cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅድሚያ ለተውሂድ በአ/ ሸኩር ካምል በሀዲይኛ ቋንቋ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
132
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

👉 የተሃጁድ ሶላት የተሃጁድ ሶላት በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ከእንቅል ተነስተው የሚሰግዱት የለሊት ሶላት ሲሆን ከፈርድ ሶላት ቀጥሎ በጣም ትልቅ ቦታ ያለው የመልካም የአላህ ባሮች መለያ የሆነ ትልቅ ዒባዳ ነው ። ለዚህም ነው ነፍስያን ከምቾቷ ከፍላጎቷ አስጥለው የጌታቸውን ምንዳ አስበው ጎኖቻቸውን ከመኝታቸው አርቀው ተሃጁድ የሚሰግዱ ሰዎችን ለየት ባለ ስጦታ አላህ ቃል የገባላቸው ። ቃል ኪዳኑም የሚከተለው ነው : – " تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمْ عَنِ الْمَضَاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ خَوْفًا وَطَمَعًا وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُون َ" سورة السجدة ( 16) " ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፡፡ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ ፡፡" የአላህ መልእከተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – መጀመሪያ መዲና እንደገቡ ዐብዱላሂ ኢብኑ ሰላም – ረዲየላሁ ዐንሁ – ሊጠይቃቸው በሄደበት እንዲህ ሲሉ ሰማዃቸው ይላል : – " يا أيها الناس أفشوا السلام وأطعموا الطعام وصلوا بالليل والناس نيام تدخلوا الجنة بالسلام " وراه الترمذي بسند حسن صحيح " እናንተ ሰዎች ሆይ ሰላምታን አዳርሱ ምግብንም አብሉ ሰዎች በተኙበትም በለሊት ስገዱ ጀነትንም በሰላም ትገበባላችሁ " ይህ ሶላት የዚህ አይነት ክብርና ምንዳ ያለው ሲሆን ምንዳውን ማግኘት የሚቻለው ከሰዎች ተደብቆ ከአላህ ጋር ብቻ ለመገናኘት በውድቅት ለሊት በኢኽላስ ሲሰገድ ነው ። ከነብዩ ንግግር በለሊት ስገዱ ሰዎች በተኙበት ከሚለው የምንረዳው የለሊት ሶላት የሚሰግድ ሰው መስገዱን ከራሱ ጋር ያሉ የተኙ ሰዎች እንኳን ሳያውቁበት ማለት ነው ። ምን ያክል ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ከዚህ መረዳት ይቻላል ። በዚህ አሽሩል አዋኺር ብዙ ሰዎች የተሃጁድ ሶላት መስጂድ ላይ በመሰባሰብ ይሰግዳሉ ይህ በጣም ጥሩ ነው ። የሚበልጠው ከፈርድ ሶላት ውጪ ያሉ የሱና ሶላቶችን እቤት መስገዱ ቢሆንም ። ተሰባስቦ መስገዱ ባልከፋ በጣም የሚያሳዝነው በዚያ ለሊት የመስጂድ የውጭ እስፒከሮች ( ድምፅ ማጉያዎች) ተከፍተው በሽተኞች ፣ ሽማግሌዎች ፣ ህፃናት ፣ አራሶች ፣ እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር እንቅልፍ እንዲያጡ በማድረግ መሆኑ ነው ። ይህ የተሃጁድ ሶላትን ፅንሰ ሐሳብ የሚፃረር ሲሆን የአለህ መልእክተኛ በቂራአት ድምፅ ከፍ በማድረግ ሌላውን አዛ ማድረግ የከለከሉበትንም ጭምር ይፃረራል ። ዑለሞች በዚህ መልኩ ሌላውን አዛ ማድረግ እንደማይቻል ይገልፃሉ ። በመሆኑም ከስሜት መከተል ወጥተን በየመስጂዱ ያሉ ድምፅ ማጉያዎችን በማጥፋት ወደ መስጂድ ስንሄድ በእርጋታና ሰዎችን በጀማዓ ሆነን እያወራን ሳንረብሽ በፀጥታ በመስገድ የምንዳው ተቋዳሽ እንድንሆን ማድረግ አለብን ። አላህ አውቀው ከሚሰሩት ያድርገን ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🎤 አንኳኳ ይከፈትልሃል አላህ ባሮቹ ወደርሱ እንዲቀርቡ ከፀጋው እንዲጠይቁት የሱ ሁሉን ቻይነት የራሳቸው ደካማነት እንዲያውቁ ወደርሱ እንዲዋደቁ ጭንካቸውን መከራቸውን እረሃባቸውን እርዛታቸውን ሐዘናቸውን ለሱ ብቻ እንዲነግሩት ይፈልጋል ። ከርሱ በስተቀር ደራሽ ፣ ረጂ ፣ ሰጪ ፣ ከመከራ አውጪ አለመኖሩን አውቀው የሱን በር እንዲያንኳኩ ወደርሱ እንዲዋደቁ ከርሱ ተስፋ እንዳይቆርጡ አዟቸዋል ። እሱን የጠየቀ እንደሚያገኝ በመሎኮታዊ ቃሉ ገልፆላቸዋል ። ለምኑኝ ምላሽ እሰጣችኋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል ። ታዲያ ሙእሚኖች ለጭንቃቸው ለመከራቸው ለምን ይሆን የሱን ደጃፍ ትተው የሙታን ደጃፍ የሚያንኳኩት? የፉጡር ፊት የሚያዩት ? የራሳቸው ቢጤ ድሃ ሃብታም ነው ብለው ከኃላው የሚከተሉት ? ሲጠይቁት የሚያቀርብ እያለ የሚገላምጥ ፍጡር የሚለማመጡት ? ጭንቅ ላይ ያላችሁ ያአላህ በሉ የተስፋ ቃሉን አስታውሱ እንደ ተራራ የገዘፈው ጉዳያችሁ ለናንተ እነጂ ለሱ ምኑም አይደለም ። ዐለማት ቢጠይቁት ለሁሉም እንደ ፍላጎቱ ሰጥቶ ከሱ ፀጋ መርፌ ከባህር ላይ ምንም እንደ ማይቀንሰው ምንም አይቀንስም ። ስለዚህ ያአላህ በሉ ለሱ ንገሩ ደጋግማችሁ አንኳኩ አትሰልቹ ። የአልጋ ቁራኛ የሆናችሁ ፣ በእዳ የተያዛችሁ ፣ ጠላት ያስጨነቃችሁ ፣ ልጅ ያጣችሁ ፣ እርዝቅ የራቃችሁ ፣ ሰላም የናፈቃችሁ ያአለህ በሉ ። አትሰልቹ አንኳኩ ይከፈታል የፍጡር ደጅ ያልሰለቻችሁ የጌታችሁ ደጅ አይሰልቻችሁ ። ማን ደጅ እንደቆማችሁ አስቡ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ የሆነው ጌታችሁ ደጅ ላይ ናችሁ ያአላህ በሉ አንኳኩ ይከፈታል ። ዱዓእ ዒባዳ ነው ትልቅ ዒባዳ የተውሒድ ንጥረ ነገሩ ነው ። ባሪያው እሱን ሲለምን በምላሱም በሰራካላቱም ጌታውን እያመለከ ነው ። ለዚህ ነው አላህ እሱን ከመለመን የሚኮሩትን እንዲህ በማለት የዛተባቸወረ :– " وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِين َ" سورة غافر ( 60 ) " ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ ፡፡ " ዱዓእን እሱን መገዛት እንደሆነ ነግሮን እሱን ከመለመን የሚኮሩት ተዋርደው ጀሀነም እንደሚገቡ ዝቶ ነገረን ። ዱዓእ ተውሒድ ነው ። ተወኩል ነው ። ረጃእ ነው ። ስለዚህ የሁለት ሀገር ምኞታችን ተሳክቶ የጌታችንን ውዴታ ለማግኘት ወደርሱ ደጅ እንቅረብ ከፉጡር ደጅ እንራቅ ያአላህ እንበል ። እነዚህን የመጨረሻ ቀናቶች እንጠቀም ያለፈንን ለማካካስ እንበርታ እንቁም እጃችንን እንዘርጋ ወደ ላይ እናንጋጥ ያአላህ እንበል ከቀብር ጭንቅ ፣ ከሲራጥ ፈተና ፣ እሱ ፊት ራቁት ቆሞ ከማፈር ፣ እድለ ቢስ ከመሆን እንዲጠብቀን ያአላህ እንበል እናንኳኳ ይከፈታል ። አንኳክተው ከሚከፈትላቸው ባሮቹ አላህ ያድርገን ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

የወረቀት ብር ኖት ዘካህ ~~~~ በጥንት ዘመን ሰዎች ግብይት የሚፈፅሙት እቃን በእቃ በመለዋወጥ ነበር። የልውውጥ ገበያ ለአጠቃቀም አስቸጋሪ በመሆኑ የተነሳ ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ ሄዶ አንዳንድ እቃዎችን (ለምሳሌ በሃገራችን አሞሌ ጨው) እንደመገበያያ ገንዘብ በመጠቃቀም ተተካ። ይሁን እንጂ እነዚህ እቃዎች ለአያያዝ አስቸጋሪ በመሆናቸው የተነሳ ሰዎች ወደ ሌሎች አማራጮች ማማተር ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ ነበር ወርቅና ብር ለመገበያያነት መዋል የጀመሩት። ወርቅና ብር ታዲያ በጊዜ ሂደት በአንጣሪዎች አማካኝነት ተመሳሳይ መጠንና ክብደት እንዲይዙ ተደርገው ለአስተማማኝነታቸው ማህተም ዲዛይን ተደርጎባቸው መዘጋጀት ያዙ። እነዚህን ገንዘቦች ለደህንነታቸው በመስጋት ገንዘብ መንዛሪዎችና አንጥረኞች ዘንድ በማስቀመጥ መተማመኛ ደረሰኞችን በምትካቸው ይቀበሉ ነበር። ሰዎች በነዚህ ድርጅቶች ላይ ያላቸው እምነት በጨመረ ቁጥር ደርሰኞቹ በግብይት