cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

Show more
Advertising posts
9 043
Subscribers
+424 hours
+337 days
+21230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ሥላሴ የራሴ አክሊል ናቸው። ሥላሴ የአንጻረ ገጽታዬ ማማተቢያ ናቸው። ሥላሴ የዐይኖቼ ብርሃን ናቸው። ሥላሴ የጆሮዬ መስሚያ። ሥላሴ የጉንጮቼ ወዝ። ሥላሴ አፍ መክፈቻዬ ናቸው። ሥላሴ የከናፍሬን የአነጋገር አልጫነት የሚያጣፍጡ መለኮታዊ ጨው ናቸው።      ሥ ላ ሴ   የአንገቴ ማዕተብ ነውሥላሴ ከድካሜ ያፀናኛል ፣ ሥላሴ ኃይሌና መጠጊያዬ ነው። ሥላሴ መታመኛዬ ነው። ከእናቴ ማሕጸን ጀምሮ በሥላሴ ፀንቼ እኖራለሁ! ይህን ላደረገልኝ ለሥላሴ ምን ወሮታ እከፍላለሁ❓ በልዩ ችሎታው ለፈጠረኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። በቸርነቱ ለአሳደገኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። በመሐሪነቱ ጠብቆ እስከዚህች ሰዓት ለአደረሰኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። እንደ በደሌ ላልፈረደብኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለጌታዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለንጉሤ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለአምላኬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለአለቃዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። . . . በሥላሴነትህ እታመናለሁ - በሦስትነትህም እመካለሁ!🤲🤲🤲            📖 የዓርብ ሰይፈ ሥላሴ https://t.me/eotcy https://t.me/eotcy https://t.me/eotcy
Show all...
🙏 17 2
+++ የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት ++         አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ እንጅ የምፈጽም ባለመሆኔም ምክንያት በድቡሽት ላይ እንደተሠራ ቤት ሆኛለሁ። ጥልቀት በሌለው አኗኗር ላይ የተገነባው መንፈሳዊነቴ ጎርፍ በጎረፈ፣ ነፋስ ባለፈ ጊዜ የሚናወጥ ደካማ ሆኖብኛል። ዓለምን ለማሳለፍ ዳግመኛ መምጣትህን ባሰብሁ ጊዜ እደነግጣለሁ። ጻድቃን “አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና” እያሉ የምትመጣበትን ቀን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሴት በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ እኔ ግን አሁንም ለንስሐ ዕድሜ እንድትጨምርልኝ እለምናለሁ። በተራራው ስብከት ጊዜ ተገኝቼ ስታስተምር ባልሰማህም፤ በደብረ ታቦር በተገለጥህ ጊዜ ክብርህን ካዩት መካከል ባልሆንም፤ በደብረ ዘይት እጅህን ጭነህ ከሾምኻቸው ውስጥ ባልመደብም አንተ ግን ለእኔ ምሕረት ማድረግን አትሰለችም። ወደ አንተ ባልመጣ እንኳን በተኛሁበት መጥተህ “ልትድን ትወዳለህ?” ማለትህ አይቀርም። ከሰማይ የወረድህልኝ ሆይ! ኢያሱ ለእስራኤል ርስታቸውን እስኪያወርሳቸው ፀሐይን እንዳቆምህለት በምድር ላይ ያለን ኃጥአን ልጆችህ ሰማያዊት ርስትህን ሳንወርሳት ፀሐይ አትጥለቅብን፤ ዕድሜአችን አይለቅብን።  አሜን! ( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ) ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂ https://t.me/eotcy
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

23🙏 10
+ጊዝው ገና ነው+
አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከዕለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ።  አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ።  ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱም አይሠራም። ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ።  ሌላው ደግሞ ተነሳና፥ “እኔን ላከኝ። ፈጣሪም አለ፥ ገነትም አለ፥ ሲኦልም አለ፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ።” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል። ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ፥ ለማዘግየት ይፋጠናል። በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።” (1 ተሰ 2:18) ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል፥ ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል። እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም። ስለ ጸሎት ብታስብ፥ "አሁን ደክሞሃል። ጊዜው አይደለም። ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል። ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ። የምትጾምበት ጊዜ አይደለም፤ ሌላ ጊዜ ትጾማለህ።" ይልሃል። ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ፤ ጊዜው አይደለም፥ ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል። ንስሃ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ፥ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም። ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ፥ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል። 🟢🟡🔴 በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ፥ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) እንደሚል እናስታውስ። ለመዳናችን ቀጠሮ አንስጥ።
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

23🙏 4
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው @eotcy              @eotcy @eotcy              @eotcy @eotcy              @eotcy
Show all...
