cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Sumeya sultan

ነጻ ሃሳብ! ነጻ ግጥም!! ሃሳብ አስተያየት በ @Sumeyaabot አድርሱኝ

Show more
Advertising posts
990
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

(በሱመያ ሱልጣን) የተፈጥሮ ነገር ሆነ እና አርቴፊሻል የሆኑ ጌጣጌጦች ከሰውነት ቆዳዬ ጋር አይጣጣሙም። ቀበጥ ብዬ ላድርግ ያልኩ ቀን በማቆሳሰል ይኮረኩመኛል። እና ረጅም አመታትን ጆሮ ጌጥን ማድረግ ትቼ ኖሬ ከ እለታት በ አንዱ ቀን ከ እህቴ ጋር በ አንድ ጌጣጌጥ መሸሻ በኩል ስናልፍ ወደ አንዱ እግረመንገዳችንን ጎራ አልን። አንድ አነስ ያለች የ ብር ጆሮ ጌጥ ደስ አለችኝ እና ገዛሁ። ለ ቀናት ተደስቼ አድርጊያት ብዙ ሳትቆይ በ አንዱ ምሽት እንዴት ብሎ እንደጠፋብኝ እንኳን ሳላውቀው አንዱ ወልቆ ጠፋ። ተናደድኩ። ደበረኝ ምናምን እና "ድሮም ስቀብጥ እንጂ ላይበረክትልኝ ነገር ማን ግዢ አለኝ?" ምናምን ብዬ ተነጫንጬ ተኛሁ። በማግስቱ አመሻሽ ላይ የሆነ እቃ ፈልጌ የእጅ ቦርሳዬን ስዘረግፍ በ ወርቅ ማስቀመጫ የሆነ ነገር "ዱብ" አለ። አየነው። ስከፍተው የሚያምር የወርቅ ጆሮ ጌጥ ነበር። ማን እንዳስቀመጠው እንኳን ያወቅኩት ቆይቼ ነው። እሱንም ያን ሰው እንዳመሰግነው እራሱ እድሉን አልሰጠኝም። ጽሁፉ ከ ጆሮ ጌጥ የዘለለ ነው ትርጉሙ። አላህ ህይወታችሁ ላይ እናንተ" ይገባኛል!" ብላችሁ ከምታስቡት በላይ የሚገባችሁን ያውቃል። ብር ጠፋብኝ ብዬ ሳለቃቅስ በወርቅ የካሰ ጌታ እጆችን አንስተን የለመንነውን የሚረሳ ይመስላችኋል?? ሊያውም በጾመ አካላችን ተዋድቀን የለመንነውን? በሉ በሶብር እና ሶላት እርዳታውን ሻቱ! ሃያ! @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
27
እንግዳዬ (ሱመያ ሱልጣን) "ቂም ይዞ ጸሎት..."የሚለውን አባባል አጣቅሳ በ ንጹህ ልብ ጾምን የመጀመርን ትሩፋት ስትተነትን በልቤ የበደሉኝን ሰዎች እያስታወስኩ " ነገ አላህ ፊት አቁሜ ካልከሰስኩ በቀር በ ይቅርታ የማድነው ቁስል የለኝም"ብዬ በማሰብ ላይ ነበርኩ። "ምናልባት እናንተ ምን እንደበደላችኋቸው እንኳን ሳታውቁ የተቀይሙባችሁ፣ ነገ አላህ ፊት በ እልፍ በደላችሁ ሊወቅሷችሁ ያጎበጎቡትን እናንተ ዛሬ ለ አላህ ብላችሁ ይቅር ባላችሁት ምክንያት አላህ ፊት ምህረትን ሲቸራችሁስ?" ስትል ለ እልፍ ወንጀሌ ማርታ ስል "አፍወን ሊላህ!" ብዬ የበደሉኝን እና "በድለውኛል" ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ይቅር አልኩና በሬ ላይ ያለው እንግዳዬን በ ንጽሁ ልብ ልቀበለው ተሰናዳሁ። የናንተ የ እንግዳ አቀባበል እንዴት ነው? @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
