en
Feedback
የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ⚽️ HFF

የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ⚽️ HFF

Open in Telegram

It is our channel to discuss and provide information on the development of football in the Harari region

Show more
318
Subscribers
+124 hours
+47 days
+1830 days
Posts Archive
የሐረሪ ክልል የ2016 ዓ/ም የትምህርት ቤቶች እግር ኳስ ውድድር ግንቦት 2/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ በኢማም አህመድ ስቴዲየም በድምቀት የተጀመረ ሲሆን ውድድሩም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የሚሳተፉበት ይሆና፤፤

በሐርሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የ2016 ዓ/ም የ1ኛ ሊግ የእግር ኳስ ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ። ፌዴሬሽኑ ለተከታታይ 4 ወራት በ10 ክለቦች መካከል #በዙር #በጥሎ ማለፍ እና #በአሸናፊዎች አሸናፊ የውድድር መርሀ ግብር ውድድር ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን፡- በዚህም መስረት :- የዙር ውድድር 1ኛ ሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ የ30,000.00 ብር፣ የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሽላሚ:: የዙር ውድድር 2 ተኛ ፈዲስ ግብርና ምርምር የ 20,000.00 ብር እና የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ:: የዙር ውድድር 3 ተኛ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የ10,000.00 ብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ:: የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ሐኮም ወረዳ የ20,000.00 ብር እና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ፡- የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ የዙር እና የጥሎ ማለፍ ውድድሩን በአሸናፊነት ማጠናቀቁን ተከትሎ በዙር ውድድር 2ተኛ በመሆን ካጠናቀቀው የፍዲስ ግብርና ምርምር እግር ኳስ ክለብ ጋር የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ የተገናኙ ሲሆን የፈዲስ ግብርና እግር ኳስ ክለብ የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከትሎ 30,000.00 ብር እና ዋንጫ ተሽላሚ ሆኗል:: በተጨማሪም የውድድሩ ኮከቦች የተሸለሙ እና የተበረታቱ ሲሆን:- ኮከብ ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ዳዊት ኮከብ ረዳት ዳኛ ገላዬ ገበየው ኮከብ ተጫዋች ዘላለም ዘፈኑ /ከሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ ኮከብ ግብ አግቢ አብዱላሂ አህመድ / ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሰላዲን መኩ /ከሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ ኮከብ አሰልጣኝ ካሳ ሙላት /ከሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ተሸላሚ ሲሆን በውድድሩ ላይ ውጤት ላስመዘገብ ቡድኖች ፣ ተጫዋቾች እና በውድድሩ ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት በዕለቱ በክብር እንግድነት በተገኙት ክብር አቶ ሙኽታር ሳሊህ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር እንዲሁም የድሬዳዋ መስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጉሌድ መሐመድ አና የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ፈትሒ አብዱሰመድ የማበረታቻ ሽልማት የተበርከተላቸው ሲሆን በኘሮግራሙ ላይም ሌሎች የክልሉ አመራሮች እንዲሁም የክልሉ ማህበረሰቦች በመገኘት ውድድሩን ታድመዋል:: ምስጋና ለሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ለሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለሐረሪ ክልል ብዙሀን መግናኛ ኤጀንሲ ለሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቃል ፒክቸርስ እንዲሁም ለ2016 ዓ/ም የ1ኛ ሊግ እግር ኳስ ውድድር ተሳታፊ ክለቦች በሙሉ በሐረሪ እግር ኳስ ስፖርት ቤተሰብ ስም ፌዴሬሽኑ ላቅ ያለ ምስጋና የቀርባል:: ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ እግር ኳስ ውድድር የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ቅዳሜ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ፍፃሜውን ያገኛል፡፡ በዚህ መሠረት የሐኪም ወ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ እግር ኳስ ውድድር የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ቅዳሜ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ፍፃሜውን ያገኛል፡፡ በዚህ መሠረት የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ክለብ የዙር እና የጥሎ ማለፍ ውድድሩን በአሸናፊነት ማጠናቀቁን ተከትሎ በዙር ውድድር 2ተኛ በመሆን ካጠናቀቀው የፍዲስ ግብርና ምርምር እግር ኳስ ክለብ ጋር የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታውን ያካሂዳል፡፡ለተጋጣሚ ቡድኖች መልካም ዕድል🙏🙏🙏

በክልላችን የስፖርት ታሪክ ባለውለታ እና እጅግ ስመ-ጥር ስፖርተኞችን ካፈሩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች አንዱ የሆነው የአሚር ሀቦባ ስቴዲየም ለሰልጠና እና ለውድድር ምቹ የማድርግ ስራ ተጀመረ፡-
+8
በክልላችን የስፖርት ታሪክ ባለውለታ እና እጅግ ስመ-ጥር ስፖርተኞችን ካፈሩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች አንዱ የሆነው የአሚር ሀቦባ ስቴዲየም ለሰልጠና እና ለውድድር ምቹ የማድርግ ስራ ተጀመረ፡-

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን :: ዒድ ሙባረክ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን :: ዒድ ሙባረክ!

የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ቅዳሜ መጋቢት 21/2016 ዓ/ም ጀጎል ከ ሐኪም ወረዳ የዋንጫ አሸናፊ ለመሆን ባካሄዱት ጨዋታ የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ቡድን
+1
የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ቅዳሜ መጋቢት 21/2016 ዓ/ም ጀጎል ከ ሐኪም ወረዳ የዋንጫ አሸናፊ ለመሆን ባካሄዱት ጨዋታ የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ቡድን የጀጎል እግር ኳስ ቡድንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከተሎ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል::

የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ዕሮብ መጋቢት 18/2016 ዓ/ም ሙርቲ ጉቱ ከ ሐኪም ወረዳ ለዋንጫ ለማለፍ ባካሄዱት ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1 ለ
የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ዕሮብ መጋቢት 18/2016 ዓ/ም ሙርቲ ጉቱ ከ ሐኪም ወረዳ ለዋንጫ ለማለፍ ባካሄዱት ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1 ለ 1 አቻ በመሆን ወደ መለያ ምት ያመሩ ሲሆን በመለያ ምቱሙ የሐኪም ወረዳ እግር ኳስ ቡድን ሙርቲ ጉቱ እግር ኳስ ቡድንን 7 ለ 6 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ::

የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ጀጎል ከ ሸንኮር ለዋንጫ ለማለፍ ባካሄዱት ጨዋታ የጀጎል እግር ኳስ ቡድንን 1 ለ 0 በሆነ
የ2016 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የ1ኛ ሊግ የጥሎ ማለፍ እግር ኳስ ውድድር ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ጀጎል ከ ሸንኮር ለዋንጫ ለማለፍ ባካሄዱት ጨዋታ የጀጎል እግር ኳስ ቡድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ::