cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Robe High School and Preparatory(9-12)

እንኳን ወደ Robe_High_School_&_Preparatory በሰላም መጡ ይህ ቻናል የተከፈተው በቀላሉ ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን Information ለማግኘት እንዲረዳ የተዘጋጀ ነው። @Robe_High_School_and_Preparatory ለአስተያየት ለጥቆማ 👉 @Robeschool_bot

Show more
Advertising posts
251
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ማስታወቂያ የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል። በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ  እንገልፃለን ። ማሳሰቢያ :- የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን። የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች Website: https://placement.ethernet.edu.et SMS: 9444 ትምህርት ሚኒስቴር   
Show all...
የጥሪ ማስታወቂያ በ2015 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ከታች በተገለጸው መሰረት 👉 የካቲት 27 እና 28 መሆኑን እናሳውቃለን!   
Show all...
#ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ  (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት  ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንድትችሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን። ማሳሰቢያ:- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን። ትምህርት ሚኒስቴር!      
Show all...
የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ  በ2015 ዓ.ም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ የካቲት 20/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።        
Show all...
የእጩ ፍሬሽማን ተማሪዎች ወይም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ፕሮግራም ትምህርት የተማሪዎች ምደባ በዚህ ሳምንት ምናልባት ነገ  ወይም ከነገ ወዲያ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ፨ትክክለኛውን ቀን አላሳወቁም‼️
Show all...
የጥሪ ማስታወቂያ በ2014 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን የ2ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና በላይ አምጥታችሁ በ2015ዓ.ም. ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በየካቲት 24, 25 እና 26፣ 2015ዓ.ም. ሐረማያ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት አንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡ ማሳሰቢያ፦ 1ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ ፤ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ትምህርት ያጠናቀቃችሁበትን ትራንስክሪፕት እና የ2ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ፤ 6 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶግራፎችን እንዲሁም በግል የምትጠቀሙባቸውን ብርድልብስ ፣ አንሶላ ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ፡፡ 2ኛ.ተማሪዎች የመኝታ ክፍል ድልድላችሁን የ2ኛ ክፍል መለያ ቁጥራችሁን በመጠቀም በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ (www.haramaya.edu.et) በመግባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 3ኛ. ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ካደረገባቸው ቀናት በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ይገልጻል፡፡        
Show all...
የጥሪ ማስታወቂያ #በ2014 የትምህርት ዘመን የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ 50% እና በላይ በማምጣት ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹህ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግቢያ ቀን የካቲት 20/2015 እና 21/2015  መሆኑን የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር ዳይሬክቶሬት ገልጿል። ዝርዝር መረጃውን ከማስታወቂያው ይመልከቱ።        
Show all...
የጥሪ ማስታወቂያ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያም በላይ አምጥታችሁ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች:- ምዝገባ  በበየነ መረብ ”Online”  👉 ከየካቲት  20-26/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን  የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ  የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ 👉 የካቲት 27-28/2015 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ማሳሰቢያ፤ ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎችን በዩኒቨርስቲዉ ድህረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑን እንድታውቁ፡፡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ 1ኛ.  የ12ኛ  ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ቅጂው 2ኛ.  ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ቅጂው 3ኛ.  የሌሊት አልባሳት 4ኛ.  4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ 5ኛ. የስፖርት ትጥቅ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የካቲት  29 እና 30 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡       የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት        
Show all...
የጥሪ ማስታወቂያ በ2015 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ ፨ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎቹ እና ስማችሁ ከ ̈ የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በግሸ አባይ (ይባብ ካምፓስ፣ 👉ከየካቲት 20/2015 እስከ 22/2015 ዓ/ም ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡       
Show all...
#AAU በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡ የካቲት 15 ቀን እና የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ 1ኛ - የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ   ኮፒ፣ 2ኛ - ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ 3ኛ - ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡ ➢ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡ ➢ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡ ➢ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን ➢ ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ➢ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ➢ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ                                                             ሬጅስትራር     
Show all...