cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Creative G hub

Show more
Advertising posts
835
Subscribers
+124 hours
-47 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አረም ነኝ አዝመራ መሃል ስፈጠረ ገለባ መዛኝ ወደሽኝ ሰው አድርገሽኝ ፤ መሃላሽ ነፍሴን የገዛኝ አረም ነኝ ደበሎ ለባሽ ፍጥረቴ ካዘነ ጎጃም ማርያምን ማዕተብሽን እንጂ ልደሰት መሳቅ አላሻም እንበላ የተከልሽው ዳስ ዘፋኝም አልቃሽ ያለበት ለኖረ አርባ ተደርሶ ለሞተ ተዘፈነበት እንበላ ህልም እልም እንጂ አልቆየን አልኖርነው ነገር ብናምር ብንስቅ  ኖሮ እንደ ሰው እንኖር ነበር ። አንገትሽ የቀይ ዳማ በ'ያ ላይ እናቱ ስማ ያወዛች ያጊያጌጠችው የነካሽ እንዲጣፍጠው ገላሽን ከማር ሰራችው ።    .. ይገፋል የጎጃም እጁ ይንጣል የጎጃም እጅ ተገፍቶ ተገፍቶም እርጎ ተንጦም አይብ እንዲያበጅ ወንድምሽ ቁመተ ሎጋ በ'ያ ላይ ጥርሰ በረዶ ቀረ እንጂ እሱም እንደሰው የዘመን አሟሟት ለምዶ እንኳን ወንድምሽ ጥይት ያለው ሰው እንኳን ወንድምሽ ትጥቅ ያላነሰው ምድረ ጎጃሜ ሆዱን ሲብሰው እሳት አይደል ወይ የሚተኩሰው ምነ' ሃገሩ ተቀጣጠለ ምነይ ሐገሩ ተመሳቀለ ከጠላ - ውሃሽ ፣ ደም የቀለለ እያት ወገቧ ፣ የ እግዜር ሁለት እጅ እኔን ህጻኑን የታቀፈበት ዝናር ማዕረግህን አስታጥቀንና እባክህ በላይ እንመርበት @creativ_hub
Show all...
1
HEnok Bekele
Show all...
HEnock bekele
Show all...
እንደተፋሰሰው ◦◦◦ባይኖረው ማበሻ እንደመጣነው ልክ ◦◦◦ባይኖር መመለሻ ◌ አደግን እንዳልነው ◦◦◦ባይኖር ሕጻንነት ሲኦል እንደከረምን ◦◦◦ባይኖር ደሞ ገነት ◌ እንደሸመጠጥነው ◦◦◦ባንሆን ሀቀኛ እንቅልፍ እንዳጣነው ◦◦◦“ጧ!” ብለን ባንተኛ ◌ ሰውን እንዳማነው ◦◦◦መውደድ ባንችልበት እንደ ጥጋባችን ◦◦◦ዝቅ ባንልበት ◌ አውሬ እንደሆንነው ◦◦◦ሆዳችን ባይብሰው የጎዳነውን ልብ ◦◦◦አፍቅረን ባንክሰው ሕይወት ምን ነበረ ? ◦◦◦ምንስ ነበረ ሰው ? ◌ ብቻ ብዙ ጊዜ . . . ሰባብረን የጣልነው ◦◦◦ስላየን ሲጠገን መኖርን ወደድነው ◦◦◦እግዚአብሔር ይመስገን።
ሄኖክ በቀለ ለማ
Show all...
°°°ስለዚህ እግዚአብሔርን፥ ቤተሰቦቼን፥ የቅርብ ወዳጆቼን፥ የመጀመሪያ (ትዝታሽን ፡ ለእኔ ፥ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ) መጽሐፌን በማንበብ፥ በማኄስ እና በማስተዋወቅ ሰው ጋር እንዲደርስ ያደረጋችሁትን አንባቢያን ከልብ አመሰግናለሁ። “ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” የተሰኘ የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፌ በጃዕፈር መጻሕፍት አሳታሚና አከፋፋይ በኩል በዋናነት በዕለተ ረቡዕ ወደ እናንተ ይደርሳል። Esubalew Abera N.
Show all...
5
Good news fellas 💚
Show all...
