en
Feedback
Nathan casting agency

Nathan casting agency

Open in Telegram

The best place to get the best casting jobs Our services -casting models - for music clips - movies - series dramas - fashion shows - television shows Contact: 0920358051

Show more
Ethiopia16 170The category is not specified
408
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
😘ያበደው ፍቅሬ😘 ✍ ፅዮን ልብ ወለድ ክፍል 1 ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ። እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው... መፃፍ ጀመርኩ አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል። ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ.... ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻልኩም በሀሳብ ወደ ተገናኘንበት ጊዜ ጋለብኩ.... ከምናምን አመት በፊት በክህደት የተሰበረ ልቤ ላይ ትኩስ ሀዘን ተደምሮበት ግራ ቀኜን ሳላይ እግሬ ወደመራኝ ስጓዝ ሲጥጥ ብሎ እግሬ ስር የቆመ መኪና ከሀሳቤ አነቃኝ... አልደነገጥኩም እንደውም ተናደድኩ ለምን ፍሬኑን ያዘው? ለምን አልገጨኝም? ብሽቅ... የማይገኝ እድል አስመለጠኝ.... ይህን ሁሉ የማስበው ከመኪናው ወርዶ በአካባቢው ከነበሩ ሰዎች ጋር የስድብ ናዳ ሲያወርድብኝ ነው። "ያምሻል.... እያዬሽ አትሄጂም..... መሀል አስፓልት ላይ ምን ትሰሪያለሽ...... እብድ ነሽ..... ጦስ ውስጥ ከታው ነበር........." አይገርምም አንድ እንኳን ችግሬን ለማወቅ የፈለገ ምን ሆና መሀል አስፓልት ላይ ተገኘች ያለ ሰው የለም.... አስመሳይ ብቻ። እጄን ይዘው ወደዳር ወስደውኝ የጀመሩትን ስድብ ያዘንቡብኝ ጀመር... ለትንሽ ሰከንድ አየሁዋቸው... ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ 'ዞር በሉልኝ አስመሳዮች' ያልኳቸው አላስደነገጠኝም ምክንያቱም ይሉኝታም ሆነ ሀፍረት ከኔ በእጥፍ እርቀዋል... ይሉኝታ የተሰጠው ለሰው ነው እኔ ደግሞ ከሰውነት ደረጃ በትንሹ ወርጃለው..... ምናልባትም እንደማስበው አልወረድኩ ይሆናል ግን በቃ ለኔ የሚሰማኝ ያ ነው...... በበረሀ ላይ ያለ እህል ውሀ የተጣልኩ..... ሙቀት ሀሩሩ ያነደደኝ..... ከአካላቴ አብዛኛውን በከሀዲዎች የተነጠኩ.... ለመኖር ተስፋ ለመሞት አቅምና ወኔ የሌላት ፍጡር እንደሆንኩ ይሰማኛል። አዎ ለመሞትም እኮ አቅም እና ወኔ ያስፈልጋል.... ወኔ ቢኖረኝማ ይህን ጊዜ ሙት አመቴ አልፎ ነበር። ስልችት፣ ድክም፣ ልፍስፍስ እላለሁ... ማሰብ ያደክመኛል... መብላት መጠጣት ይሰለቸኛል... ስሜን ጠርተውኝ እንኳን 'አቤት' ማለት ትልቅ ተራራን የመግፋት ያክል ይሆንብኛል። የልብ ስብራት ብቻ ሳይሆን ከአካል ክፍሎቼ እያንዳንዳቸው ስብርብር እንክትክት እንዳሉ ይሰማኛል። በቃ ዝምምምም ብሎ መኖር ከነኝህ ጊዜያቶች በአንዱ ነው እንግዲህ ከዚህ ሰው ጋር የተገናኘሁት.... በቆሙበት ትቻቸው እየሄድኩ ነው ከኋላዬ የራቀ ድምፃቸው ይሰማኛል..." ያማታል መ ሰ ለ ኝ..." እኔ ግን እየሄድኩ ነው... ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ..... ይቀጥላል.... ቻናላችንን ይቀላቀሉ ከወደዳችሁት ❤️ ━━━━━━━━ ✦ ሀሳብ አስተያየታችሁን @nahita2 አድርሱኝ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 @fkrnahiwot @fkrnahiwot ♥♥♥♥♥♥♥ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fkrnahiwot ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @nahita2

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል ❻ ✍ በሼን . . . ቀናቶች ነጎዱ ሀኒ ጋር የነበረን ነገር በጥፍ እያደገ መጣ ቶሎ ቶሎ መደዋወል ቀን በቀን መገናኛት ብቻ ሀሪፍ ግዜዎች በማይረሱ ትዝታወች እየታጀቡ አለፉ ሀኒ በጣም ደስተኛ እየሆነች መጣች። ከኔ ይልቅ መገናኛታችንን በጣም የምትፈልገው እሷ ሆነች እኔ ግን ቀናቶች በሄዱ ቁጥር ለሷ ያለኝ ነገር እየጨመረ፣ የማላቀው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ቢመጣም መጨነቄ ግን አጅጉን በዝቷል ትንሽ ነገር እንኳ አሞኛል ስትለኝ ቀኗ ደርሶ የማጣት የማጣት የምር የምትለየኝ እየመሰለኝ ሁሉንም ቀን ዶክተሩ በደብዳቤው ያላት ነገር ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል መልሼ ደግሞ ነገን ማን ያቃል? እላለሁ የሀናን የመንፈስ ጥንካሬ ሳስታውስ። ዛሬ ደስ እያለኝ ደስ በሚል መንፈስ ታጅቤ ነው በጥዋት የተነሳሁት ምክንያቱም ዛሬ የኔ ቀን ነው የኔ እሁድ ጥሎብኝ አሁድን በፍቅር ነው ኘየምወደው አንዳንዴ ገና አርብ ላይ ሁኜ ነው እሁድን በጉጉት የምጠብቃት አንዳንዶች እሁድ ደባሪ ቀን ነው ፣ እሁድ አራት ቀን ነው የሚሆንብኝ ምናምን ሲሉ ስሰማ በጣም ያበሳጩኛል እንደውም በእሁድ እና በሰኞ መሀከል ሌላ ዳግም እሁድ ቢኖር ሁላ ደስ ይለኛል ምክንያቱም እሁድ ነዋ ቀኑ። ካልጋየ እንደተነሳሁ እንደወትሮየ የመጀመሪያ ስራየ ያደረኩት ሻወር መውሰድ ነበር ከሻወር ጨርሼ ስወጣ እህቴ ቁርስ እያቀረበች ነበር የምቀይረውን ልብስ እንድታዘጋጅልኝ ነግሪያት ለቁርስ እንደተቀመጥኩ የስልኬ መጥሪያ ሲያቃጭል ሰማሁት እህቴን ስልኬን ከመኝታ ቤት እንድታቀብለኝ አድርጌ ወደ ቁርሴ ተመለስኩ በመሀል አንተ ቆንጆዋ ብለህ ሴቭ ያደረከው የማንን ስልክ ነው አለችኝ እህቴ የሚጠራውን ስልክ ወደኔ ይዛ እየቀረበች,,, ፈገግ አልኩ ሀኒ ነበረች ስልኳን ከወሰድኩ ቀን ጀምሮ ቆንጆዋ ብየ ነበር የመዘገብኩት ስልኩን ከህቴ ተቀብየ ላነሳው ስል ተዘጋ ወዲያው መልሼ ደወልኩ ስልኩ እንደተነሳ አንተ አይጥ እየተኮራ መሆኑ ነው እንዴ ስልክ የማታነሳው የሚለው የሀኒ ድምፅ ተሰማ ብኮራስ ምን ያንሰኛል ያለውሀ የምዋጥ ቆንጆኮ ነኝ ብየ መለስኩላት ሳቀች እና ቀጠሮአችን እንደተከበረ ነዋ አይደል አለችኝ በጥያቄ ቅላፄ? የምን ቀጠሮ አልኳት አውቄ ነበር,, ቀጠሮ እንዳለን አረሳሁትም ትናት ማታ ላይ ስንለያይ ነገ የሆነ የምወስድብህ ቦታ አለ ብላኝ ነበር ቦታውን ግን አልነገረችኝም ትናት ምን ነበር ያልኩህ አለች ኮስተር ብላ ተናዳለች ስትናደድ ድምፇ ይቀየራል እ,እ,እ አልኳት እንደገና ያስታወስኩ አስመስየ አኔኮ እየቀለድሽ ስለመሰለኝ ነበር እንጂ እንዳወራንማ አረሳሁትም ስላት ስታናድ በቃ እንደደወልኩልህ እንድትወጣ ደሞ እናዳታረፍድ ቻው ብላ የኔን ቻው ማለት ሳጠብቅ ስልኩን ዘጋችው ወዲያው ማነች ቆንጆዋ ብለህ ሴፍ ያደረካት ሴት አለችኝ በድጋሚ የጥያቄዋ ፍጥነት ስልኩ አስኪዘጋ በጉጉት ስጠብቅ እንደነበር ያሳብቅባታል እህቴ በእድሜ ታናሼ ብትሆንም ለነገሮች ያላትን የአመለካከት ብልጠት እና አረዳድ ስለማቅ ምንም ነገር አልደብቃትም የሀኒን ግን አስካሁን ለምን እንዳልነገርኳት ገርሞኛል የጀመርኩትን ሻይ እየጠጣሁ ስለ ሀኒ አንዳችም ነገር ሳላስቀር እንዴትና መቼ እንደተዋወቅን ፣ ስለ ሀኒ ውበት ፣ ስለባህሪዋ ፣ ስላሳለፍናቸው ሀሪፍ ግዜዎች ፣ ሹራቡ ኪስ ውስጥ ስላገኛሁት ፖስታና ውስጡ የያዘውን መልክት ፣ ዶክተሩ ስለ ሀኒ የጤና ሁኔታ ያላትን የ ጭንቅላት እጢ ተጠቂ እንደሆነችና ቢበዛ ከ አራት ወር በላይ በሂወት ልትቆይ እንደማትችል,, ብቻ አንድ በአንድ ዲያሪየ ላይ ያሰፈርኩትን በሙሉ እንደወደድኳት ጭምር እንደትረካ ተረኩላት አንገቷን አቀርቅራ ዝም ብላ ቆየችና ግን እንዴት አለችኝ? ድንገት ካቀረቀረችበት ቀና ብላ አይኗቿ እምባ አዝለዋል እንዴት የሚለው ጥያቄዋ ስላልገባኝ መልስ አልሰጠሁዋትም ነበር ትንሽ ቆይታ እንዴት እንደዚህ አይነት ከባድ ችግር ይዛ ለዛውም የምትሞትበትን ቀን ተነግሯት እንዴት እንደዚህ አንተ ጋር ልትሆን ቻለች እንዴትስ ያላንድ ጭንቀት ለዛውም ቀን በቀን ትዝናናለች አንተስ ብትሆን እንዴት ይሄን እያወክ አብረሀት መሆንን መረጥክ እሺ አብረህ መሆኑን ሁን እንዴት።እንደምትሞት እና በቅርብ እንደምታጣት ውስጥህ እያመነ እንዴት ልትወዳት ቻልክ ብላ አፋጠጠችኝ እውነቱን ለመናገር የሀኒ ነገር ሁኔታ እኔንም ሁሌ ያስገርመኝ ነበር መልስ ስላጣሁ እንጂ ብዙ ጥያቄ የሚፈጥሩ ነገሮች ገጥመውኛል ከተራ ራስ ምታት ውጭ አንድም ቀን ጠንከር ያለ ህመም አይቸባት አላቅም ፣ ሁሌም ሳቂታና ተጫዋች ናት በተለይ እኔ ጋ ስትሆን በደስታ ብዛት እንደህፃን ልጅ ነው የምትቦርቀው ግን ደግሞ እሷን እንዲህ ነው ብሎ መጠየቅ ስለምፈራ ችላ ብየው ዛሬን ብቻ ከሷጋ ደስተኛ መሆንን መረጥኩ ነገን ማን ያቃል ,,, ደሞ እንደዚህ ይሆናል ብየ አልነበረም ስቀርባት ደብዳቤውን ካነበብኩ በዃላ ሀኒ ሰው እንደሚያስፈልጋት ስላወኩ ብቻ ቀርቢያት በምችለው ሁሉ ከጎኗ ልሆን እና ባላት ትንሽ ግዜ ደስተኛ ሁና እንድትኖር ስለፈለኩ ነበር ሆን ብየ ጓደኛ አድርጊያት የሚያስደስታትን ነገር ለማድረግ ስጥር የነበረው እያደር ግን ነገሮች እራሳቸው መልካቸውን እየቀየሩ መጡ እንዲህ ነው የሚባል የተለየ ነገር ባናደርግም እኔ ግን ለሀኒ የነበረኝ ስሜት ተቀይሮ ነበር ደሞ እኛ ስለፈለግን ስላልፈለግን ብቻ እኳ አደለም ሰውን ልንወድ እና ልናፈቅር የምንችለው አንዳንዴኮ እኛ ባልገመትነው እና ባላሰብነው ሁኔታ ነገሮች እራሳቸው በራሳቸው ግዜ እዚህ ስሜት ውስጥ ያስገቡናል መላመድኮ ከባድ ነው እኔም ጋ የሆነው ይሄው ነው። ይሄ ይሆናል ብየ አስቤ አልቀረብኳትም ግን ሆነ ሀኒ የምትወደድ ልጅ ነበረች ወደድኳት , , አንዳንንዴ ያንቺ እንዳልሆነ እና እንደማታገኝው እያወቅሽስ ታፈቅሪ የለንዴ ደሞ ,, ነገ ምን ይሁን ምን ይፈጠር ማን ቀድሞ ይሙት ማንም እሚያቅ የለም አየመሰለን እራሳችንን እናስጨንቃለን እንጅ አልኳት ስሜታዊ ሁኜ ነበር ስናገር የነበረው መጨነቄን በሀኒ መውደድ ውስጥ የደበኩት ይመስል በድፍረት ነበር የመለስኩላት ምንም ነገር አላለችኝም ,, ላፍታ ዝም ብላ ከቆየች በዃላ እንደምትወዳት ግን ታቃለች እሷ አለችኝ ነግሪያት እንደማላቅ እና የሚሰማኝን ነገር ሁሉ ከተለያየን በዃላ ዲያሪየ ላይ እንደምፅፈው ነገርኳት እሺ እሷስ ትወድሀለች ስትል ሌላ ጥያቄ አስከተለች እሱን አላቅም ግን ሁሌም ከኔ ጋ ስትሆን ከምንም በላይ ደስተኛ እንደምትሆን እና ቶሎ ቶሎ እንደምናፍቃት ሁሌም ነው የምትነግረኝ ብየ መለስኩላት ፈገግ አለችና እሽ መች ነው የምታስተዋውቀኝ አለችኝ? ደስ ባለሽ ቀን አልኳትና ቀና ብየ የግርግዳውን ሰአት ተመለከትኩ ሰአቱ እንዴት ይሮጣል አልኩ በሆዴ ወዲያው ተነስቼ በፍጥነት መለባበስ ጀመርኩ አለባበሴ ከወትሮው የተለየ ነበር ያለማጋነን ሽክ ብለሀል የሚለው ቃል ይገልፀኝ ነበር ለዚህ ደሞ እህቴ የመጀመሪያዋ ምስክር ነበረች ዛሬ የምትመለስ አትመስልም እንዳትጠለፍ አለችኝ ከላይ ወደታች በግርምት እያየችኝ በገመድ ነው ብየ ቀልጄባት ሀኒ እስከምትደውል ድረስ ፀጉር ቤት ለመሄድ አስቤ ከቤት ወጣሁ ። ገና የግቢው በር ላይ ሳልደርስ ሀኒ ደወለች አነሳሁት ,, የት ነህ አለችኝ ከቤት ልወጣ እንደነበር እና እስከምትደውል ፀጉር ቤት ልሄድ እንደነበር ነገርኳት