14🙏 7
ንስሐ ምንድን ነው? ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑ፣ መፀፀቱ፣ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው። በአጭሩ ንስሐ ማለት ትርጉሙ ይህ ሲሆን፤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበን ቀጥሎ የተጠቀሱትን ፍችዎች ያጠቃለለ ሆኖ እናገኘዋለን። ➙ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ሚልኪያስ 3፥7 ➙ ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው። 2 ቆሮንቶስ 6፥19 ➙ ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው። ሮሜ 13፥11 ➙ ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው። ኤፌሶን 5፥14 ➙ ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው። ሕዝቅኤል 36፥25-27 ➙ ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያቢሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ነው። ዮሐንስ 8፥34-36 ➙ ንስሐ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው። ምሳሌ 28 ፥13 ➙ ንስሐ ኃጢአትን ከተዉ በኋላ በፍጹም መልሶ አለመስራት ነው። https://t.me/eotcy ➙ ንስሐ ስለ አለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ፤ ያለፈውን የኃጢአት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው። ኢዩኤል 2፥12 ➙ ንስሐ ፍጹም የሆነ የሕይወት ለውጥ እንጂ ጊዜያዊ ስሜት አይደለም፤ ሮሜ 12፥2 ➙ ንስሐ ኃጢአትን ሲሠሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መሻት ነው። መዝሙር 73፥28 ➙ ንስሐ የአዕምሮ መታደስ ነው። ሮሜ 12፥2 ➙ ንስሐ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ማቴዎስ 25፥1-13 ➙ ንስሐ በቀራንዮ መስቀል ላይ እኛን ለማዳንና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የፈሰሰልንን የክርስቶስን ደም እንድናስብ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሃብት ነው። ➙ ንስሐ ከኃጢአት የሚያነጻ ሱራፌል ከመንበረ ሥላሴ የወሰዱት የእሳት ፍም ነው። ኢሳያስ 6፥4 https://t.me/eotcy ➙ ንስሐ ከሚመጣው የመጨረሻ መከራና ሃዘን መዳኛ ወይም ማምለጫ መንገድ ነው። ዮናስ 3፥10 ➙ ንስሐ እግዚአብሔር የሰውን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና ከኃጢአት ውጤት የሚያድንበት መሳርያ ነው። ➙ ንስሐ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋ የእግዚአብሔር እጅ ነው። መዝሙር 50/51 ➙ ንስሐ እግዚአብሔር ወደ ሰው የሚጣራውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ መመለስ ነው። ዮሐንስ 7፥51። ኤፈሶን 4፥30 ➙ ንስሐ ስለ አለፈው ኃጢአት ከመፀፀት የተነሳ የተሰበረ ልብ ነው። መዝሙር 50/51፥17 ➙ ንስሐ ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ተፀፅተው ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይታረቁ በብርቱ በሚጥረው ሰይጣን ላይ የተገኘ ድል ነው። መዝሙር 123/124፥ 6-7:: ወስብሃት ለእግዚአብሔር ! (የንስሐ ሕይወት) ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂ https://t.me/eotcy
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

19🙏 7💯 3😡 2👏 1
#ይህንን_ያውቃሉ የሦስቱ ዲያቆናት ምሳሌነት ምንድን ነው ? ቅዳሴ ላይ እንደሚታወቀው ልዑካኑ  ከሁለት እስከ ሃያ አራት ድርስ ሊደርሱ ይችላሉ አምስቱ ልዑካን  ማለት ሁለት ካህን ሦስት ዲያቆናት በአጠቃላይ የአምስቱ አማዕደ ምሥጢራት ምሳሌ ናቸው ሦስቱ ዲያቆናት የየራሳቸው ምሳሌነት አላቸው 1. የዋና ዲያቆን (ሠራዒ ) ይህ ዲያቆን የቅዱስ እስጢፋኖስ ምሳሌ ነው መጾር ወይም መስቀል ይዟ መቀደሱ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀበለውን ሰማዕትነት ለማሰብ ነው 2. ተጨማሪ (ንፍቅ ) ዲያቆን ይህ ዲያቆን ደግሞ መጥመቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ ነው ከፊት ከፊት እየቀደመ  ካህናቱን መምራቱ ሊቀ ካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፊት ቀድሞ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጥርጊያውን መንገድን የማዘጋጀቱ ይህ ዲያቆን መብራት ወይም ጠፋፍ የሚያዙ ከመስዋዕት ከማቅርብ አልፎ በዚህ ይመሰላል 3. ፍሬ ሰሞን (መጽሐፍ ገላጽ )   ይህ ዲያቆን የሐዋርያት አባቶቻችን ምሳሌ ነው እንዴት ቢሉ መጽሐፍ ይዞ በአራቱም አቅጣጫ ይዞራል ይህም ሐዋርያት በአራቱ አቅጣጫ ወንጌልን የመስበካቸው ምሳሌ ነው ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂ @eotcy @eotcy @eotcy
Show all...
