cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አርባ_ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ስብስብ

Advertising posts
505
Subscribers
+224 hours
+47 days
+1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጫት ዝግጅትና ጥንቅር/ አቡል ቡኻሪ ሰዒድ ሙሳ
Show all...
ፈገግ አድርጎኛል! እውነታውም ይሔው ነው። ~እኔም የምላችሁ ነገር ቢኖር…ተመርቃችሁ ስትወጡ፣መቀጠርን አታስቡ። የራሳችሁን ስራ ለመጀመር እውቀት ላይ ትኩረት አድርጉ።እንኳን ድግሪ ማስተርም አሁን ላይ አላገለገለም።በዘመድም አትመኩ። ከዚህ ባለፈ ደሞ ልክ እንደዚህ ልጁ ተመርቃችሁ ስትወጡ የተማራችሁትና ኢንዱስትሪው ዓለም ላይ ያለው ሥራ ላይገናኝ ስለሚችል ከመደበኛ ትምህርታችሁ ጎን ለጎን ብቁ የሚያደርጓችሁን ተግባር ተኮር አጫጭር ኮርሶች በኦንላይንም ሆነ የሚሰጡ ተቋማት ካሉ አፈላልጋችሁ ተማሩ። ዝም ብላችሁ ዲግሪ አለን ብላችሁ ከተኮፈሳችሁ፤ አሁን ላይ እንኳን ድግሪ ማስተር ያለውም ቅጥር እያሳደደ ነው። • ስለዚህ አብዛሃኛው ኮርስ በነፃ ኢንተርኔት ላይ ስላለ፤ አላማ አንግባችሁ በአጭር ጊዜ ለሥራ  ብቁ የሚያደርጓችሁን አጫጭር ኮርሶች ውሰዱ። በአሁኑ ወቅት ኢንዱስትሪው ላይ ተፈላጊ የሆኑ የዳታ ኢንጂነሪንግ ኮርሶችን፣ ከኮዲንግ/ፕሮግራሚንግ ጋር ተያያዥ የሆኑ መስኮችን፣ ከኤአይና አውቶሜሽን ጋር የተገናኙ ነገሮችን በደንብ ተማሩ። •«የተማረ ወድቆ አይወድቅም!» ይላልና ያገሬ ሰው ቀጥሉ። እውቀት በራሱ ሀብት ነው። =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
👍 1
ሟቹ "ጌታ!" ~ ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል። · * ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ። – "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት። · ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ። · ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው። * "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ። – "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ። · አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል። · * "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው። – "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት። * "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ። – "አዎ" አሉት። · ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:– "እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!" … የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው። … መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ። "ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው። · ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34። ---------- "ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29) · ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል። "አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30) · ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል። "ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው። #ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32) እያስተዋልክ ነው?! እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል። "በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33) ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ። "ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34) (ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 11/2011) የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 2 1
አል-ጁሙዓ‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍አሏሁ'መ ሶሊ ወሲሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሀመድ‼️ * «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.» || https://t.me/Arbaminchuniversitymuslimstudent
Show all...