cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አግንቸው/Aginechew

"መሪ ሰዎች መሄድ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይወስዳቸዋል። ታላቅ መሪ ግን ሰዎች መሄድ ባይፈልጉም ለጥቅማቸው መሄድ ወደሚገባቸው ቦታ ይወስዳቸዋል።"                                     Rosalynn Carter

Show more
Advertising posts
282Subscribers
No data24 hours
-17 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

💥አዕምሮን መመገብ💥 💫ሰውነታችን በየቀኑ ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘት እንደሚያስፈልገው ሁሉ አዕምሯችንም በየጊዜው ገንቢ በሆኑ አስተሳሰቦች መገ'ንባት ይኖርበታል። 💫ሰውነታችንን የማይረባ ምግብ ከመገብነው እንደሚታመም ሁሉ ፣ አዕምሯችንም መጥፎ ሀሳቦችን ካስተናገድንበት ይታመማል። 💫በህይወት ሩጫ በትክክለኛው መስመር ላይ ለመሮጥ ከፈለግን አዕምሯችንን ገንቢ ሀሳቦችን ልንመግበው ግድ ይለናል። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👍 1
የሀሳብ ሀይል❗️ 💫ሀሳቦቻችን የእኛን እውነታ የመቅረፅ ሀይል አላቸው። 💫አሉታዊ አስተሳሱቦች በራስ አለመተማመንን ፣ ፍርሃትንና ጭንቀትን ያመጣል። 💫አወንታዊ አስተሳሰብ ደግሞ በራስ መተማመንን ፣ ድፍረትንና ስኬትን ያመጣል። 💫የአስተሳሰብ ሀይል የተመሠረተው በመሳሳብ ህግ መርህ ላይ ነው። ⏹ይህ ማለት:- ➧በአሉታዊ ሀሳቦች እና ስሜቶች ላይ ካተኮርን አሉታዊ ልምዶችንና ውጤቶችን ወደ እኛ እንሰበስባለን። ➧በአወንታዊ ሀሳቦችና ስሜቶች ላይ ካተኮርን ደግሞ አወንታዊ ልምዶችንና ስሜቶችን ወደ እኛ እንጠራለን። 💨የሀሳብ ሀይልን የመጠቀም ስልት➛➛➛ ●የማስተዋል ችሎታን መለማመድ ●አፍራሽ አስተሳሰቦችን መቃወም ●ስኬትን በአይነ ህሊና ተመልከት ●ራስን በአወንታዊነት ክበብ ●ምስጋናን ተለማመድ ●እርምጃ ውሰድ 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
3👍 1
🥀ለውጥን መግራት🥀 🗣ትራየን ኤድዋርድስ እንዳለው " አስተሳሰቡን ፈፅሞ የማይቀይር ፣ስህተቶችን የማያርም ሰው ነገ በምንም መልኩ የተሻለ ብልሀት ያለው አይሆንም።" 🌟ለውጥ የማይቀር ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። 🌟በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ነገር በሂደት ይለወጣል። 🌟የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን ልዩ ከሚያደርገው አንዱ አስተሳሰብ በመኖሩ ነው። 🌟አስተሳሰቡን ፈፅሞ የማይቀይር ቁሞ ቀር ከሆነ ለማረምም፣ለመታረምም እድል አይኖረውም። 🛑ስለዚህ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የጤነኛ ሰው ባህሪ ነው። 💭ለውጥን ለመግራት የሚረዱ ቁልፍ መንገዶች ✅የለውጥን አዝማሚያ እና ለውጥ የሚጠይቀንን ነገሮች ማጤን፣ ✅ለውጥን ማቀድና ለለውጥ መዘጋጀት፣ ✅ራሳችንን ለለውጥ ምቹ በሆነ ስፍራ ላይ ማድረግ፣ ✅ሆን ተብሎ የሚደረግ ለውጥ። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👍 2 1