🙏 20 17
ትዝብት
ልጅቷ ሥራ የላትም ፣ ከመኖሪያዋ አጠገብ ካለው የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዘወትር እየተገኘች ልመናዋ ሥራ ስጠኝ ብቻ ከሆነ ሰንብታለች፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር “እባክህን አምላኬ ውዬ የምገባበት ሥራ ስጠኝ” እያለች ትጸልያለች፡፡ አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ደርሳ ወደ ቤቷ ስትመለስ ከአንድ መሥሪያ ቤት አጠገብ ትደርስና የተለጠፈ የሥራ ማስታወቂያ አይታ ቆማ ማንበብ ትጀምራለች፡፡ የሥራው ዓይነት እና የትምህርቱ ደረጃ ሁሉ በዝርዝር ሰፍሯል፡፡ ሁሉም እሷ ልታሟላ የምትችለው መስፈርት ነበር፡፡ ደሞዙም አንድ ሺህ ብር ይላል፡፡የመሥሪያ ቤቱ ለመኖሪያ ቤቷ ቅርብ መሆን፣ የትምህርት ደረጃ መስፈርቱ ከእርሷ የትምህርት ደረጃ ጋር መመሳሰል፣ የመነሻ ደመወዙም ቢሆን ይህ ሁሉ ተደምሮ የመቀጠር ጉጉቷን ከፍ አደረገው፡፡ ይኹን እንጂ ከሌሎች ተመዝጋቢዎች ጋር መወዳደር ግድ ስለሆነ የማለፍና ያለማለፍ ጉዳይ እንዳለ ስትረዳ በጣም ተጨነቀች፡፡ ስለዚህ ተመዝግባ ስታበቃ ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አቅንታ “እባክህን ይህን ፈተና አሳልፈኝና የሥራውን እድል ስጠኝ” ስትል ተማጸነች፡፡ ሁሉም አልፎ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ደረሰና በናፍቆትና በጉጉት ታጅባ ለማንበብ ሄደች፡፡ውጤቱ ግን የእሷን ማለፍ የሚያረጋግጥ አልነበረም፡፡ የእሷ ስም የለም ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ ምንም ሳትናገር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሮጠች፡፡ እዚያም እንደደረሰች “መድኃኔዓለም ታዘብኩህ” ስትል የምሬት ድምጽ አሰማች፡፡ @eotcy ይህ በሆነ በሳምንቱ ሌላ ማስታወቂያ በሌላ መ/ቤት ወጣ፡፡ ደመዎዙ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ነበር፡፡ ይህን ስታይ እንደመጸጸት አለችና “የእኔ መድኃኔዓለም ለካስ ይሄ እንደሚሻል አውቀህ ነው ያኛው እንዲያልፈኝ ያደረከው፣ እባክህን ይቅር በለኝ የአፌን አትቁጠርብኝ ይህን ግን እንዳትከለክለኝ አደራ” ስትል ተማጸነችና ተመዝግባ ውድድሯን ጀመረች፡፡ ሁሉም አልቆ ውጤት ሲለጠፍ አሁንም የእሷ ስም የለም፡፡ ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ አሁን በጣም አዘነች፡፡ በሃይማኖቷ ላይ ያላት ተስፋ ሲሟሽሽ ተሰማት፡፡ በረዶ እንደወረደበት ሰው የክርስትና ወኔዋ ቀዘቀዘ፡፡ ጊዜ ሳታባክን ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሄደችና  “አሁንስ በጣም ታዘብኩህ” ስትል እሱ የሰጣትን ምላስ እሱው ላይ ዘረጋችው፡፡ @eotcy በዚህ ሁለት ሳምንታት አለፉና አንዲት ጓደኛዋ አንድ መሥሪያ ቤት የሥራ ማስታወቂያ መለጠፉን ነግራት አልመዘገብም ብላ በማኩረፏ በብዙ ጉትጎታ ከቦታው ደረሰች ማስታወቂያውን ስታነበው ሁሉም መረጃ ከሷ ጋር የሚሄድ ሲሆን ደሞዙም ከመጀመሪያው በሁለት እጥፍ ጨምሮ ሦስት ሺህ ብር ይላል፡፡ ከሚቀር እስኪ ልሞክረው ብላ ተመዘገበች፡፡ ተገቢውን ሁሉ አድርጋ የመጨረሻ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ከስፍራው ተገኘች፡፡ አሁን ስሟ አንደኛ ተራ ቁጥር ላይ ተለጥፏል፡፡ በከፍተኛ ብቃት ማለፏን ስታይ ዕንባዋ በዐይኗ ግጥም አለ፣ ሁለቱን ዐይኖቿን ስትጨፍናቸው ቋጥረው የያዙትን የደስታ ዕንባ በጉንጮቿ ላይ ከለበሱት፡፡ ቃል ማውጣት አልቻለችም እየበረረች ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መጣችና እየተንቀጠቀጠች ከታቦቱ ፊት ቆማ ለአፍታ ውስጧን አዳመጠች፡፡ ውስጧም አምላኳን በዚሁ ቦታ ተገኝታ ታዘብኩህ ስትል እንዳማረረችው አስታወሳት ያኔ “የኔ መድኃኔዓለም ታዘብከኝ አይደል?” አለች ለራሷ ብቻ በሚሰማ ድምጽ በቀስታ፡፡ @eotcy 🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂 እኛስ በክርስትና ውጣ ውረድ በማይገባን መዓረግና በሌለን አቅም መድኃኔዓለምን  ስንት ጊዜ ታዝበነው ይሆን? አሁን እኛ እሱን ለመታዘብ ብቃቱ አለን ? እሺ ይሁን እሱስ እኛን አንድ ጊዜ ከፍ አንድ ጊዜ ዝቅ እያልን በክርስትና ጉዞ ብልጭ ድርግም በማለት ስንጓዝ ስንት ጊዜ ታዝቦን ይሆን ለማንኛውም አይደለም እግዚአብሔርን ሰውንም እንኳን ቢሆን ለመታዘብ አንቸኩል ያ ሰው እኛንም ሊታዘበን ይችላልና፡፡
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

43🙏 19👏 4😭 3
ክፉ ሀሳብ እያሰቃያችሁ ነውን??     @eotcy      ክፉ ሀሳብ ሳትፈልጉት መጥቶ አዕምሯችሁ ውስጥ ይታሻል?በጣም የሚዘገንን ክፋት በአዕምሯችሁ ውስጥ ይርመሰመሳል⁉️ እኔኮ ይሄን ላስበው በፍፁም አልችልም አዕምሮዬ የሌላ ሰው እየመሰለኝ ነው ትላላችሁ? ኸረ ይሄ ክፉ ሀሳብ ውስጤ ከረመብኝ በምን ላስወግደው ብላችሁ ተጨንቃችኋል?🤔🤔      አዕምሮ ሀሳብን እንዳይገባ የሚከለክል አጥር የለውም። አጥር የሌለው ቤት ሁሉ ነገር ዘው እንደሚልበት አዕምሮ ውስጥም ብዙ ዓይነት ሃሳብ ዘው ብሎ ይገባል። አዕምሯችን የተጠረገ አስፓልት ነው ሃሳቦች እንዳሻቸው እየነጠሩ ይጓዛሉ። የእግዚአብሔር ሀሳብ ያልፍበታል፤ የሰይጣን ሀሳብ ያልፍበታል፤ የስጋና የደም የምኞት ሃሳብ ያልፍበታል። እነዚህ ሁሉ ሃሳቦች የኛ አይደሉም።    ️ በመንገድ የሚያልፈው ሰው ሁሉ የምናውቀው የኛ ሰው አይደለም። የምናውቀውን ብቻ አቁመን ሰላምታ እንሰጠዋለን። ሃሳብም በአዕምሯችን ሽው ብሎ ሲያልፍ ለሁሉም ሀሳብ እጅ አንነሳም✖️✖️ የእግዚአብሔር ሃሳብ የሆነውን ቅልብ አድርገን እንይዘዋለን አላሳልፍም ብለን የራሳችን እናደርገዋለን።       