en
Feedback
ሲዲ ስፖርት/CD Sport

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

Open in Telegram

ክላሲክ እና ዳይናሚክ ስፖርት በዩ-ቱብ https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=Yk8kAbDyLZZzoTp- ሲዲ ስፖርት በአራዳ ራዲዮ 95.1 - ትክክለኛ የሀገር ዉስጥ እና የባህርማዶ ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል። "ሙያን ለሙያተኛ"

Show more
4 075
Subscribers
No data24 hours
-27 days
+6730 days
Posts Archive
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኦሊምፒክ ሊዮን በቀጥታ ስርጭት ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ https://www.youtube.com/live/wZ40rqki94c?si=3ymZb4nTEbN_Uoui

ሪያል ማድሪድ ከ አርሰናል በቀጥታ ስርጭት ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ https://www.youtube.com/live/Af1LhzIV0S0?si=sx6pXzO9DeSwS7gH

ይህ አዲሱ የዩቱብ ገፃችን ነው።ውድ ቤተሰቦቻችን ገፁን ሰብስክራይብ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን https://youtube.com/@dynamicsport1098?si=zQ2OvPMGbZD65Jer

የአርሰናሉ ግብጠባቂ ዴቪድ ራያ ከጉዳቱ አገግሞ ከቡድኑ ጋር ሆቴል ገብቷል።ለምሽቱ የማንችስተር ሲቲ ፍልሚያም ዝግጁ እንደሆነ ታውቋል። ሲዲ ስፖርት/cd sport
የአርሰናሉ ግብጠባቂ ዴቪድ ራያ ከጉዳቱ አገግሞ ከቡድኑ ጋር ሆቴል ገብቷል።ለምሽቱ የማንችስተር ሲቲ ፍልሚያም ዝግጁ እንደሆነ ታውቋል። ሲዲ ስፖርት/cd sport

አስቶንቪላ በመጨረሻው ቀን 3ት አጥቂ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም ጫፍ ላይ ደርሷል።ራሽፎርድን ከማንችስተር ዩናይትድ፣ማርኮ አሴንሲዮን ከፒ ኤስ ጅ እና ዥዋ ፍሊክሽን ከቸልሲ ለማዘዋወር የወረቀት ስራዎችን
አስቶንቪላ በመጨረሻው ቀን 3ት አጥቂ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም ጫፍ ላይ ደርሷል።ራሽፎርድን ከማንችስተር ዩናይትድ፣ማርኮ አሴንሲዮን ከፒ ኤስ ጅ እና ዥዋ ፍሊክሽን ከቸልሲ ለማዘዋወር የወረቀት ስራዎችን እያጠናቀቁ ነው። ሲዲ ስፖርት/cd sport

#ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች አስቸኳይ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ 1.የስራ መደቡ - ሴኒየር አካውንታንት የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ ብዛት - 3 ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም
#ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች አስቸኳይ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ 1.የስራ መደቡ - ሴኒየር አካውንታንት የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ ብዛት - 3 ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው። 2.የስራ መጠሪያ - ሴኒየር መሀንዲስ የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ ብዛት - 3 ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው። አመልካቾች ሲሺያችሁን ይዛችሁ መገናኛ አካባቢ እንግሊዝ ኢምባሲ ከመድረስዎ 100 ሜትር ቀደም ብሎ ባለው ሜናሮል ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።ለበለጠ መረጃ በ0911404917 ላይ ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ። ይፍጠኑ ቅድሚያ ለሚመጣ ቅድሚያ ይሰጣል!

#ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች አስቸኳይ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ 1.የስራ መደቡ - ሴኒየር አካውንታንት የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ ብዛት - 3 ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው። 2.የስራ መጠሪያ - ሴኒየር መሀንዲስ የስራ ልምድ - ከ5 አመታት በላይ ብዛት - 3 ደመወዝ በድርድር ሲሆን አጓጊ ጥቅማጥቅሞችም አለው። አመልካቾች ሲሺያችሁን ይዛችሁ መገናኛ አካባቢ እንግሊዝ ኢምባሲ ከመድረስዎ 100 ሜትር ቀደም ብሎ ባለው ሜናሮል ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።ለበለጠ መረጃ በ0911404917 ላይ ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ። ይፍጠኑ ቅድሚያ ለሚመጣ ቅድሚያ ይሰጣል!