❤ሁሉም ነገር ይለወጣል❤ 🗣እንደ ጆርጅ ዊል አባባል " በዚች ምድር ላይ ያሉ ሁሉ የሚጋሩት አይቀሬ ክስተት የወደፊቱ ክስተት ሳይጠበቅና ሳያሳውቀን የመምጣት ባህሪ አለው።" ⏺ለውጥ ከውጭ በግድ የተጫነብን ይሁን፣እኛ የፈጠርነው ወይም ደግሞ በጉጉት እየጠበቅነው የምንገኘው በህይወታችን ግን እጅግ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ክስተቶች አንዱ መሆኑ አያከራክርም። ●በህይወታችን በአራት ዋና ዋና ለውጦች ውስጥ እናልፋለን። ⭕️በእኛ ላይ የሚመጣ ለውጥ ⭕️በዙሪያችን የሚከሰት ለውጥ ⭕️በእኛ ውስጥ የሚከሰት ለውጥ ⭕️እኛው ራሳችን የምንፈጥረው ለውጥ ►ራስን መለወጥ ሌሎችን ከመለወጥ ይበልጣል። ►ለውጥ ሁሌ ለዋጭ ሲሆን ራሱ ግን ተለዋጭ አይደለም። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
🌹ተላምዶ🌹 ☄️ተላምዶ እርስ በርሳቸው ቸጎዳኝተው ከሚከሰቱ የተለዩ ሁኔታዎች ጋር የምንተዋወቅበት ወይም የምንላመድበት ስነ ልቦናዊ ሂደት ነው። ☄️በጣም ታዋቂ ከሆኑት የተላምዶ ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ የፓቭሎቭ ውሾች ናቸው። ሩሳዊው ሳይንቲስት ፓቭሎቭ ለውሾች ምግብ በሰጠ ቁጥር ደውል ይደውላል። ይህን ጊዜ ውሾቹ ምግባቸውን ሲያዩ አፋቸው በምራቅ መሞላቱ የማይቀር ነው። ፓቭሎቭ ይህን ለተወሰነ ጊዜ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ምግብ ሳያቀርብ ደውል ደወለ። እንደዚያም ሆኖ ውሾቹ አፋቸው በምራቅ ተሞላ። ምክንያቱም ከደውሉ ድምፅ ጋር ምግባቸው እንዲቀርብላቸው መጠበቅን ተላምደው ነበር። ☄️አብዛኛው ባህሪያችን የተላምዶ ውጤት ነው። ☄️መልካም ልምዶችን ለማግኘት ቢያስቸግሩም ለመሸከም ቀላል ናቸው። ☄️ መጥፎ ልማዶች በቀላሉ ቢገኙም ለመሸክም ይከብዳሉ። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👏 1
💥ራስን መምራት💥 💫ለመማርም ሆነ ለማወቅ ሀሳብ ያስፈልጋል። 💫ሌላ ሰው አንተን ተክቶ ሊያስብልህ አይችልም። 💫 ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር አጣጥሞ አዕምሮውን ፕሮግራም ማድረግ የሚፈልግ ሰው በራሱ አዕምሮ መመራት አለበት። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ሌሎች ሰዎች በዘፈቀደ አዕምሮውን ፕሮግራምድ ያደርጉታል። 💫አዕምሮህ እንዳስፈለጋቸው የሚጠመዝዙት ጨርቅ ፣ እንደአሻቸው የሚጨፈልቁት ጭቃ፣እንዳሻቸው የሚያሾሩት እንዝርት እንዲሆንላቸው በታዛዥነች የሰዎች ጥገኛና ተከታይ መሆን የለብህም። 💫የህይወት መሪው በእጅህ (በአዕምሮህ) ነው ራስህን ምራበት። 💫ጥገኛ ተከታይ አለመሆን ማለት አፈንጋጭ ወይም አስከታይ መሆን ማለት አይደለም። 💫ራሱን የሚመራ ሰው ጥገኛ ወይም አፈንጋጭ ተከታይ ወይም አስከታይ ለመሆን ፍላጎት የለውም። 💫ከሰዎች የሚሰማውንና የሚማረውን በጭፍን አይቀበልም፣ በጭፍን አይጥልም። 💫ትክክለኛውንና የተሳሳተውን ሀሳብ ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እያመሳከረ ፣ እያየ ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት እያስተካከለ ራስን የመምራት ህግን ተግባራዊ ያደርጋል። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👍 2
💥ፅናት💥 💫በስንፍና ወይም በፍርሃት ፣በተፈጥሯዊ ተግዳሮት ወይም በሰው ሰራሽ ፈተና ሳንበገር በእውቀታችን መሠረት ተግባራችንን የመምራት ፅናት ማዳበር ይገባል። 💫ለእውነታ ታማኝ የመሆን አስተዋይነት ያስፈልገናል። 💫እውነታ ላይ ተመስርተህ እውቀት መገንባት ፣ በእውቀት ላይ ተመስርተህ መምረጥና መወሰን፣ በውሳኔህ ላይ ተመስርተህ መፈፀም ከተጨባጭ ተግባር አንፃር ለእውነታ ታማኝ መሆን ነው ። 💫ድርጊትና ተግባር የእውነታ ውጤት ነው። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👍 2