😍 1
አሻም አሻም internet  ትንሽ ስለ ጠጅ እንጨዋወት :  በነገራችን ላይ አብሾ ያለበት ሰው ካልሆነ በቀር ጠጅ በቁም እና በጥፊያ አይጠጣም ።  ዝግ ብለው ያልጠጡት ጠጅ ላይበሌ ይባላል ። ስለ - ላይበሌ   በኋላ እናወራለን ። በለው ተሰማን ታውቁታላችሁ ? ጠጅ እንዳሁኑ ለ ሰፊው ህዝብ ከመፈቀዱ በፊት የነገስታት ብቻ መጠጥ ነበር ። ካባ ጥለው ገበታ ዘርግተው የሚጠጡት የክብር መጠጥ ።  መኳንንት ጠጅ አዛዥ የሚባል ሹም ነበራቸው ። ከ ጠጅ አጣጣል እስከ አቀራረቡ ድረስ ይቆጣጠራል ። የጠጅ አዛዡ በስሩ የሚሰሩ ባለሟሎች አሉት ። በጊዜው ከሃገሩ ሁሉ ከፍ ያሉ እድለኞች ማለት የጠጅ አዛዥ ባለሞሎች ነበሩ ። ጠጅ ንጉስ ፊት ከመቅረቡ በፊት መብላላቱ ፣ መብሰሉ እና አስፈላጊውን ጥንካሬ ማግኘቱ ይቀመሳል ። ታዲያ እነዚ ባለሟሎች ከህዝብ መሃል ጠጅ እንዲቀምሱ የሚፈቀድልቅቸው ብቸኛ እድለኞች ናቸው ።  ስማኝማ internet  :  ኢንግሊዛዊ ሃገር ተጓዥ በአይኔ አየሁ ብሎ በግል ማስታወሻው ላይ እንደዘገበው አንድ ባለሟል ሙሉ ብርሌ ጠጅ ሲጠጣ በመገኘቱ ንጉሱ  2 ዋንጫ ጠንካራ ጠጅ ከጋበዙት በኋላ ሞት ተፈርዶበታል ። በጊዜው ጠጅ በ ብርሌ ሳይሆን በ ፈረንሳይ ብርጭቆ ነበር የሚጠጣው ። ከዛ በፊት ደግሞ ከ ቀንድ በተሰራ ዋንጫ እንደቀሲስ ከላዩ በ ነጭ ነጠላ መሳይ ጨርቅ ይከናነብ እና ንጉስ ፊት ይቀርባል ። የፈረንሳዩ  ብርጭቆው አፉ ሰፊ ስለሆነ የጠጁ ሽታ አፍንጫ ጋር ይደርስና ቶሎ አናት ላይ ይወጣል ። ብርሌን ግን አስተውለሃት ከሆነ እዛው አፍ ላይ ግጥም ትላለች እንጂ አፍንጫ ጋር አትደርስም ።  ለዛ ነው በጊዜ ሂደት ብርሌ እየተለመደ የመጣው ።  ከ አጼ ዩሃንስ በፊት ቤተ መንግሥትን አልፎ የወጣ ጠጅ አይገኝም ።  ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ስለ በለው ተሰማ ላጫውትህ ። ሰውየው የ ጎጃም በረንታ ብቸና ሃብታም ገበሬ ነበር  ከጓሮው ጌሾ እና  ብዙ ቀፎዎች አሉት።  እንደነገሩ የ አካባቢው ገዢ ነበር እና  ፍሪዳ አርዶ ድግስ ሲደግስ ለአምሮቱ ደግሞ ጠጅ ይጥላል ። ይሄን ያየች እህቱ ብትመክረውም " ንጉስ ድሃ ሲደሰት ደስ ይለዋል እንጂ እንዴት ይከፋል " ብሎ ይቆጣት ነበር  ። ታዲያ ጠጅ ጥሎ ግብር ሰብስቦ ዳስ ድሶ ማብላት ማጠጣቱን የሰሙት ንጉስ ተክለሃይማኖት በ 2 ቀን መንገድ በረንታ ድረስ መጥተው በለው ተሰማ ጋር ለ 3 ቀን ይቆያሉ ። 