cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋህዶ ሃይማናኖቴ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ "እግዚአብሔር ልጆቹን ወደ ጽድቅ ተራራ ጠራቸው ፤ ሰብስቦም ስለ አምላክነቱም አስተማራቸው"፡፡ ወዶ እና ፈቅዶ እዚህ ቻናል ተሰብስበን እድንማማር የረዳን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነና የተከበረ ይሁን ለዘለዓለሙ #አሜን፡፡

Show more
Advertising posts
249
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጥር_10 #ጾመ_ገሃድ ጥር አስር በዚህች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና። እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው። በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ። በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ። የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው። መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው። ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 💚  •✥• @tewahdowochnen  •✥•💚 💛  •✥• @tewahdowochnen  •✥•💛 💖 •✥• @tewahdowochnen  •✥• 💖              ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧
Show all...
✨እነሆ አዲስና የሚያስደንቅ ምሥጢር! ጆሮዎቼ የእረኞችን ዝማሬ አስተጋቡ። ቀዝቀዝ ያለ ጣዕመ ዜማ አይደለም። ከፍ ብሎ የሚሰማ ሰማያዊ ዜማ እንጂ። መላእክት ይዘምራሉ ! የመላእክት አለቆች ድምጻቸውን በአንድ ያስማሙታል ኪሩቤል አጥንትን የሚያለመልም ምስጋናቸውን ያሰማሉ። ሱራፌል ክብሩን ያወድሳሉ።እግዚአብሔርን በምድር የሰውን ልጅንም በልእልና አይተውታልና ሁሉም በአንድነት ሆነው ይህንን በዓል ያከብራሉ። ልዑለ ባሕርይ የሆነው እርሱ እኛን ለማዳን ሲል እዚሁ ከታች አደረ ። ከታች የነበረውን ማንነታችንን በምሕረቱ ከፍ ከፍ አደረገው።
Show all...
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 🔴ሌላ ተወዳጅ መዝሙር ❤️ቅዱስ ገብርኤል መጥተህ አረጋጋን https://www.vidmateapp.com/subpub/yqh5/site?url=aHR0cHM6Ly93d3cueW91dHViZS5jb20vd2F0Y2g/dj1kVWNkc2RjQUxUWQ==&f=sy 🔥Trending video shared via VidMate🔥 🎉Best downloader for video and image on YouTube, WhatsApp status, Facebook, Instagram... 🎉Platform for FREE latest movies🎥🎥 👇Download VidMate Now!👇 https://www.vidmateapp.com/?subpub=sharing
Show all...

#እናት_አለኝ እናት አለኝ የምታብስ እንባ አያታለሁ ስወጣ ስገባ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ ራቁቴን ብቆምም አፍሬ ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት #አዝ ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ ራቁቴን ብቆምም አፍሬ ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት @zemeriwochu @Abalibanos333
Show all...
የኛ ዘመን ሰማዕትነት                            በሐሰተኛ ዓለም  እውነተኛ ሆኖ መገኝት ገንዘብ ከሰው አስበልጦ ከመውደድ ይልቅ  ሰውን ከገንዘብ አስበልጦ መውደድ መቻል                            ከማስመሰል ሕይወት ራስን ሆኖ መገኝት።                                  