Hakim Mereja
Open in Telegram
2 424
Subscribers
No data24 hours
-147 days
-4330 days
Posts Archive
2 424
መታወቅ ያለባቸዉ 10 ለደም ግፊትና ለልብ ጤና ተስማሚ ምግቦች
👇👇👇
ዩቱዩቭ ቻናላችንን ሰብስክራይቭ ያድርጉ
https://youtu.be/D778ysCZ6jE
2 424
👨👨👦👦#እንደት_ሊፈጠር_ይችላል?
👁🗨ነገር ግን ለማመን የሚከብድ ከሁለት አባት የሚወለዱ መንትዮች እስካሁን ተፈጥረዋል:: አፈጣጠሩም ከላይ በሁለተኛዉ የመንትያ አይነት ላይ እንደገለፅኩት እናት በአንድ የወር አበባ የኡደት ጊዜዋ ከሁለቱም የእንቁላል ማምረቻ እንቁልጢ ሁለት እንቁላሎችን በአንድ ጊዜ ስትለቅ እና በዚያን ወቅት ከሁለት ወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ስታደርግ እና ሁለቱ የተለቀቁት እንቁላሎች በሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬ (sperm) ከተሰበሩ የሚፈጠር የመንትያ አይነት አይነት ነዉ::
•••●◉
ዶር ዳዊት
2 424
❀]☞#መንትዮች ከሁለት አባት ሊወለዱ ይችላሉ ብለዉ አስበዉ ያዉቃሉ?
✔️እርግጠኛ ነኝ አስበዉት አያዉቁም:: ለዛሬ ሀኪም መረጃ ፔጅ ከሁለት አባት እንደት መንትዮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ትገልፃለች:: መልካም ንባብ!
✔️ከሁለት አባት መንትያ መፈጠር በእንግሊዘኛዉ ሄትሮፓተርናል ሱበርፈከንደሽን (heteropaternal superfecundation) ይባላል::
✔️ይህ ክስተት ብዙ ግዜ አይከሰትም ነገር ግን አሜሪካ ዉስጥ በተሰራ ጥናት ከ400 መንትያዎች ዉስጥ አንዱ በዚህ heteropaternal superfucundation አማክይነት የሚፈጠር ነዉ::
👉መጀመሪያ ስለመንትያ አፈጣጠር እንደሚከተለዉ ልግለፅላችሁ::
👁🗨አንድት ሴት በአንድ የወር አበባ ኡደት ወቅት ከእንቁላል ማምረቻ እንቁልጢዋ አንድ እንቁላል ብቻ የምትለቅ ሲሆን በዚህን ጊዜ አንድ ልጅ ታረግዛለች ነገር ግን አይደንቲካል ቲዊን (identical twin) የምንለዉ የመንትያ አይነትም ይህ አንዱ እንቁላል በአንድ የወንድ የዘር ፍሬ (sperm) እኩል ለሁለት ከተከፈለ የሚፈጠር የመንትያ አይነት ነዉ::
👁🗨አንዳንድ ጊዜ አንድት እናት በአንድ የወር አበባ የኡደት ጊዜዋ ከሁለቱም የእንቁላል ማምረቻ እንቁልጢ በአንድ ጊዜ ሁለት እንቁላልን ወደ ማህፀንዋ ልትለቅ ትችላለች:: በዚህ ጊዜ ሁለቱም እንቁላሎች በአንድ ወንድ ሁለት የዘር ፍሬ (sperm) ከተሰበሩ ሁለተኛዉ የመንትያ አይነት ማለትም ፍራተርናል ቲዊን (fraternal twin) ወይም መንታ ምጅ ከአንድ አባት (homopaternal superfecundation) የሚባለዉ ይፈጠራል::
👁🗨ከላይ በፎቶዉ የምትመለከቷቸዉ ጥቁርና ነጭ ህፃናት መንትያ ሲሆኑ ከሁለት አባት የተፈጠሩ ናቸዉ::
Continue…
2 424
👁🗨አብዝኛዎቹ ሱስ አምጭ እፅዋት #ዶፓሚን (dopamine) የተባለዉን ከአእምሮ የሰዉነት ክፍላችን የሚመነጭ ንጥረ-ነገር እንዳይሰባበር በማድረግ በደም ዉስጥ በማብዛት ሲሆን ይህ ኬሚካል (ዶፓሚን) ሲበዛ ደስታን ይሰጣል::
