cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋህዶ ክብሬ ናት

ማህተባችንን አንበጥስም። እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ነን። እውነተኛውን እንጀራ የማያስርበውን እንጀራ ያገኘንባት እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ይህንንም እናምናለን። "አንቺን ተስፋ ያደረጉ አያፍሩምና ከልጅሽ ዘንድ አማልጂን" "ክብር ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡"

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
203
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

፳፩. ሙሴ ከሞተ በኃላ እየመራ ወደ እስራኤል የወሰዳቸው ማን ነው?Anonymous voting
  • አሮን
  • ኢያሱ
  • ሳሙኤል
  • አፍኒን
0 votes
፳፪. ወንድሙን ሲጠየቅ የእርሱ ጠባቂ ነኝ ያለው ማን ነው?Anonymous voting
  • አቤል
  • ዘሩባቤል
  • ትዕማር
  • ቃየን
0 votes
#የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው☝ ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም #የመመኪያችን_ዘውድ_የንጽሕናችንም_መሰረት ያላት #ወላዲተ_አምላክ_ድንግል_ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ••●◉ ✞ ◉●•• 👉#ነቢየ_እግዚአብሔር_ኢሳይያስ_ድንግል_ትጸንሳለች_ወንድ_ልጅም_ትወልዳለች ኢሳ 7፥14 ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት #የወርቅ_ልብስ_ተጎናጽፋ_ንግሥቲቱ_በቀኝህ_ትቆማለች መዝ 44፥9 ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ #ፀሐይን_የተጎናጸፈች_ጨረቃን_የተጫማች_አስራ_ሁለት_የክዋክብት_አክሊል_በራሷ_ላይ_ያላት ራዕ 12፥1 ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ  እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡ ••●◉ ✞ ◉●•• #የድንግል_ማርያም_ልደት_በነቢያት_አንደበት ••●◉ ✞ ◉●•• #መሠረታቲሃ_ውስተ_አድባር_ቅዱሳን_መሠረቶችዋ_በተቀደሱ_ተራሮች_ናቸው፡፡መዝ 86፥1 ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ #መሠረታቲሃ_ውስተ_አድባር_ቅዱሳን_መሠረቶችዋ_በተቀደሱ_ተራሮች_ናቸው በማለት ትንቢት  ተናግሯል፡፡ #የተቀደሱ_ተራሮች ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ••●◉ ✞ ◉●•• 👉ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን9 #የእመቤታችን_ማርያም_ትውልዷ_ባባቷ_በኩል_ከንጉሡ_ከዳዊት_ወገን_ነው_በናቷም_በኩል_ከካህኑ_ከአሮን_ወገን_ነው_የአባቷ_ስም_ኢያቄም_ነው_የእናቷም_ስም_ሐና_ነው፡፡ብላ ታስተምራለች፡፡ ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት #ትወፅእ_በትር_እምሥርወ_ዕሴይ_ወየዐርግ_ጽጌ_እምኔሃ_ከዕሴይ_ሥር_በትር_ትወጣለች_አበባም_ከእርሷ_ይወጣል፡፡ኢሳ 11፥1 ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም #መልካሟ_ርግብ_ማርያም_ሆይ_ደስ_ይበልሽ_ከእሴይ_ሥር_የተገኘሽ_መዓዛሽ_ያማረ_አበባ_አንቺ_ነሽ በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡#በአባቶችሽ_ፈንታ_ልጆች_ተወለዱልሽ መዝ 131፥13) የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡ ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡሰሎሞን #ንዒ_እምሊባኖስ_መርዓት_ንዒ_እምሊባኖስ_ንዒወተወፅኢ_እምቅድመ_ሃይማኖት_እምርእሰ_ሳኔር_ወኤርሞን_አምግበበ_አናብስት_ወእምአድባረ_አናምርት_ሙሽራዬ_ሆይ_ከሊባኖስ_ከእኔ_ጋር_ነዪ_ከሊባኖስ_ከእኔ_ጋር_ነዪ_ከአማና_ራስ_ከሳኔር_ከኤርሞን_ራስ_ከአንበሶች_መኖሪያ_ከነብሮችም_ተራራ_ተመልከች መኃ 4፡፥8 በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ ••●◉ ✞ ◉●•• 👉የዚህ ትንቢት ምስጢርም #የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ  ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 👉ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ _እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ #የአናብስት_ልጅ_አልኩሽ_ሰሎሞን_እንዲህ_ሲል_እንደተናገረ፡- #ሙሽራዪት_ሆይ_ከሊባኖስ_ተራራ_ነዪ_ከአንበሶች_ጒድጓድ_ወጥተሽ_ነዪ_ከምርጥ_ነገድነት_የተነሣ_ከሚመካ_ወገን_የመወለድሽ_ዜና_እጅግ_ግሩም_ነው በማለት_አመስጥሮታል፡፡ ••●◉ ✞ ◉●•• 👉#እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ══════◄✣••✥••✣►══════ 👉ይቀጥላል............... ══════◄✣••✥••✣►══════ ✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨✝✨ 🙏እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅ🙏 #share #share #share #share ✍ፀሐፊ: የአብስራ ተስፋዬ 📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
Show all...
