕሳነ መምህራን የሚመሰክሩት ጉዳይ ነዉ። ለሀገር ሲባል እንጅ የቅደመ ፈተና ዝግጅቱ ለዐቅመ-ፈተና የሚያበቃ እንዳልነበር በወቅቱ ከነበረዉ ሁነት መረዳት ይቻል ነበር። 2. የፈተና ወቅት ዝግጅት ፈተናዉ በሚሰጥበት ወቅት የነበረዉ ሁለተናዊ እንቅስቃሴ ሚዛን የሚደፋ እና ምቹ የሆነ ዝግጅት በመንግስት በኩል አልነበረም ። በተማሪዎች በኩልም ቢሆን በፈተና ወቅት የነበረዉ ዝግጅት ከቅድመ ፈተና ዝግጅት የተለዬ እንዳልነበር በርካታ ሁነቶች ያመላክቱ ነበር። በዚያን ወቅት ተማሪዉ ለፈተና የሚዘጋጅበት ሳይሆን ስለመኖሩና ስለሀገሩ፣ የሚያስብበት ነበር። መንግሥትም ቢሆን እንደ ሀገር የማስተዳደር ዐቅሙ ፈተና ውስጥ የገባበት ወቅት እንደነበር የሚካድ አይደለም። በአጠቃላይ በወቅቱ የነበረዉ በተለይም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል (ዋግኸምራ ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ ወልቃይት ፣ ሰሜን ወሎ ፣ ደቡብ ጎንደር ፣ደቡብ ወሎ ፣ሰሜን ሸዋ ፣ ኦሮሚያ ብሔረሰብ ዞኖችና አፋር ክልል እንዲሁም አሁንም በጠላት ስር የሚገኙት የአማራ አካባቢዎች) የፈተና አሰጣጡን በእጅጉ የሚፈታተን ጉዳይ ነበር። በአጠቃላይ ሃገሪቱ የነበረችበት ነባራዊ ሁኔታን ጨምሮ የፈተናዉ በዚያ ወቅት በተለይም የአማራ ክልል እና አፋር ክልል አካባቢዎች ሰላም አለመኖሩ ብቻም ሳይሆን ሀገር ጭንቅ በነበረችበት መሆኑ እንዲሁም ወቅቱን የሚመጥን በቂ ዝግጅት ባልነበረበት ሁኔታ መሆኑ በተማሪዎች ላይ የማይሽር ጠባሳ ጥሏል። በሌላ በኩል በአንፃራዊነት ሰላም የነበሩ አካባቢዎች የሀገሪቱን የሰላም እጦት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቴክኖሎጅ የታገዘ ፈተናን በቡድን እየሠሩ እንደነበር በርካቶች የሚያውቁት እውነት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በጦርነት ቀጠና የነበሩ እና በጦርነቱ ዙሪያ የነበሩ ተማሪዎች በእጅጉ አስቸጋሪ የፈተና ጊዜ እንዳሳለፉና የሀገሪቱ መንግሥትም ከወራሪዉ ኃይል በላይ ጠባሳ እንደጣለባቸዉ ባደረግነው ጥናት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ 3. ድኅረ-ፈተናን በተመለከተ
Show all...
ፈለገ አሳምነው ወ አስራት ወልደየስ ነፃ አምሐራ https://t.me/asaminew_tsige
Show all...
የአማራ ተማሪዎች ማህበር እንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ጎንደር ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር ለበርካታ ወራት ከትምህርት ገበታቸው ገታ አድርገው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ፤ ህዝባችንየአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የገጠመውን ሁለንተናዊ ጦርነት ሲጋፈጡ ለቆዩ የማህበሩ አመራሮችና አባሎች የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የእውቅና እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ ፒያሳ ክ/ከተማ ቀበሌ 03 #በሀዝ_ሆቴል ነገ በ06/06/2014 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30-6:30 ይካሔዳል። ስለሆነም ሁሉም ተጋባዥ እንግዶች የቀበሌ መታወቂያ እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ተማሪ ከሆኑ ደግሞ የቀበሌ መታወቂያና Campus ID በመያዝ የፕሮግራሙ ታዳሚ ይሆኑ ዘንድ ተጠርተዋል። አማራ እና ስለአማራ ህዝብ የምትቆረቆሩ ሁሉ፣ የአማራ ህዝብ ከመጣበት የጥፋት ውርጅብኝ እንታደገው ዘንድ መደራጀት፣ ማደራጀት እና ተሰባስቦ መምከር ግድ ሆኖብናል ። ስለሆነም አማራዎች ሆይ እኛም ለመዳን ኢትዮጵያንም ለማስቀጠል ኑ ተሰባስበን እንምከር። አተማ፡ የአማራ ትውልድ ተቋም። ቀን 05/06/2014ዓ.ም https://www.facebook.com/1927041750923051/posts/2756902221270329/?app=fbl
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.