👁🗨የረጅም ጊዜ #ትዉስታ (remote memory) በአእምሮ ዉስጥ አሚግዳላ (amygdala) በሚባለዉ ክፍል ላይ ይቀመጣል::
👁🗨የእናት ጡት ለህፃን ልጅ አስፈላጊ የሆነዉን ሁሉንም የምግብ ንጥረ-ነገሮች ሲኖሩት ከፀሀይ ብረሃን የምናገኘዉን ቪታሚን ድ ግን በበቂ የለዉም::
👁🗨የሰዉ ልጅ ልብ ጭንቅላት ከሞተ በሑዋላ ስራዋን ሳታቀርጥ የመስራት አቅም አላት:: ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ እንደሌላዉ የሰዉነት ክፍላችን በአእምራችን ስለማትታዘዝና በራሳ ማከናወን ስለምትችል::
👁🗨ፅንስ በእናት ማህፀን ሳለ በሳንባዉ አይተነፍስም:: ምክንያቱም ሳንባ በፈሳሽ የተሞላ ስለሆነ:: ለፅንስ እንደ መተንፈሻ ሳንባ የሚያገለግለዉ የእንግደ ልጅ በሚባለዉ ሲሆን ፅንሱ በሳንባ መተንፈስ የሚጀምረዉ ወድያዉ እንደተወለደ ነዉ:: ከእናት ወደ ፅንስ ምግብ የሚተላለፈዉ በእትብት ነዉ::
👁🗨አማካይ የእንቅልፍ ሰዓት ከ4 - 9 ሰዓት ነዉ::
•••●◉
ዶር ዳዊት
2 424
❀]☞#የጤና_የእውቀት_ማዕድ☜[❀ በሀኪም መረጃዎች | #እዉቀት ጤናም : ሀገርም ነዉ_✍️ መልካም ንባብ!
✔️ቀላል ወይም ትንንሽ የሚመስሉን ነገር ግን አደጋቸዉ የከፋ እና በጤናችን ላይ ከፍተኛ ቀዉስ የሚያስከትሉ ነገሮች ከጤና እዉቀታችን እና ግንዛቤያችን ማነስ የሚከሰቱ ናቸዉና ካለዎት አናሳ ሰዓት 2 ደቂቃዎን ብቻ በመስጠት ስለጤናዎ ብዙ እና ጠቃሚ እዉቀትን ይቅሰሙ::
👁🗨ጤነኛ #የደም_የስኩዋር መጠን ከ8 ሰዓት ፆም በሓላ ሲለካ ከ70 - 126 ነዉ:: ከ126 ከበለጠ የስኩዋር በሽታ ሲሆን ካነሰ ግን የደም የስኩዋር ማነስ ነዉ:: ክበፍጥነት ካልታከመ ከሁለቱመካከል በደቂቃዎች ዉስጥ ገዳይ እና አደገኛዉ የደም የስኩዋር መጠን ማነስ ነዉ::
👁🗨#ፎሊክ_አሲድ የሚባለዉ ንጥረ-ነገር ለአእምሮ አፈጣጠር ጠቃሚ ሲሆን አንድት እናት በመጀመሪያወቹ 3 ወራት የዚህ ንጥረ-ነገር እጥረት ካለባት አእምሮ የሌለዉ (anencephaly) ወይንም አናሳ የአእምሮ ክፍሎች ያሉት ልጅ ልትወልድ ትችላለች::
👁🗨የሰዉነት #ሚዛናችንን ጠብቀን ለመሄድ ከአእምራችን በተጨማሪ ጀሮአችንን እንጠቀማለን::
👁🗨ልብ የኩላሊትን የማጣራት አቅም መቆጣጠሪያ ንጥረ-ነገር ስታመርት ኩላሊትም ለልብ ግብረ-መልስን ለመስጠት ንጥረ-ነገር ታመርታለች ስራቸዉን በመናበብ ይሰራሉ::
👁🗨#ቪያግራ (viagra) የተባለዉ ለስንፈተ-ወሲብ የሚሰጥ መድሃኒት የብልት የደም ቱቦዎችን በማስፋት በብልት የደም ቱቦ ዉስጥ የደም ክምችት በመፍጠር እንድቆም ያደርጋል:: ነገር ግን የከፋ የጎንዮሽ ችግር የሚያስከትል እስከ ሞት ድረስ ይዳርጋል:: የልብ ድካም እና የደም ግፊት ላለባቸዉ እንድወስዱት አይመከርም::
Continue…
2 424
#ቃሪያን በመመገብ የሚገኙ #አስር (10) የጤና በረከቶች
✔️ቃርያ አብዛኛውን ጊዜ ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት ሲሆን እንደሀገራችን ባሉ ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን በሚመገቡ ሀገራትም ይዘወተራል::
