en
Feedback
Crypto Insights | analysis | tips

Crypto Insights | analysis | tips

Open in Telegram
5 679
Subscribers
No data24 hours
-217 days
-12030 days
Posts Archive
✳️ Firewall ምንድን ነው? ጥቅሙስ? ▫️ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ ባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለመበከል ነው። ▫️ማንኛውም የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለቫይረስ ኢላማ ነው። የኮምፕዩተር ቫይረስ በግለሰብ፣ በድርጂቶች፣ በመንግስቶች፣ በነጋዴወች ወዘተ ይሰራል። ▫️የሌላውን አበላሽተው ለመደሰትም ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ። የዚህንም ያህል የታመሙ ሰወች አሉ። ሁሉም የየራሱ አላማ አለው። የኮምፕዩተር ቫይረስ ውስብስብ ግን መጠኑ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጻር በጣም ትንሽ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ክብደቱና ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ግን አደገኛ ነው። ▫️አንቲ ቫይረስ፤ አንቲ ቫይረስ የተሰራው የኮምፕዩተር ቫይረስን ለመከላከል ነው። አሁን ከቅርብ አመታት ወዲህ እራሱ ዊንዶውስ አንቲ ቫይረስ(Windows Defender) በነጻ ለተጠቃሚው ይሰጣል። ሆኖም ግን ሌሎችም የሚሸጡ ነጋዴወች አሉ። ተጠቃሚው እራሱ የትኛውን አንቲ ቫይረስ መግዛት እንደሚፈልግ ይወስናል ማለት ነው። እንደጥራቱ ይለያያል። ▫️የነጻ አንቲ ቫይረሶችም አሉ። በሰፊውና ባይነቱ ለመከላከል ግን የሚገዛው ይሻላል። ለማንኛውም ዊንዶውስ በየጊዜው ስለሚጠቃ አንቲ ቫይረስም ቢሆን ሁሉንም ጥቃት አይከላከልም። አንቲቫይረስ እየሰሩ የሚሸጡ ነጋዴወችም እራሳቸው ቫይረስ ይሰራሉ እየተባለ ይታማሉ። ▫️ፋየርዎል ያልተፈቀደ የኮምፒዩተር ኔትወርክን በመጠቀም ከኮምፒውተር የሚገባንና የሚወጣን ያልተፈቀደ ግንኙነትን ለመከላከል የተነደፈ የደህንነት ስርዓት ነው።   ▫️ፋየርዎል ከኮምፒዩተር በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባውን እና የሚወጣውን የኔትወርክ ትራፊክ ይቆጣጠራል።  ▫️ፋየርወል በእንግሊዘኛው እሳት የሚከላከል ግድግዳ እንደማለት ነው። ፋየርወል ከውጭ ወደ ኮምፒውተራችን በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባን ቫይረስ መሰል የመረጃ በካይ፣ አጥፊ፣ ሰራቂ፣ ሰላይ ፕሮግራሞች እንዳይገቡ በመጠኑም ቢሆን የሚከላከል ሲሆን በጣም ጠቃሚና ለመረጃ ደህንነት አስፈላጊ የኮምፒውተር ማስተካከያ ነው። ▫️ስለዚህ ኮምፒውተታችንን ከኢንተርኔት ጋር የምናገናኝ ከሆነ የኮምፒውተራችንን Firewall on ማድረግ ይጠበቅብናል ማለት ነው። ስለዚህ ለኮምፕዩተርም መከላከያ የሚሆን ፋየርወል አለ። ▫️ለምሳሌ፣ የእርስዎ የግል ኮምፒውተር ፋየርዎል áŠ¨áˆŒáˆˆá‹ ወይም ፋየርውሉ ዝግ(Off) ከሆነ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ሰርጎ ገቦች(ሀከር) ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ። ▫️ሁለት አይነት ፋየርወሎች አሉ። አንደኛው ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ጋር አብሮ እዛው ተጠቃሚው ያገኘዋል። (መጨረሻ ላይ ያለውን Step ይከተሉ) ለምሳሌ የዊንዶውስ ኮንትሮል ፓነል ላይ ሄዶ ፋየርወሉን እንደ አስፈላጊነቱ (ከፍተኛ ወይም መካከለኛ) መጠን ላይ መርጦ መቀስቀስ ይቻላል። የሚገዙ አንቲቫይረስ ፕሮግራሞችም የራሳቸው ፋየርወል አላቸው። ሌሎችም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ፋየርወል አላቸው። ▫️የኮምፒውተታችንን ፈየርወል ለማስተካከል ቅደም ተከተል Windows 10, 8, 7: ላይ Control Panel > System and Security > Windows Firewall > Turn Windows Firewall on or off 1 the bubble next to Turn off Windows Firewall (not recommended) and then select OK. 2 To disable the firewall for private and public networks, select Turn off Windows Firewall (not recommended) in both sections. 📌   @Techteaching1 📌

