cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ምስክሮች

.✧❖✧✦✧❖✧✦✧❖✧✦✧❖ ይህ ቻናል ቅዱስ የአምላካችን ቃል በ ሉቃስ ወንጌል 24:47_48 ባዘዘን መሰረት ምስክሮቹ ሆነን ስለ ጌታ መንግሥት ና ተያያዥነት ያላቸውን ፁሁፎች የምናቀርብት ቻናል ነው። .✧❖✧✦✧❖✧✦✧❖✧✦✧❖✧✦ ሀስብ አስተያየት ካላቹ በ @witnesses116_bot አድርሱን ━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━ WELL COME! ━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
223
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መማር ድንቅ ዝማሬ በይደነቅአብ ጥላሁን SEP 16 MARSIL TV WORLDWIDE
Show all...
🟨መደምደሚያ🟨 ለጊዜው ከላይ ያቀረብኳቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች ረስተን ወይም አሳማኝ እንዳልሆኑ ቆጥረን፣ ለመዳን (ለመዳን የሚለው ቃል ይሰመርብት) የቅድስት ማርያም ወይም የሌሎች ቅዱሳንና መላእክት አማላጅነት ያስፈልገናል ማለት ምንድን ነው ጉዳቱ ብለን እንጠይቅ ይሆናል። ለመዳን የሚያስፈልገን የክርስቶስ የአማላጅነት ስራ ብቻ እንደሆነ በግልጽ መጻሃፍ ቅዱስ ላይ መስፈሩን ስላሳየሁ ይህን ጥያቄ መጠየቅ “መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ጥለን የማያስተምረውን መከተል ምንድን ነው ጉዳቱ” ብሎ እንደመጠየቅ እቆጥረዋለሁ። ለመዳን የቅዱሳን በተለይም የቅድስት ማርያም አማላጅነት ያስፈልገናል የሚለውን ትምህርት ችላ ብለን የምናልፈው ተራ ልዩነት እንዳልሆነ ግን ባጭሩ በማብራራት ጽሁፌን ልደምድም። እንዳንድ ሰዎች “ያለማርያም አማልጅነት ዓለም አይድንም” ማለታቸውን ማሰቡ የነገሩን አሳሳቢነት ግልጽ ያደርገዋል። ለመዳን የቅድስት ማርያም ወይም የሌሎች ቅዱሳን አማኞች ወይም የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት ያስፈልጋል ማለት ክርስቶስና የክርስቶስ ሞት በቂ አይደለም እንደማለት ይቆጠራል። ለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ ለመዳን ከክርስቶስ ሞት በተጨማሪ መገረዝ ያስፈልገናል ላሉ የገላትያ አማኞች የጻፈውን ደብዳቤ ማንበብ በቂ ነው – ገላ 5፥2 – 6 “እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፦ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም. . . በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።” ይላል። ልክ በክርስቶስ መስቀል ላይ ግዝረትን መጨመር ክርስቶስን ጥቅም አልባ በማድረግ ከክርስቶስ ጸጋ እንደሚለይ ሁሉ በክርስቶስ መስቀል ላይ የቅዱሳንንና መላእክትን ምልጃ ለመዳን እንደ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ክርስቶስን ጥቅም አልባ በማድረግ ከክርስቶስ ጸጋ ይለያል። ለመዳን የክርስቶስ ስራ ላይ ምንም መጨመር ስለማይቻል ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 3፥8 – 9 ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ያለኝን ጥሩ ነገር እንኳ እንደ ጉዳት ብሎም አንደ ጉድፍ እቆጥራለሁ የሚለው። እነዚህን የገላትያ አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር መታረቂያው ብቸኛው መንገድ የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ ሌላም መጨመር እንደማይቻል ሲያስጠነቅቃቸው እንዲህ ይላል – “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” ገላ 1፥6 – 9። ወንጌል ሰውን ከእግዚአብሔር ለለየው ችግር “መፍትሄ ተግኝቷል፣ መፍትሄውም ራሱን ለሁሉ ቤዛ በመስጠት በእግዚአብሔርና በሰው መካከለኛ ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ብሎ የሚያውጅ የምስራች ቃል ነው። ጌታ ኢየሱስ በያዘው ይህ መካከለኛ የመሆን ድርሻ ላይ ቅድስት ማርያምን ይሁን ሌላ ሰውን ወይም መልአክን መጨመር ሐዋርያቱ ከየትኛውም ጥንታዊ ቤተክርስቲያን መመስረት በፊት አስቀድመው ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ መጤ “ወንጌል” ነው። እግዚአብሔር ያክብራችሁ @Witnesses116
Show all...