ላይ ለክፍያ መዋል ያዙ። የወረቀት ብር ኖት ታሪካዊ አነሳሱ በዚህ መልኩ ነበር። በጊዜው እነዚህ ከገንዘብ መንዛሪ ድርጅቶች የሚመጡ ወረቀቶች ሰውየው በነዚህ የግል ድርጅቶች ዘንድ ወርቅ/ ብር እንዳስቀመጠ በመግለፅ ወረቀቱን የተቀበለ ሰው ሄዶ ወርቁን/ ብሩን መውሰድ እንደሚችል ከመጠቆም ባለፈ ኦፊሴላዊ ይዘትም ሆነ የህግ ከለላ አልነበራቸውም። አገልግሎታቸው በሰፋ ቁጥር ግን በጊዜ ሂደት መንግስታት የህግ ሽፋን ሊሰጡ ግድ ብሏቸዋል። በዚህን ጊዜ የታወቀ ተመን በመስጠት ላምጪው እንዲከፈል አስገዳጅ ህግ ወጣ። የማተሙ/ የማሳተሙ ኃላፊነትም የመንግስታት ሆነ። ይህ ነገር የተጀመረው በ1833 እንደሆነ ድርሳናት ይጠቁማሉ። (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ነው።) መንግስታት ካላቸው ተቀማጭ የወርቅ መጠን በላይ እነዚህን የወረቀት መገበያያዎች ገበያ ላይ ሲያቀርቡ ጊዜ ግን በነባሩ የወርቅ መገበያያ ላይ ፈተና ተደቀነ። በዚህን ጊዜ የወረቀት መገበያያዎችን ወደ ወርቅ ከመቀየር የሚከለክል ህግ መውጣት ያዘ። በዚህ ረገድ ቀዳሚዋ ብሪታኒያ ስትሆን ይህ የሆነውም በ1931 ነበር። አሜሪካ በ1934 ተከተለቻት። የክልከላው ተግባራዊነት ግን ድንበር ተሻጋሪ ሳይሆን በሃገራቱ ውስጥ የተገደበ ነበር። ሃገራት ከሃገራት ጋር ሲገበያዩ ግን የወረቀት ብሩን ወደ ወርቅ የመቀየር ውላቸውን ይጠብቁ ነበር። ከ1971 ጀምሮ ግን የወርቅ መጠን እያነሰ ስለመጣ አሜሪካ ይህንኛውን አሰራር ጭምር አቆመች። የመጨረሻው ወርቅን ለግብይት ተመን የመጠቀም አሰራር በዚህ መልኩ ተዘጋ። የወረቀት ብር ኖት ምንነትን በመግለፅ ላይ እነዚህን ታሪካዊ ለውጦች በማሳለፉ የተነሳ የኢስላም ምሁራን እይታቸው ሊለያይ ችሏል። የብዙሃን ዑለማዎችን አቋም ብቻ ሳሰፍር የወረቀት ብር ማለት እራሱን የቻለ የተለየ መገበያያ ገንዘብ ሲሆን ወርቅና ብርን (ሲልቨር) የሚመለከቱ ህጎች ይመለከቱታል። የየሃገራቱ የወረቀት ኖት እራሱን የቻለ አንዱ ከሌላው የሚለይ ገንዘብ ነው። ለማሳጠር ስል ለዚህ ትርጓሜ የሚውሉ አጋዥ መረጃዎችን አልጠቅስም። እነዚህ የወረቀት ብር ኖት ሲጀመሩ አካባቢ ዘካ ይወጅብባቸዋል ወይስ አይወጅብባቸውም በሚለው ላይ በኢስላም ምሁራን መካከል ውዝግብ ተከስቶ ነበር። የልዩነቱ መነሻ ለዚህ ገንዘብ ምንነት የተሰጡ ትርጓሜዎች መለያየት ነበር። ነገር ግን ይሄ መገበያያ በከፍተኛ መጠን በመስፋፋቱና የወርቅና የብርን ቦታ በመተካቱ የተነሳ ውዝግቡ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ከስሟል። ስለዚህ ትኩረታችን ይህ የወረቀት ብር ኖት ለዘካ መጠን በሚደርስበት መነሻ ተመን (ኒሷብ) ላይ ይገደባል ማለት ነው። የወረቀት ብር ኖት ዘካ የሚወጅብበት መነሻው ተመን (ኒሷብ) ስንት ነው? በዚህ ላይ ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል። አንደኛ:– የወረቀት መገበያያ ኖት መነሻ የዘካ ተመን የብር (ሲልቨር፣ ፊዷ) ኒሷብ ነው ያሉ አሉ። ይህም 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ነው። ሁለተኛ:– ኒሷቡ የወርቅ ኒሷብ ማለትም 20 ወቄት ውይም 85 ግራም ነው ያሉ አሉ። ሶስተኛ:– መነሻው መጠን ከወርቅና ከብር መነሻ ተመኖች ዝቅ ያለው ነው ያሉ አሉ። ከሶስቱ ሃሳቦች ውስጥ ሶስተኛው ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ በርካታ ዑለማዎች ደምድመዋል። መነሻቸውም 1ኛ፦ ድሃዎቹን የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋል። 2ኛ፦ ለዘካ አውጪውም ከውዝግብ ቀጠና ለመውጣት፣ ከተጠያቂነት ስጋት ለመትረፍ ይበልጥ ሰላማዊ ነው። 3ኛ፦ የመጀምሪያዎቹን ሁለት አቋሞች ያንፀባረቁ ምሁራን የሚያቀርቧቸውን መርጃዎችና ትንታኔዎች አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የሚያቀራርበው ይሄኛው ነው። 