✳️ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌሮች 🚩 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁለገብነትን ተከትሎ ዘርፉን ለማበልፀግና ብዙኃንን ተሳታፊ ለማድረግ ተቋማት እና ግለሰቦች የቴክኖሎጂውን ሶፍትዌሮችን በነጻ ያቀርባሉ፡፡ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መካከል ሁለቱን ለዛሬ እናስተዋውቃችሁ፡፡ ▫️1.ቴንሰርፍሎው/ TensorFlow ይህ ሶፍትዌር የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለማበልፀግ በስፋት ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡ በተጨማሪም ዳታዎችን በማጠናቀር የትንበያ መላምቶችን ለማዘጋጀት የላቀ አቅም ያላቸው ቁጥርን ማስላት የሚያስችሉ ክምችቶችን ይዟል፡፡ 🚩ቴንሰርፍሎው ድምፅን እና ምስሎችን ለሚለዩ የተለያዩ መተግበሪያዎች የጀርባ አጥንት መሆኑ ይነገራል፡፡ ድሮፕቦክስ፣ ኢቤይ፣ ትዊተር፣ ኡበር እና ኢንቴልን የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ሶፍትዌር ጥቅም ላይ በማዋል ይታወቃሉ፡፡ ▫️2. አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን / IBM Watson አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን በተቋማት የሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮችን እንዲሁም ግኝቶችን ለማፋጠን የተሻለ አቅምን መፍጠር እንደሚችል ይነገርለታል፡፡ ብዙ ተቋማት ሶፍትዌሩ የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ዳታቸውን ለማጥናት፣ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለማሰባሰብ፣ ሾለ ስራቸው ጥልቅ እይታን ለማግኘት እና ቀጣይ የስራ አፈጻጸማቸውን በቀላሉ ለመተንበይ አገልግሎት ላይ ያውሉታል፡፡ 🚩በትምህርት፣ በጤና ጥበቃ፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርት እንዲሁም በኃይል ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ሶፍትዌሩን አገልግሎት ላይ በማዋል ውጤት አግኝተውበታል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ሶፍትዌር በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን ይጠቁማሉ፡፡ 📌   |  - @Techteaching1 - |   📌

✳️ በብሉቱዝ በኩል ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት መከላከል እንችላለን? ▫️ብሉቱዝ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የምናደርጋቸውን የመረጃ ልውውጦች ያለ ውጫዊ መረጃ ማስተላላፊያ ቁስ ስልካችንን ከድምጽ፣ ከማፈላለጊያ እና ኤሌክትሮኒክስ ጋር በበይነ-መረብ ቁሶች አማካኝነት የሚያገኛኝ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ▫️ብሉቱዝ ምቾት የሚሰጥ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አመቺ ቴክኖሎጂ ቢሆንም ዋና ዋና የደህንነት ሥጋቶችንም ሊያመጣ ይችላል፡፡ ▫️ከዚህ በታች ለተንቀሳቃሽ ስልክዎ የደህንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ የብሉቱዝ ተጋላጭነቶችን እና የመጠበቂያ መንገዶች አቅርበንላችኋል፡፡ • አጠቃላይ የሶፍትዌር ተጋላጭነት መከላከል። - ብዙዎቹ በብሉቱዝ መሣሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ሶፍትዌሮች ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ አይደሉም፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት አዲስ እና የማይታወቅ ደህንነት ተጋላጭነት በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አንዲሁም በሌሎች መገልገያዎቻችን ላይ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ - ከደህንነት ስጋት ነጻ የሆነ ሶፍትዌር የሌለ በመሆኑ ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ • በስውር ማዳመጥ መከላከል። - የብሉቱዝ ምስጠራ (encryption) ወንጀለኞች መረጃዎችን እና የስልክ ጥሪዎችን እንዳያዳምጡ ለማድረግ ያስችላል ፡፡ - ስለዚህ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የብሉቱዝ መሣሪያዎች ለደህንነት ተጋላጭ የሆኑ ክፍተቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ወቅታዊና የዘመኑ ብሉቱዝ ምርቶችን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ • የአገልግሎት ማቋረጥ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ። - በአጥፊ ቫይረሶች ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችንን በመጉዳት ጥሪ እንዳንቀበል እና የባትሪያችን ኃይል በማዳከም የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች ሊያስተጓጉሉን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ብሉቱዝ በማንጠቀምበት ወቅት ብሉቱዛችንን ልንዘጋ ይገባል፡፡ • ብሉቱዝ የሚያካልለው ስፋት ታሳቢ ማድረግ። - ብሉቱዝ ዲዛይን ሲደረግ በግል አውታረ-መረብ ስፋት ነው፡፡ ይህም ማለት ብሉቱዝ ከመሣሪያዎቻችን ጥቂት የእግር እርምጃዎች ርቀት በኋላ ተደራሽ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ባለንበት እና ጥቃት ሊፈፅም በሚችል ማንኛውም አጥቂ አካል መካከል ያለንን ርቀት እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ ምክንያቱም ጥቃት ፈጻሚዎች ክፍት ብሉቱዝ መኖሩን ከርቀት የሚያመለክቱ መተግበሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በማንጠቀምበት ጊዜ ብሉቱዛችንን ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡ - ብሉቱዝ የሚጠቀሙ ጆሮ ማዳመጫዎች (earphones) ላይ ጥንቃቄ ማድረግ በርካታ ብሉቱዝ የጆሮ ማዳመጫዎች አደገኛ የደህንነት ክፍተት ማስተናገጃ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አጥቂዎች ይህን ተጋላጭነት በመጠቀም ንግግሮቻችንን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡ - በቫይረስ የተጠቃ መሣሪያ የሚያገኘውን መረጃ ለጥቃት ፈጻሚው ያስተላልፋል፡፡ - ይህ ለመከላከልም በቀላሉ የሚገመት የፋብሪካ ምርት ፒን ኮድን /PIN code/ ለመገመት አዳጋች በሆነ ኮድ መቀየር ጠቃሚ ነው፡፡ 📌   |  -@Techteaching1 |   📌

✳️ ድህረገፅ ዴቨሎፕመንት(WEBSITE DEVELOPMENT) ➲ ድረ ገጽ( WEBSITE) - የዌብ ፔጆች ስብስብ ሲሆን በአንድ ዶሜን ኔም(DOMAIN NAME) የሚጠሩና ተመሳሳይ ሰርቨር ላይ የተቀመጡ ናቸው:: ➲ ዶሜን ኔም ለምሳሌ WWW.GOOGLE.COM WWW.FACEBOOK.COM 🚩 የድረ ገጽ አይነቶች(TYPES OF WEBSITE) ▫️1.ስታቲክ (STATIC WEBSIRE) - የማይቀያየር ኮንተንት ወይም ይዘት ያላቸው እንዲሁም ከHTML,CSS የተሰራ የዌብ ፔጆዎች ስብስብ ነው ሁሌም ቢሆን ተመሳሳይ ኮንተንት ያቀርባሉ ዳታ ቤዝ የላቸውም ማለትም መረጃ ከዳታቤዝ አይመጣም እንዲሁም ወደ ዳታቤዝ መረጃን አያስገባም ሰርች ማደርግ አንችልም፡፡ ▫️2.ዳይናሚክ ድረ ገጽ(DYNAMIC WEBSITE) - ተለዋዋጭ መረጃዎችን የያዘ ከዳታ ቤዝ ጋር የተሳሰረ ማለትም መረጃዎችን ከዳታቤዝ የሚመጣ እንዲሁም ወደ ዳታ ቤዝ የሚልክ በሰርቨር ሳይድ የኮንፒተር ቋንቋ የተሰራ ሲሆን ለምሳሌ PHP,ASP.NET, Python, Ruby, C#, and NodeJS ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡ ▫️ስልዌብሳይት ይህን ካልን ስታቲክ ድረ ገጽ( (STATIC WEBSIRE) ለመስራት ምን ያሰፈልገናል ? - ቴክስት ኢደተር እንደ ኖት ፓድ,እንዲሁም የሰራነውን የምናይበት ዌብ ብራውዘር ያስፈልገናል - ስታቲክ (STATIC WEBSITE) ምሳሌ👇 <HTML> <HEAD> JOSIE TECH </HEAD> <BODY> <P>JOSIE TECH </P> </BODY> </HTML> አዲስ ኖትፓድ ከፍተን ሴቭ ስናደርግ ለምሳሌ TEST.HTML ሆኖም TEST ቦታ የፈለግነውን ስም መስጠት ይቻላል ግን HTML ግዴታ ነው ፡፡ የኮድ ማብራራያ ህግ 1 - HTML መክፈቻ ታግ 👉🏽<HTML> - ርዕስ የሚቀመጥበት ታግ መክፈቻ 👉🏽<HEAD> - ርዕስ 👉🏽TECH TECHNOLOGY - ርዕስ የሚቀመጥበት ታግ መዝግያ 👉🏽</HEAD> - ሃተታ የዌብሳይቱ ዋና አካል መክፈቻ 👉🏽<BODY> <P>TECH TECHNOLOGY</P> - ሃተታ የዌብሳይቱ ዋና አካል መዝግያ 👉🏽</BODY> - ውጤት TECH TECHNOLOGY 📌   |  - @Techteaching1- |   📌