እንዲጀምር ሚፈልግ
እንዲጀምር ሚፈልግ

እንዲጀምር ሚፈልግ
እንዲጀምር ሚፈልግ

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል ➎ ✍ በሼን . . . ሀኒኮ እንዲህ ስትስቅና ስትጫወት ላያት እንኳን ያን ያክል ለነገሩ ባለቤት ቀርቶ ለሰሚው የሚከብድ ችግር የያዘች ይቅርና ተራ ጉንፋን እንኳ የያዛት አትመስልም አልኩ ለራሴ ይህን እያውጠነጠንኩ ሳለ ታክሲ መጣ መሰል እስኪ አስቁመው የሚለው የሀኒ ድምፅ ከሄድኩበት ሀሳብ መለሰኝ ወዲያው የአቁምልኝ ምልክት ወደታክሲዋ እጄን ጠቆምኩ እንዳጋጣሚ የመጣችው ታክሲ የጋቢና ወንበሮች ሁለቱም ክፍት ነበሩና እኔና ሀኒ ተከታትለን ገብተን ጉዞ ወደቤት ተጀመረ ደስ የሚል ግዜ ነበር አለችኝ ዞር ብላ እያየችኝ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል ግን አይኔን ትንሽ አሞኛል አልኳት ምን ሁነክ አመመክ አለችኝ እኔንጃ ግን ልጅ እያለሁ ትኩር ብየ ቆንጆ ሳይ አይኔን ያመኝ እንደነበር አስታውሳለሁ አልኳት ፈገግ እንዳልኩ ,, ሂድ ወረኛ አለች እና ንግግሯን በሳቅ አጀበችው ሁሌ ሳቂ አልኩ በውስጤ ለምን እንደሆነ አላቅም ብቻ ሀኒ ስትስቅ ውስጤ ድረስ ዘልቆ የሚገባ የደስታ ስሜት ይሰማኛል ምን እያሰብክ ነው ? የሷ ጥያቄ ነበር ሳስብ የነበረውን ያወቀችብኝ ይመሰል ድንግጥ አልኩ በዚህ መሀል የሀኒ ስልክ ጠራ አይኔን ወደ ስልኩ ላኩ በእንግሊዘኛ ፊደላት DAD ተብሎ ተመዝግቧል የተደወለው ስልክ አነሳችውና ሀሎ ዳድ አለች ከወዳኛው የሚመጣው ድምፅ አይሰማኝም ነገር ግን አንዳንድ የቤተሰብ ጉዳይ እያወሩ እንደሆነ ከሀና መልስ ለመረዳት ችያለሁ, , አንድ አንድ እያሉ ብዙ ካወሩ በዃላ ወደ መጨረሻ አልቆይም ባባየ በቅርብ እመጣለሁ, ,, እኔም በጣም ነው የናፈከኝ ብላ ተሰናብታ ስልኩን ዘጋችው ዳድ ነው አለችኝ ስልኳን ወደኪስዋ አያስገባች ምንም አልመለስኩላትም ግራ ገባኝ ፖስታው ውስጥ ያነበብኩት ደብዳቤ ላይ አባት እንደሌላት አባትም እናትም ሁና ያሳደገቻት እናትዋ እንደሆነች ነበር ያን እያውጠነጠንኩ መውረጃችን ደረስንና ወረድን ጨለም ብሏል አንችን ልሸኝሽ እና እመለሳለሁ ብያት ሹራቧን የያዘውን ፌስታልዋን እንዳንጠለጠለች መንገድ ጀመርን ብዙ አላወራኋትም ቤቷ ስንደርስ ሳተኝ በፊት ደውላለሁ አልኳትና ጉንጯን ሳም አደረኳት እሽ እኔም ካልተኛሁ አነሳለሁ አለች ፈገግ ብላ , ,,ቤት አስክደርስ ድረስ ሀሳቤ የሀና ነገር ነበር አባቴ ያለችኝ ነገር ደሞ ይበልጥ አወዛገበኝ ቤት እንደደረስኩ ራት በላሁኝ እና እንደወትሮየ የቀን ውሎ መመዝገቢያ (ዲያሪየን) አወጣሁና ሀኒ ጋር ያሰለፍነውን ሀሪፍ ግዜ ስለሀኒ እየተሰማኝ ያለውን ስሜት ስለ አባትዋ ብቻ ሁሉንም አንድ በአንድ በፅሁፍ አሰፈርኩት እና ደግሜ ለራሴው አነበብኩት ፈገግ አልኩ,, ልብሴን ቀየርኩና ወደመኝታ ክፍሌ አመራሁ እና ጋደም አልኩ ካልጋየ ጎን የተቀመጠችው ትንሽየ ቴፕ መደበኛ የመዝናኛ የሬዲዮ ስርጭት እየስተላለፈች ነበር ጆሮየን እሱ ላይ ጣል አደረኩ የፕሮግራሙ አጀንዳ ደግሞ የትዳር አጋርዎን ወይም ፍቅረኛዎን በምን አጋጣሚ ነበር ያገኙት የሚል ነበር ,,, አድማጮች ከስርጭቱ የተላለፈውን ስልክ በመጠቀም እየደወሉ አጋጣሚዎቻቸውን ተናገሩ ካንዳንዶቹ ውጭ የብዙወቹ የትዳር አጋጣሚ ተመሳሳይ ነበር በመስሪያ ቤት ፣ ሰርግ ላይ፣ በፌስቡክ ፣ በዘመድ ፣ በትምርት ቤት ሂወት ,,,ወዲያው ሀኒ ትዝ አለችኝ ቶሎ ብየ ደወልኩላት እና ሬድዮ እንድትከፍት ሀሪፍ ፕሮግራም እንደሆነ የጣቢያውን ቻናል ነግሬ እንደምንም አሳመንኳት እና እሽ አለችኝ ከዛም ቶሎ አልኩና ስርጭቱ መስመር ላይ ደወልኩ መስመሩ ተይዟል ደግሜ ደወልኩ አሁንም ተይዟል ተናደድኩ የመጨረሻ አንዴ ልሞክር አልኩና ስደውል ጠራልኝ ወዲያው ስልኩ ተነሳና አንድ ቀጭን የሴት ድምፅ ሀሎ ጤና ይስጥልኝ ማን እንበል ከየት ነው አለችኝ ስሜን እና ያለሁበትን ከየት እንደሆነ ተናገርኩ መናገሬን ቀጠልኩ ያሁን ፍቅረኛየን እና የወደፊት ሚስቴን ሀኒን ያገኛሁዋት ታክሲ ውስጥ ነበር ያን ቀን ታክሲ ውስጥ ከሀኒ ጎን ነበር የተቀመጥኩት ቁንጅናዋ በጣም የተለየ ነበር እንዳየኋት ነበር ልቤ የደነገጠላት በምን በተግባባሁና በተዋወኩ እያልኩ ሳስብ አጋጣሚ ሁኖ ቆንጆዋ ሀኒ ተሰርቃ ይሁን ጥላው ባዶ ኪስዋን ነበር ታክሲ ውስጥ የነበረችው ስትጨነቅ አየሀኋት እና ሂሳብ ከፈልኩላት ያን ቀን የኔና የሀኒ ግንኙነታችን ሀ ተብሎ ተጀመረ በግዜ ሂደት በጣም እየተግባባን መጣን ሀኒ ሁሉ ነገርዋ የምትወደድ ልጅ ስለሆነች ከልቤ አነገስኳት እሷም እንደዛው አሁን በጣም የምንዋደድ ፍቅረኛማቾች ሁነናል ባሁን ሰአት ሀኒ ከጎኔ ባትሆንም መስመር ላይ ስርጭታችሁን እየተከታተለች ስለሆነ እባካችሁ በጣም እንደምወዳት እና በድጋሚ ግን ታክሲ ላይ ስትወጣ ብር ሳትይዝ እንዳትወጣ መልክቴን አድርሱልኝ አመሰግናለሁ ብየ ስልኬን ዘጋሁት እንደዘጋሁት ወዲያው ሀኒ ደወለች በጣም እየሳቀች ነበር አንተ ደፋር በጣም ነው ያስደነገጥከኝ እሽ ምንም ያልገመትኩትና ያላሰብኩት ነገር ነው ዘና አድርጎኛል አስደንግጦኛልም ግን በጣም አመሰግናለሁ አለችኝ። ቀናቶች ነጎዱ ሀኒ ጋር የነበረን ነገር እያደገ መጣ ቶሎ ቶሎ እንደዋወላለን ቀን በቀን እንገናኛለን ሀሪፍ ግዜወች እናሳልፋለን ሀኒ በጣም ደስተኛ እየሆነች መጣች ከኔ ይልቅ እሷ መገናኛታችንን በጣም ትፈልገው ጀመረች እኔ ግን ቀናቶች በሄዱ ቁጥር ለሷ ያለኝ ነገር እየጨመረ ቢሄድም መጨነቄ ግን በዝቷል ትንሽ ነገር አሞኛል ስትለኝ ቀኗ ደርሶ የማጣት የማጣት እየመሰለኝ ሁሉንም ቀን በደብዳቤው ላይ የገለፀችው ዶክተሩ ያላት ነገር ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል •••• ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fkrnahiwot ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @nahita2 ❥❥________⚘_______❥❥

