cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
209
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

+ ጻድቅ ሆኖ ተመለሰ + አባ ፕሮፎርዮስ እንዲህ ሲሉ ገጠመኛቸውን ያስታውሳሉ ፦ ‘በጥምቀት በዓል ሰሞን ውኃው ተጸልዮበት ከተባረከ በኋላ ለካህናት ወደ ሰዉ ቤት መሔድና ጠበል መርጨት የተለመደ ሥርዓት ነው፡፡ የሆነ ዓመት ላይ ይህንን ጠበል እየረጨሁ ምእመናንን ለመባረክ ከቤተ ክርስቲያን ወደ መንደር ወጥቼ ነበር፡፡ በየቤቱ በር አንኳኳና ‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ /ጌታ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ.../ እያልሁ እያዜምሁ እገባለሁ፡፡ ብዙ መኖሪያ ቤቶች ወዳሉበት መንደር እንደዘለቅሁ አንድ በብረት በር የተዘጋ ትልቅ ጊቢ ጋር ደረስሁ፡፡ ከፍቼ ዘልቄ ገባሁ ፤ ጊቢውን የሞላውን መንደሪን ፣ ሎሚና ብርቱካን የተተከለበት የአትክልት ሥፍራ አልፌ ቀጥ ብዬ ገባሁ፡፡ ሕንጻው ወደ ምድር ቤትና ወደ ላይኛው ፎቅ የሚያስወጡ ሁለት ደረጃዎች አሉት፡፡ ወደ ላይ ወጥቼ አንዱን በር ሳንኳኳ አንዲት ሴት ብቅ ብላ በሩን ከፈተች፡፡ ‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ ብዬ ማዜም ስጀምር በፍጥነት አስቆመችኝ፡፡ ይሁንና ድምፄ በደንብ ተሰምቶ ስለነበር ከግራ ከቀኝ ካሉት ክፍሎች ውስጥ ወጣት ሴቶች ወደ ኮሪደሩ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ነገሩ ገባኝ ፤ ‘አሃ ዘልዬ የገባሁት ለካ መሸታ ቤት ከሚሠሩ ሴቶች ቤት ኖሯል?’ አልኩኝ በሆዴ፡፡ ‘እባክዎን ይሒዱ አባ’’ አለች ቀድማ የወጣችው ሴት ‘እነዚህ ሴቶች መስቀል መሳለም የሚገባቸው አይደሉም ፤ እኔን ያሳልሙኝና ቶሎ ይሒዱ’ አለች በችኮላ፡፡ ኮስተር አልኩና ‘ካህን ነኝ ቤቱን ሳልባርክ አልሔድም’ አልኳት ‘እሱን ይችላሉ እነዚህ ሴቶች ግን መስቀሉን አይሳለሙም’ ብላ ፍርጥም አለች፡፡ ‘መስቀሉን መሳም የሚገባው አንቺ ሁኚ እነርሱ በምን እናውቃለን? እግዚአብሔር መስቀሉን መሳለም የሚገባው ማን ነው ብሎ እኔን ቢጠይቀኝ ኖሮ መስቀል መሳለም የሚገባው ለአንቺ ሳይሆን ለሴቶቹ እንደሆነ በነገርሁት ነበር፡፡ ምክንያቱ ከምትመጻደቂው ከአንቺ ይልቅ የእነርሱ ነፍስ ትሻላለች’ ብዬ ገሠጽኋት፡፡ ደንግጣ ዝም አለች ፤ እኔም ሴቶቹን ወደ እኔ እንዲመጡ ጠራኋቸው፡፡ ከዚያም ‘‘አመ ተጠምቀ እግዚእነ በዮርዳኖስ...!’ እያልኩ ከመጀመሪያው በበለጠ ኃይል መዘመር ቀጠልሁ፡፡ እግዚአብሔር ወደ እነዚህ ምስኪን ነፍሳት እንድመጣ እንዳመቻቸልኝ ስላወቅሁ ውስጤ በደስታ ተሞልቶ ነበር፡፡ ሁሉም መስቀሉን ተሳለሙ፡፡ ሁሉም ያጌጠ ልብስ ለብሰው ሊወጡ ተዘጋጅተው ነበር፡፡ እንዲህ አልኳቸው ፦ ልጆቼ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፤ እግዚአብሔር የሚወደው ሁላችንንም ነው፡፡ እርሱ መልካም ነውና ለኃጢአተኞችም ለጻድቃንም ዝናምን ያዘንባል፡፡ እርሱ የሁላችን አባት ነውና ለሁላችን ይጨነቃል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ወደ እርሱ መምጣት እርሱን መውደድና መልካም መሆን ብቻ ነው፡፡ እርሱን ውደዱ ምንኛ ደስተኛ እንደምትሆኑ ታያላችሁ’’ በመደነቅ ይመለከቱኝ ነበር ፤ በተጨነቀች ትንሽ ነፍሳቸው ውስጥ የሆነ ነገር እንደቀረ ያስታውቅ ነበር፡፡ ‘እናንተን ለመባረክ እግዚአብሔር ዛሬ ወደዚህ ቤት የመምጣትን ክብር ስለሠጠኝ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ’ አልኳቸው፡፡ ለመሔድ ስነሣ ‘እግዚአብሔር ለዘላለም ይባርካችሁ’ አልኳቸው ፤ ‘አሜን አባ’ ብለው በአንድነት መለሱ ፤ ጉዞዬን ቀጠልሁ፡፡ 💒💒💒💒💒 ይህንን አጭር ታሪክ በኦርቶዶክሱ ዓለም እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ እጅግ ውብ መጻሕፍት አንዱ ከሆነው ‘Wounded by Love ፤ The Life and the Wisdom of Saint Porophyrios’ ከተሰኘው የአንድ መነኩሴን ሕይወት የሚተርክ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ 💒💒💒💒💒 ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‘እግዚአብሔር በጽድቁ ከሚመካ ጻድቅ ይልቅ ስለ ኃጢአቱ የሚያለቅስ ዘማዊን ይወድዳል’ ይላል፡፡ በእርግጥም ራስን አጽድቆ የሌላውን ሰው ኃጢአት የማሰብን ያህል ኪሳራ በክርስትና ሕይወት የለም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበው የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት ሲቆጥር ሳይሆን የራሱን በደል ሲቆጥር ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‘እኔ መተላለፌን አውቃለሁና ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና’ እንዳለው እግዚአብሔር ኃጢአትህ ተሰረየችልህ የሚለው ሰው የራሱን ኃጢአት ዘወትር የሚያስብ ሰው ነው፡፡ የነነዌው ቅዱስ ማር ይስሐቅ ‘መላእክትን ከሚያይ ሰው ይልቅ የራሱን ኃጢአት የሚያይ ሰው ይሻላል’’ ይላል፡፡ ባለ በገናው ‘እባክህ ጌታዬ ሥጠኝ መስታወት ፤ የሰው ሥራ ትቼ የእኔን አይበት’ እንዳሉ የራሱን በደል ማየት ከሚችል በቀር ይቅርታን የሚያገኝ የለም፡፡ ለብዙዎቻችን ከራሳችን ይልቅ የሰው ጉድፍ ማውጣት ይቀልለናል፡፡ ሰው ሆኖ ሌላ ሰውን ኃጢአተኛ ነህ የማለትን ኃጢአትና ትዕቢት ግን የለም፡፡ የሰዎችን ድክመት ባየን ጊዜ ከመሳደባችን በፊት እኛ ከዚያ ሰው በኃጢአት ብዛት በምንም እንደማንሻል ማሰብ አንደበታችንን ይሰበስብልናል፡፡ አባ ሲድራስ የተባለ አባት አንድ ወጣት መነኩሴ የወይን ፍሬ ሰርቀሃል ተብሎ ከገዳም ሲባረር አይቶት ተከትሎት ወጣ፡፡ አባታችን ወዴት ትሔዳለህ ሲሉት ‘እሱ ወይን ሰረቆ ከተባረረ እኔ የሠራሁት በደል ብዙ ነውና አብሬው ብወጣ ይሻላል ብዬ ነው’ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት መነኩሴውን ከመባረር አዳኖታል፡፡ ወዳጄ እኔና አንተ በወንድማችን የምንፈርደው ከእርሱ የባሰ የተሸሸገ በደል ተሸክመን መሆኑን አንርሳ፡፡ ‘እኔ እንኳን ብዙ ኃጢአት የለብኝም’ የምንል ከሆነ ግን በድሏል ካልነው ሰው የከፋ ለንስሓ መንገድ የሌለው በደል ውስጥ ነን፡፡ እግዚአብሔር ሊያድነን የሚችለው ከምናምነው ኃጢአታችን እንጂ ከመመጻደቃችን አይደለም፡፡ በወንጌል ጌታችን ከተናገራቸው ታሪኮች እጅግ የተዋቡት ምንባባት ኃጢአታቸውን ያልደበቁና ያልተመጻደቁ ኃጢአተኞች ታሪክ ነው፡፡ የዘኬዎስ ፣ የባለ ሽቱዋ ማርያም ፣ ልትወገር የነበረችው ሴት ወዘተ ታሪኮች ኃጢአታቸውን አምነው ይቅርታ ያገኙ ሰዎች ታሪኮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ ታሪክ ስለ አንድ ቀራጭ ይናገራል፡፡ በቤተ መቅደስ ፈሪሳዊውና ቀራጩ ጎን ለጎን ቆመው ይጸልያሉ፡፡ ፈሪሳዊው በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እንኳን ራሱን ዝቅ አያደርግም፡፡ አፉን ሞልቶ ጽድቁን ያወራል፡፡ ጽድቅን ተናግሮ የሚገኝ ነገር ያለ ይመስል ‘እጾማለሁ ፣ ዐሥራት አወጣለሁ’ እያለ ይመጻደቃል፡፡ አልፎ ተርፎ ‘እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ’ ብሎ የቀራጩን ኃጢአተኝነት ለእግዚአብሔር አሳሰበ፡፡ ወዳጄ ሺህ ጊዜ በጎ ብትሠራ እንዲህ አደረግሁ ያልህ ቀን ዋጋ ታጣለህ ፣ ስለ ሌሎች ሰዎች ኃጢአት ማውራትና ማሰብ እስካልተውህ ለእኔ ፈሪሳዊ ነህ እያለን ነው መሐሪው ጌታ፡፡ ቀራጩ ግን ‘‘በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ’’ ይላል ጌታችን፡፡ በእውነት እንዴት ያለ ቃል ነው፡፡
Show all...