● አስተዋይነት● 💨ለእውነታ ታማኝ የሆነ አስተዋይነት ከልብ መቀበል ከህሊና መፃፍ በድርጊት መተርጎም ሰው መሆንን ማሟላት ነው። ◉ወደ ላይ የተወረወረ ድንጋይ ተመልሶ ይወድቃል እንደ ፊኛ አይንሳፈፍም።ከስሩ ሌላ ድንጋይ ሲኖር ይቀመጣል፣ እንደውሃ ፍስስ ብሎ አይንቀሳቀስም። ድንጋዩን በጠንካራ ሹል ብረት ስንመታው ይሸራረፋል፣እንደ ጭቃ ስምጥ ስምጥ አይልም። ድንጋዩ ሲምንቶ ተቀብቶ በፀሀይ ሲደርቅ ይጣበቃል፣ እንደቅባት አይቀልጥም።ምክንያቱም ይህ ተፈጥሮ ነው። በፍልስፍና "The law of Identity" በሚል ይጠሩታል። 🛑በተፈጥሮ ህግ ፍልስፍና መሠረት የማንኛውም ሀሳብ እውነትነትና ሃሰትነት፣ትክክልነትና ሀሰትነት፣ጠቃሚነትና ጎጂነት የሚዳኘው ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እንደሚገጥም በማመሳከር መሆን አለበት። 🛑ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር የማይገጥም ሃሳብ እውነተኛ ሃሳብ አይሆንም። 🛑በጭፍን ስሜት ወይም በጭፍን እምነት ተመርተን ተፈጥሯዊ ምንነቶች ከሃሰተኛ ሃሳብ ጋር እንዲገጥሙ ማዘዝ አይቻልም። 🛑በተቃራኒው ሃሳቦቻችን ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እንዲገጥሙ ማድረግ አለብን። 🛑ለዚህም ነው የአዕምሯችን ቀዳሚ ስራ ተፈጥሯዊ ማንነቶችን ማገናዘብ እና ማወቅ ነው። 💫ስለዚህ ሃሳቦቻችን ሁሉ ከእውኑ ተፈጥሮ ጋር እንደመነጩና እንደሚጣጣሙ የሚያረጋግጥልን አዕምሯዊ አቅም በቋሚነት ለመጠቀም መምረጥ አለብን። 💫 ይህን አቅም በሳይንሳዊ መንገድ መጠቀም ነው። ➛ይህም ለእውነታ ታማኝ መሆን ማለት ነው። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
💥ቀላል መፍትሄ ይኖራል ነገር ግን በቀላሉ አይገኝም💥 ☄️ለከባድ ችግር ቀላል መፍትሄ ለትልቅ ስኬትም ቀላል የለውጥ መንገድ ሊኖረው ይችላል። ☄️ቢሆንም ግን ቀላል መፍትሄና ቀላል መንገድ በፍፁም በቀላሉ አይገኙም። ☄️እጅግ የሳይንስ ግኝቶች፣የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና የቢዝነስ ሀሳቦችም ታሪካቸውን ስንሰማ ብዙውን ጊዜ ከጥቃቅን መንስኤዎች ጋር ተያይዘው የምናገኛቸው ያለምክንያት አይደለም። ☄️ለስኬት ዝግጁ የሚሆኑት ለአመታት እውቀት፣ሙያና ክህሎት አዳብረው፣ ሁልጊዜ በትኩረት አዕምሯቸውን ስለሚጠቀሙ ነው ። ☄️ብዙ ቀላል ተግባራት፣ለጊዜው ውጤታቸው ትንሽ ስለሚመስሉ ቸል እንላቸዋለን። ግን በትኩረት ብናከናውናቸው ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ። ☄️ለረጅም ጊዜ ጠብታ ውሃ ሳያቋርጥ ከተንጠባጠበ ድንጋይ ይበሳል። ☄️የተለመደውን እየሰሩ ማግኘት የሚቻለው ያንኑ የተለመደውን የድሮውን ውጤት ነው። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
1
💥ስኬታማ መንገድ💥 💫ስኬት የሆነ ቦታ ላይ ደርሶ የሚቆምና የሚደነዝዝ አይደለም፣ እየተነቃቃና እየጨመረ የሚሄድ እንጂ። 💫 ስኬት በየጊዜው እየጎመራ የሚቀጥል አስደሳች ህይወት። ►ይህ የስኬት ምህዋር ይባላል። 💫የስኬት ሞተራችን ሌላ ሳይሆን አዕምሯችን ነው። 💫መሪያችን ሌላ ሳይሆን አዕምሯችን በመጠቀም የምናሰላው የራሳችን ሀሳብ ነው። 💫እንቅስቃሴያችን ሌላ ሳይሆን የራሳችን ስራና ጥረት ነው። ☄️ማሠብና መስራት ወይም እያሰቡ መስራት! 💫ስኬትን የሚያስገኝ ተዓምር የለም። 💫ትክክለኛ አስተሳሰብ ግን ተዓምር የሚያስኙ ስኬቶችን ያቀዳጃል። ☄️አዕምሯችን በአግባቡ እንዲሰራ የሚያደርግ ስኬታማ የህይወት ሶፍት ዌር መቅረፅ ይገባል። 💥ንቁ ሰው! ሰላም አዳር🕊 "መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
Show all...
👍 2