cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

THRONE of GOD/ የእግዚአብሄር ዙፋን

Bible is the only true scripture በዚህ ቦታ ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸውንና 👉 ትምህርቶች 👉 የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦች 👉 የህይወት መርህ 👉 የእግዚአብሄር ሀሳብ 👉 የመጨረሻው ዘመን በመጽሐፍ ቅዱስ 👉 የክርስቶስ መምጣት 👉 ክርስትናና ህይወት 👉 የመሳሰሉትን የምንካፈል ይሆናል 💎💎💎 #join ያድርጉ ✍️✍️ @Nahom777 ✍️✍️

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
129
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
(7) 2021 New Protestant Guraggna Mezmure

ሰላም እንዴት ናችሁልኝ?? ዛሬ አንድ ከፍል ላወራችሁ ፈለኩ። የሐዋርያት ስራ 1:8-11 👉 ከፍ ብላችሁ ስታነቡት በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ ኢየሱስ ትዕዛዝ እንደሰጣቸውና ከሰጣቸው በኃላ በቁ 8 ላይ ምን ተቀብለውና መቼ እንደሚወጡ ይነግራቸዋል =>የሚቀበሉት ይህ ነው''ነገር ግን #መንፈስ ቅዱስ በእናንተ በወረደ ጊዜ #ኃይልን ትቀበላላችሁ። ''ይላል በመጀመሪያ የሚወርደው መንፈስ ቅዱስ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት #ኃይልን እንቀበላለን። ሀሌሉያ ኢየሱስ ጌታ ነው። ይህም ሲቀበሉ በሆነ ቦታ ወይም በተወሰነ አካባቢ አይደለም ምስክር የሚሆኑት በኢየሩሳም፣ በይሁዳ፣በሰማሪያ ይልና እስከ #ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ይላል።እኛም ምድር ዳር ድረስ ምስክሩ ያደረገን ጌታ ክብር ለአምላክችን ይሁን =>ቁጥር 9 ከተናገራቸው በኃላ ማረጉን ይነግረናል ይህም እያዩት ከፍ ከፍ አለ።ደመናም ከአይናቸው ሰውራ ተቀበለችው ይለናል። የክብር አምላክ ሀሌሉያ 👉ኢየሱስም ወደሰማይ ሲያርግ ሲመለከቱት ሁለት ነጭ ልብስ የለበሱ ስለኢየሱስ የሚመሰክሩ ሰዎች ለደቀ መዛርቶች ተገለጡላቸው በአጠገባቸውም ቆሙ። ዋና የምወደው ክፍል ይሄ ነው።11 👉እነዚህ ሁለቱ ነጭ የለበሱ ሰዎች ለገሊላ ሰዎች ሲነግሩዋቸው ''የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኃል? ይሉዋቸዋል እና በእንደዚህ ሲሉዋቸው የተረዳሁት ነገር የሆነ ሊሰሩ የሚገባ ነገር እንዳለ ተረዳሁ። ሲቀጥል #ይህ #ከእናንተ #ወደሰማይ #የወጣውን #ኢየሱስ #ወደ #ሰማይ #ሲሄድ #እንዳያችሁ፥ #እንዲሁ #ይመጣል አሉዋቸው =>ይህ ክፍል በጣም እወደዋለሁ በተለይ እንዲሁ ይመጣል የሚለው። ስለዚህ ኢየሱሳች ይመጣል። =>ኢየሱስ ለምን ተመልሶ ይመጣል????? 👉በዮሐንስ ወንጌል 14:2-3 በግልፅ አስቀምጦልናል።እንዲህ ይላል። የዮሐንስ ወንጌል 14 👉👉👉 2 በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፥እንዲህስ ባይሆን ባልኃችሁ ነበር፤ #ስፍራ #አዘጋጅላችሁ #ዘንድ #እሄዳለሁና። 3 #ሄጄም #ስፍራ #ባዘጋጅላችሀ፥#እኔ #ባለሁበት #እናንተም #ደግሞ #እንድትሆኑ #ሁለተኛ #እመጣለሁ #ወደእኔም #እወስዳችኋለሁ። ይለናል ስለዚህ ኢየሱስ ሁለተኛ የሚመጣው ድጋሚ ሊሰቀል ሳይሆን ለምስክሮቹን ቤት አዘጋጅ ከእርሱ አጠገብ እንዲቀመጡ ነው። ዋው ምን አይነት አምላክ ነው ያለን በጌታ። ክብር ለሙሽራው ድጋሚ ለሚመጣልን ለሚወስደን ለኢየሱሳችን ይሁን። በዚህ ደስስስስ ሊለን ይገባል። ታዲያ እንደዚህ እንበለው ማራናታ ጌታችን ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ናልንንንን @BIBLEAPOLOGETICS #THRONEOFGOD ሀሳብ ካላችሁ @messengermelsha7
Show all...
