cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰንፔር ሚዲያ Sapphire Media

መንፈሳዊ መጣጥፎችን ግጥሞችን ወጎችን አጫጭር ልቦለዶች አስደናቂ ታሪኮችን ትምህርታዊ ፅሁፎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን። "ትውልድ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ተሰቀለው ክርስቶስ ተመልከቱ!!!" https://youtu.be/KRKo3x7iYNw http://Instagram.com/sapphiremedia4god tiktok.com/@sapphiremedia1

Show more
Advertising posts
463
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በሀዋሳ አዲስ ከተማ ሙሉ ወንጌል የወጣቶች የድራማና የስነፅሁፍ ህብረት የተሰናዱ ሁለት ዝግጅቶች #ብኤርለሃይሮኢ ቀን: ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 29 ቦታ:በሀዋሳ አዲስ ከተማ ሙሉ ወንጌል ሰዓት: 11:00 #ሎዶቅያዊት ቀን: ግንቦት 02 ቦታ:በሀዋሳ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሰዓት: 11:00
Show all...
ኢየሱስ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅንቷል። ተከታዮቹ ፍርሃት እስኪገባቸው ድረስ ፍጥነቱ ጨምሯል “ወደ ኢየሩሳሌም ለመውጣት በመንገድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ተገረሙ፣ ሌሎች የተከተሉት ደግሞ ፈርተው ነበር።” (ማር 10፥32)። በማርቆስ ወንጌል ትራኬ ውስጥ፥ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እርሱም ብዙ መከራ ይቀበላል፣ በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ይናቃል፣ ይገደላል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ ይነሣል። ማቴዎስም ኾነ ሉቃስ ይህንን የማርቆስን ትራኬያዊ አቅጣጫ በቅርበት ይከተሉታል። ነቢዩ ኢሳያስ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ” እንደሚል፣ ይህ መንገድ ተጠርጓል፣ ጌታም እየተራመደበት ይገኛል። ይህ ሥጋ ለባሽ ኹሉ ወደ ሚመለከተው ክብር የሚወስደው መንገድ የሚያመራው ወደ ቀራንዮ ጎልጎታ ነው። ታዲያ፣ኢየሱስ በዚህ መንገድ ላይ ሳለ ፦   1. ሶስት ጊዜ ስለ መከራው፣ ሞቱና ትንሳኤው አስቀድሞ ይተነብያል (ማር 8፥31፣ 9፥31፣ 10፥33-34)።   2. ሶስቱንም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ለዚህ ትንበያ ምላሽ ይሰጣሉ (8፥32፣ 9፥33-34፣ 10፥35-41)። ሆኖም ግን የሚሰጡት ምላሽ የእርሱን ተልዕኮ  እንዳልተገነዝቡ ያሳያል። ጴጥሮስ ኢየሱስን “ይገሥጸው ጀመር” (8፥32)፣ ሐዋርያት “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው” እያሉ ይከራከራሉ (9፥34)፣ የተወሰኑትም “በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝህ፣ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድልን” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ፣ ይህንን ያደመጡም በመቀደማቸው ይቆጣሉ (10፥37)።   3. ሶስት ጊዜም ኢየሱስ እርሱን መከተል ምን ማለት እንደኾነ የደቀ መዝሙርነትን ምንነት እየገሰፀ ያስተምራቸዋል (8፥34-37፣9፥35-37፣ 10፥42-45)። ዐይነ ስውሩን ሁለት ጊዜ እደፈወሰው (8፥22-26) ደቀ-መዝሙርቱም እንዲኹ ሁለት ጊዜ መዳሰስ እስኪያስፈልጋቸው ድረስ ታውረዋል፣ ልባቸው ደንዝዟል። የኢየሱስ ተልእኮ አልገባቸውም ነበር። 1. “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (8፥34) 2. “መጀመሪያ ለመሆን የሚፈልግ፣ ከሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ይሁን” አላቸው” (9፥35) 3. “ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋይ ይሁን፤ "ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ይሁን፤ የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣምና።” (10፥43–45) እንዳንዘነጋ፣ ይህ ቀን ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ቤዛ የኾነበት ቀን እንደኾነ ኹሉ፣ የእርሱን ፈለግ የምንከተልበትም ቀን ነው። ኢየሱስ ሞቶ ከተነሣ በኋላ፣ እነዚህ ደቀ መዛሙርት የደቀ መዝሙርነት ትርጕም ገባቸው። ከራሳቸው በላይ ዝቅ ብለው ሌሎችን አገለገሉ። አልፎም እነርሱም እንደ ጌታቸው ለመሰቀል፣ ለመሠየፍና ለመወገር ፈቃደኞች እስኪሆኑ ለሌሎች ኖረው አለፉ። የማርቆስ ጥያቄ አሁን ያነጣጠረው በእኛ ላይ ነው! ተልእኮው ገብቶናል? የደቀ-መዝሙርነት መንገዱ ገብቶናል? ግን ገብቶናል? የማርቆስ ግሣጼ፣ ኢየሱስ ‘ተልእኮው ያልገባቸው ተከታዮች የሉትም’ የሚል ነው። ሳምሶን ጥላሁን
Show all...