📲በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት🌐 እየተጠቀምን በተደጋጋሚ ብቅ የሚሉ ማስታወቂያዎችን እንዴት ነው ልናስቆማቸው የምንችለው? 💢ቀለል ያሉ 2 መንገዶችን ልጠቁማቹ... #1ኛው_መንገድ: 1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና #Settings መግባት 2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Site Settings የሚለውን መምረጥ 3⃣. Site Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Pop-ups and redirects የሚለውን ክሊክ ማድረግ 4⃣. Pop-ups and redirects የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF 5⃣. OFF የሚለውን መምረጥ፡፡በቃ ካሁን በሃላ አስሬ ብቅ እያሉ የሚበጠብጣችሁ ማስታወቂያዎች ይጠፋሉ።👍 🔆2ኛው_መንገድ:- Turn On the Data Saver - እዚያው የምትጠቀሙበት ክሮም ብራውዘር ላይ ዳታ ሴቨር (Data Saver) #On ለማድረግ፦ 1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና Settings ውስጥ መግባት 2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Data Saver የሚለውን መምረጥ 3⃣. Data Saver የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF 4⃣. -ON የሚለውን መምረጥ በቃ አለቀ፡፡👍 ‼️ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 💻📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ🔺🔺 @Techteaching1✨