ታሪኩ እንዲቀጥል ሚፈልግ ካለ👍 ሌላ እንዲጀምር ሚፈልግ ካለ✋

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል ❹ . . . ኧረ ምንም ችግር የለ ሀኒ አለችኝ በተቆራረጠ ድምፅ ፊቷን በግድ ፈገግ ለማድረግ እየሞከረች ፊትሽኮ ምንም ሰላም አይታይበትም በዛ ላይ አይንሽ ቀልቷል እንዳለቀሽ ያስታውቃል አልኳት ምንም ሳትመልስልኝ አንገትዋን አቀርቅራ ፀጥ አለችኝ እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ አልዋጥልሽ አለኝ ድንጋጤየ ጨመረ ቀጥታ ወደቢሮው ገባሁና ይቅርታ ዶክተር ምንድነው እየሆነ ያለው ለምን ታስጨንቁኛላችሁ ብየ ጮህኩ እምባ እየተናነቀኝ ያኔ ነበር ዶክተሩ ከብዙ የማስተዛዘኛ ቃላት እና ምክሮች በዃላ የጭንቅላት እጢ (brain tumoer) እንደተገኘብኝ እና በመጠንም ትልቅ እጢ ስለሆነ በቀዶ ጥገና ሊድን እንደማይችል ግፋ ቢል በሂወት ልቆይ የምችለው ከ 3 ወር እንደማይዘል የነገረኝ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ በተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝ ከዛች ቀን ጀምሮ ሂወት ጨለመችብኝ ሁሉ ነገር አስጠላኝ ብቸኝነት ጓደኛየ ሆነ ስቃይ እና ለቅሶ የዘወትር ስራየ ሆኑ ሳራ ልታፅናናኝ ብዙ ትለፋች ትደክማለች ለኔ ግን ሁሉም ቀን አንድ ነበር የስቃይ እና የጭንቀት ቀን ሳራ እንደነገረችኝ ደክተሩ በመጀመሪያ የፈለገው አንድ ያለችኝን እናቴን አስጠርቶ ለሷ ለመንገር እንደነበር እና ሳራን ሲያማክራት ግን እናቴ የልብ ድካም በሽተኛ እንደሆነችና አንድ ያለሁዋት ብቸኛ ያይን ማረፊያዋ እኔ ስለሆንኩ ይህን ብትሰማ ወዲያው በድንጋጤ እንደምትሞት ስለነገረችው ነበር ሁሉንም ነገር ለኔ እና ለሳራ የነገረን እኔም ከዛች ቀን ጀምሮ የውስጤን ስቃይ አፋኜ ይዤ እናቴም ጠርጥራ ወይ ሰምታ አንድ ነገር እንዳቶንብኝ ስል እሷ ጋር ስሆንና እሷ ባለችበተ ቦታ ሁሉ በማስመሰል ደስተኛ የሆንኩ ያክል ጥርሴን በለጭ እያደረኩ ለብቻየ ስሆን ደሞ ህመሜና ጭንቀቴ በለቅሶ ይወጣ ይመስል ሳነባ እውላለሁ አየህ አቤል አንተ በሌላ የተረጎምከው እምቢታየ ምክንያቱ ይሄ ነበር ለምን የማልጨርሰውን ነገር እጀምራለሁ አንተስ ጋር ሁኛ ምንም ላልፈጥርልህ ለምን ደስታህን አጨልማለሁ አቤል እኔኮ እንኳን ለሰው ደስታ ልፈጥር ይቅርና ደስታ ራሱ ምን እንደሆነ የጠፋብኝ የመኖር ገደቤን አውቄ ሞቴን የምጠብቅ ሴት ነኝ ላንተ አልገባም አቤል አንተ ደሞ ብዙ ነገር ይጠብቅሀል ገና ስለዚህ ተስፋ ያላት የምትወድህ ልጆች ወልዳልህ ቤትህን በደስታ የምትሞላልህ ሴት ታስፈልግሀለች ለዚህ ነበር ሁሌም ጥያቄህን በእምቢታየ ስሸሽ የቆየሁት ምንአልባት ግን ዛሬ ትረዳኛለህ አቤል አሁን የምፈልገው ነገር አንድ ነገር ብቻ ነው " የቃል አደራ" ይህን ሀዘኔንን ካንተ ውጭ ማንም አውቆ ከንፈሩን በሀዘን እንዲመጥልኝ አልፈልግም እና ደሞ ይሄ ነገር እናቴ ጆሮ ከደረሰ ያለጥርጥር እንደምትሞትብኝ አውቃለሁ ስለዚህ በፈጣሪ ስም አደራ እጠይቅሀለሁ ሁሌም የደስታ ሂወት እመኝልሀለሁ ። ይል ነበር ፖስታው ወስጥ ያገኛሁት ወረቀት ላይ በፊቱም በጀርባውም የተፃፈው ረጁሙ ደብዳቤ ,,,,እንደነበረ አጥፌ አዛው ፖስታ ውስጥ ጨምሬ ከሹራቡ ኪስ አኖርኩትና ወዳልጋየ አመራሁ እህቴ ራት አትበላም እንዴ ስትለኝ ነበር አለመብላቴንም ያስታወስኩት ,, ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም ነበር መብላት አላሰኛኝም አልኳትና አልጋ ላይ ጋደም ብየ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ አቤል የሚባለው ሰው ይሄን መልክት ሲያነብ ምን ይሰማው ይሆን ሀናንስ ምን ያክል ግዜ ነው በሂወት የምትቆየው የሀናን እናትስ ልጃቸውን ሲያጡ ምን ይሆኑ ይሆን ብቻ ብዙ ብዙ አሰብኩኝ ልክ ብዙ ቀን የምንተዋወቅ የቅርብ ሰው የሆነች ያክል ነበር የተሰማኝ ይህን እያብሰለሰልኩ በመሀል ደውልልሻለሁ ያልኳት ነገር ትዝ አለኝ እንዳረብሻት በቃ ጧት ደውልላታለሁ አልኩ ለራሴ ቆይቼ ግን ደሞ ሌላ ነገር እንዳታስብ አልኩና ደወልኩላት ገና ትንሽ እንደጠራ አነሳችው ምንም ነገር እንዳልሰማ ሰው ሁኜ ነበር ያወራሁዋት ,,, ተኝተሽ ነበር እንዴ አልኳት ኧረ አልተኛሁም አለች ምን እየሰራሽ ስለኔ እያሰብሽ ነዋ አልኳት ሳቀችና አዎ በጣም እያሰብኩ ነበር አለችኝ ምን ምን አሰብሽ አስኪ ንገሪኝ ? እእእ ታክሲ ላይ የጠፋኝን ብር አንተ እንደሰረከኝ እና ቆንጅየ ሌባ እንደሆንክ ብላ መለሰችልኝ መልሷ አስቆኛል እንዴ ይህን ያክል አንገብግቦሻል እንዴ ብሩ ደሞስ ብሰርቅሽ የታክሲ ከፍየልሻለሁ አይደል እንዴ ውለታማ አትካጅ አልኳት ሳቀች መልሳ ብቻ እንዲህ እንዲህ እያልን ብዙ ነገር እያወራን በመሀል ስልኬ ተቋረጠ ባላንሴን ሳየው 00:12 ሳንቲም ይላል ተናደድኩ ወዲያው ደወለችልኝ ምን ሁነህ ነው የዘጋኸው አለችኝ የቴሌዋ ሴት መኝታ ክፍሌ መጥታብኝ ነው አልኳት አልገባትም ማናት የቴሌዋ ሴት ብላ ጠየቀችኝ እንዴ አታቂያትም ያች ያለወት ቀሪ ሂሳብ ምናምን የምትለው ስላት ካርድ ዘግቶ መሆኑ ገባት እና በጣም ሳቀች አስከትላ 5 ብር ሞልተህ ነው እንዴ ታዲያ ሴት ጋር የምትደውለው አለችኝ ምንችግር አለው ለመጀንጀን አልደወልኩልሽ አልኳት እየቀለድኩ ,, ልጀነጅንም አምሮሀል እንዴ ?,, ውይ እኔ እንኳ ያንቺ አይነት ቆንጆ የመጥበስ እቅድ ስለሌለኝ አልጀነጅንሽም አልኳት ኮስተር ብየ ለምን ሲባል አለችኝ ቆንጆ መጥበስኮ የተለኮሰ ስቶቭ ላይ መቀመጥ ነው ማን ይቃጠላል መለስኩላት በድጋሚ ሳቀች ለምን እንደሆነ እንጃ ግን ስትስቅ የሆነ ስሜት ይሰማኛል በቃ ልተኛ ነው አለች ብዙ ነበር ያወራነው እሽ በቃ ተኚ ነገ ሹራብሽን ልትወስጅ ስትመጭ የሰረኩሽ ብር ስላላለቀ እጋብዝሻለሁ እሺ ለካ ሹራብ አለኝ ረስቸው አለችኝ በቃ ነገ ደውልልሻለሁ አልኳት እና ቼው ስትለኝ እኔም ውድድ አደርግሻለሁ አልኳት በቀልድ ለዛ ሳቀችና እንዴ ማን እወድሀለሁ አለህ ? አይ በቃ ጆሮየ ነው ማለት ነው ብየ ቀለድኩባትና ቼው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ ,,, አይገርምም ሹራቡ እኔ ጋር መኖሩን ረስታው ነበረ ደስ አለኝ ምክንያቱም የፖስታውን ወሬ ታነሳብኛለች ብየ እየፈራሁ ነበር ያንቀን ማታ እንቅልፍ አለወሰደኝም ነበር በቃ ዝም ብየ ካንዱ ሀሳብ ወደ ሌላ ሀሳብ ስገላበጥ አደርኩ ለራሴ ግን አንድ ነገር ቃል ገብቼ ነበር ፖስታውን እንዳላየሁት አድርጌ መመለስና የሀናን የቅርብ ጎደኛዋ መሆን ከዛም እሷን ያስደስታታል ብየ የማስባቸውን ነገሮች በሙሉ ለሷ ማድረግ ብቻ ብዙ ሰአቴን ለሷ መስጠት ,, በሚቀጥለው ቀን ከሰአት ቡሀላ ተደዋወልንና ሹራቧን ልመልስላት ከሀናን ጋር ተገናኛን ሀኒ የዝናቡ ቀን ምሽት ካየዃት በላይ በጣም ውብ ሁና ነበር የመጣችው ፍዝዝ ብየ አየኋት ምንድነው አንተ ተመሰጥክኮ አለችኝ አውቀሽ ነዋ እንደዚህ ቆንጀ ሁነሽ የመጣሽው? እንዴት አለችኝ ተሳስቼ እንድጠብስሽ ነዋ አልኳት ስቄ ኧረ አንተ ቆንጆ አጠብስ ምን አስጨነቀህ ,, እንዳጋጣሚ ያን ቀን ዙም ሲኒማ አማርኛ ኮሜዲ ፊልም መቶ ነበርና ካልገባን አልኳት ይመሻል ቤት ይቆጣሉ ሌላ ቀን ይሁንልኝ አለች ,,እንደመግደርደር እንደሆነ ገብቶኛል ባክሽ እኔም ሴት ሁኜ ሁለት አመት አይቸዋለሁ አንዳንቺ ግን አልግደረደርም ነበር ሌላ ግዜ ደሞ ለልማት ምናምን