የተበላሸ ነገር ወደ ሆዳችን ስናስገባ በፍጥነት በሽታው ይጀምረናል ወደ አዕምሮም መጥፎ ሀሳብ ሲገባም አጣዳፊ የአዕምሮ ሁከት ይጀምረናል  ከዛ በአዕምሮህ ወደላይ ወደታች ያሯሩጥሀል። ስለዚህ ምን እንደምትሰሙ፣ ምን እንደምታዩ ተጠንቀቁ ይላል ቃሉ። ይሁዳም የሆነው እንደዚሁ ነው። ሰይጣን በይሁዳ አዕምሮ ውስጥ ሀሳብ አገባበት እርሱም ሃሳቡን ንብረቱ አድርጎ ተቀበለው። ወዲያው አዕምሮው ተቃወሰ።     🔑🔑 ሃሳብ ወደ አዕምሯችን እንዳይገባ መከላከል አንችልም። ይህ ከኛ አቅም በላይ ነው። ነገር ግን አንድ ነገር ማድረግ ትችላለህ እርሱም የገባውን ክፉ ሃሳብ በተሻለ ሃሳብ ማሸነፍ ትችላለህ። @eotcy     🔴ሰይጣን ጠላት ነው፡፡ አእምሮ ደግሞ ቤት ነው፡፡ ሰይጣን መቼም የማይታረቅህ የዘላለም ጠላትህ ነው። ሰይጣን ቤትህን የቆሻሻ ዓለም እስኪያስመሰለው ድረስ  ክፉ ሃሳብን ከመጣል አያንቀላፋም፡፡ ጠላት የጣለውን ከቤትህ ማስወጣት ያንተ ትጋት ነው፡፡ ችላ ካልከው ግን አንተ ራስህ ለመግባት እስክትቸገር ድረስ ቤትህ ቆሻሻ በቆሻሻ ይሆናል፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ሳይበዛ የጣለውን ጥቂት በጥቂት አስወጣው፡፡ በዚያም ቤትህ በእግዚአብሔር ጸጋ ንጹህ ይሆናል።     📌 ስለዚህ ለምን ክፉ ሀሳብ ውስጤ ገባ ብለህ አትብሰልሰል። ይሁዳ ከነጴጥሮስና ዮሀንስ የተለየ ፍጥረት ስለነበር አይደለም ሰይጣን የተጠቀመበት ይሁዳ ውስጥ የገባው ክፉ ሀሳብ እነጴጥሮስ ውስጥም ገብቶ ድል ነስተውት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሃሳቡ እንዳይገባ ማድረግ አትችልም እንዲወጣ ግን ማድረግ ትችላለህ። @eotcy        ክፉ ሀሳብ ውስጥህ ሲመጣብህ መልካም በሆነው ድል በሚነሳው በወንጌል ቃል አክሽፈው። አቤቱ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ውስጤ ሰርጎ የገባውን ክፉ ሀሳብ በስምህ ጠርገህ አስወግድልኝ፤ ከነዚህ ክፉ ሃሳቦች መዳን ወዳለሁና አቤቱ ከስራቸው ነቅለህ ጣላቸው ብለህ ፀልይ⛪️⛪️። እግዚአብሔር ይንቀልላችሁ!! 📌 "ወፍ ከራስሕ  በላይ  እንዳትበር  ማድረግ አትችልም ይሁን እንጅ በአናትህ ላይ መጥታ ጎጆ እንዳትሠራ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ልክ እንደዝሁ መጥፎ ሐሳብ ወደ አዕምሮህ እንዳይገባ ማድረግ አትችልም ነገር ግን የገባውን አለማስተናገድ ትችላለህ" ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ ✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥    @eotcy  @eotcy
Show all...