3 ቀን ሙሉ የታሰበለትን ያላወቀው በለው ጠጅ እያጠጣ ቁርጥ እያበላ ቢያቆያቸውም የንጉስን ትዕዛዝ ተላልፎ ጠጅን ለጣለበት ትምክህቱ በ አደባባይ የ ቀኝ እጁን እና የግራ እግሩን እንዲቆረጥ ፈርደውበታል ። ይሄን ያየች እህቱ  እኔ እየነገርኩህ አንተ እየተቆጣህ የኔም መቀመጫ ያንተም መሄጃ አጣህ እነማይ ሳይሰማ በረንታ ሳይሰማ የጁ ተለቀሰ ለ በለው ተሰማ  ።  ብላ አልቅሳለታለች ። እዚህ ጋር የ ሃገሬውን ስንኝ ቋጣሪነት እና የግጥም ጥልቀት የጨዋታችን ግብ ስላልሆነ ለ internetኡ እንተወዋለን ። በነገራችን ላይ ጠጅ ቤት አግዳሚ መቀመጫው አረንጓዴ ፣ ብርሌው አንገቱ እና የወገቡ ስፋት እኩል የሆነ ነጭ ፣ መቅጃው እና አስተናባሪው የሚለብሰው ካባ ደግሞ ሰማያዊ እንደሆነ አስተውለሃል ? ይሄን እንተወውና ጠጅ ቤቶች ከመፈጠራቸው ጠጅ ለህዝብ ከመፈቀዱ በፊት እንዲሁ ጊዜ ጌታሁን የሚባል ጠጅ ወዳጅ የጎጃም ሃብታም ገበሬ ነበር ስለሱ ላጫውትህ ። ጊዜ ጌታሁን የደጋ መቄት ባለ ብዙ ቀፎ ገበሬ ድግስ ካለ ጠጅ ሳይፈራ የሚጥል  ደብዛ ማርያም የምትባል ደብርን ጎረቤቱ አርጎ ይሚኖር ትጉህ ገበሬ ነው ። ለ አስተርዮ ማርያም ጥቂት ካህናትን ሰብስቦ በዝግ አልፍኝ ውስጥ ከደገሰው ድግስ ሲያበላ ከጣለው ጠጅም ያቀምሳቸዋል ። ታዲያ ካህናቱ ለ ወዳጃቸው እየተናገሩ በ አመቷ አስተርዮ አንዱ ካህን 5 ሌላው ካህን 4 ወዳጃቸውን አስከትለው መምጣት ጀመሩ እና  እንዲህ እንዲህ እያሉ በ አንዱ የአስተዮ ማርያም እለት ጊዜ ጌታሁን ቤት ብዙ ካህናት የታደሙበት ድግስ ተደገሰ ይሄ ጠጅ እንደ ውሃ ፈሰሰ እንደ ጉድ ተጠጣ ። ያን ያዪ ጎረቤቶች ጊዜ ጌታሁንን ይከሱት እና ደብረታቦር አጼ ዩሃንስ ፊት ተከሶ ይቀርባል ። ንጉስ ተክለ ሃይማኖት እና ራስ ሚካኤልም ግብር ይዘው አጼ ዩሃንስ ቤት ደብረታቦር መጥተው ነበር ። ከሳሾች አባት አያቶቻችን ከጎሮዋቸው ቀፎ ፣ ከጎራቸው ጌሾ ጠጅ ጥለው ተወርሰዋል ይወረስ አሉ ። ተከሳሽ ደግሞ " ሃገሬ ዋሻው ሙሉ ማር እኔም 10 የንብ ቀፎ አለኝ ጠጅ ጥዬ መጠጣት ማጠጣቴን አልካድኩም ይፈረዱ ፍረዱ አለ "  አጼ ዮሃንስም ለማርያም ቀን ነው አይደል የደገሰው ? አዎ እና ድግስ ደግሶ ጠቦት ፍሪዳ  አርዶ ጠጅ ጥሎ እመቤታችንን በዘከረ ለምን ጽዋዋን አጠጣህ ብዬ ነው የምከሰው ? ከራሱ ጓሮ ጣለ እንጂ አልሰረቀ አላጠፋ ሲሉ ከዛ ጊዜ ጀምረው ለ ክፍለ ሃገሩ ሰው ጠጅ ጥሎ ማጠጣትን ፈቀዱ ። ከተሜ አያቶቻችን ገጠር ጎራ የሚሉት ዘመድ ጥየቃ ሳይሆን ጠጅ ቀመሳ ነበር ልልህ ነው ። ጠጅ ከዛ ጊዜ ጀምሮ እያደገ መጥቶ የመጀመሪያ በ ጠርሙስ ታሽጎ የሚሸጥ አገው ምድር የሚባል ጠጅ በ 1940 መጥቶ ነበር ። በ 1955 ደግሞ በ ሃይለስላሴ የተመረቀ ኢትዮጵያውያን እና ጣሊያናውያን ባለሃብቶች የገነቡት ሳባ የጠጅ ፋብሪካ ስራ ጀምሯል ። ወላ " ንግስት የተጣራ የማር ጠጅ " የሚባል ብራንዱን ከ 1960 ጀምሮ ኤክስፖርት አድርጓል ። የሳባ ጠጅ በቀን እስከ 10,000 ሊትር ጠጅ የመጣል አቅም ነበረው ። ከጠጅ ቤት ጀብደኝነቶች አንዱ የሞላ ብርሌ ጭንቅላት ላይ አስቀምጦ መደነስ እንደሆነ ታውቃለህ ? ታዲያ ጠጅ ቁርጥ እና ጥብስ ተበልቶ በዝግታ እንጂ ወጣወጥ አብሶ ቀይ ወጥ ተበልቶ አይጠጣም ። እንደሱ አይነት አጠጣጥ ላይበሌ ይባላል ። እዛው ጠጥተህ እዛው ትውከት ። ጠጅ  ትክክለኛ ያልኮል መጠኑ አለመታወቁ አንዱ ችግር ነው ።  የሳባ ጠጅ የሚጥላቸው ግን ከ 6 % - 11 % የአልኮል ይዘት በ ሊትር አለው ተብሎ ይገመታል ። በነገራችን ላይ ጠጅ ቤቶች ከጠዋት 11 ሰዓት ጀምሮ ነው የሚከፈቱት ። ጠዋት ላይ ወይራ ይጨሳል ማጣጫ ምናምን ይቀራረባል በዛው አንጋግተው ውሎ ይጀምራሉ ። በ ደርግ ጊዜ በቀን መጠጥ ቤቶች እንዲከፈቱ ስለማይፈቀድ ከ ምሽቱ 11 ሰዓት በፊት ጠጅ ሲሸጥ ወይም ሲጠጣ የተያዘ የጠጅ መቅጃውን አሊያም ብርሌውን ይዞ ከተማ እንዲዞር  በማድረግ አብዮታዊ ቅጣት ይቀጣል ። የከተማችን ጠጅ ቤቶች ከምንም በላይ ስማቸው ልዩ ነው ። ለዛሬ አንዳንዱን እናስታውስ እና እናብቃ ;  ይገባዋል ጠጅ ቤት ፣ እድሜ ቀጥል ጠጅ ቤት ፣ ገደል ግቡ ጠጅ ቤት ፣ መግቢያው በዚህ ነው ጠጅ ቤት ፣ አፋጀሽኝ ጠጅ ቤት ፣ ማሚቴ ጠጅ ቤት ፣ ውቂያኖስ ጠጅ ቤት ... ሙሉበት ።   አሻም አሻም internet 👐🏼
Show all...
1💔 1
Yeshak abrham
Show all...
2
-------- አልጣልኩት አላቸነፍኩት አላባረርኩት ዛሬም እንደ እግረኛ ጦር ጥቁር ሀዘን..... ዳግም ጦሩን ሰብቆ ወጋኝ አዬ! ቁስሌን እንኳ የማክበት ቁስል የሌለው ገላ ጠፋኝ! : ሀዘን ሆይ..... ምን ብሆን ነው የምትራራው? እንዴት ብሞት ነው የምትረካው? : እድሜዬ ከማላውቀው ጋ ምን ተዋውለሻል? ህይወቴ'ስ ለሀዘን ስንቴ ሰግደሻል?
Yeshak abrham
Creativ_hub
Show all...
1😍 1
#Wede_gtm 🎬 A stage scheduled for Saturday  december 23  📍kazanchis fendika cultural center 🕰 starting from 8 : 30 am local #ወደ_ግጥም 🗓 ታህሳስ 13 ከ 8 : 30 ጀምሮ ካዛንቺስ ፈንድቃ የባህል ማዕከል ይካሄዳል
Show all...