የሐዋሪያት ስራ 1 8፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። 9፤ ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። 10፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤p 11፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። ትንሽ ማብራሪያ ከታችች ያለውን አንብቡት ትባረኩበታላችሁ። 👇👇👇👇👇👇👇👇 @BIBLEAPOLOGETICS #THRONEOFGOD @messengermelsha7
Show all...
አስቸኳይ የፀሎት ጥሪ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 1,ለአማራ ክልል #ፀልዩ #ለባህር ዳር #ለራያ #ጎንደር 2,#ለአፋር እና #ሶማሌ ክልል ፀልዩ 3,#በትግራይ #የንፁሀን ዜጎች ደም እንዳይፈስ🔥 4,ለ #በኢትዮጵያ ላይ ሪቫይቫል እንዲሆን ፀልዩ🔥 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” — ኤፌሶን 6፥12 #ሁሌ ፀልዩ #ሁሌ ፀልዩ #ሁሌ ፀልዩ #Share አድርጉ @SisayAzusaRevivall @SisayAzusaRevivall @SisayAzusaRevivall
Show all...
ርዕሱ።ባለጥሪ .👉 ባለጥሪ ማለት የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን #ባለ እና #ጥሪ ናቸው። #ባለ ማለት በራሱ ችሎ ትርጉም ሊሰጥ የማይችል ነገር ግን ከቃላት ፊት ለፊት ወይም በመነሻ ቅጥያ ሲገባ ባለቤትነት ሲያመለክት #ጥሪ ማለት ደግሞ በዝግጅት እንዲመጣ ወይም እንዲገኝ ያለበት ሰው የሚነገረው ንግግር ማለት ነው። 👉. ባለጥሪ ማለትና ደግሞ በአንድ ዝግጅት ላይ እንዱገኝ የተጠራ ሰው ወይም ለዝግጅቱ የተጋበዘ ሰው ማለት ነው። 👉 በመፅሐፍ ቅዱሳችን ከተጠሩ ብዙ አገልጋዮች(አባቶቻችን) ጥቂቶቹ እንመለከታለን። እነዚህም ተጋባዦች ሲሆኑ ጋባዡ ደግሞ እግዚአብሔር ለአገልግሎቱና ለክብሩና ለህዝቡ ሊያስተዳድሩ የመረጣቸውና የጠራቸው እግዚአብሔር ነው። #ሙሴ °።ዘፀአት 2 ። 👉 ሙሴ ከሌዊ ወገን የተወለደ ነው። በዚያን ዘመን በግብፅ፣ ምድር ባሪያ ሆነው ያገለግላሉ ነበር። በዚያ ዘመን ንጉስ ፈርኦን ስለነበር ያስጨንቃቸው አልፍም የዕብራውያን አዋላጆች ወንድ ከሆነ እንዲገደል ሴት ከሆነች ደግሞ ትዕዛዝ አወጣ። ዘፀአት 1:18 👉 ሙሴ ሲወለድ ውብ ስለነበር እስከ 3 ወር ሸሸገችው ከዛ በላይ መሸሸግ ስለማትችል በወንዝ ዳር ተጣለ፤ተጥሎም የፈርኦን ልጅ አግኘችው አንስታው በፈርኦን ቤት አደገ።ዘፀአት 2:5-10። Part.2 👉 ሙሴ እንዴት ተጠራ??? ይቀጥላል አስተያየት ወይም ሀሳብ ካላችሁ @Melsha777 #THRLNEOFGOD @BIBLEAPOLOGETICS
Show all...
ሰላሙን ይብዛላችሁ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ሰሞን #ባለጥሪዎቹ እና #በተጠራንበት_ጥሪ_በሚገባ_እንመላለስ በሚል ርዕስ ጌታ ያስተምረናል።እንማራለን
Show all...