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል 3 ✍በሼን . . . ላንበው አላንበው ከራሴ ጋር ሙግት ገጠምኩ ካፍታ ሙግት በዃላ ወረቀቱን አውጥቸ ዘረጋሁት እና ማንበብ ጀመርኩ ገና የተወሰኑ መስመሮች እንዳነበብኩ ልቤ በድንጋጤ ስንጥቅ አለ የማነበውን ነገር ማመን ከበደኝ ደግሜ አነበብኩት አሁንም ያው ነው የተቀየረ ነገር የለም ውስጤ ብዙ ነገር ተመላለሰብኝ መልስ በማላገኝለት ጥያቄ እራሴን አስጨነኩኝ, ,,,,ሚስኪን የሰው ልጅ ሸክላ በሆነች ድንገት በምትሰበር ሂወት ውስጥ እየኖርን ስንቱን ነገር ስናስብ እና ስናቅድ ስንቱን ነገር ስናወርድ እና ስናወጣ እንውላለን ብቻ ሰውነት ከባድ ነው ,,የምር አንጄቴን በላችኝ ለካ ከላይ ስንታይ ሌላ ውስጣችን ሌላ ነን ለዛ ነው ስለማንም ከላይ ብቻ አይቶ መፍረድ ከባድ ነው የሚባለው,, በደማቅ ሰሚያዊ እስክርቢቶ በቀጫጭኑ ተፅፎ በሀዘን የተሞላው ደብዳቤ ቃል በቃል የሰፈረው እንደሚከተለው ነበር ,,,,,,ይህን ነገር ስፅፍልህ ውስጤ በሀዘን እየደማ ማስመሰል የሰለቸው ፊቴ በእምባ እየራሰ ነበር ማልቀሱና ስቃዩ ለኔ እንግዳ ነገሮች አይደሉም ነገር ግን አስከዛሬ የውስጤን ህመም ለማንም ተንፍሸው አላቅም ለማንም እነደማልናገር የገባሁትንም ቃል ያፈረስኩባት ቀን ይች ቀን ስለሆነችም ነው መሰል ስቃየም ህመሜም እጥፍ የሆነብኝ ላንተው አስቤ በእምቢታየ መፅናቴ ፈፅሞ ባልገመትኩት አና ባላሰብኩት መልኩ ለሚስኪን እናቴ የዋልከውን መልካም ውለታ እየካድኩ እንደሆነ ግዜህንም እያባከንኩ እንደሆነ ይባስ ብየ ሂወትህን እያበላሸሁ እንደሆነ የገባኝ በቅርብ ነበር የጋብቻ ጥያቄህን በእምቢታ መመለሴን በኩራት እና በአልፈልግህም አይነት ስሜት ስታየው እንደቆየህ አውቃለሁ ይባስ ብለህ ያልሆነ ውሳኔም ልትወስን እንደነበር ሳራ ነግራኛለች ነገር ግን ሁሉም አንተ እንደምታስበው አልነበረም ብዙ ግዜ የውስጤን ስቃይ ልነግርህ እሞክር ነበር ነገር ግን ገና ለመናገር ሳስብ እምባየ እየቀደመ አቅም ያሳጣኛል ለዛም ነበር ሁሌ አንተ ጋር ስንገናኝ እያለቀስኩ እመለስ የነበረው ዛሬ ግን ካቅሜ በላይ ሁኗብኛል ለምንስ የኔ አልበቃ ብሎ ያንተን ሂወት የማበላሸው ? ለዛም ነው ዛሬ የቱንም ያክል ከባድ ቢሆን እውነቱን እና ይዠው የቆየሁትን ስቃይ እንድታውቅ የፈለኩት አቤል እኔ ማለት ለውጭ ሰው ስታይ ደስተኛ ተጫዋች ነገን ናፋቂ ባለተስፋ ወጣት ነኝ እውነታው ግን የናትዋን የተከፋ ፊት ላለማየት ብላ በማስመሰል ደስተኛ ለመሆን የምጥር ስቃይና ሀዘኗን በውስጧ አምቃ ይዛ የስቃይ ቀን እየገፋች የምትሞትበትን ቀን በሰቀቀን የምጠብቅ ገና በጥዋቱ የጨለመባት ተስፋ ቢስ ሴት ነኝ አቤል የምታስታውስ ከሆነ ከአደጋው ቡሀላ በተደጋጋሚ እራሴን ያመኝ ነበር ስራ ከምገባበት ቀን ይልቅ እናቴ እንዳትጨነቅ በማሰብ ስራ ሄድኩ እያልኩ ጎደኛየ ቤት ተኝቸ የማሳልፍበት ቀን ይበዛ ነበር ያኔ ታዲያ የተለመደው የራስ ምታቴ ይሆናል እያልኩ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር እያደር ግን ህመሙ እና ስቃዩ እየበረታብኝ ሲመጣ ከሳራ ጋር ተነጋግረን የስራ ፍቃድ ጠይቀን ሆስፒታል ሄድን ዶክተሩ ስሜቶቹን እና ምልክቶቹን ከጠየቀኝ ቡሀላ አይቻቸው በማላቃቸው የህክምና መሳሪያዎች ብዙ አይነት ምርመራ አድርጎልኝ የተወሰኑ መዳኒቶች ከሰጠኝ ቡሀላ በቀጣይ ቀን እንድንመጣ ቀጥሮኝ ወደ ቤት ተመለስን የዛን ቀን ለሊት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ አሞኝ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነበር የነጋው እንደነጋ ሳራ ጋር ተደዋውለን ሆስፒታል ሄድን ሆስፒታል እንደደረስን ዶክተሩ ቢሮው እየገባ አገኘነው ተከትለነው ጋባንና ስለውጤቱ ጠየቅነው በመጀመሪያ ምንም መልስ ሳይመልስን ዝም ብሎ አንዴ እኔን አንዴ ደሞ ሳራን እያፈራረቀ በትኩረት ካየ ቡሀላ ሳራን አንዴ ውጭ ቆይን አላት እና በሩን ዘጋው ከዛም በትህትና እንድቀመጥ ጋበዘኝና ፊት ለፊቴ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ በመቀጠል አከታትሎ ስለ ስራየ እና ማን ጋር እንደምኖር ጠየቀኝ እኔም መልሱ ለምን እንደተፈለገ ባይገባኝም ስራየ የመንግስት ስራ እንደሆነና የምኖረውም ከእናቴ ጋር ብቻ እንደሆነ መለስኩለት በዝምታ ከቆየ ቡሀላ ሌላስ ማለቴ እህት ወንድም ወይ የቅርብ ዘመድ አለኝ ይቅርታ ዶክተር ችግር አለንዴ ይሄ ሁሉ ጥያቄ አልኩት ኖ ጀስት ለማወቅ ያክል ነው አለኝ ፈገግ እያለ በቅርብ የሚኖር የምቀርበው ዘመድ እንደሌለ እና አባቴም ሟች እንደሆነ እናትም አባትም ዘመድም ሁና ያሳደገችኝ እናቴ እንደሆነች ነገር ግን ገና ልጅ እያለሁ የጠፋ የት እንደሚኖር የማላቀው ወንድም እንዳለኝ ነገርኩት , thankyou ቆንጆ አለኝና በቃ ጨርሰናል አንቺ ጋ ሳራን አስገቢያትና አንቺ ውጭ ቆይኝ አለኝ እየሆነ ያለው ነገር ይበልጥ ግራ አጋባኝ አስጨነቀኝም የቢሮውን በር ከፍቸ ወጣሁና ለሳራ እንድትገባ እንደፈለገ ነግሪያት ገባች አሷ ከገባች በዃላ በሩ ላይ ተለጥፌ የሚያወሩትን ነገር ለመስማት ሞከርኩ ነገር ግን ምንም ነገር አይሰማም ነበር ዝም ብየ በትግስት እሷ አስክትወጣ መጠበቅ ጀመርኩ, ,በጣም ቆየች ምን ይሆን ያቆያት ለምንስ ሁለታችንንም ለየብቻ ማናገር ፈለገ ጥያቄውስ ምንድነው? እያልኩ ብዙ ሀሳብ እና ጭንቀት ውስጤ ሲመላለስ ድንገት በሩ ተከፍቶ ሳራ ወጣች ፊትዋ ከስክስ ብሏል አይኗቿ ቀልተዋል እንዳለቀሰች ያስታውቅባታል ድንገት ድንጋጤ ውስጤን ሲወረኝ ተሰማኝ ምነው ሳራ ችግር አለ ብየ ጠየኳት አይ ኧረ,, ምንም ችግር የለም ሀኒ አለችኝ በተቆራረጠ ድምፅ ፊቷን በግድ ፈገግ ለማድረግ እየሞከረች •••••• ይቀጥላል