በጥላቻ ከአበደው ዓለም ጋር ከመተባበር  በፍቅር ለመኖር መስዋዕትነትን መክፈል                በቂም በቀል ከመኖር  ይልቅ የይቅርታ ሰው መሆን                                        ከግንፍልተኝነት ይልቅ ትዕግሰተኛ  መሆን መቻል  አስተዋይነት ራስን      መግዛት  በአጠቃላይ በዓለም እየኖሩ       ከዓለም ሐጢያአት መንጻት/መጠበቅ ይቻላል ጌታም ሐዋርያትን  ከዓለም ሐጢአት እንዲጠበቁ አስተምሯቸዋል  ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱ የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብ መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ  ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።1ኛ ዮሐ-መልዕክት ምዕ፡ 2 ቁ 15-16  ዓለም ደግሞ የራሷ የሆነውን ነው የምትወደው በሐጢአቷ የሚተባበራትን ነው የምትወደው  በማይመስሏት ላይ መከራ የምታጸናው ለዚህ ነው መከራው ግን ለክርስቲያኖች የሰማዕትነትን አክሊል አሰጥቷቸዋል  በፅኑ ተጋድሎ ውስጥም አልፎ ሰማዕትነትን ማግኝት ታላቅ ክብር ነው ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ እንዲህ እያለች ታስባቸዋለች ሰማዕታትም የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ ለተራበ አንበሳ ሲሠጡ ወደ እሣት ሲጣሉ ቆዳቸውን ገፈው ሲጎትቷዋቸው በመንኮራኩር ሲፈጯቸው በመጋዝ ሲሰነጥቋቸው ቁልቁል ሲሰቅሏቸው ከዚህ የበለጠ የተለያየ መከራ ሲያፀኑባቸው  እምነታቸው ፅኑ ስለሆነ ታግሰው ይህንን ዓለም ድል ነሱት  ሥራቸው ሲነገር ስማቸው ሲወደስ ለዘለዓለም ይኖራል              ይህንን የመሰለ እምነት ያስረከቡን አባቶች እያሉን    እኛ በዘመናችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መኖር አቅቶን ሕገ እግዚያአብሔርን መጠበቅ ሰማዕትነት ሆኖብናል  ለእኛ የከበደን ለእነዚህ ቅዱሳን ግን የየእለት እለት ሕይወታቸው የተመራበት መንገድ    ነው  እኛ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር ለምን አቃተን ብለን እራሳችንን ብንጠይቅ እግዚያአብሔርን መስለን መኖር ሲገባን ዓለምን መስለን እየኖርን ስለሆነ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ ያለው ይህንን ዓለም ድል ነስተን የሰማዕትነትን አክሊል እንድንቀዳጅ እንደ ፈቃዱ እንኑር ፈቃዱም የታወቀ ነው።             ወስብሐት ለእግዚያአብሔር           ወለወላዲቱ ድንግል        ወለመስቀሉ ክቡር                             ሰማዕትነት ታላቅና ክቡር  የሆነ,   በብዙ ተጋድሎ የሚገኝ
Show all...
ተዋህዶ ሃይማኖቴ ❤️❤️❤️❤️ ከ ስእለ አድህኖዋ ላይ ወዝ ሚወጣት የ እመቤታችን ድንቅ ተአምር እዩ 🙏 ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ  🥰🥰🥰🥰 በየካ አባዶ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ❤️❤️❤️ ታላቅ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም ድንቅ ተአምር የተዘጋጀ ጉባኤ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት እመቤታችን ድንግል ማርያም በነገው እለት ከበረከቷ እንካፈላለን ከ ግብፅ ሀገር የመጣችው ይህች የ እመቤታችን ስእል እምነታ ችንን እያጠነክር, ሃይማኖታችንን ሊመሰክር የ እግዚአብሔርን እፁብ ድንቅሥራ ልናይበት ድንቅ ሥራ እግዚአብሔር ሰርቶልናልና ደስ ይበላችሁ ❤️❤️❤️ 🥳🥳🥳🥳🥳🥳 አላየሁም አልሰማሁም የለም  የለም ይሄው ተናግረናል ይህ ድንቅ ይህ የእመቤታችን ከፊቷ ወዝ ሲወጣ በአይናችን ያሳየናል ይህ ድንቅ ተአምር ነው የስጋም የነፍስም  ደዌ እንፈወሳለን ያየነውን እንናገራለን የሰማነውንም እንመሰክራለን እግዚአብሔር ከእኛ ጎን ሆኖ ቅድም ዓለም የነበረው በ ቅዱሳን ዘመን የነበረው በእኛም ዘመን ይህን ሰርቷልና በእመቤታችን አማላጅነት ምታምኑ ሁላችሁ ኑ እዩና መስክሩ ዳስሱ እና ተፈወሱ ለምኑ እና አግኙ ኑ ልጆቼ ከጉልላቴ ከ ራሴ  ከንጉሴ ተአምር ላካፍልላቹ ሰማያዊ ተአምርን አይናችሁ ይይ  ተባረኩልኝ ልጆቼ ትለናለች ነገ 02/03/15 በ የካ አባዶ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን እንገናኝ ከ እዚቹ የ ገነት መሰላል እመቤታችን ወዝ ተቀብተን እንፈወሳለ ታላላቅ መርሀግብሮችን ዘርግታ ከ መአዛዋ ልትከፍለን እማምላክ ኑ ብላናለች አይቀርም 🙏🙏
Show all...
Repost from N/a