✝✝✝ እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ልደታ ለማርያም ድንግል "*+ ✝ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: ✝ " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " =>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: +ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: +እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8) =>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: +ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: +ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: +እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: +በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: +እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) +"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9) +እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- -ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,027 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: =>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ) 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቴክታና በጥሪቃ 4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር =>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጧም ሰው ተወለደ:: እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Show all...
ግንቦት 1/2014 🌿እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ኢያቄም እና ከቅድስት ሃና የተወለደችበት ቀን ነው። 🌿ቅዱስ ራጉኤል ለሄሮክ የጨረቃ እና የከዋክብትን ምስጢር የገለጠበት ቀን ነው።ራጉኤል ማለት እግዚአብሔር ሐያል ነው፤እግዚአብሔር ተበቃይ ነው;ማለት ነው። 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 @Amanuel_Amanuel
Show all...
❤️እናቴ❤️ 🌹የመጀመሪያዬ እሬስቱራንት == የእናቴ ጡት 🌹የመጀመሪያዬ ሽንት ቤት ==የእናቴ ልብሷ 🌹የመጀመሪያዬ ትምህርትቤት=የእናቴ ኩሽና 🌹የመጀመሪያዬ ዶክተር == እናቴ 🌹የመጀመሪያዬ ጓደኛዬ ===እናቴ 🌹የመጀመሪያዬ አልባሼ == እናቴ 🌹የመጀመሪያዬ መኪናዬ== የእናቴ ጀርባ 🌹የመጀመሪያዬ ጠበቃዬ== እናቴ እናቴ በህይወቴ ላደረግሽልኝ ነገር ሁሉ አመሰግንሻለሁ 🔰እረጅም እድሜ ለሁሉም እናቶች ለእናት 5 ልጅ መንከባከብ ቀላል ነው ግን 5 ልጅ 1 እናትን ውለታዋን ለመመለስ ከባድ ነው አቤት እናትነት ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም ። 🙌ለሁሉም እናቶች በአለም ላይ ላሉ ፈጣሪ እድሜና ጤና ያድላቹ ብርታቱን ያድልልን🙌 ካንቺ ያስቀድኝ እማ እናት አለሜ❤️❤️ 🎙የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm ••••••፨፨♥፨፨••••••• @Etelawyan 🇪🇹 ••••••፨፨♥፨፨•••••••
Show all...
ረባንም አልረባንም ወደዚች ምድር እኛን ለማምጣት የ 9 ወር ፅኑ መከራ ለተቋቋማችሁ የአለም እናቶች በሙሉ እንኳን ለእናቶች ቀን ደረሳችሁ ዛሬ የናንተ ነች 💙💙 🌹እናት ከፍጥረት ሁሉ ለምን እንደምትለይ ታውቃላችሁ?? እናት በሂወት ኖረችም አልኖረችም ተፅዕኖዋ በልብ ውስጥ ታትሞ ጊዜና ዘመን አያደበዝዘውም❤️ እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሰን😍 ክብር ለእናቶቻችን አምላክ እድሜያቸውን ያርዝምልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️ ይኑሩልን እኛ አንድንኖር ❤️❤️❤️❤️አብራችሁኝ ዋሉ ዛሬ ስለ እናቶች ክብር ስንዘምር ስንመሰክር ቀናችንን ውብ አድርገን እንውላለን የአብስራ ነኝ ፈጣሪ ለእናቶቻችን እሽግ እና ሽሽግ የሆነዉን ልዩ ስጦታ〰〰☺️ ፈጣሪ ይስጥልን ብያለሁ በፀሎት አንረሳሳ ✍ፀሐፊ: የአብስራ ተስፋዬ 📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
Show all...
Repost from RAMA
4 More join us👇 @Wintana_wb @Winaedit2 በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ በደም የገዛሀኝ ባለውለታዬ በቃዬል ጎዳና እንዳልጓዝ እርዳኝ በቀናው መንፈስህ ወደፅድቅህ ምራኝ https://t.me/joinchat/UuHwHi9qRPlrCOx0 ✝️✝️✝️
Show all...
#ምሬሃለው_በለኝ ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም/2/ መሃሪው መድሃኒዓለም ይቅር ባይ እንዳንተ የለም #አዝ በሃጢአት ድንኳኖች ይብቃ መቀመጤ የቀናውን መንፈስ አድሰው በውስጤ የምህረት አይኖችህ ይዩኝ በይቅርታ ስለ ድንግል ማርያም እስራቴን ፍታ /2/ #አዝ  ቸል በማለቴ የደምህን ዋጋ  ተመልሼ ገባሁ ከጥፋት መንጋጋ  ሰላሜ ደፍርሶ ተቅበዝባዥ ሆኛለሁ  ስለ እናትህ ብለህ ማረኝ እልሃለሁ  ስለ ድንግል ማርያም ማረኝ እልሃለሁ #አዝ በከንቱ መሻቴ ሥጋ ነፍሴን ቀብሮ አቅም አጥቻለሁ አጥንቴ ተሰብሮ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንድታደርገኝ ስለ ድንግል ማርያም ከሃጢአቴ አጠበኝ ስለ ድንግል ማርያም ምሬሃለሁ በለኝ #አዝ ከንፈሮቼን ከፍተህ ልቁም ለምስጋና አንተን የጋረደኝ ጣሪያ ይነሳና አልብሰኝ ፅድቅህን ይቅር መራቆቴ ስለ ድንግል ማርያም መልሰኝ ከቤቴ /2/ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 https://t.me/natanimyemazmurgroup https://t.me/natanimyemazmurgroup
Show all...