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል ❹ . . . ኧረ ምንም ችግር የለ ሀኒ አለችኝ በተቆራረጠ ድምፅ ፊቷን በግድ ፈገግ ለማድረግ እየሞከረች ፊትሽኮ ምንም ሰላም አይታይበትም በዛ ላይ አይንሽ ቀልቷል እንዳለቀሽ ያስታውቃል አልኳት ምንም ሳትመልስልኝ አንገትዋን አቀርቅራ ፀጥ አለችኝ እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ አልዋጥልሽ አለኝ ድንጋጤየ ጨመረ ቀጥታ ወደቢሮው ገባሁና ይቅርታ ዶክተር ምንድነው እየሆነ ያለው ለምን ታስጨንቁኛላችሁ ብየ ጮህኩ እምባ እየተናነቀኝ ያኔ ነበር ዶክተሩ ከብዙ የማስተዛዘኛ ቃላት እና ምክሮች በዃላ የጭንቅላት እጢ (brain tumoer) እንደተገኘብኝ እና በመጠንም ትልቅ እጢ ስለሆነ በቀዶ ጥገና ሊድን እንደማይችል ግፋ ቢል በሂወት ልቆይ የምችለው ከ 3 ወር እንደማይዘል የነገረኝ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ በተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝ ከዛች ቀን ጀምሮ ሂወት ጨለመችብኝ ሁሉ ነገር አስጠላኝ ብቸኝነት ጓደኛየ ሆነ ስቃይ እና ለቅሶ የዘወትር ስራየ ሆኑ ሳራ ልታፅናናኝ ብዙ ትለፋች ትደክማለች ለኔ ግን ሁሉም ቀን አንድ ነበር የስቃይ እና የጭንቀት ቀን ሳራ እንደነገረችኝ ደክተሩ በመጀመሪያ የፈለገው አንድ ያለችኝን እናቴን አስጠርቶ ለሷ ለመንገር እንደነበር እና ሳራን ሲያማክራት ግን እናቴ የልብ ድካም በሽተኛ እንደሆነችና አንድ ያለሁዋት ብቸኛ ያይን ማረፊያዋ እኔ ስለሆንኩ ይህን ብትሰማ ወዲያው በድንጋጤ እንደምትሞት ስለነገረችው ነበር ሁሉንም ነገር ለኔ እና ለሳራ የነገረን እኔም ከዛች ቀን ጀምሮ የውስጤን ስቃይ አፋኜ ይዤ እናቴም ጠርጥራ ወይ ሰምታ አንድ ነገር እንዳቶንብኝ ስል እሷ ጋር ስሆንና እሷ ባለችበተ ቦታ ሁሉ በማስመሰል ደስተኛ የሆንኩ ያክል ጥርሴን በለጭ እያደረኩ ለብቻየ ስሆን ደሞ ህመሜና ጭንቀቴ በለቅሶ ይወጣ ይመስል ሳነባ እውላለሁ አየህ አቤል አንተ በሌላ የተረጎምከው እምቢታየ ምክንያቱ ይሄ ነበር ለምን የማልጨርሰውን ነገር እጀምራለሁ አንተስ ጋር ሁኛ ምንም ላልፈጥርልህ ለምን ደስታህን አጨልማለሁ አቤል እኔኮ እንኳን ለሰው ደስታ ልፈጥር ይቅርና ደስታ ራሱ ምን እንደሆነ የጠፋብኝ የመኖር ገደቤን አውቄ ሞቴን የምጠብቅ ሴት ነኝ ላንተ አልገባም አቤል አንተ ደሞ ብዙ ነገር ይጠብቅሀል ገና ስለዚህ ተስፋ ያላት የምትወድህ ልጆች ወልዳልህ ቤትህን በደስታ የምትሞላልህ ሴት ታስፈልግሀለች ለዚህ ነበር ሁሌም ጥያቄህን በእምቢታየ ስሸሽ የቆየሁት ምንአልባት ግን ዛሬ ትረዳኛለህ አቤል አሁን የምፈልገው ነገር አንድ ነገር ብቻ ነው " የቃል አደራ" ይህን ሀዘኔንን ካንተ ውጭ ማንም አውቆ ከንፈሩን በሀዘን እንዲመጥልኝ አልፈልግም እና ደሞ ይሄ ነገር እናቴ ጆሮ ከደረሰ ያለጥርጥር እንደምትሞትብኝ አውቃለሁ ስለዚህ በፈጣሪ ስም አደራ እጠይቅሀለሁ ሁሌም የደስታ ሂወት እመኝልሀለሁ ። ይል ነበር ፖስታው ወስጥ ያገኛሁት ወረቀት ላይ በፊቱም በጀርባውም የተፃፈው ረጁሙ ደብዳቤ ,,,,እንደነበረ አጥፌ አዛው ፖስታ ውስጥ ጨምሬ ከሹራቡ ኪስ አኖርኩትና ወዳልጋየ አመራሁ እህቴ ራት አትበላም እንዴ ስትለኝ ነበር አለመብላቴንም ያስታወስኩት ,, ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም ነበር መብላት አላሰኛኝም አልኳትና አልጋ ላይ ጋደም ብየ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ አቤል የሚባለው ሰው ይሄን መልክት ሲያነብ ምን ይሰማው ይሆን ሀናንስ ምን ያክል ግዜ ነው በሂወት የምትቆየው የሀናን እናትስ ልጃቸውን ሲያጡ ምን ይሆኑ ይሆን ብቻ ብዙ ብዙ አሰብኩኝ ልክ ብዙ ቀን የምንተዋወቅ የቅርብ ሰው የሆነች ያክል ነበር የተሰማኝ ይህን እያብሰለሰልኩ በመሀል ደውልልሻለሁ ያልኳት ነገር ትዝ አለኝ እንዳረብሻት በቃ ጧት ደውልላታለሁ አልኩ ለራሴ ቆይቼ ግን ደሞ ሌላ ነገር እንዳታስብ አልኩና ደወልኩላት ገና ትንሽ እንደጠራ አነሳችው ምንም ነገር እንዳልሰማ ሰው ሁኜ ነበር ያወራሁዋት ,,, ተኝተሽ ነበር እንዴ አልኳት ኧረ አልተኛሁም አለች ምን እየሰራሽ ስለኔ እያሰብሽ ነዋ አልኳት ሳቀችና አዎ በጣም እያሰብኩ ነበር አለችኝ ምን ምን አሰብሽ አስኪ ንገሪኝ ? እእእ ታክሲ ላይ የጠፋኝን ብር አንተ እንደሰረከኝ እና ቆንጅየ ሌባ እንደሆንክ ብላ መለሰችልኝ መልሷ አስቆኛል እንዴ ይህን ያክል አንገብግቦሻል እንዴ ብሩ ደሞስ ብሰርቅሽ የታክሲ ከፍየልሻለሁ አይደል እንዴ ውለታማ አትካጅ አልኳት ሳቀች መልሳ ብቻ እንዲህ እንዲህ እያልን ብዙ ነገር እያወራን በመሀል ስልኬ ተቋረጠ ባላንሴን ሳየው 00:12 ሳንቲም ይላል ተናደድኩ ወዲያው ደወለችልኝ ምን ሁነህ ነው የዘጋኸው አለችኝ የቴሌዋ ሴት መኝታ ክፍሌ መጥታብኝ ነው አልኳት አልገባትም ማናት የቴሌዋ ሴት ብላ ጠየቀችኝ እንዴ አታቂያትም ያች ያለወት ቀሪ ሂሳብ ምናምን የምትለው ስላት ካርድ ዘግቶ መሆኑ ገባት እና በጣም ሳቀች አስከትላ 5 ብር ሞልተህ ነው እንዴ ታዲያ ሴት ጋር የምትደውለው አለችኝ ምንችግር አለው ለመጀንጀን አልደወልኩልሽ አልኳት እየቀለድኩ ,, ልጀነጅንም አምሮሀል እንዴ ?,, ውይ እኔ እንኳ ያንቺ አይነት ቆንጆ የመጥበስ እቅድ ስለሌለኝ አልጀነጅንሽም አልኳት ኮስተር ብየ ለምን ሲባል አለችኝ ቆንጆ መጥበስኮ የተለኮሰ ስቶቭ ላይ መቀመጥ ነው ማን ይቃጠላል መለስኩላት በድጋሚ ሳቀች ለምን እንደሆነ እንጃ ግን ስትስቅ የሆነ ስሜት ይሰማኛል በቃ ልተኛ ነው አለች ብዙ ነበር ያወራነው እሽ በቃ ተኚ ነገ ሹራብሽን ልትወስጅ ስትመጭ የሰረኩሽ ብር ስላላለቀ እጋብዝሻለሁ እሺ ለካ ሹራብ አለኝ ረስቸው አለችኝ በቃ ነገ ደውልልሻለሁ አልኳት እና ቼው ስትለኝ እኔም ውድድ አደርግሻለሁ አልኳት በቀልድ ለዛ ሳቀችና እንዴ ማን እወድሀለሁ አለህ ? አይ በቃ ጆሮየ ነው ማለት ነው ብየ ቀለድኩባትና ቼው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ ,,, አይገርምም ሹራቡ እኔ ጋር መኖሩን ረስታው ነበረ ደስ አለኝ ምክንያቱም የፖስታውን ወሬ ታነሳብኛለች ብየ እየፈራሁ ነበር ያንቀን ማታ እንቅልፍ አለወሰደኝም ነበር በቃ ዝም ብየ ካንዱ ሀሳብ ወደ ሌላ ሀሳብ ስገላበጥ አደርኩ ለራሴ ግን አንድ ነገር ቃል ገብቼ ነበር ፖስታውን እንዳላየሁት አድርጌ መመለስና የሀናን የቅርብ ጎደኛዋ መሆን ከዛም እሷን ያስደስታታል ብየ የማስባቸውን ነገሮች በሙሉ ለሷ ማድረግ ብቻ ብዙ ሰአቴን ለሷ መስጠት ,, በሚቀጥለው ቀን ከሰአት ቡሀላ ተደዋወልንና ሹራቧን ልመልስላት ከሀናን ጋር ተገናኛን ሀኒ የዝናቡ ቀን ምሽት ካየዃት በላይ በጣም ውብ ሁና ነበር የመጣችው ፍዝዝ ብየ አየኋት ምንድነው አንተ ተመሰጥክኮ አለችኝ አውቀሽ ነዋ እንደዚህ ቆንጀ ሁነሽ የመጣሽው? እንዴት አለችኝ ተሳስቼ እንድጠብስሽ ነዋ አልኳት ስቄ ኧረ አንተ ቆንጆ አጠብስ ምን አስጨነቀህ ,, እንዳጋጣሚ ያን ቀን ዙም ሲኒማ አማርኛ ኮሜዲ ፊልም መቶ ነበርና ካልገባን አልኳት ይመሻል ቤት ይቆጣሉ ሌላ ቀን ይሁንልኝ አለች ,,እንደመግደርደር እንደሆነ ገብቶኛል ባክሽ እኔም ሴት ሁኜ ሁለት አመት አይቸዋለሁ አንዳንቺ ግን አልግደረደርም ነበር ሌላ ግዜ ደሞ ለልማት ምናምን