4ኛ፦ ለዚህ የወረቀት መገበያያ ኖት የዘካ ተመን ከወርቅና ከብር (ሲልቨር) አንዱን መጠቀም ግድ ከሆነ ከሁለት አንዱ ቀድሞ የደረሰውን ኒሷብ በምን አሳማኝ መነሻ ልንዘለው እንችላለን? እንደሚታወቀው የብር (ሲልቨር) ኒሷብ ዛሬም በነብዩ ﷺ ዘመን ከነበረው አይቀየርም። ዛሬም እንደ ጥንቱ 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል። ይህ አቋም የሰዑዲያህ የታላላቅ ዑለማእ ምክር ቤት፣ የእውቀታዊ ምርምር ቋሚ ኮሚቴ (ለጅነተ ዳኢማህ)፣ በራቢጦተል ዓለመል ኢስላሚ ስር ያለው ቀራረል መጅመዒል ፊቅሂይ እና የሌሎችም ምርጫ ነው። ወቅታዊ የወርቅና የብር ዋጋ
```````````
ሰሞኑን ለማጣራት እንደሞከርኩት ወቅታዊ የወርቅ ዋጋ የሚሸጥበት በግራም ባለ 21 ካራት 3,000 ባለ 18 ካራት ደግሞ 2,600 ብር ነው። የብር መሸጫ ዋጋ ደግሞ በብር 100 ብር ነው። ስለዚህ [ሀ] የወርቅ ዘካ ኒሷብ የሆነውን 20 ዲናር (85 ግራም) በወቅቱ የ21 ካራት ዋጋ 3,000 ብር ስናባዛው 255,000 ብር ሲሆን [ለ] የብር ዘካ ኒሷብ ደግሞ 200 ዲርሃም (595 ግራም) በወቅቱ ዋጋ 100 ብር ሲባዛ 59,500 ብር ይሆናል። ስለዚህ ከሁለቱ ኒሷቦች የብሩ ስለሚያንስ ከላይ በቀረበው 3ኛው አቋም መሰረት ይህንን መጠን 59,500 መነሻ እናደርጋለን ማለት ነው። እናም ይህና ከዚህ በላይ መጠን ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል ማለት ነው። ስለሆነም ለዘካ መጠን የደረሰ ገንዘብ ኖሮት አመት ከቆየ የገንዘቡን የ1/10ኛውን እሩብ ማለትም 2.5% ዘካ ያወጣል ማለት ነው። ስሌቱን ግልፅ ለማድረግ ጥቂት ምሳሌዎችን ልስጥ፦ 1– አመት የዞረ 300,000 ብር ያለው ሰው የ 300,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 300,000 x 0.025=7,500 ብር 2– አመት የዞረ 450,000 ብር ያለው ሰው የ 450,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 450,000 x 0.025=11,250 ብር 3– አመት የዞረ 5 ሚሊዮን ብር ያለው ሰው የ 5,000,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 5,000,000 x 0.025=125,000 ብር ይሆናል ማለት ነው። (ረመዳን 15/1442፣ ሚያዚያ 20/ 2013) https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/Tawihd/2032 https://t.me/joinchat/VORMo-ySDAH3s4Pi
Show all...
ጥቂት ነጥቦች፣ ለዒልም ፈላጊዎች ~~ መቼም የዒልም አንገብጋቢነት ለማናችንም የሚሰወር አይደለም። በተለይም በዚህ ጅህልና በተንሰራፋበት፣ ውዝግብ በነገሰበት፣ ሺርክና ቢድዐ በተስፋፋበት ዘመን የእውቀት አስፈላጊነት ለማንም አይሰወርም። ሰው ሁሉ ማወቅን ይመኛል። ነገር ግን እውቀት በትጋት እንጂ በምኞት አይገኝም። ምኞታችንን እውን ለማድረግ እንቅፋቶች ቢበዙብንም የምንችለውን እናድርግ። በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጥቂት ማለት ወደድኩኝ። 1. መማርን አትሰልች፡- ቁጭ ብለህ ኪታብ ተማር። ዒልምን ለመቅሰም ቀዳሚው መንገድ ከሚያስተምር ብቁ ሰው ዘንድ መቅራት ነው። ባይሆን የሚያስተምርህ ሰው በእውቀቱ ብቁ፣ በአካሄዱ ጤነኛ መሆን አለበት። “ይሄ እውቀት ዲን ነው። ዲናችሁን ከማን እንደምትወስዱ አስተውሉ” ይላሉ ኢብኑ ሲሪን ረሒመሁላህ። - ባይሆን ቅደም ተከተል ጠብቅ። ያላቅምህ ዘለህ ከፍ ያለ ኪታብ አትጀምር። አቅምህን አገናዝበህ ከስር ጀምረህ ተማር። - ባይሆን ስትቀራ የለብ ለብ ሳይሆን አድምተህ ቅራ። “ይህን ኪታብ ጨርሻለሁ” ለማለት ሳይሆን በኢኽላስ ቅራ። ለሌሎች ለማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ ቅራ። የቀራሀውን ሙራጀዐ (ክለሳ) ማድረግ ይልመድብህ። የዛሬው ኪታብ በሚገባ ከተያዘ በቀጣይ የምትማረው ኪታብ ክብደት በብዙ ይቀንሳል። ሙሉ በሙሉ አዲስ አይሆንብህም። አያያዝህ ለብ ለብ ከሆነ ግን ኢኽላስህን ታጣለህ። ከሰው ዘንድ ታፍራለህ። ጊዜህንና ልፋትህን ታባክናለህ። 