🔸የማብራሪያ ጥያቄ ⚫️ 8 የሞቱ ወይም የተነጠቁ አማኞች በሰማይ ሆነው ስለኛ ሊጸልዩ ይችላሉ? በጣም ግልጽ ባይሆንም አማኞች ወደ ሰማይ ከሄዱም በኋላ እግዚያብሔር በገለጠላቸውና እነርሱም ምድር ላይ ሳሉ በነበራቸው እውቀት ተመስርተው ሊጸልዩ እንደሚችሉ ፍንጭ ከመጽሃፍ ቅዱስ ማግኘት ይቻል ይሆናል (ራዕ 6፥10)። ወደ እነርሱ መጸለይ ግን ጣኦት አምልኮ ውስጥ ሊያስገባን እንደሚችል ከላይ ለማሳየት ሞክሪያለሁ። እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድና ተነሳሽነት እንደሙሴና ኤሊያስ ሊገልጣቸውና መልእክት ሊሰጣቸው ይችላል ይሁን እንጂ እነዚህን በምድር የሌሉ አማኞች ስም እየጠሩ ወደ እነርሱ መጸለይ ግን በእግዚአብሔር ፊት ከጣኦት አምልኮ በተጨማሪ በመናፍስት ጠሪነትም ሊያስጠይቀን ይችላል (1ሳሙ 28፥1 – 28) ብየ አስባለሁ። “አይ የሞቱ ቅዱሳን ስለእኛ ይጸልያሉ እንዲጸልዩልንም ደግሞ ወደነሱ ብንጸልይ ምንም ችግር የለውም” ከሚል እምነቱ ወይ ፍንክች የሚል ሰው ይኖር ይሆናል። ለዚህም ሰው በድጋሜ ማሳስብ የምወደው ከላይ በዝርዝር እንዳሳየሁት በህይወት ያሉ ይሁኑ የሌሉ የቅዱሳን የምልጃ ጸሎት የመዳን ቅድመ ሁኔታ ሊሆን እንደማይችልና የምልጃ ጸሎታቸውም ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ብቸኛ ብቃት ያለውን የክርስቶስን የምልጃ ስራ የሚተካ ሊሆን እንደማይችል ነው። 🟡 9 መላእክትስ ስለእኛ ይጸልያሉ? መላእክት የሚድኑትን አማኞች የሚረዱ መናፍስት ስለሆኑ እግዚያብሔር ባሳያቸውና በተልዕኳቸው በሚገጥማቸው ነገር ተመስርተው ሊጸልዩ ወይም ጌታን ሊጠይቁ ይችላሉ። በመጽሃፍ ቅዱስ እንደምናየውም ከተገለጡልን (ከተገለጡልን የሚለው ቃል ይሰመርበት) ጥያቄ ልንጠይቃቸው እንችላለን (ልክ በምድር ላይ ላሉ ቅዱሳን አማኞች የጸሎት ጥያቄያችንን በአካል ወይም በደብዳቤ ወይም በሌላ መንገድ እንደምናስታውቀው ማለት ነው)፣ እነርሱም ካወቁት ሊመልሱልን ካላወቁት በእኛ ቦታ ሆነው እግዚአብሔርን ሊጠይቁልን ይችላሉ (ዘካ 1፥7-15)። ነገር ግን በምናባችን እያሰብንና ለጌታ እንደምናደርገው በመንፈሳዊ ተመስጦ ሆነን ወደ መላእክት መጸለይ ከላይ በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች መሰረት የእግዚአብሔርን ቦታ ለፍጡር መስጠት ስለሆነ በጌታ ፊት በጣኦት አምላኪነት ያስጠይቀናል ብየ አምናለሁ። ይቀጥላል...... @Witnesses116
Show all...