✔️ቃሪያ በቪታሚን ኤ & ሲ (Vitamin A & C) : ፖታሽየም (Potassium) : ፎሊክ አሲድ (Folic Acid) እና ፋይበር (Fiber) የበለፀገ ነዉ::
👉👉ቃሪያን በመመገብ የሚገኙ 10 የጤና በረከቶች የሚከተሉት ናቸዉ:-
👁🗨በሽታን የመከላከል አቅም ያዳብራል
👁🗨የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል
👁🗨የስኳር በሽታን ይከላከላል
👁🗨የሰዉነት ክብደት ይቀንሳል
👁🗨ቁስል በፍጥነት እንዲድን ያደርጋል
👁🗨የቆዳ መሸብሸብን እንዳይኖር ያደርጋል
👁🗨ለአይን ጥራት እና ጤናማነት ይጠቅማል ምክንያቱም ቃሪያ የቫይታሚን ኤ (Vitamin A) ንጥረ ነገር መገኛ ስለሆነ
👁🗨የደም ግፊት በሽታን ይከላከላል - ምክንያቱም ቃሪያ በቫታሚን ሲ (Vitamin C) የበለፀገ ሲሆን ይህ ማዕድን ያላቸዉ በደም ግፊት ህመም የመጠቃት እድላቸዉ ትንሽ ነዉ
👁🗨ለሰውነታችን ጠቃሚ ያልሆኑ ንጥረነገሮችን በማስወገድ እና የፋይበር ምንጭ በመሆን የሆድ ድርቀትን እንድሁም የፊንጢጣ ክንታሮትን ይከላከላል
👁🗨አይረን (Iron) ከአንጀት ህዋሳት ወደ ደም ስር እንድመጠጥ በማድረግ የደም ማነስን ይከላከላል
•••●◉
ዶር ዳዊት
ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት ፔጃችንን ላይክ እና ፎሎዉ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
ምንጭ:- WebMed
2 424
👁🗨ከለውዝ #ጥቅሞች ውስጥ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፤
1️⃣የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል - ስለዚህ በስኳር በሽታ የመያዝ እድላችንን ይቀንሳል፤
2️⃣የልብ በሽታ ይከላከላል - የደም የስብ ክምችትን ስለሚቀንስ:: ስለዚህ ከድንገተኛ የልብ ህመም (heart attack) እና እስትሮክ ይከላከላል ማለት ነዉ፤
3️⃣ክብደት ይቀንሳል - ብዙ የፕሮቲን መጠን እና ትንሽ የካሎሪን መጠን ስላለዉ በትንሽ መጠን ተሎ የመጥገብ ስሜት እንድሰማን በማድረግ ብዙ ካሎሪን እንዳንወስድ ያደርጋል:: ትንሽ የካሎሪን መጠን በሰዉነታችን ሲኖር ሰዉነታችን በዉጣችን የተከማቸ ስብን ወደ ካሎሪ በመቀየር ክብደት እንድንቀንስ ያደርጋል፤
4️⃣የሰዉነትን የበሽታ የመከላከል አቅም ይጨምራል፤
5️⃣በካንሰር በሽታ በተለይ የበጨጏራ ካንሰር እንዳንያዝ ይከላከላል፤
6️⃣የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል - ስለዚህ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የመርሳት በሽታ ይከላከላል፤
7️⃣የድብርትን ስሜት ይቀንሳል፤
8️⃣የሐሞት ጠጠርን ይከላከላል፤
9️⃣እድሜን ያረዝማል፤
🔟በብዙ ጠቃሚ ንጥረ-ምግቦች የበለጸገ ነው::
ዶር ዳዊት
2 424
👉👉አስር #የለዉዝ (#Peanut) የጤና በረከቶች
🖐ሰላም የሀኪም መረጃ ቤተሰቦች🖐
👁🗨በሀገራችን በብዙ መደብሮች የማይጠፋው ለውዝ ተወዳጅ እንደሆነ ይታወቃል:: ጠቀሜታውን እያወቅን እንድንመገበው በዛሬው ጥንቅራችን እናነሳለን::