🙏 35 10
ከዝሙት መሸሽ እያነበባችሁ ሼር ልጄ ሆይ ከጎደኛህ ቤት ሄደህ ጓደኛህ ባይኖር ሚሥቱ ብቻ ብትኖር እቤት አትግባ ነውር ነው። አንተ ባታሥብ እንኳ ያየህ ሠው በሐሜት ያሰናክልሀልና። እናንተም ሠው ናችሁ እና በፈተና ትወድቃላችሁ መልካም ወንድ የሠው ሚሥትን ፊቷን ሞልቶ አይመለከትም፣ መልካም ሤትም እንደዛው የሠው ባልን ከባሏ ውጭ ያሉትን ፊቷን ሞልታ አትመለከትም። ሞልቶ ከተመለከታት በዝሙት መንገድ እየሄደ ነው ወይም እየሄደች ነው። መልካም ወንድ በጨዋታ ከሴት ጋር አይላፋም፣ ይህን ካደረጉ ክብራቸው ከጫማቸው በታች ነው!!! መልካም ወንድ ሠው በሚያጠራጥረው መልኩ ከሤት ጋር አይቀራረብም። ልክ በሌለው መቀራረብ ተሠናክለው እራሳቸውን ያዋረዱ ብዙዎች ናቸው። / የጓደኛቸውን ሚስት ወይም ባል እያማገጡ ህሊናቸው እንደ ጦር እየወጋቸው እየኖሩ ያሉ በርካታ ናቸው።!!!    የዝሙት ፈተናን ለማለፍ ሸሽተክ አምልጥ እንደ አባታችን ዮሴፍ እጋፈጠዋለሁ ካልክ ትወድቃለክ። ረጅም መንገድ ከማታውቀው ተቃራኒ ፆታ ጋር ተቀምጠው አትጓዝ። መቀራረብ፣ መተዋወቅን፣ መተዋወቅ፣ መዋደድን፣ መዋደድ መፋቀርን፣ ማፍቀር ዝሙትን ወልዶ ከልዑል እግዚአብሔር ደጅ ያሶጣኻል። ወይንም ያሶጣሻል!!! ዘወትር ደሙ ያልደረቀ ሥጋ እየበላክ መዓዛውን በአፍንጫህ የሚሰነጥቅ አልኮል እየጠጣህ እራሴን ከዝሙት እጠብቃለሁኝ ማለት      ግመል ሠርቆ አጎንብሶ መሄድ ማለት ነው። ሤት ልጅ በአፍህ አምሮብሻል ቆንጆ....ነሽ ብለህ ሥታደንቅ በአንደበትክ እየዘሞትክ ነው። በየመንገዱ ልዑል እግዚአብሔር ያሣመራቸውም ይሁኑ በቀለማ ቀለም አምረው ብታገኛቸው አይንህን ከሷ ላይ ቶሎ ካልነቀል በአይንህ እዘሞትክ ነው። ተጠንቀቁ!!! በአሁኑ ዘመን ዲያቢሎስ በውበት ሠበብ ፍቅር አስመስሎ የዝሙት መንፈስ አውርዷል። እራሳችንን እንጠብቅ እግዚአብሔር ከዚህ መንፈስ ይጠብቀን ምን ጊዜም ቢሆን ፈሪሐ እግዚአብሔር ይኑረን። ወሰብሐት ለእግዚአብሔር... 🟢 @eotcy 🟢 🟡 @eotcy 🟡 🔴 @eotcy 🔴
Show all...
🙏 51 5😭 3
.                   ግን ለምን❓ መጽሐፍ ቅዱስ የኛ ሆኖ ሳለ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አውጥተው ሚጠይቁን ሌሎች ናቸው ለምን ይህ ሆነ? ለምን ጠያቂ አልሆንም? ለምን በጥያቄ አስጨናቂዎች አልሆንም? 👉እውነት ነው ሁላችንም ዘመን የማይሽረው ስህተትን እየሰራን ነው። ✝ በአንድ  ወቅት አንድ ህጻን ልጅ መጽሐፍ ቅዱስ ሊነካ ሲል እናቱ ይሄ የእግዚአብሔር ነው እያለች ትቆጣዋለች ልጁም በዚህ ድርጊቱ ይቀጥልበታል  እናም አንድ ቀን እንደተለመደው ሲነካ እናት "የእግዚአብሔር ነው አትንካአላልኩህም ነበር ወይ!" ስትለው ልጁም :-" የእግዚአብሔር ከሆነ ለምን አንመልስለትም?" ብሎ መለሰላት 👉 ሁላችንም ትራሳችን ውስጥ፣ በየመጽሐፍ መደርደሪያው ላይ ያኖርነው መጽሐፍ ቅዱስ  ቅዱስ ካስባሉት አንዱና ዋነኛው ወደ ቅድስና ስለሚመራን ነው ። እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ለሁሉም ነገር መልስ ኖሮን ሳለ በእራሳችን ስህተት ብዙ ሺ በጎችን አጥተናል። እያጣንም እንገኛለን በዚሁ መተኛታችን ከቀጠልን ዘመንና ትውልድ ይወቅሰናል "...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2 ☟︎︎︎ ━━━━━━━━━━━━━━━ ☟︎︎︎     ♡ ㅤ   ⎙ㅤ     ⌲         ✉️       ˡᶦᵏᵉ     ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

21🙏 13
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.