🔴የማብራሪያ ጥያቄ 🔶 6 ኢየሱስ ከማን ጋር ነው የሚያስታርቀን? ከእግዚአብሔር ጋር! እግዚአብሔር ስንል አብን፣ወልድን፣መንፈስ ቅዱስን ማለታችን ነው። ታዲያ ወልድን ከጨመረ ራሱን በራሱ ይለምናል ማለት ነውን? አይደለም – በሁለተኛው ማለትም ጌታ ኢየሱስ ብቻ በሚሰራው የምልጃ ስራ ማማለድ ማለት በአንደበት መለመን ማለት ሳይሆን ሀጢያትን ይቅር ማስባል የሚችል ደም ማቅረብ እንደሆነ ለማሳየት ሞክሪያለሁ። ስለዚህ አንድ ሰው ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርቦ “ይቅር በለኝ” ሲል፣ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በሚለየው ግብሩ ለሰው ልጆች ሃጢያት ማስተሰረያ የሚሆን ደሙን ስላፈሰሰ ያንን ሰው ሳይኮንነው ይቀበለዋል፤ አብና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በሮሜ 8፥1 እንደሚናገረው “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ [ስሌለ]ለባቸው” ያንን ሰው ሳይኮንኑ ይቀበሉታል ማለት ነው። 🛑 7 ጻድቃን ስለኛ እንዲጸልዩ (የምልጃ ጸሎት እንዲያቀርቡ) ወደ እነርሱ መጸለይስ እንችላለን? በጭራሽ፣ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ወደየትኛውም ጻድቅ ሰው (በህይወትም ያለ ይሁን የሌለ ወይም የተነጠቀ) መጸለይ ትክክል አለምሆኑን የሚያሳዩ 3 ምክንያቶች ላቅርብ፦ አንደኛ፣ በመጽሃፍ ቅዱስ አንድ ሰው ወደ ሌላ በህይወት ያለም ይሁን የሌለ ሰው ሲጸልይ ፈጽሞ ስለማናይና ይልቁንም በመጽሃፍ ቅዱስ እንደምናየው ጸሎት ሁልጊዜ ወደ እግዚያብሔር ብቻ በመሆኑ። ሁለተኛ፣ ራዕይ 5፥8። 8፥3፡4 የአማኞች ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብ የአምልኮ እጣን እንደሆነ እናያለን። ስለዚህ ጸሎት ራሱ አምልኮ ስለሆነና ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም ማምለክ ስለሌለብን ወደ ፍጡር መጸለይ ትክክል አይደለም። ሶስተኛ፣ ወደ ፍጡር መጸለይ የእግዚአብሔርን ባህርይ/ክብር ለፍጡር ማላበስ ስለሆነ። ስለሌሎች ሰወች መጸልይም ይሁን ሌሎች ስለእኛ መጸለያቸው ክርስቲያናዊ መብታችንና ሃላፊነታችን ቢሆንም፣ እንዲጸልዩልን ወደ “ጻድቃን” መጸለይ ግን በሁሉም ወይም በብዙ ቦታ በአንድ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር መገኘት ይችላሉ ብለን እንድናስብ፣ የሁሉንም ሰው ቋንቋ እንደ እግዚአብሔር መስማት ይችላሉ ብለን እንድናምን፣ ሰወች በልባቸው ወይም ድምጻቸውን እንኳ ዝቅ አድርገው የሚጸልዩትን ሁሉ ጸሎት እንደ እግዚአብሔር መስማት ይችላሉ ብለን እንድናምን፣ እንዲሁም ርቀት ወይም ሌላ ነገር ሳይገድባቸው እንደ እግዚአብሔር ሲጠሩ ይሰማሉ ይመልሳሉም ብለን እንድናስባቸው በማድረግ የእግዚአብሔርን ክብርና ቦታ እንድንሰጣቸው ያደርገናል። በመጽሃፍ ቅዱስ እንደምናየውና ጳውሎስ እንዳደረገው ሌሎች