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 . . . አንዴ ግራ ኪሷን ደሞ ወደ ቀኝ ከዛ የዃላ ኪሷን ብቻ አያፈራረቀች ሁሉንም ፈተሸቻቼው እና በጣም ስደነግጥ አየዃት ቆዳ የቀደደ በግ ጠቢ እንኳ እንደዛ አይደነግጥም ። ምነው ችግር አለ ? የኔ ጥያቄ ነበር አይ ብር ጣልኩ መሰል አለች አሁንም ወደ እግሯ ስር ሞባይልዋን አብርታ እያየች ብዙ ብር ነው እንዴ ? ስደነግጥ አሳዘነችኝ ኧረ ብሩ እንኳ ብዙ አደለም ግን የ ,ታ ,ክ ,ሲ ,,,, ብላ ሳጨርስ ስለገባኝ የት ነሽ አልኳትና የታክሲውን ከፈልኩላት ተረጋጋች ድንጋጤዋም ከፊትዋ ላይ ቀስ እያለ ሲለቃት ታየኝ በጣም አመሰግናለሁ አለችኝ ምንም አይደል ግን ከዚ በዃላ ብር ሳይኖርሽ ታክሲ ላይ አይወጣም እሺ, ,, ቀልድ እንደሆነ ገብቷታል ሁለት ብር ከፈልኩ ብለህ ልትመክረኝ ባሎነ ፈገግ ብላ ,, በዚህ መሀል ከጀርባችን አንድ ጎርነን ያለ ድምፅ "ሳይሻገር ወራጅ አለ አለ" ሰውየው ወራጅ በሚልበት ቅፅበት ታክሲዋ ዜብራ መሀል ገብታ ኑሮ መቆም አልቻለችም ይቅርታ ቦታው ስለማይመች ነው ቦታ ይያዝና ትወርዳለህ አለ እረዳቱ ሰውየው በጣም ተቆጣ ይባስ ብሎ ረዳቱን መዘለፍ ሁላ አማረው ረዳቱ ምንም አልመለሰም ሹፌሩ ጣልቃ ገብቶ ይቅርታ ጋሼ ቀደም ብለህ ወራጅ አለ ማለት ነበረብህ አለው ተሻግሮ ታክሲዋን እያቆመ ሳንቲም መልቀም ብቻ አይደለም የሰው መብትም እክብሩ ብሎ ወረደ እንደው የታክሲ ላይ ስራ ታጋሽ ላልሆነ ሰው በጣም ፈታኝ እና አስቸጋሪ ነው ሚስኪን ሹፌር ሹፌር በመሆኑ ብቻ ከስር ሞተር፣ ከፊት ለፊቱ ትራፊክ፣ ከዃላ ደግሞ ተሳፋሪ እያቃጠለው ይውላል እረዳቱስ ቢሆን ጋሽየዋ እትየዋ እያለ አክብሮ በጫነ ባንዳንድ ታክሲ ላይ ሲወጡ ብቻ መብታቸው ትዝ እያላቸው ከሂሳብ በፊት ሀሳብ በሚሰጡ እና ከነቤታቸው አመል እየገቡ በራሳቸው ጥፋት ያዙኝ ልቀቁኝ በሚሉ ተሳፋሪወች እየተዘለፈ የስንቱን ሰው ባህሪ እያሟሸ ይውላል .... በርግጥ ለተሳፋሪ የማይመቹ ጥሩ ስነምግባር የሌላቸው ረዳቶችም ሆነ ሹፌሮች እንዳሉ እሙን ነው ነገር ግን ሁሉንም ባንድ አይን ፈርጆ ለዛውም በራስ ጥፍት ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ግን ተገቢ ነው ብየ አላምንም ።ሰአቴን ተመለከትኩ ሁለት ሰአት ሊሆን ነው መሽቷል አልኩ ለራሴ ሰአቴን አይቼ ቀና ስል ቆንጆዋ በሀሳብ ጭልጥ ብላላች ምን ይሆን እንዲህ ጭልጥ ያደረጋት ስል ራሴን ጠየኩት ?? ቆንጆዋ ሀሳቧን ሳትጨርስ ታክሲዋ ፌርማታዋን ጨርሳ አንድ አንድ እያልን ተንጠባጥበን ከታክሲዋ ወረድን ። ካፊያው ባለበት ቀጥሏል ቆንጆዋ ልጅ የያዘቻትን ትንሽየ ዣንጥላ ዘረጋቻት እና ወዴት ነህ አለችኝ ሳልመልስላት አንዴ መጣሁ ብየ ሱቅ መፈለግ ጀመርኩ አንድ እየተዘጋ ያለ ሱቅ አገኘሁና ለፀጉሯ ላስቲክ ገዝቼ ወደሷ ተመለስኩ ላስቲኩን ስገዛ ዣንጥላ መያዝዋን እረስቼው አልነበረም። ሆን ብየ ነው ያደረኩት ያው ቆንጆ ሳይ እንዲህ ያደርገኛል "ክፉ አመል" ላስቲኩን ስሰጣት በጣም ደስ ሲላት ተመለከትኩ እኔስ ምን ፈልጌ ,,,, አመሰግናለሁ አለች እኔም ይገባኛል , አልኩና ከተል አድርጌ በየት በኩል ነሽ ስል ጠየኳት ዣንጥላዋ ትንሽየ ስለነበረች ከዝናቡ ለመራቅ የግድ ወደቆንጆዋ መጠጋት ነበረብኝና ወደሷው ተለጠፍኩ የተቀባችው ሽቶ በጣም ደስ የሚል መአዛ አለው እኔ በዚህ ነኝ ብዙም አይርቅ ብላ በእጇ የመንገዱን አቅጣጫ ጠቆመችኝ እንዳጋጣሚ እኔም በዛ በኩል ነበር ማለፊያየ አከባቢው ላይ አልፎ አልፎ ውር ውር ከሚሉት መኪኖች ውጭ ብዙ ሰው አይስተዋልም በዝናቡ ታጅበን ወክ ማድረግ ጀመርን። በነገራችን ላይ ከቆንጆ ልጅ ጋር በዝናብ ወክ ስታደርጊ በመብረቅ የመመታት አድሉ ሰባ በመቶ ይጨምራል አልኳት ኮስተር ብየ ሳቀች እና አለቀልህ በቃ አለችኝ ኧረ ባክሽ አንቺ ለራስሽ አለቀልሽ አልኳት: ቆንጆ ነኝ እያልክ ባልሆነ አለች ዙራ እያየችኝ የምር ደመናው ጋርዶሽ ይሆናል እንጂ በጣም ቆንጆ ነኝ አልኳትና አስከትየ ተማሪ ነሽ ወይስ ሰራተኛ ስል ጠየኳት ሁለቱም ውስጥ የለሁበትም አለች ቀዝቀዝ ብላ እና ምንድነሽ ስል ሌላ ጥያቄ ደረብኩ ሰው ነኛ ብላ አሾፈች እና ሲሪየስሊ የዚህ ሀገር ልጅ አይደለሁም ዘመድ ጋር መጥቼ ነው አለችኝ አንድ አንድ እያወራን ትንሽ ከሄድን በዃላ በቃ ደርሻለሁ በዚህ ጋር ነው የምገባው አለችኝ ትልቅ የግቢ በር እያሳየችኝ ደስ አላለኝም መንገዱ ቀረበብኝ ምክኒያቱን ባላቅም ትንሽ በሆነችው የጋራ ቆይታችን ደስ እያለኝ ነበር ዝም ስላት አንተስ አልደረስክም አለችኝ አንቺ ምን አለብሽ ዣንጥላሽን ይዘሻል በዛ ላይ ሹራብም ለብሰሻል እኔ ገና የግር መንገድ ይጠብቀኛል በዛላይ በጥዋት ስለሆነ ከቤት የወጣሁት እንደምታይኝ በቲሸርት ነኝ ብርዱ ከዝናቡ ጋር ተባብሮ ነገ ደርቄ ነው የምታገኝኝ : ,,,ባጃጅ አታገኝም እንዴ ? የሷ ጥያቄ ነበር ባጃጆች አይጠፉም ነገር ግን እኔ የምሄድበት ቦታ ባጃጆች አይገቡም አልኳት የሰማችኝ አትመስልም አይኗ ስልኳ ላይ ከሚደወል ቁጥር ላይ አፍጧል ከታክሲው ላይ ከወረድን ሰአት ጀምሮ በተደጋጋሚ እየተደወለላት ነበር ግን አንዴም አላነሳችው ያሁኑንም ዘጋችው እና ቀና ብላ አየችኝ እና ድንግጥ ነገር አለች እና በቃ ቸው አለችኝ : እንዴ እንዲህ ነው ቼው የሚባለው አልኳት ገርማኛለች,, አይ መሸቷል መሰል እየተደወለብኝ ነው አለች አልተረጋጋችም አሁንም እሺ እንቺ እያለሽ እኔ ብርድ ልሙት አልኳት አይገርምም የምር በርዶኝ ነበር እስካሁን ግን አልታወቀኝም ነበር እሺ ትጠብቀኛለክ የሚደረብ ነገር ላምጣልክ አለችኝ የምሯ አልመሰለኝም ነበር አይ ገብተሽ ስትወጪ ሌላ ነገር ስለሚመስል እሱን የለበሽውን ብስጭኝ አይሻልም? አልኳት ምንም አልመለሰችልኝም የለበሰችው ጥቁር ባለኮፊታ ሹራቧን አውልቃ ሰጠችኝ ደስ ብሎኝ ተቀበልኳት ልግባ በቃ አለችኝ የፀጉሯን ላስቲክ እያስተካከለች እንዴ በምን አገኝቼሽ ልመልስልሽ ነው ስልክሺን እንኳ ልውሰድ እንጂ አልኩ ስልኬን አውጥቼ ። እየተጣደፈች ስልኳን ነገረችኝ ማን ብየ ሴቭ ላድርገው ጠየኳት? ደስ ባለህ አለችኝ አይ በስምሽ ነው የምፈልገው ስላት እሺ ሀናን , ,በቃ አሁን መግባት ትችያለሽ ያው ዛሬ ዝናብ ስለሆ አልሳምኩሽም አልኳት የስንብት እያቀፍኳት ደፋር አለችኝ እና ጥላዋን እንደያዘች ወደ ትልቁ በር አመራች እኔም የቆንጆዋን ጥቁር ሹራብ ለብሼ ከዝናቡ ሽሽት ሩጫየን ጀመርኩ ካፊያ የነበረው ወደ ዶፍ መጠኑን ጨምሮ መዝነብ እንደጀመረ ከቤቴ ደረስኩ ያመለጥኩት አይነት ስሜት ተሰማኝና በመሮጤ ኮራሁ ቤት ከገባሁ በዃላ በቀጥታ ያደረኩት ለቆንጆዋ መደወል ነበር ብዙ ጠራና ሊዘጋ ሲል አነሳችው ስልኬን ስለማታቀው እራሴን አሳወኩና ሰላም መግባቷን ጠየኳት ሰላም ገብታለች , ,በቃ ገና መግባቴ ነው ልብሴን ልቀይርና ደውላለሁ ብያት ትንሺም ቢሆን በካፊያ የረጠበውን ልብሴን መቀየር ጀመርኩ ከቲሸርቴ ላይ የደረብኩትን የቆንጆዋን ልጅ ሹራብ አወለኩና ወንበሩ ላይ ዘርሪው ብየ እኔ ካለሁበት ፈንጠር ብላ ለተቀመጠችው እህቴ ወረወርኩላት በዚህ መሀል ነበር ታዲያ አንድ ፖስታ ከሹራቡ ኪስ የወደቀው በቁሜ አነሳሁትና አገላብጨ አየሁት ተፈቷል ወስጡ የሆነ የታጠፈ ወረቀት አለ ከፖስታው ጫፍ የሷ ስም እና ስልክ ተፅፎበታል ላንበው አላንበው ከራሴ ጋር ሙግት ገጠምኩ ካፍታ ሙግት በዃላ ወረቀቱን አውቼ ዘረጋሁት እና ማንበብ ጀመርኩ ,,,,,ገና የተወሰኑ መስመሮች እንዳነበብኩ ልቤ በድንጋጤ ስንጥቅ አለ•••••• ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fekrnahiwot ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥❥________⚘_______❥❥

