cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Abas Ibnu Muhibu

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ደርሶች ደዕዋዎች እንዲሁም ማንኛውም ጠቃሚ መልእክቶች በአላህ ፍቃድ ይለቀቃሉ ቻናሉን ለመቀላቀል ከታች ያለውን link ይጫኑ! @Ibnumuhibu

Show more
Advertising posts
206
Subscribers
No data24 hours
+27 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

الزنا حرام بلا شك الشيخ صالح الفوزان حفظه الله ورعاه ዚና ሀራም ነው ያለጥርጥር!!! 👉 ሙስሊም ወንድምና እህቶች ስንታችን ከዚናና ለዚና ከሚዳርጉ መንገዶች ርቀናል??ወሎህ/ሽ፣ምሽትህ/ሽ የት ነበር??መስጅድ ወይስ space? ጫካ ወይስ Library?? ከአጅነብይ ጋር ወይስ ከወንድ ጓደኛህ ከሴት ጓደኛሽ ጋር?? እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ በአሏህ!!! ኧረ የራሳችን ክብር ቢቀር እስልምናን በኛ ምክነያት ማስጠልሸት ይሰቅጥጠን በአሏህ!!። 📌 ዚናንኮ እንዳሰሩት ሳይሆን እንዳትቀርቡት ነው የተባለው። وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ! እኛ ግን የት ነን ከዚህ የቁርአን አንቀፅ??በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች https://t.me/Wku_ms_Official_Channel
Show all...
🌸 በሱና brand ተዋብ/ቢ            በዘመናችን ሰዎች ፋሽንን እንደ ጣኦት እያመለኩት ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም። ወንዱ ሴቱ ወጣቱ አለፍ ሲልም ጓልማሳው ነጋ ጠባ ፋሽን ለመከታል ይጥራል። ዛሬ በሺ ምናምን የገዛውን ልብስ ከወር በሇላ fashion ያልፍበትና ይጥለዋል ከዛም ዳግም በሺ ምናምን አዲሱን fashion ልብስ ይገዛል እሱም ግዜው ያልፍበትና ይጥለዋል እያለ ይቀጥላል.....          ወጣቱ social media ላይ መረጃ ከመፈለግ ይልቅ አዲስ የወጡ ፋሽኖችን ለመከታተል ግዜና ገንዘቡን ይጨርሳል። ታዋቂ አርቲስቶች፣ ኳስ ተጫዋቾች፣ ዘፋኞች.... ምን ለበሱ? ምን በሉ? ምን ጠጡ?ጸጉራቸውን እንዴት ተቆረጡ ....... ሚለውን ያጠናል ከዛም አራዳ ነኝ ብሎ ሚያስበው ፋራው ወንድማችን tv መስኮት ላይ or ስልኩ ላይ ያየውን ከልተገበርኩ ብሎ እሪ ካካ ይላል...          አለች ደግሞ እህታችን የዘፋኞችን እና የፊልም አክተሮችን Fashion መከተል ያሳበዳት። ሳምንት በሳምንት አለባበስ ምትቀያይረዋ። ባለንበት ዘመን ሸሪዐዊ ልብስ የተረሳበት ግዜ ነው ሙስሊም ሴቶች በሱሪ ተወጥረው ፤ ጸጉራቸውን ገልጠው መሄድ የጀመሩበት መሸፋፈን እና አይናፋርነት እንደፋርነት የታየበት ግዜ ። እንደው ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ቢያዩን ኖሮ ምን ይሉን ነበር ይሆን??      ወጣቶች ሆይ እስኪ ወደ ቀድሞ ማንነታችን እንመለስ በሱና እንዋብ። ያአኺ ሱናን ምትከተል ከሆነ ሰላም ታገኛለህ በአለባብስህ፣ በጸጉር ቁርጥህ፣ በአመጋገብህ በሁለመናህ ሱናን ተላበስ በአላህ ፍቃድ በዱንያም በአኼራም ደስተኛ ትሆናለህ። "ያ ሸባብ ሱና ግዜ የማይሽረው brand ነውና እንዋብበት" https://t.me/Abu_fewzaann
Show all...
ዘኑን በመባል የሚታወቁት ነብይ ማን ናቸው ??Anonymous voting
  • ዩኑስ
  • ዳውድ
  • ኢብራሂም
  • ሙሳ
0 votes
ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን? ~ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:– "የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር። ① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣ ② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣ ③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም] የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ? ① ከቻልን አጅሩ የማይቋረጥ ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ። ② ወይ ደግሞ እውቀትን በማሰራጨት ላይ ድርሻ ይኑረን። (ይህም በሁለት መልኩ ሊሆን ይችላል። ተምሮ በማስተማር። ያወቁትን በማካፈል። ወይም የዑለማዎችን እውቀት በማሰራጨት።) ③ ወይ ደግሞ ልጆቻችንን በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው። ከነገ በፊት ዛሬ እንመልከት። ከነዚህ መስኮች ውስጥ የቱ ላይ አለን? = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

