cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስትያናት ፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
157
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 11-13/2013 ዓ.ም ለሶስት ቀን ተከታታይ ጉባኤ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በሚል አብይ ርዕስ ቅዱስ ያሬድን እንዘክር መቅረት የተከለከለ ነው መርኃግብሩ ከ11:00 ጀምሮ 1:00 የሚያበቃ ይሆናል በዕለቱም የመዝሙር፣የኪነ ጥበብ፣የወንጌል ማዕድ ተዘጋጅትዋል እንዲታደሙ ተጋብዘዋል። የሰማችሁ በማሰማት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በቤተክርስቲያን ስም እንማፀናለን። መልካም ቀን
Show all...
የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት): ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 11-13/2013 ዓ.ም ለሶስት ቀን ተከታታይ ጉባኤ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በሚል አብይ ርዕስ ቅዱስ ያሬድን እንዘክር መቅረት የተከለከለ ነው መርኃግብሩ ከ11:00 ጀምሮ 1:00 የሚያበቃ ይሆናል በዕለቱም የመዝሙር፣የኪነ ጥበብ፣የወንጌል ማዕድ ተዘጋጅትዋል እንዲታደሙ ተጋብዘዋል። የሰማችሁ በማሰማት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በቤተክርስቲያን ስም እንማፀናለን። መልካም ቀን
Show all...
ቅዱስ ፓትርያርኩ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመውን ቃለ ዐዋዲ በይፋ መረቁ ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን የምትመራበት ቃለ ዐዋዲ በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ አማካኝነት በእንግሊዘኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰበካ ጉባዔ ማደራጃና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁአን አበው ሊነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተመርቋል፡፡ ምንጭ፦ የኢኦተቤ ቴሌቪዥን
Show all...
✝✝✝ እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ልደታ ለማርያም ድንግል "*+ ✝ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: ✝ " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " =>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: +ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: +እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8) =>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: +ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: +ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: +እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: +በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: +እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) +"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9) +እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- -ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: =>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ) 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቴክታና በጥሪቃ 4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር =>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጧም ሰው ተወለደ:: እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Show all...
#ከትንሣኤ_እሁድ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ፡- #ሰኞ #ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ #አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ #አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ #ቅድስት_ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ #ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ #ዳግም_ትንሣኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
Show all...