እንዲጸልዩልን በደብዳቤ ወይም በአካል ወይም በመልክተኛ ወይም በሌሎች ዘመናዊ መንገዶች ተጠቅመን መንገር እንችላለን እኛም ለቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ በቅርብም ይሁን በሩቅ ለምናውቃቸው አማኞችና ሰዎች መጸለይ እንችላለን ይገባናልም። ወደ ፍጡር መጸለይ ግን ፍጡራንን እንደእግዚአብሄር ማየትና ማክበር ነው ስለዚህም ጣኦት አምልኮ ነው ብየ አምናለሁ። ይህ እንግዲህ ለጻድቃን በጸሎት የሚቀርበውን ምስጋናና ውዳሴ ወይም መዝሙር ሳይጨምር ነው። እነዚህን ከጨመርናቸው ነገሩ ምን ያህል የጣኦት አምልኮ ውስጥ የሚያስገባ የእግዚአብሔርንም ቅናት የሚያነሳሳ እንደሆነ መገመት አያስቸግርም። ይቀጥላል...... @Witnesses116
Show all...
የማብራሪያ ጥያቄ 🛑 3 ቅድስት ማርያም አታማልድም ማለት ክብሯን አያሳንስምን? የቅድስት ማርያምም ይሁን የሁሉም ቅዱሳን አማኞችና መላእክት አላማ “እርሱ [ክርስቶስ] [እንዲ]ልቅ” (ዩሃ 3፥30) እንጂ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠውን በእግዚአብሔርና በሰው መካከላኛ (አማላጅ) የመሆንን ድርሻ በመጋራት ራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ ስላልሆነ ለቅዱሳን ይሁን ለመላእከት ጌታ የፈቀደላቸውን ቦታ ብቻ መስጠት ከቅዱሳንና መላእከት ጋር የሚያወዳጀን እንጂ የሚያጣላን ወይም የማርያም ጠላቶች የሚያስብለን አይደለም። ይህንንም ማድረግ የቅድስት ማርያምን “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” የሚለውን ምክርን በመጠበቅ እንድናከብራት ያደርገናል እንጂ የእርሷን ክብር ቅንጣት አይቀንሰውም። 🛑4 ክርስቶስ አማላጅ ነው ማለት ክብሩን አያሳንስምን? ከላይ እንዳየነው ክርስቶስ አማላጅ ነው ማለት ክርስቶስ መካካለኛስ ነው ማለት ነው፣ ሃጢያትና በደላችንን ደምስሶ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀን አዳኛችን ነው ማለት ነው። አዳኝ ክርስቶስ ብቻ ነው ማለት ባፈሰሰው ደሙም ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት ብቸኛው መንገድ ነው ማለት ክብሩን ለሌላ ከማጋራት ይጠብቀናል እንጂ ክብሩን ቅንጣት አይቀንሰውም። 🛑 5 የኢየሱስ ደም (ሞት) የሚያነጻን ካለፈ (ከውርስ) ሃጢያት ብቻ አይደለምን? በጭራሽ፣ የኢየሱስ ደም ከማንኛውም ሀጢያት በማንኛውም ጊዜ እንደሚያነጻን 1ኛ ዩሃንስ 1፥7 እና 2፥1-3 በግልጽ ያስተምራሉ። የክርስቶስም የምልጃ (የአንደበት ልመና እንዳልሆነ ለማስታወስ እወዳለሁ) አገልግሎት ምድር ላይ ያቆመ ሳይሆን አሁንም ትኩስ በሆነ ደሙ የሰዎችን ሃጢያት እየደመሰሰ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚያስታርቃቸው 1ኛ ዩሃንስ 2፥1-3፣ ዕብ 7፥25 እንዲሁም ዕብ 9፥24-26 በግልጽ ያስተምራሉ። ይቀጥላል........ @Witnesses116
Show all...