#ለውዝ #Peanut
👁🗨ለውዝ የጥራጥሬ አይነት ሲሆን በፕሮቲን ፣ ስብ እና ሌሎች አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች እንደ የማግንዥየም (magnesium) : የፎሌት (folate) : የቪታሚን ኤ (vitamin A) : የኮፐር (copper) እና አርጅኒን (Arginine) የበለፀገ ነው ፤ በአንጻሩ ደግሞ የካርቦሀይድሬት ይዘቱ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጥናቶች እናዳመለከቱት ከሆነ ለውዝ ውፍረት ለመቀነስ እና የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል::
👁🗨ነገር ግን ለለውዝ አለርጂክ የሆኑ ሰዎች በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም:: ምክንያቱም መሰል አለርጂዎች ህይወትን ሊቀጥፉ ይችላሉ:: በቀን ሳይበዛ የተወሰኑ የለውዝ ፍሬዎችን መውሰድ እጅግ ይረዳል፡፡
👉👉 55 ግራም (¼ cup serving) ለዉዝ (Peanut):
* ካሎሪ: 207
* ፕሮቲን: 9 ግራም
* ስብ: 18 ግራም
* ካርቦሀይድሬት: 6 ግራም
* ፋይበር: 3 ግራም
* ስኳር: 1 ግራም ይይዛል::
Continued…
2 424
✍ #የፊንጢጣ_መሰንጠቅ (Anal Fissure)
👉 #ዉድ የሀኪም መረጃ ፔጅ ተከታታዮች የፊንጢጣ መሰንጠቅ (Anal Fissure) ፊንጢጣንና የፊንጢጣ ቱቦን በሚሸፍነው የውስጠኛው ስስ ሽፋን ሲተረተር ወይንም ሲሸነቆር ይፈጠራል፡፡ ይህ ስስ ሽፋን ምንም ፀጉር ፣ የላብ አመንጪ እጢዎች ወይም ዘይት አመንጪ እጢዎች የሌሉትና በርከት ያሉ የህመምን ስሜት የሚቆጣጠሩ ነርቮችን ያሉበት ስለሆነ የፊንጢጣ መሰንጠቅ ሲኖር ከፍተኛ የህመም ስሜት ይኖረዋል፡፡
#ለፊንጢጣ_መሰንጠቅ_አጋላጭ_ሁኔታዎች
📌 በእድሜ ህጻን መሆን
📌 ድርቀት
📌 የወለደች ሴት
📌 የፊንጢጣ ወሲባዊ ግንኙነት ካለ
👉👉 #የፊንጢጣ #መሰንጠቅን #የሚያስከትሉ #መንስኤዎች
📌 ወፈር ያለ ሰገራ ካለ
📌 ድርቀት
📌 ከባድ የሆነ ማስቀመጥ
📌 በፊንጢጣ በኩል ወሲባዊ ግንኙነት
📌 የፊንጢጣ ኪንታሮት
📌 የፊንጢጣ ካንሰር
📌 የአንጀት ቱቦ ህመም
📌 ኤች.አይ.ቪ
📌 የአባላዘር በሽታ
👉👉 #የፊንጢጣ_መሰንጠቅ_ምልክቶች
📌 ከባድ የፊንጢጣ ህመም በተለይ ሰገራ በሚወጣበት ወቅት
📌 ደም የቀላቀለ ሰገራ እና ደም ብቻዉን መፍሰስ
📌 የፊንጢጣ ቆዳ ላይ መላጥ/ቁስለት
?? ፊንጢጣ አካባቢ እባጭ መኖር
👉👉 #የፊንጢጣ_መሰንጠቅ_ህክምና
📌 ዉሃ አብዝቶ መጠጣት
📌 በፋይቨር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ
📌 ለብ ባለ ዉሃ ዉስጥ ጨዉ ጨምሮ ከ10 እስከ 20 ደቂቃ መዘፍዘፍ በተለይ ሽንት ቤት ከመጠቀም በፊት ቢሆን ይመከራል
📌 የሰገራ ማለስለሻ መድሐኒት መወሰድ
📌 ቀዶ ህክምና ናቸዉ።
ዶር ዳዊት
#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 https://instagram.com/hakimmereja?igshid=YmMyMTA2M2Y=
2 424
የኢትዮጵያን ግማሽ ያክሉን ሀኪሞች የያዘዉን የአለማችን አንጋፋ ሆስፒታል ላስተዋዉቃችሁ 👉 #ማዮ_ክሊኒክ (#Mayo_Clinic) ይባላል::
👁🗨በአሜሪካ የሚገኝ ትልቅና አንጋፋ ሆስፒታል ነዉ።
👁🗨የተመሠረተው ከ157 አመት በፊት January 27, 1864, ሲሆን በዓለማችን ላይ አሉ ከሚባሉ አንጋፋ ሆስፒታሎች አንዱ ነዉ።
👁🗨ይህ ሆስፒታል 4,500 ዶክተሮችና ሳይንቲስቶች ሲኖሩት ተጨማሪ 58,400 ሌሎች የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች አሉት።
👁🗨 #የሚሰጣቸዉ_አገልግሎቶች
~የህክምና ትምህርት
~ጥናት (Research)
~የህክምና አገልግሎት ነዉ።
👁🗨ሀገራችን ያሏትን አናሳ ሀኪሞች ከእጅ ወደ አፍ በማይሞላ ደመወዝ መቅጠር ተስኗት እንደ ማዮ ክሊኒክ ያሉ ሆስፒታሎች ግን በተመቻቸላቸዉ ጥሩ የጤና ሲስተም ከራሳቸዉም አልፎ ለአለም በህክምና ጥናቱ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦን በማበርከት ላይ ይገኛሉ::
👁🗨በሀገራችን እንደዚህ አይነት አንጋፋ ሆስፒታሎች ይኖሩን ዘንድ የሁላችንም ጥረት እና ግፊት ያስፈልጋል::
ዶር ዳዊት
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 https://instagram.com/hakimmereja?igshid=YmMyMTA2M2Y=
2 424
#የደም_ግፊትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች 👉 #ከወደዱት_ያጋሩት!
👁🗨የተመጣጠነ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ማድረግ
👁🗨የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘዉትረዉ ማድረግ
👁🗨በየቀኑ የሚመገቡትን የስብና የቅባት መጠን መመጠን ወይም መቀነስ
👁🗨የስኳር ፣ በተለይም ጣፋጭ ምግቦች እና መጠጦች መጠጥን መገደብ
👁🗨የጨዉ አመጋግብን መመጠን
👁🗨በየቀኑ የተለያዩ ምግቦችን ይመገቡ (የተመጣጠነ ምግብ መመገብ)
👁🗨የጥራጥሬ ምግቦችን አዘዉትሮ መመገብ
👁🗨በየቀኑ ብዙ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን መመገብ
👁🗨የአበባ እህሎች ላይ የተመሰረቱ ምግቦችን ይመገቡ፤ ሲመገቡ ጨዉ አልባ የሆኑ
የአዝርእትና ኦቾሎኒ ምግችን መመገብ
👁🗨የአሳ ምግቦችን ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ መመገብ
👁🗨የስብ መጠናቸዉ አነስተኛ የሆኑ ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን መመገብ
👁🗨የዶሮ ስጋ እንዲሁም ቀይ ስጋን ተመራጭ ማድረግ
👁🗨ንፁህ ዉሃ አዘዉትረዉ መጠጣት
👁🗨ንጹህ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ መመገብ
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 https://instagram.com/hakimmereja?igshid=YmMyMTA2M2Y=
2 424
#EthioHealthInfo || የማታዉቋቸዉ ስለኢትዮጵያ አሁናዊ የጤና መረጃ!
❇️የኢትዮጵያዉያን አማካኝ የእድሜ ጣሪያ - #የወንዶች 66 አመት ሲሆን #የሴቶች ደግሞ 70 አመት ነዉ
❇️አንድት ኢትዮጵያዊት እናት በህይወት ዘመኗ በአማካኝ 4.3 ልጅን ትወልዳለች
❇️በኢትዮጵያ #1ሺህ ከሚወለዱ ህፃናት ዉስጥ #29.5ቱ ጨቅላ ህፃናት ይሞታሉ
❇️በኢትዮጵያ ከሚወለዱ #100ሺህ ህፃናት መካከል #የ401ዱ ህፃናት እናቶች በወሊድ ምክንያት ይሞታሉ
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 https://instagram.com/hakimmereja?igshid=YmMyMTA2M2Y=
2 424
ኢትዮጵያውያን ነርሶች ሸዋረገድ ኅይለ ሥላሴና ጦቢ ሳህሌ በስዊድን በትምህርት ላይ እያሉ - 1951 ዓ.ም
Ethiopian nurses studying in Sweden, Shewareged Haile Selassie & Tobie Sahle, pictured with a Swed baby at Karolinska Hospital in 1959 G.C
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 https://instagram.com/hakimmereja?igshid=YmMyMTA2M2Y=
2 424
]☞#የልባችን_ብቸኛ_ባህሪያት!
♨️የአንድ ጎልማሳ የልብ መጠን የእጅ ጭብጥ ያክል ነዉ!
♨️ልብ በቀን 115 ሺህ ጊዜ ትመታለች!
♨️የልብ ምት ድምፅ የሚፈጠረዉ በዉስጧ በሚገኙ ፣ ደም ወደ ኋላ እንዳይመለስ በሚከላከሉ ፣ ቫልቭ (valve) በሚባሉ ክፍሎቿ መዘጋትና መከፈት በሚፈጠር ፍሪክሽን ነዉ!
♨️የሰዉ ልጅ አእምሮ ቢሞትም ልብ ምቷን ልትቀጥል እና ደም ወደ ሰዉነት ክፍላችን ማሰራጨት የሚያስችል ተፈጥሮ አላት። ምክንያቱም በሌላ የሰዉነት ክፍል ዉስጥ የማይገኙ ነገር ግን በልብ ብቻ የሚገኙ ኤስኤ ኖድ (SA node) የሚባሉ ሴሎች ስላሏት ሲሆን እነዚህ ሴሎች በሰዉነታችን ብቸኞች ያለ እምሯችን ትእዛዝ ስራቸዉን በራሳቸዉ መስራት ስለሚችሉ ነዉ። ምሳሌ ብጠቅስላችሁ የእስራኤሉ መሪ አርያል ሻረዉ አእምሮዉ ሙቶ ልቡ ደም እየረጨች ለአመት መቆየቱ በነዚህ አስደናቂ ሴሎች ስራ ነዉ።
ዶ/ር ዳዊት
___________
ሀኪም መረጃ
☞🅢🅗🅐🅡🅔
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎 fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 @hakimmereja
2 424
]☞#ስለአእምሯችን!
የአንድ ሰዉ brain የአንድን iPod ወይም USB flash drive ያክል ትንሽ gigabytes ብቻ የመልእክት ማስቀመጫ ቦታ ሊኖረዉ ይችላል ፤ ነገር ግን በጣም በፍጥነት ማደግ የሚችልና እስከ 2.5 petabytes (ሚሊየን gigabytes) ድረስ የሚበዛ መልእክትን መያዝ የሚችል አስደናቂ የሰውነት ክፍል ነዉ።
በአንድ ሰዉ ጭንቅላት ዉስጥ ከ 100 ቢሊየን በላይ መልእክት አስተላላፊ ኒዉሮን (nueron) የሚባሉ ሴሎች አሉ።
አንዷ ኒሮን ከ 5-50 መልእክቶችን (action potentials) በሰከንድ መላክ ይችላል።
እነዚህ መልእክቶች ወደ ሰዉነተዎ የሚላኩት ከ 70-120 ሜትር በሰከንድ ፍጥነት በመጓዝ ነዉ።
ዶር ዳዊት
___________
ሀኪም መረጃ
☞🅢🅗🅐🅡🅔
❀꧁Hakim Mereja꧂❀
Facebook 🔎fb.me/Hakim.Mereja
Telegram 🔎 t.me/HakimMereja
Instagram 🔎 @hakimmereja
2 424
ዶክተር አያናው ኢታኑ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ዶክተር አያናው በወልድያ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እና ሀኪም በመሆን ያገለግል ነበር:: ዶክተር አያናው ህይወቱ ከማለፉ በፊት በፌስቡክ ገፁ የፃፈውን መልዕክት ላይ "ይህ ጊዜ ለእኔ ከተፈቀደልኝ ጊዜ ዉጭ የጭማሬ ህይወት እና አመት ነዉ" በማለት ከ4 ቀን በፊት የፖሰተው ነበር። ለዶክተር አያናው ዘመድ ፣ ወዳጅ ፣ ቤተሰብ እና ጓደኞች መፅናናትን እንመኛለን!