2. አዳምጥ፡- ቁጭ ብለህ የምትማርበት በአቋሙ ጤነኛ፣ በእውቀቱ ብቁ ሰው ካላገኘህ እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ። ዘመናችን ዒልም ለሚፈልግ ሰው መንገዶቹ የገሩበት ዘመን ነው። የታላላቅ ዑለማዎችን ትምህርቶች ከቤትህ ቁጭ ብለህ እያዳመጥክ መከታተል ትችላለህ። ዐረብኛው የሚቸግርህ ከሆነ የምታምናቸውን ኡስታዞች ትምህርት በተገራልህ ቋንቋ ቤትህ ሆነህ በድምፅ መከታተል ትችላለህ። ስለዚህ በቴሌግራም፣ በዋትሳፕ፣ … ወይም ከጓደኛ በመቀባበል ወጥረህ ተማር። ሪኮርድ መከታተልን የሚነቅፉ ሰዎች ሊገጥሙህ ይችላሉ። “እርሱኮ ሪኮርድ እንጂ ሸይኽ የለውም” ሊሉህ ይችላሉ። ለእንዲህ አይነት ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ከስሜቱ ጋር ያልገጠምክለት ሰው አቃቂር ማውጣቱትን አያቆምም። የውንጀላው መነሻ በአመዛኙ አካሄድህ ከአካሄዳቸው አለመግጠሙ ነው። የነሱን ሰዎች በጭፍን እንድትከተል ለሚሹ አካላት ቅንጣት ታክል ቦታ አትስጣቸው። በሽተኛ ወይም ብቁ ያልሆነ ሰው ዘንድ ተቀምጠህ ከምትማር ያለ ጥርጥር ሁነኛ የሪኮርድ ደርሶችን ብትከታተል ይመረጣል። 3. አንብብ፡- ኪታቦችን አንብብ። ሹሩሓትን አገላብጥ። ፈታዋዎችን ተመልከት። ካለህ በቀጥታ ኪታቦችን ተጠቀም። ከሌለህ መክተበተ ሻሚላን ተጠቀም። እንዲያውም መክተበተ ሻሚላ በዚህ ዘመን ትልቅ ኒዕማ ነው። አጠቃቀሙን ቻልበት። ከዚህ የተረፈውን ኢንተርኔት ተጠቀም። ጎግልን ጎልጉል። ፒዲኤፍ አውርድ። በዚህ ዘመን ጦለበተል ዒልም ሆኖ አነሰም በዛ እነዚህን የማይጠቀም ለማግኘት ይከብዳል። በነዚህ ሰበቦች መጠቀምህን ሊያጣጥል የሚሞክር ካለ እራሱን በከንቱ የሚቆልል ግብዝ ነው። በተቻለ መጠን ንባብ ላይ ብቻ ጥገኛ አትሁን። ስለዚህ ቀጥታ መማር ስትችል ንባብ ላይ ብቻ አትንጠልጠል። ቁጭ ብሎ መማር ከተገኘ “ማር ሽጠው ምን ይበሉ?!” ባይሆን ደርስህን እየተከታተልክ ከዚያም ንባብህን እንደማዳበሪያ ተጠቀመው። ልብ በል! በንባብ ዒልም መቅሰምህን የሚነቅፍ ይገጥምሃል። እርግጥ ነው ንባብ ቁጭ ብሎ እንደመማር አይደለም። ይሄ ተጨባጭ ሐቅ ከመሆኑም ባለፈ ዑለማዎች የሚያስረግጡትም እውነት ነው። ነገር ግን የዑለማዎቹ ሃሳብ “አታንብቡ” ለማለት አይደለም። ይህ ቢሆንማ ለምን ኪታብ ይፃፋል? ከንባብ የተኳረፉ ወይም ልብ ወለድ የሚያሳድዱ፣ በእንቶ ፈንቶ የተጠመዱ ሰዎች ንባብህን ስለተቹ ጆሮ አትስጣቸው። የማውቃቸው ተግባራዊ ምሳሌዎች ስላሉኝ ነው ይህን መጥቀሴ። እንዲያውም በንባብ እውቀትን የሚቀስሙ ሰዎችን የሚያጣጥሉ አካላትን ታዘብማ። “እኛ ቀጥታ ቀርተናል” የሚል ጉራ ከመንፋት በዘለለ ቁጭ ብለው በስርአት ሲማሩ አታያቸውም። ባይሆን የምታነበውን እያስተዋልክ። ጤነኛ ስራዎችን እየመረጥክ። የበሽተኞችን ስራ በመከታተላቸው የተነሳ ስንቶች አፈንጋጭ አስተሳሰብ ላይ ወድቀዋል?! 4. ተግባር አይነተኛ መገለጫህ ይሁን፡- የምንማረው ለመስራት ነው። ከዚያም ባለፈ እውቀታችንን ለማስረፅ ከሚጠቅሙን ሁነኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ባወቅነው መስራት ነው። የማይተገበር እውቀት በቀላሉ ይረሳል። ቢኖርስ ምን ሊረባ? ስለዚህ እውቀትህን በተግባር አጅበው። በብዙ መልኩ ታተርፍበታለህ። 5. የተማርከውን አስተምር፡- እውቀትን ከሚያሰርፁ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ማስተማር ነው። በማስተማር ከተማሪዎች በበለጠ የሚጠቀሙት አስተማሪዎች ናቸው። በተግባር ጀርበው። የመማር አንዱ አላማም አውቆ ማሳወቅ ነው። ስለዚህ ያወቅከውን አካፍል። ቁርኣን ከቀራህ አስቀራ። ከዚያ ያለፈ አቅም ካለህ በደርስ፣ በሙሓዶራት፣ በፅህፈት፣… አስተምር። ታገል። ያለህን ታዳብራለህ። ክፍተትህን ለመመልከት እድሉን ታገኛለህ። ለተሻለ ትነሳሳለህ። በሐቅ ላይ ጂሃድ ታደርጋለህ። የልፋትን፣ የማስተማርን ጣእም ታጣጥማለህ። 