✳️ ሶፍትዌር ምንድን ነው (WHAT IS SOFTWARE) ? - ተጠቃሚዎች የተወሰነ ሼል እንዲያከናውኑ የሚያስችላቸው ወይም ኮምፒውተሮቻቸውን ለማንቀሳቀስ ለማዘዝ የሚያገለግል የፕሮግራም ዓይነት ነው ፡፡ ሶፍትዌሮዎች በኮንፒተር እና በተጠቃሚ መካከል በመሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ኮንፒተሩ ጥቅም እንዲኖረው ተጠቃሚው የሚፈልገውን ሾል እንዲሞላ ይረዳሉ፡፡ ሶፍትዌር አይነቶዎች 🚩1. ሲስተም ሶፍትዌሮች (SYSTEM SOFTWARE) - ሃርድዌሩ እንዲሰሩ እና ኮንፒተሩ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚደርግ ወሳኝ ሶፍትዌር ነው ፡፡ሲስተም ሶፍትዌር በሃርድዌሩ እና በተጠቃሚው መካከል ግንኙነት እንዲኖር ምቹ ሁኔታን የሚመቻች የሶፍትዌር አይነት ነው ይህም በሃርድዌሩ ካለ ሲስተም ሶፍትዌር ምንም ጥቅም አይኖረውም ኮንፒተርን ጥቅም ላይ እንዲውል ከዕቃ ወደ ስማርት እና ፍላጎታችን የምንሰራበት ወሳኝና አስፈላጊ የሚደርገው ሲስተም ሶፍትዌር ነው ፡፡ ሲስተም ሶፍትዌር ምሳሌ ➲ 1.Operating System a MS Windows b macOS c Linux d iOS e Android f CentOS g Ubuntu h Unix ➲ 2. Device Drivers a BIOS Drivers b Driver Motherboard c Drivers Display d Drivers ROM e Drivers Printer f Drivers USB g Sound Card Driver h VGA Driver ➲ 3.Firmware a Computer Peripherals b Embedded Systems c UEFI d BIOS ➲ 4.Utility a Norton Antivirus b McAfee Antivirus c WinRAR d WinZip e Piriform CCleaner f Windows File Explorer g Directory Opus h Razer Cortex 🚩2.አፕልኬሽን ሶፍትዌር (APPLICATION SOFTWARE) - አፕልኬሽን ሶፍትዌር አንድን ሾል ለመስራት ወይም ለማከናወን ታስበው የሚዘጋጅ የሶፍትዌር አይነቶች ናቸው ይህም ኮንፒተራን ላይ ካለ ኢንተርኔት ወይም ኦንላይን ላይ ምርምር ማካሄድ ፣ ማስታወሻ መጻፍ ፣ ግራፊክስ ዲዛይን ማድረግ ፣ ሂሳብ ማስላት፣ የኮምፒተር ጨዋታዎችን መጫወት የመሳሰሉ የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን የሚረዱ ፕሮግራሞች አፕልኬሽን ሶፍትዌር በመባል ይታወቃሉ ፡፡ ➲ 1.Word Processors a MS Word b Apple iWork-Pages c Corel WordPerfect d Google Docs ➲ 2.Database Software a MS Access b FileMaker c dBase d Clipper e MySQL f FoxPro ➲ 3.Multimedia Software a. Adobe Photoshop b Picasa c VLC Media Player d Windows Media Player e Windows Movie Maker ➲ 4. Web Browsers a Google Chrome b Mozilla Firefox c Internet Explorer d Opera e UC Browser f Safari 📌   |  - @Techteaching1- |   📌

​✳️ የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "Backup" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን? 🏳️ በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ:- 🏳️ ፍሎፒ ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡ 🏳️ ዚፕ ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡ 🏳️ ቴፕ ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡ 🏳️ ሲዲ በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ 🏳️ ፍላሽ ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ 🏳️ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡ 🏳️ ታይም ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡ 🏳️ ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡ 🏳️ ስውር የበይነ መረብ መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሼር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡ 🏳️ ፕሪንት ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡ 📌   |  - @Techteaching1- |   📌

✳️ Server(ሰርቨር) ምንድን ነው? 🔥ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት። 🏳️ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው። 🏳️Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው። 🏳️በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል። 🏳️Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው። 🏳️ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል። 📌   |  - @Techteaching - |   📌

🔆Web 3.0 (ያልተማከለ የኢንተርኔት ስርአት) 📍ሀሳቡ ትንሽ የከራረመ ሲሆን ወደፊት የኢንተርኔትን ስርአት #ይቆጣጠራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። 📍እዚህ ስርአት ላይ ማህበራዊ ድረገጾች አለቃ (ባለቤት #አይኖራቸውም) 📍እዚህ ስርአት ላይ ሁላችንም የፕላትፎርሙ (ለምሳሌ የፌስቡክ) ባለቤቶች ነን። 📍እሱ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ለምንፈጥረው ኮንተንቶችም #ባለቤቶች ነን። 📍ለምሳሌ የወ*ብ ቪድዮ ወይም የግድያ ቪድዮ ብትለቁና አንድም ላይክ👍 ሳይኖራችሁ #ሚልዮን ዲስላይክ👎 ቢኖራችሁ ምንም አይፈጠርም ምክንያቱም አካውንታችሁን የሚዘጋ አካል የለም። ማንም ምንም አያደርጋችሁም‼️ ⚠️መረጃችሁ የት ይቀመጣል? 📍የእያንዳችሁ አካውንት መረጃ ማስቀመጫ ሰርቨር አሁን እንዳለው የሚታወቅ 1 ወይም 2,3 ቦታ አይኖረውም። ሚልዮኖች ያን ፕላትፎርም ከተጠቀሙት የሚልየኖች ኮምፒውተር💻 ለዚህ ፕላትፎርም/ ሶሻልሚድያ እንደ #ሰርቨር ነው። 📍የሆነ አካል የለቀቃችሁትን መረጃ ሊያጠፋ❌ ቢፈልግ እነዚህን ኮምፒውተሮች 1በ 1 #Access ማድረግ ይጠበቅበታል። 📍ዌብሳይቶች ከላይ እንዳለው እናንተን #ማጥናት አይችሉም። 📍ዋንኛው ማንነታችሁ ቀርቶ #Anonymous ምትሆኑበትን ማንነት ትፈጥራላችሁ። ⁉️ምን እንደክፍተት ታያችሁ? 📌   |  - @Techteaching1- |   📌