🔎t.me/Hakim.Mereja🔍
2 424
4. ከፍተኛ የፕሮቲን አመጋገብን ይመገቡ
👉 ለክብደት አያያዝ ፕሮቲን በጣም አስፈላጊ ንጥረ ነገር ነው። ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን የምግብ ፍላጎትን የሚቀንስ እና ሙላትን የሚያበረታታ የ PYY ሙሉ ሆርሞን መለቀቅን ይጨምራል። እንዲሁም የሜታቦሊክ ፍጥነትዎን ከፍ ያደርገዋል እና ክብደት በሚቀንሱበት ጊዜ የጡንቻን ብዛትን ለመጠበቅ ይረዳዎታል።
👉 ብዙ ፕሮቲን የሚመገቡ ሰዎች ዝቅተኛ ፕሮቲን ከሚመገቡት ያነሰ የሆድ ስብ አላቸው።
👉 በእያንዳንዱ ምግብ ላይ ጥሩ የፕሮቲን ምንጭ ማካተትዎን ያረጋግጡ፦
🔷ስጋ
🔷ዓሳ
🔷እንቁላል
🔷የወተት ተዋጽኦ እና
🔷ባቄላ የመሳሰሉትን ፕሮቲኖች በደንብ ይመገቡ።
5. የጭንቀት ደረጃዎች ይቀንሱ!
👉ውጥረት የጭንቀት ሆርሞን በመባል የሚታወቀው ኮርቲሶልን ለማምረት አድሬናል እጢዎችን በማነሳሳት የሆድ ስብ እንዲጨምሩ ሊያደርግ ይችላል። ከፍተኛ የኮርቲሶል ደረጃዎች የምግብ ፍላጎትን ከፍ የሚያደርጉ እና የሆድ ስብ ክምችትን ይጨምራሉ።
👉ክብደት ለመቀነስ እየሞከሩ ከሆነ ጭንቀትን መቀነስ ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ነገሮች አንዱ መሆን አለበት።
6. ብዙ ጣፋጭ ምግቦችን አይበሉ!
👉ስኳር ከልክ በላይ ሲጠጣ ከበርካታ ሥር የሰደዱ በሽታዎች ጋር የተቆራኘውን ፍሩክቶስን ይይዛል። ይህም፦
🔷የልብ በሽታ
🔷ዓይነት 2 የስኳር በሽታ
🔷ውፍረት እና
🔷የጉበት በሽታን ያስከትላል።
👉 ከመጠን በላይ የስኳር መጠን በብዙ ሰዎች ውስጥ የክብደት መጨመር ዋና ምክንያት ነው።
7. ኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ!
👉(ካርዲዮ) ኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናዎን ለማሻሻል እና ካሎሪዎችን ለማቃጠል ውጤታማ መንገድ ነው። የሆድ ስብን ለመቀነስ በጣም ውጤታማ ከሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው።
8. ካርቦሃይድሬትን መቀነስ
👉የካርቦሃይድሬት መጠንን መቀነስ የሆድ ስብን ጨምሮ ስብን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው።
👉ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ከመጠን በላይ የሆድ ስብ ጋር ይዛመዳል። የካርቦሃይድሬት መጠንዎን መቀነስ ወይም በአመጋገብዎ ውስጥ የተጣራ ካርቦሃይድሬትን እንደ ጤናማ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች ወይም አትክልቶች ባሉ ጤናማ የካርቦሃይድ ምንጮች መተካትን ያስቡበት።
9. አንዳንድ የማብሰያ ቅባቶችዎን በኮኮናት ዘይት ይተኩ!