👉አድራሻችን የት ነው ? 👉መስቀል ስር ወይስ? 🙈 ✍ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች #አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው ብለው ሲናገሩ ክብር ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን መስቀል ማለት በጣም #የተዋረደ፣ #የረከሰ ና #የተረገመ ነገር ነው። ኢየሱስም እርግማን የተባለው እና የሆነው በዚህ #በመስቀል ላይ ስለተሰቀለ ነው። 👉“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” — ገላትያ 3፥13 ✍እኛ በመስቀሉ ስራ ከጠፋንበት #ተገኘን እንጂ፤ አሁን መስቀል ስር ምንም አንሰራም አድራሻችንን #ቀይረናል። 👉ኢየሱስ በሌለበት ስፍራ እኛም አንገኝም። ✍አሁን ኢየሱስ ያለው #በአባቱ ቀኝ ነው እኛም በሱ ውስጥ እሱም በእኛ ውስጥ ስላለ አሁን የእኛም አድራሻ መስቀል ስር ሳይሆን #በአብ ቀኝ ነው። ✝መስቀል ከሁለት ሺ ዓመት በፊት የነበርንበት ቦታ ነው፤ በዚያ ጊዜ ና ቦታ የነበረው ስራ ተጠናቋል አሁንም አድራሻችን መስቀል ስር ከሆነማ ክርስቶስ እንዲያው በከንቱ ነው የሞተልን🤷‍♂ 👉ነገር ግን ከእርግማን ሊዋጀን ነው በመስቀል ላይ እርግማን የሆነልን። “በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።” — ኤፌሶን 2፥6-7 🔊ስለዚህ ይህን መልዕክት ያነበባችሁ ሁሉ አሁንም አድራሻዬ መስቀል ስር ነው ካላችሁ ድነታችሁን ና የኢየሱስን ስራ ማራከስ ነው የሚሆንባችሁ 🙈 እወዳችኋለሁ ❤️ ❤️ @sLeHiYwEt @melsha777 👉 ህይወት ኢየሱስ ነው ❤️
Show all...
#ካትሪን_ኩልማን #የተዓምራት_አገልጋይዋ "ጉባኤው በፀጥታ እንደተሞላ ባለበት ሁኔታ ፕሮግራም መሪውም ሆነ ዘማሪዎች ወደ መድረኩ ሳይወጡ ምንም አይነት የስብከት አገልግሎት ሳይጀመር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በተቀመጡበት ቦታ እንዳሉ መለኮታዊ ፈውሳቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡" "ምንም አይነት ለቅሶና ጩኸት ሳይሰማ የእግዚአብሔር ጆሮዎች ከመስማት የታቀቡ እስኪመስል ድረስ ከልክ ያለፈ ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ሳይጮህ ጉባኤው በፍፁም ፀጥታ ተሞልቶ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ባለበት ሰዓት የመንፈስ ቅዱስ በሙላት መገኘቱና ሀቀልውናው ጉባኤውን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር የብዙ ሺዎች የልብ ትርታ በጉባኤው መካከል እስኪሰማ ድረስ የእግዚአብሔር መገኘት ከገሃዱ ዓለም ባለፈ ይገለጥ ነበር፡፡" በዚህ ፍፁም ፀጥታ መሃል "በተዓምራት .... ዓምናለሁ....!!" የሚል ድምፅ ሲሰማ ረጅምና ቀጭን የሰውነት ቁመን ያላት ረዘም ያለና ሞገስ ያለው ነጭ ልብስ የለበሰች ሴት ወደ ጉባኤው ስትወጣ በታላቅ ጩኸትና አዳራሹን በሚነቀንቅ ድምፅ ህዝቡ ይቀበላት ነበር፡፡ ወደ መድረኩ መካከል በዝግታና በእርጋታ እየተራመደች ከወጣች በኀላ ሌላው የካትሪን ኩልማን ተአምራታዊ አገልግሎት መከናወን ይጀምር ነበረ፡፡ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 🔥🔥🌨#ካታሪን_ኩልማን 🌨🔥🔥 🔥🔥🌨#የተዓምራት አገልጋይዋ🌨🔥🔥 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #share 👇👇👇👇👇👇 #join @GodGenerals1 @GodGenerals1 @GodGenerals1
Show all...
