cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የግጥም ህይወት

የተለያዩ የግጥም ስራዎች የሚቀርቡበት ፣ የግጥም እና የስነ ፅሁፍ አፍቃሪያን በተለያዩ ግጥም እና ስነ ፅሁፎች እየተዝናኑ እውቀት የሚቀስሙበት የስነ ፅሁፍ መንደር ነው ። ( የግጥም ህይወት ) ኑ የግጥምን ጥበብ እስከ ጥግ እናያለን ከ እናንተ የሚጠበቀው ቻናሉን ጆይን በማለት ለወዳጅ ፣ ለጓደኛ ፣ ለዘመድ ሼር ማድረግ ብቻ ነው። Creator @Mersha_9119

Show more
Advertising posts
4 206
Subscribers
+724 hours
+267 days
+2930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from Business Boosters
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ የ1 ሚልየን ሳይፈር ኮድ  N = - .(Dash dot) O = - - -(dash dash dash) D = - . .(Dash dot dot) E = .(Dot) S = . . .(Dot dot dot)✅✅
Show all...
Repost from Business Boosters
Photo unavailableShow in Telegram
🧑‍💻Today's Daily Cipher Morse Code WHALE W: • — — (dot dash dash) H: • • • • (dot dot dot dot) A: • — (dot dash) L: • — • • (dot dash dot dot) E: • (dot)  🗣Dash(-) means Long press for 3s Dot(•) means Normal Press
Show all...
👍 1
Repost from Business Boosters
Photo unavailableShow in Telegram
July 10 combo cards 🤞
Show all...
🤷‍♂ 1👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጊዜ እና ቀጠሮ """"""""""""""""""""" እሷ ጠብቀኝ ካልኩበት መጥቼ አጣሁት ብላ ታወራለች እኔ ግን የማውቀው እመጣለሁ ብላኝ ሄዳ እንደቀረች የእኔና'ሷ ጉዞ በዚህ ነው ያበቃው መጥታ እያጣችኝ ጠብቄያት እያጣው ግን እኮ ነበርኩኝ ጠብቀኝ ካለችኝ ቦታ ሳልል ንቅንቅ ሰዓት ከቀን ገጥሞ ወር ከዓመት ትንቅንቅ ክረምት እና በጋው በላዬ እያለፈ ልቤ እሷን ጥበቃ እንደተደገፈ ምናልባት ምናልባት በላብ በቆሻሻ መልኬ ካላደፈ በመሰንበት ብዛት ጠጉሬ ካልረገፈ ስጠብቃት ነበር በየሄደችበት እንዲቀናት በለስ ጉዳይዋን ፈፅማ ቶሎ እንድትመለስ የፀለይኩት ፀሎት ለሷ ብቻ ደርሶ ባለችበት ደልቷት ዕድሜዋ ገስግሶ በድሎቷ መሀል አንድ ጊዜ መጥታ ለመቅረብ ባትደፈር ከሩቅ አይኔን አይታ ንፁህ መጠበቄን ላለማጉደል ፈርታ እያዘነች ሄዳ እያነባች ሸሽታ ካልሆነ በስተቀር ቀጥራኝስ ካልቀረች አርፍዳ ነው ሚሆን ዘመን ቀይሮናል ብትመጣም አላውቃት እውን መጥታስ ቢሆን እሷ ጠብቀኝ ካልኩበት መጥቼ አጣሁት ብላ ታወራለች እኔ ግን የማውቀው እመጣለሁ ብላኝ ሄዳ እንደቀረች ልክ ናት በሷ ዓለም አርፍዳ ይሆናል ቀርታ ግን አይደለም ልክ ነኝ በኔ ዓለም ትመጣለች ሳልል ያለፈኝ ቀን የለም እድል ይሁን ዕጣ ወይ የአምላክ ውሳኔ አርቆ ያስቀረን ቀንሽ ወይስ ቀኔ የትኛው ይረገም የትኛው ይወንጀል አለሁ ስጠብቅሽ መጥተሽ ነው ያጣሽኝ የለብሽም በደል ሆነና ያንዳንዴ ያጋጣሚ ነገር እኔም አለኝ እውነት አንቺም አለሽ እውነት ለሀቅ የሚነገር ባድባር በሰፈሩ ለወጪ ወራጁ ለተራማጅ ቋሚው እስከምሆን ድረስ ምልክት ጠቋሚው ፀሀይ ከጨለማ ምሽት እና ቀኑ ለሚጠብቅ ገላ አንድ እንደሚሆኑ ያልገባቸው ሁሉ መሸ ነጋ ቢሉ በምስራቋ በኩል አንቺ እስከምትወጪ ከጨረቃዋ ጋ        አብረሽ ሳትመጪ ፅልመት ቢሆን ብርሀን ቀኑ ምን ትርፍ አለው ከትዝታ ውጪ እሷ ጠብቀኝ ካልኩበት መጥቼ አጣሁት ብላ ታወራለች እኔ ግን የማውቀው እመጣለሁ ብላኝ ሄዳ እንደቀረች ወይ በሄደችበት ከፀለይኩት ፀሎት አንዱም ሳይሳካ መንገዷ ተሞልቶ በእንቅፋት በሳንካ ብክንክን እንዳለች አንድ ነገር ሆና ወድቃ ቀርታስ ቢሆን ከአንዱ ጎዳና ቢሆንስ ቢሆንስ ቀጥራኝስ ካልቀረች አርፍዳ ነው ሚሆን ዘመን ቀይሮናል ብትመጣም አላውቃት እውን መጥታስ ቢሆን ። በረከት_ዘውዱ @yegtm_hywet @amharic_poet @poem_profile
Show all...
👍 5🥰 1

🤷‍♂ 2
ብቻ ስትስቅ ልያት ""'''''''' """""""" """"""" የደስታዋ ምክንያት ለመሆን ስሞክር ጭንቀቷ ላይ ቆሜ እምቢኝ ስል ልፎክር ዱካኳን ገርፌ ልሰደው እርቃኑን ሀዘኗን ደብድቤ ላሳጣው እርባኑን ስፈልግ አመሹሁ የደስታዋን ዓለም ሳቋን ለመመለስ ያልሞከርኩት የለም ጥርሷን ባየው ብዬ የጉንጮቿን ስርጉድ ከንጋት እስኪመሽ እያልኩኝ ሽር ጉድ ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ምን ያልሆንኩት አለ ያልዋልኩበት ቦታ የሷን ሳቅ ልሸምት ሸጥኩኝ የኔን ደስታ ብቻ ትሳቅልኝ ሲከፋት እንዳላይ የነጥብ ደመና እንደሌለው ሰማይ ፍክትክት እንዳለች ይቆጠር ዘመኑ ከአድማስ ይራቃት እንባና ሀዘኑ እንባዎቿን ስጠኝ ሀዘኗን ልጋራት መደሰቴ አይቀርም ፈገግ ብላ ሳያት #በረከት_ዘውዱ @Amharic_poet @Yegtm_hywet @Poem_profile
Show all...
👍 22🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.