የትኛውንም የWindows አይነት Active ለማድረግ ይጠቅማቹሀል በተጨማሪ Microsoft Office ያለ Product Key Active ለማድረግ ይጠቅማል ምንም ኢንተርኔት አይፈልግም

Super Collapse 3.cso12.28 MB

Sonic Rivals.cso121.40 MB

የተለያዩ የIPTV ሊስቶችን በቀላሉ በስልካቹ ለማየት ይጠቅማቹሀል

የሚገርም VPN ከፕሌይ ስቶር ገብታቹ ማረጋግጥ ትችላላቹ የሚሸጥና ወርሀዊ ክፍያ የሚጠይቅ VPN ነው የትኛውንም Website ይከፍታል በነፃ ዳውሎድ አድርጋቹ ፈታ ማለት ነው👍

SwiftStreamz

Ye netflix ተከታታይ ፊልሞቺን እና ኖርማል ፊልሞቺን በነፃ የምታዩበትና የምታወርዱበት ምርጥ application ነው ተጠቀሙበት።

+1
የኢትዮጲያን ቻናሎች በቀላሉ በስልካቹ ለማየት የጠቅማቹሀል #Aos tv ይህንን ብቻ አይደለም ሁሉንም የቲቪ ቻናሎች ማለት ይቻላል በስልክ በቲቪ በተለያዩ መንገዶች ለመመልከት ይጠቅማል

Join and share for HD Box Office Movies Only On Telegram
Join and share for HD Box Office Movies Only On Telegram

