cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

፩ ኛ ግጥሞች,ወጎች እና ሌሎችም

ይሄ Channel.እንሆ ለእናንተ መዝናኛ እና መገንዘቢያ እንዲሁም እራስን በመጠኑም ቢሆን መመልከቻ ይሀን ዘንድ ለ እኛ ደግሞ እኛን እና ስራችንን ከ እናንተ ጋር ለማገናኘት ይጠቅመን ዘንድ ተከፈተ፡፡ @Kalted @፩ኛግጥሞች ዛሬን ከትላንትህ የተሻለ ለማድረግ ሞክር ነገህ ከዛሬ የተሻለ ይሆን ዘንድ፡፡ @Kalted

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

• • • • • • በእያንዳንዱ ደጃ'ፍ የጌታው ስም አለ በግፍ ተሰንዶ አንዱ አንዱን እያየ ፊደሉ በሞላ ይወድቃል ተንጋዶ በየደጃፉ ላይ ቢስቅ የሚያስፈራ ጠብደል ተቀምጦ ስም ያለበት መስሎት ይጠብቃል አሉ ሌጣው ላይ አፍጥጦ ትላንትም ስቃይ ነው ዛሬም ሄደን ሄደን ደሞ እዚህ ደርሰናል. . . . . . . ስም እንዳይሰረቅ የሚጠበቅበት የፍራቻ ዘመን፡፡ ✍ቃለአብ ፀጋዬ 3/3/2014
Show all...
……… ርዕሱን አላውቀውም……… አተኩሬ አየሁት ፣ አየኝ . . . . ተንጋዶዋል ፣ ተንጋድጄበታለው……… ደብዛዛ ፊት፣ የጨፈነ ግንባር ፣ በሲጋራ ጢስ የተፈረካከሰ ከንፈር ፣ በሃሳብ የተዳጠ እራስ ያጨመጨሙ አይኖች ……… ግማሽ ሰው . . .ግማሽ አካል . . በድጋሚ አየሁት መንጋደዱ ትክክል ነው ። ቀጥ ብሎ አያውቅም ……… ሁለት መለክያ ውስኪ ይጎነጭና . . . "ውሃ ልኬ ይሄ ነው " ይለኛል . . . ሲቅም ፣ ሲያጤስም የውሃ ልኩ ነው . . . ብሎም ያምናል. . . ማመን እሱ ጋር መሆን ነው ፣ መደረግ ፣ መጨበጥ ልክ እደ ሚጠጣው የውስኪ መለክያ።. . . መጥመቂያ አፉን ስስመው ፣ ህቅ ፣ ህቅ እያለኝ ይጣፍጠኛል። "በፀጥታ ነው ማስታውስሽ ፣ ተው እንዳትይኝ ፣ መንፈሴ ሲረበሽ እረሳሻለው ፣ ማስታውስሽ በዚህ መለክያ ውስጥ ነው. . . ." ይለኛል ሳልጠይቀው ፣ ሳልከለክለው. . . . ብዙ ቀን ይረሳኝና ሊያስታውሰኝ ሲፈልግ. . "እድትሄጅም ፣ እድትመጪም አልፈልግም ፣ ከመሄድሽ ግን መምጣትሽ የበለጠ ጣፋጭ ነው" ይለኛል።. . . . ስልኩን ዘግቼ እየበረርኩ ሄድለታለው። . . . . . አይሰክርም ፤ ይሰክራልም። . . . "ለምን እደምትለዪ ታውቂያለሽ?" ከሶስት መለክያ በኃላ ይጠይቀኛል. . . እኔጃ . . . . "አትቆጥቢኝም………" በቃ እለዋለው እየከፋኝ "በቃ " . . . .. ዝም . . . ትካዜ የደኮነ ዝምታ . . . * * * በአንደኛው ቀን ላይ ……… " አርግዣለው " አልኩት "ውለጂው ፣ ጠንካራ ሴት ነሽ ፣ በእውቀትም በገንዘብም አታቀነጭሪውም " ግድ የለሽ ሆኖ ነው የመለሰለኝ . . . ውስጡን