8🥰 4👍 1
ዱዓችሁ ውስጥ ይሄን አትርሱ (ሱመያ ሱልጣን) በ ዱዓችሁ ውስጥ አል ራህማንን "አንተን ከሚያስታውሱት ጋር አወዳጀኝ!" በሉት። በ ህይወት ውስጥ ትልቁ ቅመም እሱ ነው። ስለ ቂርዓት ጉዞዋቸው የሚያወሯችሁን እና ጀነትን በነሱ መሃል በመገኘታችሁ ለማግኘት የምትከጅሉበትን አይነት ስብስብ ውስጥ መገኘትን ደግሞ ለመታደል ተሃጁድ አብዙ። "ዛሬ ይሄን ያህል ቅሪ!" ብሎ እያስታወሰ ካልቀራችሁ በቅጣት የሚኮረኩማችሁን ለማግኘት ደግሞ ሰደቃን አብዙ! በወር እና በ 2ወር ውስጥ ደግሞ እጃችሁን ይዞ የሚያስኸትማችሁን ለማግኘት ደግሞ በ አዛን እና ኢቃም መሃል ባለች ሰአት ላይ ዱዓን አትዘናጉ! ኺትማውን ደግሞ በውብ ድምፅ ምሽታችሁን የሚያሳምር አይነትን ለመታደል አላህዬን በ ትላልቅ ስሞቹ በየቂን ጥሩት! እሱ በርግጥም ሁሉን ሰሚ ነውና ደስታችሁ በ እንባ ሊያሳጥባችሁ ከፈለጋችሁ ደግሞ ለቤተሰቦቻችሁ በጎ ዋሉ እና ዱዓ እፈሱ!! ሁሉንም አንድ ላይ ለማግኘት ግን ይሄንን ረመዳን ጠንክራችሁ ስሩበት በደስታ የተጻፈ!! @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
21
ቢያስፈራም(ሱመያ ሱልጣን) ፋጢማ ቢንት አል ኸጧብ እስልምናን ከነባሏ ስትቀበል የሚደርስባት ስቃይ አልተረሳትም ። ከ ሁሉም ከ ሁሉም ደግሞ ከ ዑመር የዚያ የ አሸራ ሙበሸራ፣ የዛ ጀግና ደረቱ ለ ኢስላም ለመወጋትን የማያመነታው ባሏ፣ ዑመር ላይ ሲሆን እንኳን ለሚስቱ ሊመክት የራሱን አንገት ከዑመር መዳፎች ማስጣሉን ይጠራጠራል። ለምን? ዑመር ነዋ! ሃቢቡና ዲነል ኢስላምን በሱ ወይ በ አባ ጀህል ይነስር ዘንድ ዱዓ ያደረጉ እና በ ዑመር የጸደቀላቸው!! እናናናና... ሚስጥራቸው ተደብቆ ሊቆይ አልተቻለውም። ሰማላቸውና ከኋላው የቁርአን ንባብ ድምጽ የሚሰማበትን የቤታቸው በር እስኪያቃስት ድረስ ደብድቦ አስከፈተ። አይኑ እያየ እህቱ "ላት" እና "ዑዛን'' ትታ አላህን ልታመልክ?! እኮ የ ዑመር ሩህ ከ ጀሰዱ ሳትለቅ? እንዴት ተደርጎ?! ይህ ለመቀበል የሚከብድ የርሱ ቁስል ነበር። ከዛስ ባሏን ከመሬቱ አንጥፎ፣ እርሷን ከ አፍንጫዋ አንስሮ ፣"ዘራፍ" አለ! አልበቃውም! "ስታነበንቡ የነበረውን አምጪ!" ሲላት ያው ንዴቱ ጣራ እንደነካ ነበር። ከዛስ? አፍንጫዋን ደም ያለበሰው የወንድሟ ጡጫ ከሚያሳምማት በላይ በሺርክ የተጨማለቀ እጁ ቁርኣንን ነክቶ ሊያረክስባት መሆኑ ከበደባት እና "አይሆንም!" አለችው። የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም አይደል! ያ ሸይጧን እሱን ሲያይ መንገድ የሚቀይረውን ዑመርን "ያለ ውዱዕ አላስነካህም!" አለችው። "ታጠብ!'' ማለቷ እኮ አልነበረም ችግሩ። " ንጹህ አይደለህም!" መባሉ ነው እንጂ። እናማ እስቲ "እኔን አፏን ሞልታ ቀና ብላ ልትናገረኝ የ ልብ ልብ የሰጣትን ጉድማ ላንብበው።" አለ። ልቡ በ ኢማን ሊሞላ የ ሱራ ጧሃ 1ገጽን ንባብ ያህል ጊዜ አልወሰደበትም። ከዛስ? እሳቸውን ሊገድል የዛተባቸው ነብይ "ዑመርን የጠላ እኔን ጠላ! እሱን የወደደ እኔን ወደደ" ብለው መሰከሩለት። እና ለማለት የፈለግኩት በ ፋጢማ ቤት ከተፈጠረ የ ደቂቃዎች ትርምስ በላይ "የሰማ ቀን ይገድለናል" የሚል የከረመ ሰቀቀን ነበረበት። እናና አንዳንድ ውሳኔዎች መጀመሪያቸው ፍርሃት፣ መሃላቸው ሰቀቀን መጨረሻቸው ስቃይ ሊኖረው ይችላል። ግን እሱ! እሱ ውሳኔ የህይወትን ሙሉ ይዘት በሰኪና ይተካዋል። ለዛም ይመስለኛል "እናንተ ብቻ ለመቀየር ወስኑ እንጂ እኔ ከናንተ(በሚደርስባችሁ ነገሮች ከምትታገሱት)ጋር ነኝ ብሎ { إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِینَ } ታጋሾችን የሚያበሽረው። ከዛስ?{ إِنَّ مَعَ ٱلۡعُسۡرِ یُسۡرࣰا }"ከችግርም ጋር በርግጥ ምቾት አለ" ብሎ ያበረታው። { إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُخۡلِفُ ٱلۡمِیعَادَ }አላህ እኮ በርግጥ ቃሉን በጭራሽ አያብልም/አያፈርስም" ብሎ ስለ ቀጣዩ ምቾታችሁ ያረጋገጠው። እናማ ለውጥ ቢያስፈራም የማንሸሽበት፣ ለውጣችን ኢስቲቃማ ያለው የሚሆንበት ረመዷን ይሁንልን! @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
17👍 3
ኒዕማ ሱመያ ሱልጣን በኖርኩባቸው ጥቂት አመታት ከተማርኩት ትልቅ እውነታዎች ውስጥ 2ቱ 1ኛው እጅግ በጣም በቀላል እና በትንሽ ስራ ብዙ ትርፍ የሚገኝበት ትልቁ ጥበብ ሲሆን እሱም ለ እናት ማንኛውንም ነገር ማድረግ እና በ 100እጥፍ ዱዓ ማፈስ እና 2ኛው እናታችሁ ጓደኛችሁ አይን ውስጥ እናንተን ማየት የሚያስችላቸውን አይነት ጓደኛ ማግኘት ነው። ትላንት አመሻሹ ላይ ለ እናቴ ደውዬ የሆነ ዝም ብሎ ነገር ኦንላይን ላይ አይቼ በ 100 ብር እንደገዛሁላት እና የሚያቀብላት ሰው ስለሚደውልላት ወጥታ እንድትቀበል ነገርኳት። ወላሂ ያደርገችልኝ ዱዓ ምንም ብሰራ የማገኘው እስከማይመስለኝ ነው። ማለቴ በ 100 ብር ብቻ። ከዛ" ሃዩ እኮ ሰሞኑ መጥታ ነበር። እሷን አገኘሁ ማለት አንቺን አገኘሁ ነው።" አለችኝ። በንግግሯ ውስጥ የነበረውን እርካታ አደመጥኩት እና "አልሃምዱሊላህ በዚህ ኒዕማ ለባረከኝ!" አልኩት። ለሁላችንም የነዚህን ኒዕማ ጥፍጥና አላህ ያቅምሰን። የዱንያ ቅመሞች ናቸው رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