✳️በአንድሮይድ ስልካችሁ ላይ ያሉ የግል ፋይሎችን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩቦት ይፈልጋሉ? በስማርት ስልኮች ላይ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን እንዲሁም የተለያዩ የግል ፋይሎችን እናስቀምጥበታለን። ይህን የግል ፋይል ስልካችን የሰጣናቸው ሰዎች እንዳያይታይብን ማድረግ የሚችልባቸው ዘዴ እንጠቁማችሁ ፨መቆለፊያ /File locker/ የፋይል መቆለፊያ / File locker/ መተግበሪያ በስልካችን ላይ የያዝናቸው መረጃዎቻችን በሌች ሰዎች በቀላሉ እንዳያዩብን ከሚያደርጉ ዘዴዎች አንዱ ነው።ይህም መተግበሪያው ባለው የፋይል ማናጀር አማካኝነት የግል ፋይሎቻችንን፣ ፎቶግራፎች ወይም ቪዲዎች ያሉበትን ፎልደር በመምረጥ በይለፍ ቃል ወይም ፓዎርድ ለመቆለፍ የሚያስችል ነው። ይህንን መተግበሪያ ከጎግልፕሌይ / Google play store/ ዳወንሎድ በማድረግ መጠቀም የምንችል ሲሆን፥ ተጥቃሚዎች ይህንን መተግበሪያ በሚጠቀሙበት ጊዜ ልብ ሊሉት ይገባል የተባለው ነገር የምንሰጠው የይለፍ ቃል ወይም ፓስዋርድ በቀላሉ የሚያዝ መሆን አለበት ተብሏል ምክንያቱ ደግሞ የይለፍ ቃሉን አንዴ ከረሳን ፋይሎቻችንን ከፍተን ለማየት የምንችልበት አማራጭ ባለመኖሩ ነው። የምስል መደበቂያ መተግበሪያ /Hide pictures- keep safe vault/ይህ የምስል መደበቂያ / Hide pictures- keep safe vault/ መተግበሪያ በአንድሮይድ ስልኮቻችን ላይ ያሉን ፎቶግራፍ እና የተንቀሳቃሽ ምስሎች በሌሎች ሰዎች እንዳይታዩብን ለማድረግ የሚረዳን መተግበሪያ ነው። ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀምም እንዳይታዩብን የምንፈልጋቸውን ምስሎች ከከፈትን በኋላ ኪፕ ሴፍ/‘keep safe’/ የሚለው ላይ ሟር በማድረግ ምስሎቹን ከሌሎች ሰዎች እይታ መሰወር እንችላለን። ይህንን መተግበሪያ ስልካችን ላይ በማውረድም በስልኮቻችን ላይ ያሉንን ግላዊ ሚስጥሮች መጠበቅ እንችላለን። lፋይሎቻችን ስም በምንሰጥበት ወቅት ከፊትለፊቱ ነጥብ (.) ማስገባት ይህ መንገድ ቀላሉ እና ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ ሳያስፈልገን በስልካችን አንዲሮይድ ፋይል ማናጀር በመጠቀም ፋይሎቻችንን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን የሚያደርግልን ነው። ይህንን ለመጠቀምም በስልካችን ላይ ሴቭ የምናደርገውን ፋይል ስም ከመስጠታችን በፊት ከፊት ለፊቱ ነጥብ (.) አስቀድመን በማስገባት ስሙን ጽፈን ሴቭ ማድረግ ነው። በዚህ መንገድ ሴቭ ያደረግናቸው ፋይሎች በቀላሉ ፊት ለፊት ላይ ለሌሎች ሰዎች አይታዩም። እነዚህን ፋይሎች መልሰን በራሳችን ጊዜ ከፍተን ማየት ከፈለግንም ፋይል ማናጀር ውስጥ ከገባን በኋላ ሴቲንጉን በመክፈት ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የተደበቁ ፋይሎችን ለመክፈት የሚረዳንን /show hidden files/ ከከፈትን በኋላ በሚመጣለን ስፍራ ላይ ነጥብን በማሰቀደም የሰጠነውን ስም አስገብተን በመጻፍ መመልከት እንችላለን 📌   |  - @Techteaching1- |   📌