[የጁመአ ቀን ተወዳጅ ሱናወች] ~‌ 👉ገላን መታጠብ 👉ጥሩ ልብስ መልበስ 👉ሽቶ መቀባት ለወንዶች 👉 ሲዋክ 👉ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ 👉ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት  👉በረሱል ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ። الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ  اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 🥀 መልካም ጁመአ ተመኘሁ 🥀 በመልካም ዱአቹ አስታውሱኝ😊
Show all...
ሐላል ሪዝቅ ፍለጋ ወገብህን ይሰብረው ይሆናል፤ ግን ራስህን ቀና አድርገህ እንድትኖር ያደርግሃል።
Show all...
من أجمل التلاوات በሚገርም የድምፅ ቃና ሸይኽ ሹረይም ፈጅር ሲያሰግድ
Show all...
🎧
Show all...
እናትና አያቶቻችን ከወላጆቻቸው በወረሱት አደብ እና ባልተበረዘ ተፈጥሮአቸው ተመርተው አንድ ወይም ሁለት ባዕድ ወንድ ባለበት ቦታ ድምጣቸውን ከፍ አድርገው አይናገሩም ነበር፤ ከባዕድ ወንድ ፊት ቆመውና ቀና ብለው እያዩ አያወሩም ነበር! ዛሬ ግን የቁርኣን እና የሐዲሥ እውቀት በስፋት ከመዳረሱ ጋር እንኳ በጣም ብዙ ሐያና አደብ የጎደላቸው፣ ተፈጥሮአቸው የተበላሸ ወንዳ ወንድ ሴቶች በሺህና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ባዕድ ወንዶች ባሉበት የሶሸል ሚዲያ መድረክ ላይ ወጥተው የቀልብ መድረቅና የሐያእ መነስን ጥግ በአደባባይ ያሳያሉ፤ ዲንና ወላጆቻቸውንም ያሰድባሉ፡፡ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ! ሞት በድንገት እንደሚመጣና ጌታውን አስቆጥቶ የሞተን ሰው ከቀብር ውስጥ ስቃይ ማንም እንደማይገላግለው አውቀሽ ሳይመሽ በጊዜ ተመለሺ፡፡በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
Show all...
🔹ዛሬ ልጄን ለማሳከም ወደ አንድ ሀኪም ቤት አመራሁኝ ። የላብራቶሪ ውጤት እስኪደርስ ድረስ ዶክተሩ አንድ የማወያይህ ነገር አለ ብሎኝ ቁጭ አልኩኝ ። አንዲህም አለኝ አንድ የሚያሳስበኝ ነገር አለ ይኸውም የሙስሊም ሴት እህቶቻችን ጉዳይ ነው አለኝ ። በመቀጠልም እኔ ከሞያዪ አንፃር በተለያዮ ሀኪም ቤቶች ላይ እሰራለው በየቦታው የሚያጋጥመኝ አንድ ችግር አለ ይኸውም የሴቶች ውርጃ ነው አለኝ ። የተለያዮ ሴቶች ለማስወረድ ይመጣሉ ለምን የሚል ጥያቄ ሳነሳ አብዛኛው መልሳቸው ቤተሰብ አላወቀም የሚል ነው ይህ ማለት ደግሞ ያለ ኒካህ የተረገዘ የዝሙት ልጅ በመሆኑ ነው ። እኛ ጉዳዮ ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን የተቻለንን ምክር እንለግሳቸዋለን ነገር ግን በዚህ ዙሪያ የሚሰጥ ትምህርት አሊሞች ፣ ዱአቶች ዘንድ አናሳ ነው ለምን በዚህ ላይ አትሰሩም ፣ ለምን እህቶቻችንን አታነቁም ፣ … ወቀሳውን ጠበቅ እያደረገው መጣ ። ከመፍቴዎቹ መሀከል አንዱ ሁለት ሶስት አራት ማግባት ነው ስለዚህም የሚሰጥ ትምህርት የለም ቆይ ግን ለምንድን ነው? እያለ ወላሂ ብዙ ወሳኝ ነጥቦችንና ገጠሞቹን አወራኝ በበኩሌ ያለንበት ደካማ ጎኖቹን እያነሳ እያወራኝ ስለነበር እውነት ነው እያልኩኝ ተቀበልኩኝ እላችኃለው ከዚህ በፊትም አንድ ዶክተር ይህን ጉዳይ ቦታውን ሁሉ እየጠቀሰ ነግሮኛል አንዳንዶች እንደውም ይህን ተግባር/ማስወረድን/ ከቢዝነስ አንፃር ብቻ በመመልከት የተለያዮ ክሊኒኮችን በቦታው እንደሚከፍቱ ነግሮኛል ስለዚህ ወንድሞቼ እንዲሁም ኡስታዞች በዚህ ዙሪያ ለየት ያለ ትኩረት ተሰጥቶት በዚህ ርዕስ ላይ ዘመቻ ቢደረግ መልካም ነው T.me/dawudyassin
Show all...