ብዙዎቻችን ቤተ ክርስቲያን እንሔዳለን ፤ ጸልየን ተሳልመን ወደ ቤታችን እንመለሳለን፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ስንመለስ ጻድቅ ሆነን ተመልሰን እናውቅ ይሆን? እውቀት ገብይተን ፣ የመንፈስ እረፍት አግኝተን ፣ በአገልግሎት ብዛት የሥጋ ድካም ሸምተን እንመለስ ይሆናል፡፡ ጻድቅ ሆኖ ተመልሶ የሚያውቅ ይኖር ይሆን? ምናልባትም ቤተ ክርስቲያን ሔደን ከሰው ተጣልተን ያም ባይሆን እንደ ፈሪሳዊው የሰው ኃጢአት በመቁጠርበ ደል ሸምተን እንመለስ ይሆናል፡፡ እንደዚህ ቀራጭ ከቤተ ክርስቲያን ጻድቅ ሆኖ ተመለሰ የሚባልለት ይኖር ይሆን? ልብ በሉ ቄጤማ ገዝቶ ተመለሰ አይልም ፤ ነፍሱን አግኝቶ እንጂ! ይህ ቀራጭ ጻድቅ ሆኖ የተመለሰው የወንድሙን ኃጢአት ትቶ የራሱን በማየቱ ነበር፡፡ ጌታ ሆይ ከዚህ በኋላ ቤትህን ረግጬ ስመለስ ጻድቅ አድርገህ መልሰኝ ኃጢአቴን አይቼ ለማልቀስ ዕንባን አድለኝ ከማለት በላይ ምንም ጸሎት የለም፡፡ ይህ ቀራጭ ደረቱን ይደቃ ነበር ይላል ፤ በዝማሬ ተሻምተን ከበሮ ከምንደቃው በላይ ደረታቸውን በዕንባ የሚደቁ ትሑታን ለእግዚአብሔር ጎልተው ይታዩታል፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo
Show all...
ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ። ዮሐ 10:16 እንኳን ደስ አላችሁ የጥቁሩ ዘመን በብርሃን በይቅርታ ተፈጽሟል! እግዚአብሔር ሆይ ይህን ሁሉ ስላደረክልን ክብር ምስጋና አምልኮት እና ውዳሴ ላንተ ይገባል! @aklesyazetewahdo
Show all...
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው? ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል። ሰማዕቱ በግፍ የሚደበደቡ የካህናቱን እና የምእመናኑን እንባ ያብስልን! #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ ዲያቆን አቤል ካሳሁን @aklesyazetewahdo
Show all...