✳️ዛሬም እንደ ተለመደው በ አዲስ ነገር ብቅ ብለናል ለእናንተ ይጠቅማል ያልነውን ይዘን መተናል Why My Phone is gonna Very Slow😌. ለምንድነው ስልካችንን ስንጠቀም ቀርፋፋ የሚሆነው ወይም (ስታክ) የሚደረገው ? 1 አንድ ስልክ የሚሰራው ከ 2 ነገሮች ነው ከ Software እና ከ Hardware. የኛ ስልክ ስንጠቀም ቀርፋፋ እየሆነ ካስቸገረ ችግሩ (Software) ላይ ሊሆን ስለሚችል ወደ ስልካችንን (Setting) እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ (About Phone) የሚል አለ እሱን አንዴ (Click) እናረጋለን ብዙ ምርጫ ይመጣል ከዛ ውስጥ ➲System Update ወይም Software Update የሚለውን አንዴ(Click) እናረጋለን ከዛ የስልኩን (Software) ላሻሽለው ? ብሎ ይጠይቀናል እሺ ከማለታችን በፊት ይህን ልናደርግ ይገባል #እዚጋ ትንሽ መጠንቀቅ አለብን 🚨 👇👇👇👇👇👇 => ስልካችንን Space ነፃ ማድረግ ቢያንስ 500 Megabyte እና ከዛ በላይ => DATA ወይም WiFi ሊኖር የግድ ነው ነገርግን ከ DATA ይልቅ በ WiFi ቢሆን ይመረጣል => የስልኩ ባትሪ ከ 50% በላይ መሆን አለበት. => ስልካችንን በ Pattern እና Password ዘግተን ከሆነ ማጥፋት ወይም Off ማድረግ አለብን. => ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉንም ጠቃሚ (File) ➲ፎቶ ሙዚቃ እና ቪድዮ ወደ (MemoryCard) ኮፒ (Backup) ማድረግ የግድ ነው => ስልካችሁ (Root) ከሆነ Software Update አታድርጉ ምክንቱም Dead ሊሆን ይችላል (Software Update) ካረግን የምናገኘው ጥቅም ቢኖር ስልካችን ሙሉ በ ሙሉ 💯% ስታክ ያቆማል. ⚠🚨ማስጠንቀቂያ ከላይ ያለውን ነገርሁሉ ችላ በማለት ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግሮች #ይህ ቻናል ተጠያቂ አይሆንም. 2 የስልካችን ( Internal Storage Space ) ሙሉ እስኪሆን ማለትም የስልኩ (Space) እስኪሞላ ፊልም ሙዚቃ ጌም አለመቀበል እና አለመጫን ➲ለምሳሌ ስልካችን ፋይል የመያዝ አቅሙ ከ (Memory) ውጭ #4GB ቢሆን 4GBው እስኪሞላ አለመጠቀም ቢያንስ ከ 4GBው 1GB ወይም 500MB ማስቀረት አለብን ምክያቱም የስልካችን #Space ሙሉ በ ሙሉ ሲሞላ ስልኩ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል ስለዚህ #Full አለማድረግ ወይም Memory-Card መጠቀም. አዲስ ስልክ ስንገዛም የስልኩ ፍጥነት በ RAM ላይ የተመሰረተ ነው ሰለዚህ ስልክ ስንገዛ (RAM) ማየት በጣም አስፈላጊ ነው የምትገዙት ስልክ RAM 1 ወይም 2 ቢሆን ጥሩ ነዉ. ➲ለምሳሌ አንድ ስልክ በጣም ፈጣን ቢሆን አንድ ስልክ በጣም ቀርፋፋ ቢሆን በሁለቱ ስልክ መሀል ያለው ልዩነት የ RAM መበላለጥ ነው. #የስልካችንን RAM ስንት እንደ ሆነ ለማወቅ My Android Application ላይ ማየት እንችላለን 3 በቀን ውሰጥ ብዙ ግዜ ያለእረፍት ስልካችንን የምንጠቀም ከሆነ የስልኩ RAM ይጨናነቃል ስልካችንን ስንጠቀም RAM ብዙ ሾል ይሰራል ስለዚህ ስልካችንን ተጠቅመን ስንጨርስ (ራሙን) Clean ማድረግ አለብን ➲አንዳንድ ስልኮች(Tecno) (itel) (Huawei) የራሳቸው RAM Cleaner አላቸው. ➲RAM Cleaner ጥቅሙ ስልካችን ላይ አላስፈላጊ እና የማይጠቅሙ ነገሮችን በ ማፅዳት ስልኩ እንዲፈጥን ያደርጋል ➲አንዳንድ ስልኮች ደግሞ RAM Cleaner የላቸውም ስለዚህ #C Cleaner Application በመጠቀም RAMሙን Clean ማድረግ እንችላለን 4 ከ ስልካችን Android Version በላይ የሆኑ Application እና Game ስልካችን ላይ አለመጫን install አለማድረግ ➲ለምሳሌ ከስልካችን Android Version 4.4.2 ቢሆን ለዛ ስልክ የማይሆኑ ከስልኩ አቅም በላይ የሆኑ Application እና Game አሉ እነሱን ስልካችን ላይ አለመጫን የስልካችን Android Version ለማወቅ Setting ወስጥ ገብተን መጨረሻ ላይ About Phone የሚለውን አንዴ Click እንላለን ከዛ ብዙ ምርጫ ይመጣሉ ከዛ ውስጥ Android Version የሚለው ላይ መመልከት እንችላለን 5 ስልካችን ላይ ብዙ ከ መጠን በላይ Application አለመጫን ጠቃሚና አስፈላጊ Application ብቻ መጫን 6 ስልካችንን በቀን ውስጥ ቢያንስ (2)ግዜ Restart ማድረግ አለብን 7 አንዳንድ Launcher መጠቀም የስልካችንን (ላውንቸር) መቀየር #Microsoft Launcher በጣም ምርጥ ነው እሱን መጠቀም 📌 https://t.me/Techteaching1 📌