👉የኮኮናት ዘይት እርስዎ ሊበሏቸው ከሚችሉት ጤናማ ስብ አንዱ ነው።
👉እንዲሁም የኮኮናት ዘይት በካሎሪ ውስጥ ከፍተኛ ነው። በአመጋገብዎ ላይ ተጨማሪ ስብ ከመጨመር ይልቅ አስቀድመው ከሚመገቡት አንዳንድ ቅባቶችን በኮኮናት ዘይት ይተኩ። ከሌሎች የማብሰያ ዘይቶች ይልቅ የኮኮናት ዘይትን መጠቀም የሆድ ስብን ለመቀነስ ይረዳል።
10. የመቋቋም ሥልጠና ያካሂዱ ወይም ክብደቶችን ከፍ ያድርጉ!
👉ክብደትን ማንሳት ወይም የጥንካሬ ስልጠና በመባልም የሚታወቀው የመቋቋም ሥልጠና የጡንቻን ብዛት ለመጠበቅ እና ለማግኘት አስፈላጊ ነው።
11. ከስኳር ጣፋጭ መጠጦች መራቅ
👉ስኳር-ጣፋጭ መጠጦች ፍሩክቶስን ይይዛሉ ይህም የሆድ ስብን ከፍ ያደርገዋል። የስኳር መጠጦች በጉበት ውስጥ ስብ እንዲጨምር ያደርጋሉ።
👉የሆድ ስብን ለመቀነስ እንደ ስኳር ያሉ ጣፋጭ መጠጦችን ሙሉ በሙሉ መተው የተሻለ ነው።
12. ብዙ የተረጋጋ እንቅልፍ ያግኙ!
👉ክብደትን ጨምሮ ለብዙ የጤና ገጽታዎችዎ እንቅልፍ አስፈላጊ ነው። በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች የበለጠ ክብደት አላቸው። ይህም የሆድ ስብን ሊያካትት ይችላል።
👉የእንቅልፍ አፕኒያ ወይም ሌላ የእንቅልፍ መዛባት ካለብዎት ሐኪም ያነጋግሩ እና ህክምና ይደረግልዎታል።
👉እንቅልፍ ማጣት የክብደት መጨመር አደጋን ይጨምራል።
👉ክብደት ለመቀነስ እና ጤናዎን ለማሻሻል ካቀዱ በቂ ከፍተኛ ጥራት ያለው እንቅልፍ ማግኘት ከዋና ዋና ነገሮች አንዱ መሆን አለበት።
13. የምግብ ቅበላዎን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን ይከታተሉ ይቆጣጠሩ!
👉ብዙ ነገሮች ክብደትን እና የሆድ ስብን እንዲያጡ ሊረዱዎት ይችላሉ ፣ ነገር ግን ለክብደት ጥገና ሰውነትዎ ከሚያስፈልገው ያነሰ ካሎሪዎችን መጠቀም ቁልፍ ነው።
👉የምግብ ማስታወሻ ደብተር መያዝ ወይም የመስመር ላይ የምግብ መከታተያ ወይም መተግበሪያን በመጠቀም የካሎሪዎን መጠን ለመቆጣጠር ይረዳዎታል።
14. በየሳምንቱ ዓሳ ይመገቡ!
👉ዓሳ በማይታመን ሁኔታ ጤናማ ነው። ከበሽታ በሚከላከሉዎት ከፍተኛ ጥራት ባለው ፕሮቲን እና ኦሜጋ -3 ስብ የበለፀጉ ናቸው። እነዚህ ኦሜጋ -3 ቅባቶች የውስጣዊ ስብን ለመቀነስ ይረዳሉ።
15. የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት አቁሙ!
👉ምንም እንኳን የፍራፍሬ ጭማቂ ቫይታሚኖችን እና ማዕድናትን ቢሰጥም ልክ እንደ ሶዳ እና ሌሎች ጣፋጭ መጠጦች በውስጡ የለው ስኳር ውስጥ ከፍተኛ ነው።
👉ከመጠን በላይ የሆድ ስብን ለመቀነስ የፍራፍሬ ጭማቂን በውሃ ወይም በሎሚ ውሀ ወይም ይተኩ።
...
ጤና ይስጥልኝ
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
❀꧁Hakim Mereja - ሀኪም መረጃ꧂❀
ከወደዱት ፔጃችንን #like & #share ያድርጉ!
🔎fb.me/Hakim.Mereja🔍
ቴሌግራም 👉🏻 t.me/HakimMereja