ጠልቄ ለማየት ሞከርኩ ያው ነው. . . . ትቼው ሄድኩ. . . . . . . ከአራት ወራቶች በኃላ ደወለ. . . . "አመሽኛል"አለኝ ሄድኩለት. . . ሳይፈልገኝ ስሄድ ይጠላኛል ፣ እስከሚፈልገኝ ጠብቃለው። "ልጅሽ አላደገም " ሆድ ፣ ሆዴን እያየ ፈገግ አለ. , " ልትነካው ትፈልግ ይሁን ?" መልሱ አዎ እንዲሆን እየተመኘው ጠየኩ. . . "ሁለ……ቱንም " አለኝ . . . የወጡት ቃላቶች ሲሰባበሩ ወጉኝ . . . እሱንም እያመሙት ነበር. . "ለምን. . ?" "ሂጂ በቃ. . !" "አሁን ነው የመጣሁት እኮ ጌት" "ድኛለው ፣ ከቆየሽም ያመኛል" ወጣሁኝ……… * * * "አደራ ብሰጠው አደራ ልቤን በልቶ ተገኘ አሉ በጣጥሶ አንጀቴን የደከመን ገሎ ፉከሬ ምንድነው ቀን የጣለው ለታ እሱም እንደኔ ነው እርም የናቴን ስጋ እምልልሀለው ፍቅር ካልሰጠኽኝ እሞትብሀለው ያንእምቢ ያንእምቢ ስለመን ከርሜ ይኽው ተጃጃልኩኝ ደግሜ ደግሜ " . . . ጂጂ እያዜመች እሱ እየሰማት ደረስኩ ጠርቶኝ . . "ስንት ወር ቀረሽ " "ሰባት ወሬ ነው " "ለምን ጂጂን እደምወዳት ታውቂያለሽ ?" "አይ………" "በራሷ ውስጥ ነው የበቀለችው. . .ውበት እንዲህ ነው!" ሲጋራውን ተነፈሰው. . . እኔ ሳብኩት. . . "ለምን እዲህ ሆንክ " "ምን ሆንኩ " ተረጋግቶ ጥያቄዬን በጥያቄ አጣፋው. . . ዝም አልኩ ……… "አፈቅርሻለው " . . . ደነገጥኩ አየሁት . . . ብሎኝ አያውቅም . . . ጠጋ አልኩት . . . ሳመኝ . . አይኔን ፣ ግንባሬን ፣ ከንፈሬን . . ጎንበስ ብሎ ሆዴን . . . "እናቷ ስለምትሆኚ እድለኛ ነች !" "ወንድ ነው !" . . . . "ዛሬ አልሂድ " ጠየኩት . . "ነገ ነይ ፣ አትቅሪ " አለኝ . . . ተነሳው እጄን ያዘው . . . . "ሁለት ደቂቃ ልስማሽ " "ምን ልንገርህ ?" "ስሙን ማነው ምትይው?" "አላወጣሁለትም " "ዛብሎን . . . በይው " "ምን ማለት ነው ?" "መኖሪያ. መኖሪያ ቤት. . . ማለት ነው . . . ሁሉን ሚያኖር ሆኖ ያድጋል . . . አንቺ ስለሆንሽ እናቱ" አለኝ. . . . . . ሳምኩት. . . . * * * ከስራ እደወጣው ቤቱ ሄድኩ . . . ገመድ አንገቱ ላይ ተንጠልጥሎ ዝም ብሎዋል . . . * * * ቀበርኩት ፣ አልቅሼ ሳይሆን ታምሜ ቀበርኩት ፣ ቆስዬ ፣ ተለብልቤ ለአፈር ሰጠሁት. . ሳልረዳው ፣ ሳላውቀው ፣ ሳይገባኝ ሸኘሁት . . . * * * ከብዙ ዓመታት በኃላ የዛብሎኔ ልጅ ጠየቀኝ "አያቴ . . " "ወዬ " "ወንድ አያቴ . . . ምን አይነት ሰው ነበር?" "በአባትህ ነው ማውቀው ልጄ " አልኩት! ###### /ትዝታ/ @tiztawe @wegoch @wegoch @wegoch
Show all...