እዩ ተመልከቱት ፤ የክርስቶስን መስቀል ዛሬም ሲፈውስ ፤ የነፍስን ቁስል። © ቢቶ
Show all...
የዛሬ ሳምንት በሀዋሳ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን
Show all...
እንደምን ጨካኝ ነው በልጁ ይሉኻል፣ ኃጢአትን ሰቅለው ወንበዴዎች መኻል! . ደካማ ነው አሉ ልጁን ካላዳነ፣ ሕዝብን ባንድ አድኖ ደም እየከደነ! . ይህ ተርታ ሕዝብ ኹሉ ተባብሮ ባንድ ቃል፣ "ራስህን አድን" ብሎ ይሣለቃል፣ ነገ በሱ ሊድን መኾኑን መች ያውቃል? #ሰሙነ_ሕማማት © Abere Ayalew
Show all...
<<ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?>> <<ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።>> ዩሐ.13፥12-17 ~~~~ [ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ እግር አጠበ ባሪያውን ወርዶ እራሱን አዋርዶ] ~~~ በአቧራማዋ እስራኤል በነጠላ ጫማ (Sandals) መንቀሳቀስ የተለመደ ነበር። የጋራ ምግብ ከመቅረቡ በፊት ደግሞ ሰው እግሩን ታጥቦ ነው የሚቀመጠው፣ እጅ መታጠብ በኛ ዘንድ እንደተለመደው። ምክንያቱ ደግሞ ጠረጴዛው ዝቅ ያለ (low table) ስለሆነ ነው። ኢየሱስ ተነስቶ እግራቸውን ሲያጥብ የመጨረሻው ተራ ሎሌ ባሪያ የሚያደርገውን እየከወነ ነበር። ደቀመዛሙርቱም ራሱን 'በማዋረዱ' ሳይገረሙ አይቀሩም። የነፍሳችን ጌታና መሲህ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ፣ የአለምን ኅጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ... ሲሉት የከረሙት ሰዎች እግሩን ማጠብ ሲጠበቅባቸው እሱ ቀድሞ እግራቸውን ለማጠብ ማበሻ ማንሳቱ ባያስደንቃቸው ነው የሚገርመው። ምንም እንኳን እንደ ምድራዊ ንጉስና ነፃ አውጪ መጠበቃቸው የሚያደርጋቸውን እያንዳንዱን ድርጊቶቹን በአግባቡ ለመገንዘብ ቢከብዳቸውም፤ እንደ ስቅዩ-ሎሌ (suffering Servant) መምጣቱን አርፍደው ነው የተገነዘቡት (ኢሳ. 53)። ~~~~~~~ [ደቀመዛሙርቱ እግራቸው ቆሸሸ አደፈ ጎደፈ ፍጹም ተበላሸ ሁሉን የፈጠረ ሰውን የወደደ ጭቃውን ሊያስወግድ ወደ ታች ወረደ] ~~~~~~ ምጡቅ የሆነ፣ ሁሉን የሚገዛና ሁሉ በሁሉ የሆነ አምላክ እግር ሊያጥብ ዝቅ አለ፣ ከአቧራማ እግሮች ስር ተገኘ። "ፍጹም የቆሸሸን" ሰው ለማንፃት ፍጹም ንፁህ የሆነው ወልድ ራሱን ባዶ በማድረግ ወደ ታች ወረደ (ፊል. 2፥6-11)። ቃል መገለጡና በውርደት መንቀሳቀሱ አስደናቂ ነበር። የእግዚአብሔር ልጅ የህማም ሰው በመሆን፣ ቤት አልበኛ በመሆን፣ የድኻ ወዳጅ በመሆን፣ የኅጢአተኛ ወዳጅ በመሆን የተሰበረውን አለም ራሱን በመስቀል ለመስበር ተገኘለት። እንዴት ያለ የትህትናና የፍቅር ጥግ አሳየን! የእግራቸውን ቁሻሻቸውን ሲያፀዳ፣ አደፋቸውን ሲያጠራ ፈለጉን እንድንከተል ይመስላል "ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?" ብሎ የጠየቀን። አለሙ በኅጢአቱ ሲዳሽቅ ራሱን ለመላ አለሙ የቆረሰው ጌታ፣ ከአለሙ ድካምና ደዌ ራሱን ሳይሸሽግ የተገመሰለት አምላክ በድርጊቱ የምንቆርሰው እውነትን ችሮናል። ~~~ [እሱ ያላጠበው ከእርሱ ጋር አይኖርም አይቆርስም ከአምላክ ጋር አንድነት የለውም ጴጥሮስ ይህን አይቶ ሰውነቴን ደሞ እጠበኝ ጌታ ሆይ አለውም ተማጽኖ] ~~~~~ ኢየሱስ ስለራሱ ከነበረው ግንዛቤ አንዱ የሚያደርገውን የሚያደርግበት ምክንያትን ጠንቅቆ ማወቁ ነው።በኢየሱስ ያደረገው ስለራሱ በማቴ. 20፥28 እንዳለው "ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" ራሱን ዝቅ አድርጎ ሌሎችን ሊያገለግል ነው የመጣው። ከግዞት በኋላ እስራኤል ያጣችውን ፖለቲካዊ ነፃነትን ለእስራኤል ለመቸር ሳይሆን በኅጢአት ግሳንግስ የታፈነውን አለም ከህማሙ ለመፈወስ ነው የመጣው። እግዚአብሔር ለእስራኤል ብሎም ለአሕዛብ የሰጠውን ተስፋ በእርሱ የሚፈጸምበት እግዚአብሔር "ምርጤ፣ ባሪያዬ" ያለው መሆኑ በአግልግሎቱ ቁልጭ ብሎ ይታይ ነበር። ለዚህ ነው የገዛ የራሱን ዐለም ከውልደቱ ጀምሮ በትህትና፣ በዝቅታ፣ በመዋረድ፣ በመከራና ፍዳን በመቀበል ያናገረው። ብቸኛው ቋንቋ መስቀል የሆነው። ከማገልገሉም ባሻገር ሕይወቱ እንደሚነግረን በትህትና መሞላቱን ነው። ከአመጣጡ እስከ አሟሟቱ ድረስ ድንቅ በሆነ ትህትና የተሞላ ነው። ~~~~ [በሚደነቅ ብርሃን የሚኖር ፈጣሪ አልፋና ኦሜጋ የፍጥታት ሰሪ ማበሻ ጨርቅ ወስዶ እግር ሊያጥብ ወረደ ዝቅ አ'ረገ ራሱን ለሰው ተዋረደ] ~~~~ የኢየሱስ ዝቅ ብሎ እግር ማጠቡ ዘማሪ ደረጄ ከበደ እንዳለው "ትህትናን ሊያስተምረኝ ወዶ" ነው። ያደረገልን ራሳችንን በትህትና ዝቅ አድርገን የባልንጀራችንን እግር እንድናጥብ ነው። ጉድፉን እንድናጠራ፣ ከክፉና እኩይ እንድንከላከለው እንዲሁም ራሳችን ለባልንጀራችን አሳልፈን እንድንሰጥ ነው። "በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ" በእኛ እንዲኖር ነው። እግር ጉድፍ ሲያነሳ እንድንጠርገው በዚያም ትህትናችን እንዲታይ ተጠርተናል። ~~~~~~~ [የሁሉ ማሰሪያ አላማ ያለው ነው ጌታ ይህን አድርጎል እኔስ እንደምን ነው? የወንድሜን እግር እስካጥብ ዝቅ ካልኩ እውነትም 'የሱስን በእርግጥ ተከተልኩ] ~~~~~ ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር አጥቦ ሲጨርስ "እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና" ብሏቸዋል። በሚደንቅ ብርሃን የሚኖር ምጡቅ አምላክ እግር ለማጠብ ማበሻ ጨርቅ ወስዶ የታናናሾችን ስራ ከሰራ እኛማ እንዴት ፈለጉን አንከተል?! እንደ ክርስቶስ ተከታይ እሱን በህይወቱ ልንመስል ይገባልና፣ ትሁት መሆን አለብን። የክርስቲያን መለኪያው ክርስቶስን መምሰል ነው። ዝቅ ማለት፣ ራሱን ማወረድ፣ ራሳችንን የሚጠቅመውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሚጠቅመውንም ማድረግን ከጌታ ልንማር ይገባናል።