የማብራሪያ ጥያቄ 2 🛑በዩሃንስ ወንጌል 2፥1-9 መሰረት ማርያም የማማለድ ስራ አልሰራችምን? ማማለድ ስንል በቃና ዘገሊላ ለሰርግ የጠሯትን ጎረቤቶቿን (ዘምዶቿን) ወክላ ለኢየሱስ ጥያቄ (ጸሎት) አቅርባለች፣ ጥያቄዋም ምላሽ አግኝቷል ለማለት ከሆነ መልሴ “አዎን፣ በዚህ ስፍራ ማርያም አማልዳለች” ይሆናል። ይህን ዓይነት የማማለድ ስራም በአንደኛው የማማለድ ትርጉም ስር ሽፋን የሰጠነው ነው። በወንጌል እንዲህ ያለውን የምልጃ ጥያቄ (ጸሎት) ያቀረበች ቅድስትt ማርያም ብቻ ሳትሆን አስቀድሜ እንዳልኩ ሌሎችም ሰዎችም አድርገውታል ሊያደርጉትም ይገባል። ለምሳሌ የአይሁድ ሽማግሌዎች የመቶ አለቃውን ወክለው ስለባሪያው (ሉቃ 7፥2-10)፣ ሲሮፊንቃዊቷ ሴት ስለልጇ (ማር 7፥26-30) እንዲሁም ማርያምና ማርታ ስለታመመው ወንድማቸው ስለአልዓዛር (ዩሃ 11፥1-7) ይህንኑ የመሰለ ጥይቄ አቅርበዋል (ጸልየዋል)። ይህ የምልጃ ጥያቄ (ጸሎት) ግን ኢየሱስ ብቻ ከሚሰራው የምልጃ (የማዳን) ስራ ጋር ተነጻጻሪ እንዳልሆነ ምትክም ሊሆን እንደማይችል ከላይ ተመልክተናል። ይቀጥላል........ @Witnesses116
Show all...
#በእጅ_ያለ_ወርቅ🙏አንብቡትማ አንድ ማዕድን ቆፋሪ ነበረ ይሄ ሰውዬ ከቤተሰቦቹ ጋር በአመት ውስጥ ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የሚያሳልፈው ። ለምን ከተባለ ማዕድን በመቆፈር መሬት ውስጥ ለውስጥ ይጓዛል። የሚገርመው የሚቆፍረው ለራሱ አይደለም ለሚያስቆፍሩት ባለሀብቶች እንጂ ። 📍ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመጣ የሰው ልጅ ማዕድንን ለማግኘት መሬት ውስጥ ጠልቆ ይገባል በዚህ መሀል ህይወቱን ሊያጣ ሁሉ ይችላል ። ጨለማ ውስጥ እሩቅ ጥልቅ ይጓዛል ። ተስፋን ሰንቆ ህይወቱን መስዋእት አድርጎ ዋጋቸው ውድ የሆኑ ማዕድናትን ይፈልጋል ። ሳሰላስለው የሚገርመኝና ሀሴት የማደርግበት ነገር ቢኖር ። ከዕንቁ ፣ከሰንፔር ፣ከአልማዝ በላይ የከበረው እነሱን ያስገኘው ወልድ ❤ኢየሱስ ❤እኛን ሊፈልግ ወደ ምድር መምጣቱ 🙆 ዋጋችን እኮ ከማዕድ አንፃር ቢሰላ እንኳን ዕንቁ የዲንጋይ ከሰልን እንኳን ምንተካ አልነበርንም በከበረው ደሙ በዋጋ ገዝቶ መቀመጫችንን በአብ ቀኝ አደረገው ። ሰው እንቁ ሊፈልግ ጨለማ ለጨለማ ይንከራተታል ። ምንም የማንጠቅም በጨለማ ውስጥ ለነበርነው ስለ እኛ ተንከራተተ ስለእኛ ከሞት ታገለ ። ስለ እኛ የደም ላብ አላበው ከቅዱሳን ጋር ቀላቀለን ሰበአሰገሎችን ያበጀው ጌታ ህፃን ሆኖ ከእነርሱ ስጦታን ተቀበለ ። በእርሱ ቅድስና ካህናት አደረገን ። ታዲያ ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ስንባል