፧ ??#ይድረስ_ለፍቅረኛዬ ፧ ❤የፍቅር ቀን ለፍቅረኛዬ የጻፍኩላት ደብዳቤ💓 ፧ በትዝታ ክንፎቼ በርሬ ካልሆነ በቀረ እኔ በማልደርስበት ይድረስ ባለሽበት ለምትወጅኝ ለውዴ❤ ፧ ስለ ጤናሽ አልጠይቅሽ የማውቀው አልመታመምሽን ነው። ነገር ግን ባፈቀርሽኝ ልክ ባላፈቅርሽም የስበቤን ያህል ቀልቤን ሰብስቤ ከሰማይ በታች በተሰጠው የፊደል ቃል በወለምታም ቢሆን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ሳልገልጽልሽ እንዴት ልቅር?!! ፧ "ውዴ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም " (መኃ4:7) ነገር ግን ነውረኞች ሰዎች ሲያስጨንቁሽ ሳይ ከማዕበሉ በፊት የባህሩ ሞገድ እንደሚያልፍበት የአሳ ዝርያ እሆናለሁ። ፧ ትተውሽ እንጂ ትተሻቸው ባታውቂም እወድሻለሁ ያለሽ የምትወጅውን እረስቶ የክብር ቀለበቱን ፈቶ ለነውረኞች ሲያስር እንደማየት ሕመም የት አለና። ውዴ ሆይ ምነው ብዬ አልጠይቅሽ እኔም አለንልሽ በሚሉት መሃል እንደ ጧት ጤዛ ነኝና እንዳረግፍ እፈራለሁ። ፧ በዙሪያዬ በመከራ የሚጮሁ ብዙ እንደሆነ ባይም ከባለፈውና ከሚመጣውም ይልቅ እለት እለት የሚያሳስበኝ ያንቺ ነገር ነው። ወር ቆጥሬ ቀን ሰጥቼ ባላፈቅርሽም ወር አውጥቼ ቀን ሰጥቼ እንዳልጠላሽ በፍቅርሽ እለምንሻለሁ። ፧ ራቁቴ የተከደነብሽ ልብሴ ሆይ አንቺን ትቼ በብሔር አጥር ታጥሬ በዘረኝነት ጠበል ተጠምቄ በዋልኩበት ከሌላ ጋር እንዳረክስ ትጠብቂኝ ዘንድ ሳላውቅሽ እኔን ባወቅሽበት የፍቅርሽ ኪዳን እማጸንሻለሁ። ፧ በእርግጥ የልቤ ወለል ያልተጸዳ ሆኖ ለክብርሽ ባይመጥን እንኳ በመዳፍሽ መሃል በተሰመረው የማንነቴ ውቅር አስተውሰሽኝ እንደምትቀበይኝ ሳስብ ተስፋ አልቆርጥም። ፧ የተረከዝሽን ኮቲ አይቼ እና ሰምቼ ከተቀመጥኩበት ከዋዘኞች ወንበር ተነስቼ ልከተልሽ የልቡናዬን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅብኝም። አዎን ውዴ ሆይ ልቤ ሊከተልሽ ከሻተ የምትደርሽበት ታላቅ ኮረብታ አይከለክለውም። ፧ በሊባኖስ ተራራ እንደ ፍየል መንጋ የተሰደሩ ወዳጆችሽን ባየሁ ጊዜ ብረር ብረር ይለኛል። ነገር ግን ልቤ ስበበኛ ሆኖ በአጉል ተስፋ ወደ አንቺ የምመጣበትን ቀን ያስረዝምብኛል። በትዝታሽ እንባ የሚያቀሩ አይኖቼ ሲያስቸግሩኝ በዛፍ ስር ተሸሽጌ የክብርሽን ሞገስ ባሰብኩ ጊዜ ለአንቺ ሳይሆን ለእኔ የሚሆን ጊዜ ማገኜት ይናፍቀኛል። ፧ ሁሉ ወረት በሆነበት በዚህ ዘመን ፍቅሬ ወረት ሆኖ የጧት ዝማሬ የማታ ጠብ እንዳይሆን እምነቴ ከትንሿ ጣቴ ቀጥና በዚህም በዚያም በሚይዙኝና በሚጋተቱኝ ሰዎች እንዳይበጠስ ከወይን መጥመቂያው ከደስታ ቅጥርሽ ቦታ አሰማሪኝ። ፧ ከጎንሽ ነኝ እንደሚሉት ሳይሆን ከልብሽ ከልቤ እንድሆን ምኞቴ እውን ሆኖ እንዲቀር በሰማይ ሰሌዳ ላይ ይጻፍልኝ። አንቺን በወደድኩበት በጽጌ ረዳ አበባ ማጌጥ አልፈልግም ባየሁት በሰማሁት ባስተማርሽኝ የፍቅር መንገድ በደም ጠብታ እስከ ነፍስ መስጠት እጓዝ ዘንድ ውዴ በውድሽ እለምንሻለሁ። ፧ ሙሽሪት ሆይ መከራሽ በመከራዬ ደስታ ይሁን ከጣፈጠው ሕይወትሽ መራራ የእኔ ማንነት እንደሚጣፍጥ አምኜ እንደ እሪያ በቆሻሻ ተሰማርቼ ብቆሽሽም ሕጻን ልጅ ሲቆሽሽ የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና እኔም ወደ አንቺ እሸሽ ዘንድ ስሮጥ እጆችሽን ዘርግተሽ ተቀበይኝ። ፧ እኔ ባላኮራሽም የማታሳፍሪኝ ክብሬ ተዋሕዶ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ፧ በክርስቶስ ካሳ ወሎ ኮምቦልቻ የካቲት 7/6/2015 ዓ.ም @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ:: ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡ በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡ ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡
Show all...
መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር “እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ” የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo
Show all...
ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡ ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡ በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡ በመግለጫውም፡- ፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡ ፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡ በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.