በዚህ ምድር ላይ ሁሌም ቢሆን አንድ ነገር ማሰብ አለብን እርሱም በሰማይ ሆኖ የሚጠብቀን ጌታ አለን ይህም የሚጠብቀን ጌታ ስለኛ በአባቱ ዘንድ መኖሪያን ሊያዘጋጅልን የሄደ አባት ነው ደግሞም ለብቻችን እንሆን ዘንድ የማይፈቅድ አምላክ ነው። ከእርሱ ተወልደናልና ከወንድ ከደምና ከስጋ ፍቃድ አይደለም መወለዳችን ከእርሱ ነው እርሱም አባታችን ነው። ይህም አምላክ ሁል ጊዜ አብረነሆን እንድንሆን የሚፈልግ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሄር ሲናገር እንዲህ ይላል። #በእነርሱ_እኖራለሁ_በመካከላቸውም_እመላለሳለሁ በማለት በእኛ ውስጥና በመካከላችን የሞኖር ነው። በሌላም ቦታ እንዲህ ይላል። #የሚወደኝ_ትዕዛዜን_ይጠብቃል_አባቴም_ይወደዋል_ወደ_እርሱም_እንመጣለን_መኖርያንም_እናደርጋለን። ይህ ነው በምድር እያለን ማለትም እዚህ ጊዜያዊ በሚሆን አለም ላይ ስንኖር እግዚአብሄር በቃሉ ተስፋ የገባልን ደግሞም ከሁላችን ጋር በመሆን እየኖርን ያለነው ህይወት። እንዲሁ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ጊዜያው ባልሆነው አለም ላይ ከእርሱ ጋር እንደምንኖር ይነግረናል። በዚህ አለም ላይ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለአለማዊ ነው። የሚለወጥ ሳይሆን በማይለወጠው አለም ነው። እንባና ለቅሶ ባለበት ሳይሆን ሳቅና ሀሴይ ባለበት አለም ነው። እናም ሁላችን ይህንን ህይወት እንጠብቃለን ተስፋችን ይህ ነውና ለዘለአለም የምንኖርበት ኢየሱስም ሐዋርያትም ጳውሎስም ሲመክሩን ለሚመጣው አለም መዝገብን አድርጉ ይሉናል። የሚመጣ መንግስት አለን። ይህም መንግስት የለዘለአለም የሚኖረን ያለውና የነበረው የእርሱ የሆነው መንግስት ነው። ስሙ ለዘላለም ይባረክልን። አሜን
Show all...
እንደምን ናችሁልኝ የተወደዳችሁ ዛሬ እስቲ አንድ ትንሽ የምናስበውን ከቀኑ ጋር በማያያዝ ላውራችሁ። ሰው ሁሉ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር ለጊዜው ብቻ እደሚኖር ያምናል ባያምንም ለጊዜውና ለጥቂት አመታት ብቻ እንደሚኖር በህይወት ኖረው ከሞቱት፣ ከተለዩአቸውም ሰዎች የሚያውቁት ጉዳይ ነው። ስለዚህ ሁላችን በዚህ ምድር ላይ ስንኖር መጻተኞች ነው ለዘላለም የምንኖርበት ከሞት በኋላ የተዘጋጀልን ቦታ አለ። ጌታም እንዲህ በማለት ተናግሮአል። እናትና አባት እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም በማለት እኛ የምንሄድበት ተስፋም የምናደርጋትሽበሰው ሳይሆን በእግዚአብሄር የተሰራች መንግስት አለችን። ጌታ ስሙ ይባረክ እርሱ በዚህች አዲስቷ ኢየሩሳሌም በምትባለው ኖረ አልኖረም ክብሩ አይቀንስም ምክንያቱም ሳትኖርም ይኖር ነበርና። እና ግን እኛ ከእርሱ ጋር አብረን እንሆን ዘንድ እርሱም በመካከላችን ይሆን ዘንድ ይህችን ውብ ከተማ አዘጋጅቶልናል። ትንሽ እስቲ ወደ ብሉይ ኪዳን ልመልሳችሁና እስራኤላውያን በግብጽ በባርነት በነበሩበት ሰዓት እግዚአብሄር ታላቁን ነብይ ሙሴን በመላክ ነጻ አወጣቸው በዚህም ጊዜ በምድረ በዳ ለ40 አመት እየመራቸው ተስፋ ወደ ገባላቸው ምድር አደረሳቸው። ነገር ግን በምድረ በዳ በሚኖሩበት ጊዜ እግዚአብሄር ዳስን ሰርተው እንዲቀመጡ አዘዛቸው። ይህም ትልቅ ምልክት አለው እርሱም ከፊታቸው ለጊዜው ብቻ የማይኖሩበት ለዘለአለም የሚቀመጡበትን ስፍራ እንዳዘጋጀላቸውና የእነርሱ ካልሆነው ሰፈር አውጥቶ የእነርሱ ወደ ሆነው ሊያስገባቸው እንዳሰበ እና በዚህም ጉዞ ውስጥ ጊዜያው መሸጋገሪያ የሆነው ዳሳቸውን በመትከልና በመንቀል እንዲቀመጡ ይሰጣቸዋል። ለዘላለም ለሚቀመጡበት ለከንዓን ምልክት ነውና። (ኦሪት ዘሌዋውያን 23 ) ------------ 41፤ ይህንንም በዓል በየዓመቱ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር አድርጉ፤ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው፤ በሰባተኛው ወር ትጠብቁታላችሁ። 42፤43፤ ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በዳስ ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእስራኤል ያሉት የአገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። እናም ይህንን በዓል አሁንም ድረስ እስራኤላውያን ያከብሩታል በእርግጥ ለዛ ለወጡበት ምድር ምስክር ቢሆንም ከፊታቸውም ላለው ተስፋን የሚያሳይ በዓል ነው። ምክንያቱም ዕብራዊያን እንዲህ ይላልና። "፤ ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። " (ወደ ዕብራውያን 4: 8) ትክክለኛን እረፍት እስራኤላውያን እንዳላገኙ በዚህ ክፍል እናያለን ኢያሱ ከነዓንን ቢያስወርሳቸውም ደግሞ እንደገና በንጉስ ዳዊት ደግሞ በትንቢት መንፈስ ሌላን የእረፍትን ቀን ይቀጥርላቸዋል። እስቲ አሁን ወደ እኛ ላምጣውን እንየው እኛ በዚህ ምድር ስንኖት መጻተኛና እንግዶች እንደሆነን መጽሐፍ ቅዱሳችን በደንብ አስረግጦ ይነግረናል። ይህም አሁን ለጊዜው በሆነ ምድር እንደምንኖርና የሚወደን አባታችን ለዘለአለም ጸንታ የምትኖር ምድርን እንዳዘጋጀልን እናውቃለን። እያንዳንዳችን በተስፋ አለን ይህ ምድር ጊዜያዊ እንደሆነ አውቀን እንኖራለን እውነትም ጊዜያዊ ናት ይህንን የተፈጥሮ ሁኔታው እራሱ ያሳየናል ሰቆቃው ውድመቱ ኪሳራው አለመረጋጋቱ ሁሉ በቃ ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደምትቆይ ያሳየናል። እናም እኛ በጌታ ያመንን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጀርባ አንድ ተስፋ በልባችን በመንፈሳችን ሞልቶ አለ እርሱም አዲስቷ ኢየሩሳሌን። ለዘላለም የምንኖርባት አባታችንንም ሁሌ ፊት ለፊት በምናይበት በዛ ለዘላለም ልንኖት የቀረልን የዕረፍት ሀገር አለችን። ይህች ምንም ብትጠፋ እኛ ግን የማትጠፋ መንግስትን ከአባታችን ዘንድ እንጠብቃለን። እና የዳስ በዓል ትልቁ ምልክቱ ይህ ነው በምድር ስንኖር ዛሬም የተቀመጥንበት ሁሉ ነገር ጊዜያዊ ነው ነገ ይነቃላል ነገ እንዳልነበር ይሆናል ግን ከዮርዳኖስ ወዲያ ኢየሩሳሌም አለች ማንም የማያናውጣት የሰው ጥበብ ያላረፈባት በአምላክ የተሰራች። እና ዛሬ እስራኤላውያን ከ12 ሰዓት ጀምሮ ለ7 ቀን ያከብሩታል በተቻለኝም አቅም በነዚህ ቀናት ትኩረት ሰጥቼ ስለ ዳስ የተለያዩ ሀሳቦችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እያነሳው እናያለን። ተባረኩልኝ። በዚህ ምድር ላይ እንግዳ እንደሆነ ለገባው ብቻ እንኳን አደረሳችሁ እንግዳ መሆናችንን ለየት አድርገን ለምናስብባቸው ለነዚህ 7 ቀናቶች። አውቃለው እብድ እንደምትሉኝ ግን ያው ባይብሊካል ስለሆነ ነው። ብቻ እንደምትማሩበት አምናለሁ።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.