የምን መቆዘም ነው ልዑሉ ሲወለድ ስለ ሰው ልጆች መዳን በሰማይ ደስታ ሆነ ። ጌታችን ራሱ ደስታችን ነው በእኛ መዳን ቅዱሳን መላዕክት ከተደሰቱ አኛ እንዴት ይቀልብናል? ከዚህ በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ? #በእጅ-ያለ_ወርቅ_እንደ_መዳብ_ይቆጠራል እንዲል ብሂሉ የዳንበትን መዳን እንደ ተራ ነገር አንቁጠረው ። የተከፈልን ዋጋ ቀልድ አይደለምና አንቀልድበት ህይወታችን ደም ተከፍሎበታል ለታረደው በግ ለኢየሱስ ክብር ይሁን 🙏 የደሙን ቀለበት አስሮታል እጣቴ 💍 ሙሽራዬ ኢየሱስ ራስ ነው ለቤቴ ❤ ለስሙ የማይገዛ የትኛው ሀይል ነው💪 ሙታንን ይጠራል ድምፁ ጉልበት አለው🌬 እኔ የማመልከው ሁሉን የሚገዛው🌀 ያለና የሚኖር ስሙ ኢየሱስ ነው➕ "የታረደው በግ ሀይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታት ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ"። ዮሐ:ራዕ(5÷12) 🖊Aksan Adane ዓክሳን አዳነ te.me @AksanAdane FB.com Aksan Adane ymesihu lij🙌ተባረኩ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐
Show all...
#worship night #kenz graphics ❤️❤️share 😍😍share
Show all...
የማብራሪያ ጥያቄዎች ከላይ ባየናቸው ትርጉሞች መሰረት በብዛት እንደመከራከሪያ ነጥብ የሚነሱ ጉዳዩችንና ጥቅሶችን እስኪ እንመርምራቸው። በሮሜ 8፥34 “የሚማልደው” የሚለውን “የሚፈርደው” ብሎስ መተርጎም ይቻል የለ እንዴ? አይቻልም ባይ ነኝ። ምክንያቴም አንደኛ የአማርኛ ቋንቋ ራሱ ስለማይፈቅድልን። አማርኛ ተናጋሪ የሆነ ሁሉ በቀላሉ እንደሚረዳው በ”የሚማልድ”ና “የሚማለድ” (ማ ትጠብቃለች) መካክል ሰፊ ልዩነት አለ፣ የመጀምሪያው አማላጁን ሲያመለክት ሌላኛው ተማላጁን ያሳያል። ሁለተኛ የሮሜ 8፥34 አውድ ራሱ “የሚፈርደው” ብሎ ለመተርጎም ፈጽሞ አይመችም። ከክፍሉ አውድ ማየት እንደሚቻለው የክፍሉ ዓላማ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ ማንም አይቃወመንም፣ ማንም አይከሰንም፣ ማንም አይኮንነንም” የሚለውን ሃሳብ ማስተላለፍ ነው። እንዲሁም የሚኮንነንም የሌለው በአባቱ ቀኝ ሆኖ ስለእኛ የሚማልድልን ክርስቶስ ስለሆነ ነው በማለት ክርስቶስን የመሰለ አማላጅ ስላለን ማንም ሊኮንነን እንደማይችል ማስረገጥ ነው። ይህ ደግሞ ምዕራፉን (ምዕራፍ 8ን) ሲጀምር “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም” ብሎ ከነገረን ጋር በእጅጉ የሚጣጣም ሃሳብ ነው። “የሚማልደው” የሚለውን ቃል በ“የሚፈርደው” ከቀየርነው ግን አሁን እንዳብራራሁት ከአውዱ ጋር በእጅጉ የተስማማን ትርጉም ልናገኝ አንችልም። ሶስተኛ ከአማርኛ ቋንቋ ውጪ በሁሉም በስፋት በሚነገሩ የዓለም ቋንቋዎች ቃሉ አሻሚ ባልሆነ መልኩ “ይማልዳል” ተብሎ መቀመጡ። አራተኛአዲስ ኪዳን በተጻፈበት ጥንታዊ የግሪክ ቋንቋ ትርጉሙ በማያሻማ መልኩ “ማማለድ” ሆኖ መቀመጡ ብቻ ሳይሆን አማርኛው በግልጽ ማማለድ ብሎ ከተረጎመው የዕብ 7፥25 የግሪክ ቃል ጋር አንድ አይነት መሆኑ ቃሉን “የሚማልድ” እንጂ “የሚፈርድ” ብለን እንድንተረጉም አይፈቅድልንም። እግረ መንገዴን ማሳሰብ የምፈልገው “ማማለድ” የሚለውን ሃስብ ከምልጃ ጸሎት (ከልመና) ለይተን ማየት እንዳለብን ነው። በአባቱ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ይማልዳል ማለት በአባቱ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ይጸልያል ወይም ይለምናል ማለት ሳይሆን አንዴ በፈጸመው የመስቀል ላይ ስራው አሁንም በርሱ በኩል የሚመጡትን (በእርሱ የሚያምኑትን) ከኩነኔ ነጻ ያደርጋቸዋል፣ አብም ከኩነኔ ነጻ ስለሆኑ ልጆቹ ብሎም ወራሾች አድርጎ ይቀበላቸዋል ማለት ነው። ያቀረብኳቸው አራት ምክንያቶች ባያሳምናችሁና “የሚማልደው” የሚለውን “የሚፈርደው” ብሎ መተርጎም ይቻላል ብላችሁ እንኳ ብታስቡ የክርስቶስ አማላጅነት በሮሜ 8፥34 ላይ ብቻ የተንጠለጠለ አስተምህሮ እንዳልሆነ ከላይ በግልጽነት ለማሳየት የቻልኩ ይመስለኛል። ይቀጥላል .......... @Witnesses116 @Witnesses116
Show all...
የቀጠለ አማላጅ ማነዉ? ነገር በምሳሌ ከዚህ ሁሉ ማብራሪያ በኋላ የአማላጅነትና የአዳኝነት አንድ መሆን ላልተዋጠላቸው አንድ ተጨማሪ አገላለጽ በምሳሌ ልጨምርና ወደ ጥያቄና መልሶች ልግባ። አንድ በመጠጥ ሱስ ምክንያት ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር ሰላም የሌለውን ሰው እንደምሳሌ እንውሰድ። ይህ ሰው አበበ ይባላል ተስፋ የተቆረጠበት በአንድ ጆሮው ሰምቶ በሌላው የሚያፈስ ለመካሪ ያስቸገረ ሰው ነው። አንድ ቀን ግን እሱ ራሱ ከዚህ በፊት በመጠጥ ሱስ የተጠመደ የነበረ ሰው ይተዋወቃል። ከጨዋታ ጨዋታ ስለ መጠጥ ይነሳና ያ ቀድሞ ሱሰኛ የነበረ ሰው በመጠጥ ሱስ ምክንያት ስለደረሰበት የጤና፣ የኢኮኖሚና ማህበረዊ ችግሮች አበበን በስፋት ያጫውተዋል። እንዴት ህይወቱ ኪሳራ ውስጥ እንደገባች፣ ከተከበረ ስራው እንዴት እንደተፈናቀለና ትዳሩ እንዴት መልሶ ሊስተካከል በማይችል ሁኔታ እንደፈረሰ ልብ በሚነካ መልኩ ያወጋለታል። የመጠጥ ሱስን ከዚህ ቀደም በዚህ የክፋት ደረጃው አስቦት የማያውቀው አበበም በሰውየው እጅግ አሳዛኝ የህይወት ታሪክ ነግ በኔ ብሎ በጣም ስለፈራ መጠጥን ከዚያች ቀን ጀምሮ ርግፍ አድርጎ ይተዋል። አበበ ስለዛ ሰው ሲያወራ አንዳንዴ ከመጠጥ ሱስ ያዳነኝ ሰው ነው ይላል፣ አንዳንዴ ደግሞ ከባለቤቴ ጋር በሰላም እንድኖርና ልጆቼን እንዳሳድግ ያደረገኝ ሰው ነው ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገንዘቤን ከብክነት ያዳነ በሌሎች ሰካራም ጓደኞቼም ከመብዝበዝ ነጻ ያወጣኝ ሰው ነው ይላል። ሰውየው ለአበበ ያደረገው አንድ ነገር ብቻ ቢሆንም ከተለያየ አቅጣጫ ሲታይ ሰውየው ያደረገው ነገር አንዴ አዳኝ፣ ሌላ ጊዜ ሸምጋይ፣ ደግሞ ሌላ ጊዜ ነጻ አውጭ ሊያስብለው ይችላል። ጌታ ኢየሱስም በመስቀል ላይ አንዴ የሰራው አንዱ ስራው አምነው ለሚከተሉት ከሞት ፍርድ የሚድኑበት ስራው ነውና ከእነርሱ አንጻር ሲታይ አዳኝ ያስብለዋል፣ በሃጢያት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይተው የነበሩትን ደግሞ ወደ እግዚአብሔር የሚመልስ ስራው ነውና ይኸው ስራው በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ተፈጥሮ ከነበረው ጠላትነት አንጻር ሲታይ አስታራቂ ወይም አማላጅ ያስብለዋል (ኤፌ 2፥16-18)፣ በባርነት ከተያዝንበት የሃጥያትና የዲያብሎስ ቀንበር ደግሞ ነጻ የሚያወጣን ይኸው አንዱ የመስቀል ስራው ነውና ከዚያ አንጻር ሲታይ ነጻ አውጭ ያስብለዋል (ገላ 5፥1፤ ቆላ 1፥13)፣ ደግሞም ይኸው ስራው በአይሁድና በአህዛብ መካከል የነበረውን ልዩነት ያጠፋ ስለሆነ በአይሁድና በአህዛብ መካከል ከነበረው ግንኙነት አንጻር ሲታይ አዋሃጅ ያስብለዋል (ኤፌ 2፥14-15)። አዳኝነቱ ወይም ነጻ አውጭነቱ ወይም አዋሃጅነቱ በጊዜና በቦታ ያልተገደበ ዛሬም የሚሰራ እንደሆነ ሁሉ አስታራቂነቱም (አማላጅነቱም) ዛሬም የሚሰራና በተወሰኑ ጊዜያት ወይም የሃጥያት አይነቶች ብቻ ያልተገደበ ነው። አበበ ከመጠጥ ሱሱ ሳይድን በትዳሩ ሰላም ሊወርድና ገንዘቡን ከሚያጫርሱት የመጠጥ ጓደኞቹም ነጻ ሊወጣ አይችልም ነበር። ከሚስቱ ጋር ላገኘው እርቅና ከበዝባዦቹ ነጻ ለመውጣቱ መሰረት የሆነው ከሱስ መትረፉ ነው። እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ለምናገኘው እርቅና ከዲያብሎስ ቀንበር ነጻ ለመውጣታችን ብቸኛው መሰረት በክርስቶስ ደም ነጽተን መዳናችን ነው። ይህም መሰረት (የምልጃ ስራ) በቅድስት ማርያም ወይም በህይወት ባለ ሌላ ጻድቅ ወይም በመልአክ ጸሎት ሊተካ የማይችል ብቸኛ የክርስቶስ ስራ ነው። @Witnesses116 @Witnesses116
Show all...