😘የቆንጆዋ ጦስ😘 🔥ክፍል ❶ . . . ••••የዛሬው ዝናብ አረብ ሀገር እንዳለችው ጎረቤታችን አሞ አንዴ መጣሁ አንዴ ቀረሁ እያለ ማስፈራራቱን የጀመረው ገና በቀኑ ነበር አሞስ ብታስፈራራ አንድ የዋህ ባሏን ነው ዝናቡ ግን ስንቱን አስፈራርቶ ይዘልቀዋል •••አሁን ደግሞ መምሸቱን ሲያቅ ሊያመር ነው መሰል ማካፋት ጀምሯል እኔም አንድም ከካፊያው ለመዳን ሁለትም ብዙ ሳይመሽብኝ ቤት መግባቱን አስቤ ታክሲ ለመያዝ ከአስፓልት ዳር ተገተርኩ ,,,, አንድ ሁለት ታክሲዎች እየሞሉ ካለፉ በዃላ ብዙም ሳይቆይ አንዲት ታክሲ መጥታ እንደምንም ተጋፍቼ ቅድሚያ አገኛሁ። ታክሲዋ በሰው ጨቅ ብላ ሞልታለች ። ካንድ ወንበር ውጭ ሁሉም ወንበሮች ትርፍ ሰው ይዘዋል ሦስተኛ ወንበር ላይ አንዲት ዣንጥላ የያዘች ቆንጂየ ወጣት እና አንድ ደሞ ተለቅ ያሉ ሴትዬ ተቀምጠዋል ቆንጆዋን ልጅ እሙየ ትንሽ ጠጋ በይለት እስኪ አላት እረዳቱ በትህትና ብዙ ደስ ሳይላት ፊትዋን እንደፈረዘችው ወደ ሴትየዋ ጠጋ አለችልኝ እና እንደነገሩ ተቀመጥኩ ያው ትርፍ መጫኑ ለተሳፋሪ ምቾት ባይሰጥም እነሱ ግን ዝናቡን እና ምሽቱን ምክንያት በማድረግ አጋጣሚውን እየተጠቀሙ እንደሆነ እሙን ነው። ታክሲዋ መንገዷን ቀጥላለች እኔ ደሞ አንዴ ጎኔ የተቀመጠችውን ቆንጅየ ልጅ አንዴ ደሞ ታክሲዋ ላይ የተለጠፉትን ጥቅሶች ማስተዋሌን ቀጥያለሁ ..እሷ አታየኝም ቆንጆዋ ጆሮዋን በጠቋሚ ጣቷ እየጎረጎረች ነበር ያለማጋነን ስለቁንጅናዋ እንዲህ ነው ብሎ መናገር ከባድ ነው አይኗቿ ከንፈርዋ አፍንጫዋ ብቻ ምን አለፋቹ ልጅቱ ልቅም ያለች ውብ ናት እሷን አይቼ ስመለስ አንድ ከረዳቱ ወንበር በላይ የተለጠፈ ፅሁፍ ፈገግ አደረገኝ "ሞላ የሰው ስም ነው ጠጋጠጋ በሉ" ይላል የምር ነበር ፈገግ ያስባለኝ ልጅቱ በሷ የፈገግኩ መስሏት ዞር ብላ ባይኗ ገርመም ስታደርገኝ እኔም ሰረቅ አድርጌ አየዃት አሁንም ጆሮዋን በጣትዋ እየኮረኮረች ነበር አሁን አጋጣሚው ተመቼኝ ወሬ ለመጀመር ፊቴን በሷ ትይዩ አዙሬ እሙየ ጆሮሽ ጋር ጠበኛ ነሽ እንዴ አልኳት ማለት ? አለች ኮስተር እንደማለት ብላ አይ ቅድም ጀምረሽ ነበር ስትኮረኩሪ የነበረው እኔ ደሞ ጆሮሽ ውስጥ ኤርፎን ገብቶብሽ እሱን እየፈለግሽ መስሎኝ ነበር አልኳት መኮሳተር ፈልጋ ነበር ግን አልቻለችም ሳትፈልገው ለዘብ ያለ ብቻ የፊት ጥርስ የጎደለው ሳቅ ሳቀች ስቃ ሳጨርስ እስኪ ሂሳብ እዛ ጋ የሚለው የረዳቱ ድምፅ በመሀል ገባ ሚስጥር ኪሴ የነበረውን ዝርዝር ሁለት በር አውጥቼ ዘረጋሁለት ትልቋ ሴትዬ ከረጢታቸውን ፈተው ብር እየመረጡ ነዉ የታክሲው የውስጥ መብራት ስላልበራ መሰለኝ ብዙም እየታያቸው እንዳልሆነ ገምቻለሁ ምነው ልጄ መብራቱን ብታበራው አሉ ወደ ረዳቱ ቀና ብለው ረዳቱ ዛሬ መብራት ተረኛ ነን ማዘር አለ ከሌላ ተሳፋሪ ሂሳብ እየተቀበለ በረዳቱ መልስ ታክሲው ውስጥ ያለው ሰው በከፊል ሳቀ ,, ሆሆ እናንተም ጋር በተራ አረጉት አይ ይሄ #ተራ "አሉ ሴትየዋ ከብር መሀል በግድ የመረጧትን አምስት ብር ለረዳቱ እየዘረጉ ይሄ ሁሉ ሲሆን አይኔ ቆንጆዋ ልጅ ጋ ነበር ኪስዋን ደጋግማ ትፈትሻለች አንዴ ግራ ኪሷን፣ ደሞ ወደ ቀኝ ፣ ከዛ የዃላ ኪሷን ብቻ አያፈራረቀች ሁሉንም ፈተሼቻቸው እና በጣም ስትደነግጥ አየዃት ቆዳ የቀደደ በግ ጠቢ እንኳ እንደዛ አይደነግጥም ።ምነው ችግር አለ አልኳት ድምፄን ቀስ አድርጌ አይ ብር ጣልኩ መሰል አለች አሁንም ወደ እግሯ ስር ሞባይሏን አብርታ እያየች••••• ይቀጥላል..... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fekrnahiwot ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @nahita2 ❥❥________⚘_______❥❥

ዛሬ እንዲጀምር ሚፈልግ ካለ👍
ዛሬ እንዲጀምር ሚፈልግ ካለ👍

​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ህይወት ⸙━━━━ ◈ ⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷ ˙·٠•●♥ ተከታታይ ልቦለድ♥●•٠·˙ ⚀ የመጨረሻው ክፍል ⚀ .....ጆሮዬን ከሀዲዱ ጋር አጣብቄ አዳመጥኩ ግምቴ ልክ ነበር ። ድምፅ ሰማው። ቶሎ ብዬ ሀዲዱ ላይ ተቀምጬ እራሴን ከሀዲዱ ጋር መተብተብ ፣ መጠፈር ያዝኩ። ቀድሜ ሁለቱ እግሮቼን ከሀዲዱ ጋር ጠፍሬ አሰርኩት። ቀጥዬ እጅና እጆቼን አጠላልፌ አሰርኳቸው። ከዚያ ባቡሩን መጠበቅ ጀመርኩ። ፍሌሜን አጥቼ መኖር ስለማልችል ፣ እሷ ሞታ በመቃብሯ ላይ ቆሜ እህህ እያሉ ቀን መግፋት ስለማይሆንልኝ ባቡሩ ድጦኝ እንዲያልፍ ፈቅጃለሁ። ባቡሩ ቢቀርበኝና ህይወት አሳስታኝ ልትረፍ ብል እንኳን እራሴን ሆነ ብዬ ከሀዲዱ ጋር ተብትቤዋለሁ ለመፍታትም ባቡሩ ጊዜ አይሰጠኝም። የባቡሩን ሀዲድ እና ትብታቡን አንቼ ቀና ስል..... . ባቡሩ እየገሰገሰ ወደእኔ እየመጣ ነው።ግፋ ቢል ሁለት ደቂቃ ቢቀረው ነው። የአሸዋውን አቧራ እያቦነነ መጣ። ልቤ ተሰቀለች። መሞት ፈራው። ልቤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር። እናቴን አሰብኳት ፣ የታሰረ አባቴን አሰብኩት፣ፍሌሜን አሰብኳ ፣ ትርሃሴን አሰብኳት.....ቀና ስል...አንዲት ልጃገረድ ቢጤ እየሮጠች ወደ እኔ ስትመጣ ተመለከትኩ። በደንብ ስትቀርብ ሳያት ለየዋት። ፍሌም ነች።ባቡሩን አየውት በጣም እየቀረበኝ ነው። መልዓከ ሞትን አስቀድሞ የሚገሰግስ የሞት ሰራዊት መሰለኝ ። ፍሌም ሻርቧን ነፋሱ ነጥቋት ሲሄድ እያየው ወደ እኔ እየሮጠች " ግሩም..! ግሩም..!" አለች።....ባቡሩ ፈጠነ። እኔም የታሰርኩበትን ትብታብ በደመ ነፍስ መፈታታት ጀመርኩ። ባቡሩ ቀ.....ረ......በ... በፍጥነት የእጄን ትብታብ ፈትቼ ወደ እግሬ ገባሁ። አንዱ እግሬን ፈትቼ ስጨርስ ቀግምት 8 ወይም 7 ደቂቃ ያህል ቢቀረው ነው። ፍሌሜ በደረቷ አሸዋው ላይ እራሷን ስታ ወድቃለች። ትብታቡን ለመፈታታት እታገላለሁ። ባቡሩ ሊድጠኝ ይገሰግሳል.......... ❂───── ❁ ተ ፈ ፀ መ ❁ ───── ❂ ➲comment ፦ @nahita2 ☣ Creator ፦ @nahita2 ━━━━⸙ ፍቅር እና ህይወት⸙━━━━ ▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃ ስለተከታተላችሁን እናመሠግናለን ሀሳባችሁን ከስር ባለው link ላኩልኘ @nahita2

ሰላም ብዙ ሰው ለምንድን ነው መposet ያቆምከው እያለኘ ነው በጣም ይቅርታ ነገሮች ስላልተመቻቹልኘ ነው ካሁን ቡሀላ በደንብ እለቃለው ልቦለዶች ግጥሞች ከቨሮችን እለቃለው!።ፍሌም እንዲቀጥል ምትፈልጉ ካላቹ👍ሌላ እንዲጀምር ምትፈልጉ ካላቹ ✋ይሄን ተጫኑ አመሰግናለው።

​◈ ⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷ ˙·٠•●♥ ተከታታይ ልቦለድ♥●•٠·˙ ⚀ ክፍል ሀያ አንድ ⚀ 2⃣1⃣ . ፍሌሜም እኔ ፊት ደስተኛ ሆና ለመታየት ፈገግ ትላለች። ያ ውብ ዲንፕሏ ድምቀቱ ጠፍቶ የበርባሮስ ጉድጓድ መስሏል። ሽማግሌው የፍሄሜን የመዳን ጉጉት በእኔ ውስጥ አሻግሮ ከተመለከተ በኃላ ሊያድናት የሚችል የባህል መድሃኒት እንዳለና ሁለት ሳምንታት እንደሚፈጅ ነገረኝ።ሌላ ሰው ልከው እንዳልተመለሰ ሲነግሩኝ አላመነታሁም።ይህን ዜና በሰማው ማግስት ሰማይና ምድር ተራክቧቸውን አጠናቀው ሲለያዩ ማልጄ ጉዞ ጀመርኩ። .... የአስር ቀናት ጉዞን ተጉዤ በሀረር አቅጣጫ ወደ ገጠሩ ዘልቄ የተባለውን መድሃኒት ይዤ ግመሌን እየጎተትኩ 18 ቀን ከፈጀ አድካሚና አሰልቺ ጉዞ በኃላ ድሬ ገባሁ። የእለቱ ፀሀይ ሀሩር ነበር። ረጫሞው እንደጉድ ይፋጃል። ፍሌሜ ወዳለችበት መንደር ስቃረብ ደነገጥኩ ሀሞቴ ፍስስ አለ ብዙ ሰው ጭንቅላቱን ይዞ እያለቀሰ ፍሌም ወዳለችበት ጊቢ ይገባል ይወጣል። ይህን ሳይ እግሬ ቄጤማ ሆነ። ሆዴ ክፉኛ ተሸበረ ውስጡ የነበረው የመኖር ተስፋ እየተሟጠጠ ቀፎ ሲሆን ይሰማኛል። ከግመሏ ጀርባ ላይ ገመድ ፈትቼ ወደ ኃላ ወደ በረሃው ሸሸው። ከለቀስተኞች ውስጥ ስመለስ አይቶ የተከተለኝ ስለመሰለኝ ረጅም መንገድ ሮጥኩ። ከዚያ ዙሪያ ገባውን ቃኘውት። በረሃ ነው አንድም ዛፍ የለም። አንድ ሀሳብ መጣልኝ ከርቀት የባቡር ጣቢያ ቤት ነገር አየው። መቆጣጠሪያው ነው ብዬ ገመትኩ። ወደ እግሬ ተመለከትኩ የቆምኩት የባቡር ሀዲድ ላይ ነው። ላቡ እንደ ጅረት በክንድ እና ክንዷቼ ላይ እየተንቆረቆረ ውሃ ወደ ማይጠግበው የበረሃው አሸዋ ላይ ይንጠፈጠፋል። ቀና ብዬ ፀሀይዋን አየዋት በአናቴ ትክክል ናት። አሁን የከሰዓቱ ባቡር ከተለያየ አቅጣጫ ድሬ የሚገባበት ሰዓት ነው። ጆሮዬን ከሀዲዱ ጋር አጣብቄ አዳመጥኩ ግምቴ ልክ ነበር ። ድምፅ ሰማው። ቶሎ ብዬ ሀዲዱ ላይ ተቀምጬ እራሴን ከሀዲዱ ጋር መተብተብ ፣ መጠፈር ያዝኩ። ቀድሜ ሁለቱ እግሮቼን ከሀዲዱ ጋር ጠፍሬ አሰርኩት። ቀጥዬ እጅና እጆቼን አጠላልፌ አሰርኳቸው። ከዚያ ባቡሩን መጠበቅ ጀመርኩ። ፍሌሜን አጥቼ መኖር ስለማልችል ፣ እሷ ሞታ በመቃብሯ ላይ ቆሜ እህህ እያሉ ቀን መግፋት ስለማይሆንልኝ ባቡሩ ድጦኝ እንዲያልፍ ፈቅጃለሁ። ባቡሩ ቢቀርበኝና ህይወት አሳስታኝ ልትረፍ ብል እንኳን እራሴን ሆነ ብዬ ከሀዲዱ ጋር ተብትቤዋለሁ ለመፍታትም ባቡሩ ጊዜ አይሰጠኝም። የባቡሩን ሀዲድ እና ትብታቡን አንቼ ቀና ስል..... ........ ....... 🛎 የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል...... ፍሌም... ➲ ደራሲ Cራክ

ፍሌም ቀጣይ ክፍል እንዲለቀቅ ሚፈልግ ካለ👍

አፈቅርሻለው❤️😔❤️❤️😍😍😘 በ nahita👍👍❤️❤️የምን ዝምብሎ መስማት ነው እረ @join አርጉ @fkrnahiwot @fkrnahiwot

🙇‍♂🙇‍♂መመሰጥ አይቻልም🙇‍♂🙇‍♂🙇‍♂ nahita

እውነተኛ ታራክ ላዬ የተመሰረተ ግጥም❤️❤️❤️❤️😘😘😘😍😍😍 በati❤️😘👍👍 @fkrnahiwot @fkrnahiwot @fkrnahiwot