ባርሴሎና በሜዳው ለሌጋኜስ 1 ለ 0 እጅ በሰጠበት ጨዋታ ፈርሚን ሎፔዝ ጥርሱን አጥቷል። ላሚን ያማል የቁርጭምጭሚት ጉዳት አስተናግዷል። የላሊጋው ትንቅንቅ አስደናቂ ሆኗል። ሪያል ማድሪድ እና አትሌቲ
+6
ባርሴሎና በሜዳው ለሌጋኜስ 1 ለ 0 እጅ በሰጠበት ጨዋታ ፈርሚን ሎፔዝ ጥርሱን አጥቷል። ላሚን ያማል የቁርጭምጭሚት ጉዳት አስተናግዷል። የላሊጋው ትንቅንቅ አስደናቂ ሆኗል። ሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያላቸው ከላሊጋው መሪ ባርሴሎና ጋር አትሌቲኮ ነጥቡን እኩል ሲያደርግ ሪያልማድሪዶች ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ አጥበውታል። አትሌቲኮ ማድሪድ በ11 ተከታታይ የላሊጋ ጨዋታ በተከታታይ ድል አስመዝግቧል። የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ከባለፉት 6 ጨዋታዎች 3 ተሸንፈው ሁለት አቻ ወጥተው አንድ ጨዋታ አሸንፈዋል ።9 ጎሎችም ተቆጥረውባቸዋል። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል። ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ያሉት ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ ይሆናል። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https:
+1
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል። ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ያሉት ቡድኖች በቀጥታ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ ይሆናል። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

አማራ ክልል ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ ጠንካራ እጩዎችን አቀረበ። ታህሳስ 12 እና 13 ለሚካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ አማራ ክልል አቶ ያየህ አዲስን ለፕሬዝደንትነት እጩ አድርጎ
+2
አማራ ክልል ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ ጠንካራ እጩዎችን አቀረበ። ታህሳስ 12 እና 13 ለሚካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ አማራ ክልል አቶ ያየህ አዲስን ለፕሬዝደንትነት እጩ አድርጎ አቅርቧል። አቶ ያየህ አዲስ የቀድሞ የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል። በስፖርት አመራርነት ረዥም ጊዜ የቆዩት አቶ ያየህ አዲስ የባህርዳር ስቴዲየምን በማስገንባት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። አቶ ቢልልኝ መቆያ እና ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ክልሉ ለስራ አስፈፃሚነት በእጩነት ያቀረባቸው ናቸው። አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል። የአማራ ክልል ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር ሆነው በአመራርነት ረዥም ጊዜ ሰርተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስርአት እንዲመራ ሪፎርም በማዘጋጀት እና በመተግበር ከፍተኛ ስራም አከናውነዋል። ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ አሁንም በፌዴሬሽኑ ውስጥ በስራ አስፈፃሚነት የሚገኙ ናቸው። ሲዲ ስፖርት/cd sport

በአለም ላይ እለት በእለት የሚሰማው ዜና እጅን አፍ ላይ ያስጭናል። የቸልሲዋ ተጫዋች ሳም ኬር እና የዌስትሀሟ ክርስቲ ሜዊስ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ልጃቸውን እንደሚጠብቁ ተናገሩ። ከሁለ
በአለም ላይ እለት በእለት የሚሰማው ዜና እጅን አፍ ላይ ያስጭናል። የቸልሲዋ ተጫዋች ሳም ኬር እና የዌስትሀሟ ክርስቲ ሜዊስ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ልጃቸውን እንደሚጠብቁ ተናገሩ። ከሁለቱ ፍቅረኛማቾች የትኛዋ እንዳረገዘች እና ያስረገዘው ወንድስ ማን እንደሆነ ስካይ ስፖርት ያለው ነገር የለም። አጃኢብ !! ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል። ይህ ሲዲ ስፖርት ነው ። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