/የማያልቀው ጥያቄ/ ✍ቃለአብ ፀጋዬ አውጊልኝ'ማ አንዴ ሌትሽ እንዴት ነበር? ጠላት እና ወዳጅ ሲባረር ሲባረር ድረሱልኝ የሚል አሳዛኝ ጩኸትን እንዳልሰማሽ አልፈሽ በ አርምሞ ለማንጋት ማን አስተምሮብኝ እንደምን ለመድሽው የጭካኔን ፅናት ሰርክ የማይቆመውን የእናቶችን እንባ የምስኪኑን ዋይ ዋይ ይመለከት ይሆን ? ዙፋኑን ያረገው ከሰማዩ በላይ? @kalted 19/3/2014
Show all...
ና. . .ያዝ መለኪያህን #ቃለአብ ፀጋዬ ና ያዝ መለኪያህን ብርጭቆህን ጣለው ካሰብከው ለመድረስ የጀመርከው መንገድ ኪስ እርቃን የሚያስኬድ እጅግ እረጅም ነው ይልቅ ና ከ'ኔ ጎን የያዝኩትን ይዘህ በትንሿ ባቡር ጥፋ አለምን ጥለህ . ና እናጋጭ ና እናጋጭ ከሚሉት ተነጠል ሁሉም በ'የልኩ ከሚደሰትበት ጎራ ተቀላቀል መለኪያህን ጨብጥ. . . . እወድቅ እንደው ብለህ ለምን ትሰጋለህ ምርኩዝ የሚሆኑ አጫጭር ቤቶችን እየተደጋገፍክ ቤትህ ትደርሳለህ ይልቅ ና ከ'ኔ ጎን መለኪያህን ይዘህ በትንሿ ባቡር ጥፋ አለምን ጥለህ፡፡ @kalted 22/4/214
Show all...
የሀገር እንባ ግለት ✍ቃለአብ ፀጋዬ ኧረ ቀን ሲመሻሽ የማታ የማታ ሰው በቂም ተጠምዶ ማን መላውን ይምታ ለኔስ መላው ይደር ለነገ ይቆየኝ ዛሬን ጠላት ልምታ ጠላቴ ሳይመታኝ እንደው ግን የጠላት የት ይሆን ድንበሩ ያጥራችን መዝጊያ የታል በሬ በሩ የበርታ ከበሮዉ ከሗላ ሲደለቅ ለምን ይላል ልቤ ከከበሮው ጋራ ድም .....ድልቅ ድም....... ድልቅ! የ'የሩሳሌምን ሴቶች ታዘብኳቸው መከራውን ብቻ ለኢትዮጵያ እናቶች አውሰው አውሰው ሰርጋቸው አማረ ከደስታ ተጋብተው ይኸው የኛ እናቶች አይናቸው ታወከ ተላቅሰው ተላቅሰው የ እየሱስን ትንቢት ለ እኛ አቀብለው ነጋም ዋይታ ጩኸት ጠባም መከራ ነው አውን ለዚህ ትንግርት ማን መላውን ይምታ እኔን ግን ይቆየኝ ቅድሚያ ጠላት ልምታ ለ እናት መላ ምቱ እናትን አትምቱ እንባቸው ሲበዛ ይነዳል እሳቱ ክፉ ነው ክፉ ነው የ ሀገር እንባ ግለት ነዳ ነደን ሳናልቅ በመታቹት መላ ጠላቷን ምቱላት!፡፡ Share& join 👇👇👇 ✍ @kalsagi @Kalted ☝️☝️☝️ 15/3/2014
Show all...
ንገሩት....... ሸለለ አሉ ጀግና ግዳይ ሰው ገደለ ከቶ ማን ይንገረው........ በሙታን ድሎች ነው እሱ የከበረ። እዩ ram
Show all...
ሲገባኝ.................. ህልሜ ነው ጠላቴ በእውር የሚመራኝ እጅግ እያማረ የእውኔን ያስጠላኝ፡፡ ✍kaleab 21/2/2014 @Kalsagi
Show all...