የዝቅታን መንፈስ ይስጠን! ~~~~~~~ [ባሪያ ከሚያኖረው አይበልጥም አላቸው መልክተኛም አይበልጥ ይልቁን ከላከው እንግዲህ ጌታችሁ እኔ ይህን ስፈጽም አድርጉት ለሁሉም ዛሬ ሁኑ እናንተም] ~~~~~~ ባሪያ ከጌታው እንደማይበልጥና እኩልም እንዳይደለ ሁሉ ጌታ የፈፀመው ድርጊት እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች ልንከተለው የተገባ ነው። እግር ማጠብ ግዴታ እግር ማጠብ አይደለም። ክብርን መተው፣ ራስን ዝቅ ማድረግ፣ ራስን ማዋረድ፣ ራስን ለሌሎች መቁረስ፣ ትህትና ነው። ጌታ ያደረገውን እርስ በእርስ እያንዳንዳችን እናደርገው ዘንድ የተገባ ነው። የክርስቲያን መለያው፣ የአማኝ መታወቂያው የክርስቶስን ፈለግ መከተሉ እስከሆነ ድረስ አንዳችን ለሌሎቻችን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ ማገልገል ይገባናል። Every good thing in the Christian life grows in the soil of humility. Without humility, every virtue and every grace withers. That's why Calvin said humility is first, second, and third in the Christian faith. John Piper እዚህ ጋር አንድ ዝማሬን እንዘምራለን፣ አብረን በፀሎት እንቃትታለን :- [ከከበረው እንቁ ሰው ከሚሻማበት እኔስ ትህትናን ባገኝ በዚ'ች ዕለት ጥማቴም ፀሎቴም ዝቅ ዝቅ ማለት] ~~~~~ <<ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?>> ዩሐ. 13፥12 መልካም ፀሎተ ሐሙስ! መልካም ቀን! © አማኑኤል አሰግድ
Show all...
Show all...
"በተራራው ጫፍ ላይ" ድንቅ መንፈሳዊ ግጥም በዶ/ር ጌዴዎን ጡሚሶ/New Amazing Spiritual Poem by DR. Gedion Tumisso/2024_2016

Show all...
ሰቆቃ ኑኃሚን አዲስ መንፈሳዊ ግጥም/በቢቶ/Seqoqa Nuhamin_New Protestant Poem/bito/Senpare Media_2024_2016

መንፈሳዊ ፊልሞች፣ ተከታታይ ድራማዎችን እና ሲትኮሞችን፤ የመድረክ ድራማዎች እና ተውኔቶች ፣ አስደናቂ ታሪኮችን እና ትረካዎች፤ ግጥሞች፣ የስነፅሁፍ ምሽቶችና ሌሎች አስደናቂ መንፈሳዊ የስነፅሁፍ ስራዎችን የሚቀርቡበት መንፈሳዊ የኪነጥበብ ቻናል ነው፡፡ "ትውልድ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ተሰቀለው ክርስቶስ ተመልከቱ!!!

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069721774543

http://Instagram.com/sapphiremedia4god tiktok.com/@sapphiremedia1