6. ከጭፍን ተከታይነት ውጣ:— ዑለማዎችን ውደድ። በእውቀታቸው፣ በግንዛቤያቸው ታገዝ። ባይሆን በስሜት መርጠህ አትግፋ፣ በጭፍን መርጠህ አትከተል። በመላው ዓለም እጅግ በርካታ የሱና ዑለማዎች እንዳሉ እየታወቀ አንተ ከሸይኽ ፉላን ውጭ ዓሊም የሌለ የሚያስመስል ሁኔታ እንዳይኖርህ ተጠንቀቅ። ሰለፊ የሆንከው ቁርኣንና ሐዲሥን በቀደምቶች ግንዛቤ ልትከተል፣ ከዑለማዎች ትንታኔ ውስጥ ከስሜት ነፃ ሆነህ ሚዛን የሚደፋውን ልታስቀድም እንጂ የሌሎችን ዑለማዎች ሃሳብ ቸል በማለት አንድ ዓሊም ላይ ተገድበህ የወደደውን ልትወድ፣ የጠላውን ልትጠላ፣ በሱ ቀጭን መስመር ላይ ተገድበህ ወላእና በራእ ልትቋጥር አይደለም። መቼስ አቡ ሐኒፋን፣ ማሊክን፣ ሻፊዒይን፣ አሕመድን በጭፍን መከተል ተወግዞ አልባኒን፣ ኢብኑ ባዝን፣ ዐባድን፣ ፈውዛንን፣… በጭፍን መከተል እንደማይቻል አይሰወርህም። ልክ እንዲሁ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊን በጭፍን አትከተል። “መዳኺላ” እያሉ ለሚያጠለሹ አካላት ሰበብ እንዳትሆን ተጠንቀቅ። ዑበይድ አልጃቢሪን፣ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲን፣… በጭፍን መከተልም የተለየ ብይን እንደሌለው አይጠፋህም። ልብ በል! የተቅሊድ ቡላና ዳለቻ የለም። ያለበለዚያ የሐጁሪን ጭፍን ተከታዮች አንድ ጥፋት እየደገምክ እንደሆነ እወቅ። 7. ሰፊውን ህዝብ አስቀድም:— መቼም ህዝባችን ያለበትን ሰፊ የግንዛቤ ክፍተት አታጣውም። ይህ ከሆነ ወንድሜ ሆይ! ከራስህ ጥቅም ይልቅ የህዝብን ጥቅም አስቀድም። በዱንያህ ልትቸገር፣ ከጎንህ የሚቆም አጋር ልታጣ ትችላለህ። ቢሆንም ለዘመናት የደከምክበትን ሸሪዐዊ እውቀት እንደዋዛ ገሸሽ አድርገህ ዱንያ ውስጥ አትስመጥ። በተማርከው ወገንህን ለማገልገል የምትችለውን ሁሉ አድርግ። በዒልም ተቋማት ውስጥ አመታትን አሳልፈው በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ የሌላቸውን ወንድሞች ማየት ያሳዝናል። https://t.me/Tawihd/1888ጠ
Show all...
♨️በኢስላም በሱና በሰለፎች ጎዳና መሞት ትልቅ ክብር ነዉ‼️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 💢አለህ በቁርዓኑ ዉስጥ በተለያዩ ቦታዎች ትክክለኛ ሙስሊሞች ኢንዲንሆን ና በኢስላምም ኢንዲኒሞት ያዘናል يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍۢ ۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ)(الحشر - 18) ♨️ኢናንተ ያመናቹህ ሰዎች ሆይ አለህን ፊሩ ነፍስ ለነገዉ አለም ያዘጋጀችዉን ትመልከት አለህን ፊሩ አለህ በሚሰሩት ሁሉ ዉስጠ ምስጥር አዋቂ ነዉ (አል-ሀሽር "18") ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ (يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ‎) (آل عمران - 102)‎ 💢ኢናንተ ያመናቹህ ሰዎች ሆይ አለህን ሚገባዉ ፊርሃት ፊሩት ኢናንተ ሙስሊም ሆናቹህ በቀር አትሙቱ (ኣሉ-ዒምራን "102") 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِۦمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ‎( (البقرة - 132) ♨️በተዉሂዱዋ ንግግር ኢብራሂም ና የዕቁብ ሊጆቻቸዉን መክረዋሉ ኢንዲህም ኣሉ ልጆቼ ሆይ አለህ ቀናዉን ዲን መርጦላቹዋል ኢናንተ ሙስሊም ሆናቹህ በቀር አትሙቱ (አል-በቀረ "132") 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ♨️በሱና