የ58 አመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ሰሞኑን አስገራሚ ቃለ ምልልስ ሰጥቷል። "አሁን ላይ በህይወት መኖሬ በጣም እድለኛ ነኝ። በአንድ ወቅት ከጓደኛዬ ጋር በመሆን አንዲት ሴት ጋር ጥንቃቄ የጎደለው እና
የ58 አመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ሰሞኑን አስገራሚ ቃለ ምልልስ ሰጥቷል። "አሁን ላይ በህይወት መኖሬ በጣም እድለኛ ነኝ። በአንድ ወቅት ከጓደኛዬ ጋር በመሆን አንዲት ሴት ጋር ጥንቃቄ የጎደለው እና ልቅ ወሲብ ፈፀምኩኝ። እሱም እሷም በHIV ኤድስ ህይወታቸው አልፏል። እኔ ግን በህይወት አለሁኝ ። የሚያስገርመው ደግሞ በደሜ ውስጥ ቫይረሱ አለመኖሩ ወይም ነፃ መሆኔ ነው። ይህንን ባለሙያዎች ምን እንደሚሉት አላውቅም ። ግን ጥናት እንዲያደርጉብኝ እፈቅድላቸዋለሁ። " ብሏል። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ትንሿ አገር ትልቅ እና ታሪካዊ ድል አስመዘገበች። ከሁለት ወር በፊት ሴፕቴምበር 5፣ 2024 እ.ኤ.አ በወዳጅነት ጨዋታ ሳን ማሪኖ በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊችተንስታይንን 1-0 በማሸነፍ የመጀመሪያ
ትንሿ አገር ትልቅ እና ታሪካዊ ድል አስመዘገበች። ከሁለት ወር በፊት ሴፕቴምበር 5፣ 2024 እ.ኤ.አ በወዳጅነት ጨዋታ ሳን ማሪኖ በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊችተንስታይንን 1-0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች ። 🤯 ትናንት ኖቬምበር 18፣ 2024 እ.ኤ.አ ሳን ማሪኖ ሊችተንስታይንን 3-1 ከረታች በኋላ ወደ ኔሽንስ ሊግ ሲ ማደጓን አረጋግጣለች። የሳን ማሪኖ የ3 ለ1 ድልን ተከትሎ:- በታሪካቸው ትልቁ ድል ከሜዳቸው ውጭ የመጀመሪያ ድል የ UEFA እና የፊፋ አባል ከሆነች በኋላ የመጀመሪያ የፉክክር ጨዋታ ድል ሆኖ ተመዝግቦላታል። ታሪካዊ ምሽት ለሳንማሪኖ። 👏 ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ሌላዋ የሴካፋዋ ሱዳን 🇸🇩 የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በብቃት በማጠናቀቅ ወደ ሞሮኮ ትኬት ቆርጣለች 🇲🇦 👏 ምንም እንኳን በሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሜዳዋ ጨዋታ ሳታ
ሌላዋ የሴካፋዋ ሱዳን 🇸🇩 የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በብቃት በማጠናቀቅ ወደ ሞሮኮ ትኬት ቆርጣለች 🇲🇦 👏 ምንም እንኳን በሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሜዳዋ ጨዋታ ሳታደርግ እና ሁሉንም ግጥሚያዎች ከሜዳዋ ውጭ ብትጫወትም በጋናዊው አሰልጣኝ ክዌሲ አፒያ ስር ጠንካራ አቋም አሳይታለች። ከምድቧ 8 ነጥብ ይዛ አንጎላን ተከትላ አፍሪካ ዋንጫ አልፋለች። ሱዳን በምድቧ ጋናን 2 ለ 0 በማሸነፍ እና 0ለ0 በማጠናቀት ከእግር ኳሷ ጠንካራ ሀገር ጋና 4 ነጥብ መውሰድ ችላለች ። ኒጀር ላይ 3 ነጥብ አንጎላ ላይ ላይ 1 ነጥብ አግኝታለች። ሲዲ ስፖርት/cd sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ዌስትሀም ፔናሊቲ አይገባውም። (ሲዲ ስፖርት/ CD Sport:ህዳር 5/2017)የዳኞች አለቃ ሃዋርድ ዌብ ጥቅምት 27 የኤሪክ ቴን ሃግ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ዌስትሃም ፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጠው አይገባም
+1
ዌስትሀም ፔናሊቲ አይገባውም። (ሲዲ ስፖርት/ CD Sport:ህዳር 5/2017)የዳኞች አለቃ ሃዋርድ ዌብ ጥቅምት 27 የኤሪክ ቴን ሃግ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ዌስትሃም ፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጠው አይገባም ነበር ብለዋል። መዶሻዎቹ ውሳኔውን ያገኙት በቫር ዳኛ ማይክል ኦሊቨር ጥቆማ ማቲያስ ዴሊት በዳኒ ኢንግስ ላይ ጥፋት ሰርቷል በሚል ነው። ዋናው ዳኛ ዴቪድ ኩት የቫር ጥሪን ከሰማ በኋላ ፍፁም ቅጣት ምቱን ሰጥቷል። ጃሮድ ቦወን ወደጎልነት ቀይሮት ዌስትሃም ማንችስተር ዩናይትድን 2-1 በማሸነፍ አሰልጣኝ ቴን ሃግ ከጨዋታው በኋላ ከ24 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከክለቡ አሰልጣኝነት ሊባረር ችሏል። "በVAR የተሳሳተ ውሳኔ ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል። መሆን አልነበረበትም። VAR እምነት የሚጣልበት ነበር ። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የዴሊት እግር ወደ ዳኒ ኢንግስ እየተጠጋ እንጂ ምንም እግሩን አልጠለፈውም። ኳሱን ስላላገኘው ለቫር ዳኞች ንክኪ ያለው መስሏቸው ነው። " ሲል ሀዋርድ ዌብ ለስካይ ስፖርት ተናግሯል። ሲዲ ስፖርት/CD Sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ቤንታንኩር ከባድ ቅጣት ሊጣልበት ነው ። (ሲዲ ስፖርት/ CD Sport: ህዳር 5/2017)የቶተንሀሙ አማካኝ ዩራጓዊው ሮድሪጎ ቤንታንኩር ሰባት ጨዋታዎች እንደሚቀጣ ይጠበቃል። ቤንታንኩር በዩራጓይ ቴ
ቤንታንኩር ከባድ ቅጣት ሊጣልበት ነው ። (ሲዲ ስፖርት/ CD Sport: ህዳር 5/2017)የቶተንሀሙ አማካኝ ዩራጓዊው ሮድሪጎ ቤንታንኩር ሰባት ጨዋታዎች እንደሚቀጣ ይጠበቃል። ቤንታንኩር በዩራጓይ ቴሌቪዥን በተደረገለት ቃለምልልስ ላይ ጋዜጠኛው ስለቶተንሀም ተጫዋቾች ማሊያ በጠየቀበት ወቅት ስለ ደቡብ ኮሪያዊው ሰን ሂዩንግ ሚን "ሰን ሜዳ ላይ ይኑር አይኑር እርግጠኛ አይደለንም ። የሰን አክስት ልጅ ሜዳ ውስጥ እየተጫወተ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ደቡብ ኮሪያዎች መልካቸው አንድ አይነት ነው።" ብሏል ። ቤንታንኩር በኋላ ላይ ደስ የማይል ቀልድ ነው የተናገርኩት በማለት ሰንሂዩንግ ሚንን ይቅርታ ጠይቆታል ሰንም "እኔ ሮድሪጎን እወደዋለሁ እያለቀሰ የጠየቀኝን ይቅርታውን ተቀብያለሁ ብሏል ።" ይሁን እንጂ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የዘረኝነት ቃል ነው በሚል ቤንታንኩር ክስ እንዲመሰረትበት ተደርጓል። ቀድሞ በወጣው የውስጥ አዋቂዎች መረጃ ሮድሪጎ ቤንታንኩር የሰባት ጨዋታዎች ቅጣት እንደሚጣልበት ታውቋል። የቅጣቱ ውሳኔ ሲተላለፍ ቶተንሀም ከማንሲቲ፣ ፉልሀም ፣ በርንመዝ፣ ቸልሲ፣ ሳውዝሀምፕተን፣ ማንዩናይትድ እና ሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተገልፆል። ቦታውን ቢሱማ አለያም የ18 አመቱ አርክ ግሬይ እንደሚሸፍኑት ይጠበቃል። ሲዲ ስፖርት/CD Sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL

ዘጠነኛ የእንግሊዝ ተጫዋች የጉዳት ሪፖርት ቀረበ። (ሲዲ ስፖርት / CD Sport:ህዳር 5/2017)ጃራድ ብራንትዋይት ሌዊ ኮልዊልን ለመተካት ከተጠራ ከሁለት ቀናት በኋላ በደረሰበት ጉዳት ከእንግሊዝ
ዘጠነኛ የእንግሊዝ ተጫዋች የጉዳት ሪፖርት ቀረበ። (ሲዲ ስፖርት / CD Sport:ህዳር 5/2017)ጃራድ ብራንትዋይት ሌዊ ኮልዊልን ለመተካት ከተጠራ ከሁለት ቀናት በኋላ በደረሰበት ጉዳት ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውጪ ሆኗል። በዚህ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውጭ የሆኑት ዘጠኝ ተጫዋቾች ሆነዋል። እነሱም:- ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ ጃራድ ብራንትዋይት ሌዊ ኮልዊል ፊል ፎደን ጃክ ግሪሊሽ ኮል ፓልመር አሮን ራምስዴል ዲክላን ራይስ እና ቡካዮ ሳካ ናቸው። እንግሊዝ ዛሬ ምሽት ከግሪክ እንዲሁም እሁድ ከሪፐብሊክ ኦፍ አየርላንድ ጋር በኔሽንስ ሊግ ትጫወታለች። ሲዲ ስፖርት/CD Sport 👉 youtube: https://youtube.com/@Classicdynamicsportofficial?si=dFklpl9UVw2ib39J 👉 tik tok : https://www.tiktok.com/@classic_dynamic?_t=8m3BSb0mxVt&_r=1 👉 telegram: https://t.me/DC4544 👉 facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064110330297&mibextid=ZbWKwL