መሞት ትልቅ ከራማ ነዉ ወንድሜ ሆይ ሱናን አጥብቀህ ያዝ በሱናም ሙት ትልቅ ክብር ታገኛለህ‼️ ✍ قـال الإمـام عبدالله إبن الـمبارك رحمـه الله تعـالى : 📝አብደሏህ ኢብኑል ሙባረክ ኢንዲ ኣሉ « إعلـم أني أرى أن الـموت الـيوم كرامـة لـكل مسلـم لـقي اللهَ على الـسنة ، فـإنّا للهِ وإنّا إليـه راجعـون ، 💢ኢወቅ ኢኔ በዛሬ ግዜ ለሁሉም ሙስሊም አለህን በነቢዩ ﷺ ሱና መገናኘት ትልቅ ክብር ኢንደሆነ ኣያለሁ አኛ የአለህ ነን ወደ አለህም ተመላሾች ነን •- فـإلى الله نشكـو وحشتنا ، •- وذهـاب الأخـوان ، •- وقلـّة الأعـوان ، وظهـور الـبدع •- وإلى الله نشكـو عظيـم مـا حلّ بهذه الأمـة من ذهاب الـعلماء وأهـل الـسنة ، وظهـور الـبدع » ♨️ብቸኛነታችንን ና የሱና ወንዲሞችን መሞት የአጋዦች ማነስ የቢድዓ ግልፅ መዉጣት ወደ አለህ ኢናቀርባለን, ኢንዲዉም ወደ አለህ ኢናቀርባለን በዚህች ኡመት የሰፈረዉ አደጋ ግዝፈት ከአህሉ ሱና የሆኑት ኡለሞች መሞት የቢድዓ ግልፅ መዉጣት‼️ 📙[ البدع "لإبن وضّاح"(صـ٨٤) ] 📙[ الإعتصـام"للشاطبي"(صـ٨٦)] 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ⚠️ልብህን ክፍት አድርገህ አስተንትን አብደሏህ ኢብኑል ሙባረክ በሱና ሆኖ የሞተን ሰዉ ሞቱን ከራማ ነዉ ያሉት በሳቸዉ ግዜ ዱሮ በታቢዕዮች ዘመን ነዉ። ታዳ ዛሬ በኛ ግዜ ሸር በበዛበት ፊትና በረቀቀበት ባጥል በነገሰበት ግዜ በሱና መሞት ሚን ይመስልሃል⁉️ ♨️ኣሁንም ልብ በል ቢድዓ የበላይ የሆነበት ያሉት በአብደሏህ ኢብኑል ሙባረክ ግዜ ያኔ በታቢዕዮች ዘመን ነዉ። ታዳ ዛሬ በኛ ግዜ የቢድዓ መዕበል በበዛበት ግዜ ቢድዓዋን ሚያነግሱና ባንዲራዋን ሚያዉለበልቡ ሰዎች በበዙበት ግዜ የቢድዓ ግልፅ መዉጣት ሚን ይመስልሃል⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 💢አለህ መጨረሻችንን ያሳምርልን ሞታችን በሱና ያድርግልን ቢድዓንም ሰባብሮ ሚያጠፋት ኣሊም ና የሀገር መሪ ይስጣን🤲 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ✍Abubekir Ibnu Selman https://t.me/Tawihd/1853
Show all...
ተውሂድ የነብያቶች ሁሉ ጥር ነው

👉 የሻዕባን ግማሽ አላህ ለነብዩ ኡማ ሙሉ የሆነ ዲን ሰጥቷል የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - ዲኑ ሙሉ ሳይሆን ወደ አኼራ አልሄዱም :: በመሆኑም ዲናችን ሙሉ ነው የማንም ሰው የአእምሮ ጭማቂ አያስፈልገውም እየአንዳንዱ ሙስሊም ነብዩን መከተል ነው ያለበት :: ለዚህ ነው ነብዩ በዚህ ዲን ላይ ከርሱ ያልሆነን ነገር አምጥቶ የጨመረ ስራው በራሱ ላይ ተመላሽ ነው ያሉት :: ከእነዚህ በዲን ላይ ከመጡ አዳዲስ ፈጠራዎች አንዱ የሻዕባን ግማሽን ማክበር ነው :: የሻዕባን ግማሽ ቀኑን በፆም ለሊቱን በሶላት ነጥሎ ዒባዳ ማድረግ ምንም አስል የለውም :: ለሊቱን በሶላት ማሳለፍን አስመልክቶ ከታቢዒን ዑለማዎች የተገኘ ሲሆን ከፊሎቹ በጀማዓ መስገድ ይወደዳል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በጀማዓ አይወደድም በነጠላ ነው ያሉ አሉ :: ይህ ተግባር ከነብዩም ይሁን ከሶሐቦች አልተገኘም ታላላቅ ሊቃውንቶች እንዳረጋገጡት :: የግማሹን ለሊት አስመልክቶ አላህ ከሙሽሪኮችና ዝምድና ከቆረጡ ወይም በመካከላቸው ( የግል ) ጥል ካለባለባቸው በስተቀር ምህረት ይሰጣል የሚል ሐዲስ አለ ደረጃው ሐሰን ነው የሚሉ ዑለሞች አሉ ይህ ማለት ሐዲሱ ሶሒህ ቢሆን እንኳን ቀኑን በፆም ለሊቱን በሶላት መለየት ይቻላል ማለት አይደለም :: የዛን ቀን ለሊት ሶላትን አስመልክቶ የመጡ ሐዲሶች መውዱዕ ናቸው ይላሉ ሙሐቂቆች ከላይ የጠቀስናቸው የታቢዒን ዑለሞች የመጣው አሰር ሶሒህ ነው ብለው ሊሆን ይችላል ነገር ግን እንደነ ኢብኑ ረጀብ አል ሐንበሊይ ኢማሙ አንነወዊ አል ሐፊዙል ዒራቂ ኢማሙ አሽሸውካኒ እና ሌሎችም ምንም ለመረጃነት የሚሆን ሐዲስ እንደሌለ አረጋግጠዋል :: በመሆኑም ለዲናች ጥንቃቄ ሲባል የሚያጠራጥርን ነገር መራቅ አማራጭ የለውም ሽኽ ኢብኑ ባዝ ይህን መስአላ በሰፊው ካብራሩና ቅድም ያልናቸውን አቅዋሎች ከዘረዘሩ በኀላ…

በአላህ ስም *🍃 4ቱን እዝነትህን አትንፈጋቸው* ① ሚስትህን ② ልጆችህን ③ ቤተሰብህንና ④ ጓደኞችህን *🍃 4 ነገሮችን ቀንስ* ① እንቅልፍን ② ምግብን ③ መሰላቸትንና ④ ንግግርን *🍃 4ቱ ላይ አትጨክንባቸው* ① የቲም ላይ ② ሚስኪን ላይ ③ ድሃ ላይና ④ ህመምተኛ ላይ *🍃 4 ሰዎችን ቅረባቸው* ① ሙኽሊስ የሆነ ሰው ② ቃሉን ጠባቂ ③ አዛኝንና ④ ታማኝን *🍃 4 ሰዎችን ራቃቸው* ① ጃሂልን ② ተከራካሪን ③ ቂልንና ④ ባዶን *🍃 4 ሰዎችን ጓደኛ* አታድርጋቸው ① ውሸታምን ② ሌባን ③ ምቀኛንና ④ ራስወዳድን *🍃 4 ነገሮችን አትቁረጣቸው* ① ሰላት ② ቁርአን ③ ዚክርንና ④ ዝምድናን *🍃 በ4ቱ ተዋብባቸው* ① በትእግስት ② በቻይነት ③ በእውቀትና ④ በቅንነት *🍃 ከ4 ነገሮች በአላህ* ተጠበቅ ① ከትካዜ ② ከሀዘን ③ ከድብርትና ④ ከስስት *2, ፊትህ እንዲበራ ትፈልጋለህ ?* ®= የሌሊት ሶላት አደራ ፡፡ 3, ጤና ትፈልጋለህ ? _®= ፆምን አጥብቀህ ያዝ ፡፡_ _4, ከጭንቅ ለመዉጣት ትፈልጋለህ ?_ _እሥቲግፋርን እንዳትለቅ ፡፡_ _5, ትካዜን ማሥወገድ ትፈልጋለህ ፡፡_ _ዱአን ሙጭጭ አድርገህ ያዝ ፡፡_ _6, የህይወትን አድካሚ ችግሮች ለማሥወገድ ትፈልጋለህ ?_ _®= "ላሀወላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ማለት አብዛ ፡፡_ _7, በረካ ትፈልጋለህ ?_ _®= በነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ላይ ሠለዋት አዉርድ ፡፡_ _8, ዘና ማለት ትፈልጋለህ_ ? _®= ቁርአንን ረጋ ብለህ በማሥተንተን አንብብ ፡፡_ _9, ያለ ድካም አጅር ትፈልጋለህ ?_ አንብበህ ሥትጨርሥ ለሌሎች ሼር አድርግ. https://t.me/eslamwiyewkt
Show all...
👉 ቀኑ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ፆም አንዳንድ ሀገሮች በክረምትና በጋ ቀንና ለሊታቸው ይለያያል ቀኑ 21 ሰኣት ሆኖ ለሊታቸው 3 ሰኣት የሆኑ አሉ አንዳንዶች ረዝመቱ ከዚህ ቢያንስም ግን ከለሊቱ በጣም ይለያያል ሌሎች ደግሞ 6 ወር ቀን 6 ወር ለሊት የሚሆኑባቸው አሉ እነዚህን ሀገሮች በተመለከተ የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ የሚከተለውን ፈትዋ ሰጥቷል ቀኑ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ላይ የሚኖሩ ሙስሊሞች ፈጅር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ፀሀይ እስከ ምትገባ መፆም አለባቸው አንድ ሰው ፆሙ ከብዶት ከአቅሙ በላይ ከሆነ አፍጥሮ በሌላ ጊዜ ቀዳእ ያወጣል ለሊቱ ረዝሞ ቀኑ ቢያጥርም ያው ነው በቀኑ ልክ መፆም ለ6 ወር ቀኑና ረሊቱ የሚረዝምባቸው ሀገሮች ሙስሊምቹ በ24 ሰኣት እያሰቡ ሶላታቸውን ማለትም በ24 ሰኣት ውስጥ አምስት ጊዜ መስገድ ይኖርባቸዋል እያንዳንዱ ሶላት ጊዜውን ጠብቆ ለመስገድ ከተቻለ ቅርብ ሆነው ፀሀይ እየወጣ ከሚገባባቸው ሀገሮች በመውሰድ ወደ ሰኣት ቀይሮ መወሰን ፆሙንም በተመለከተ እንደዚሁ የፈጅር መውጫና የፀሀይ መግቢያ ጊዜውን በመወሰን መፆምና ማፍጠር አለባቸው የሚል ነው :: http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ከተውሒድ አርማዎች.pdf1.97 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.