24
አማና( በሱመያ ሱልጣን) ጁምአ እለት ጊቢያችን ውስጥ ወዳለው አነስተኛ ሱቅ ከ ጓደኛዬ ጋር ሄደን ቸኮሌት እና ውሃ ከገዛን በኋላ የኔ ቶታል 32ራንድ መጣብኝ። በ አጋጣሚ ዋሌት ቀይሬ ስለወጣሁ በ እጄ የያዝኩት የካርዶች እንጂ የካሽ አልነበረም። ጓደኛዬም የራስዋን ሂሳብ ብቻ መክፈል የሚያስችል ብቻ ስለያዘች የኔውን በ ብድር መዝገብ ላይ ሞልቼ "ከሞትኩ ለቅሶዬን ሳትደርሺ በፊት ክፈይልኝ" አልኳት እንደ ቀልድ። ስለምፈራ እያንዳንዱ ቀኔ ላይ እዳ ካለብኝ በጣም ለምቀርበው ሰው "አደራ!" እላለሁ። ዛሬ ሄጄ ስከፍል ከስልኳ አላርም ላይ "የሱሚን አማና እንዳትረሺው" የሚል በየቀኑ ጠዋት 1ሰዓት ላይ የሚያስታውሳትን አላርም ስታጠፋ አየሁ። አማናን በዚህ ልክ የሚወጡ እስካሉ ድረስ ወላሂ ሰላም ነን!! @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
🥰 25 11👍 4
ቅኝተ " የልብ ነገር" የደራሲ ፉዓድ ሙናን @fuadmu ተከታታይ ጽሁፍ አስተያየቴ ( በ ሱመያ ሱልጣን) "ፉዓድ ሙና" የማደንቀው ጸሃፊ እንደሆነ ታውቃላችሁ አይደል? በጣም ጎበዝ እንደሆነም? አዎ ይሄው ፉዓድ ከሰሞኑ በ አንድ "የልብ ነገር" በተሰኘ ጽሁፉ ልቤን ሲያሸብረው ከረመ። "የልብ ነገር" ጽሁፍን ምናልባት ፉዓድን በቅርበት ባላውቀው "ልብ ወለድ ብቻ ነው።" ብዬ ልቤን ማረጋጋት በቻልኩ ነበር። ግን አይደለም። ደራሲው የ አካባቢውን እውነታ በሚያምሩ የቃላት ስብጥሮቹ እያስዋበ ከተለያዩ የ ቁርኣን አያዎች፣ ሃዲስ እና ቂሳዎች ጋር እያዋዛ ሃሳቡን ለልባችን በቀረበ መልኩ የሚያቀርብ በመሆኑ "እሰይ አልሃምዱሊላህ ደግነቱ ልብ ወለድ ነው" ብዬ ተረጋግቼ መተኛትን አልችልም። ምን አልባት "የልብ ነገር" ደራሲ ሌላ ሆኖ ቢሆን ያለ ምንም ጥርጥር የጽሁፉን መነሻ እውነታነት ክጄ ነፍሴን ባታለልኩ ነበር። ግን አይደለም። የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ ወላሂ እጅግ እንደሚያስፈራ ያወቅኩት በዚሁ ድርሰት ነው። እንደ "ፈሪሃ" ባሉ የፌሚንዝም እስረኞች ቤት፣ ትዳር የሚፈርስበት፣ እንደ "ኢክራም" ባሉ የ ሰውን ትዳር የሚበጠብጡ ሙስሊም እንስቶች የበዙበት፣ እንደ አቶ/ጋሽ "በርጌቾ" ቤተሰቦች ባሉ የዘረኝነትን ሙዚቃ የሚያቀነቅኑ የበዙበት፣ እንደ "ሰሚር" ያሉ አላህ መልካም የሻላቸው ነገር ግን በሚታየው ድርጊታቸው እንደ "የ ጀሃነም ሰው" እና እንደ "ሰሚራ" ያሉ በ ጨርቅ የተደበቁ በ አዲስ ትዳራቸው ላይ የሚማግጡ እንደ "የጀነት ሰው" የሚከብሩባት፣ እንደ " አህመድ" ያለ ጻዲቅ መሳይ የገዛ ጓደኛውን ወደ ሰላት እንኳ መመለስ ያልሞከረ የሚገንባት....ብቻ ብዙ ብዙ በሚሰሩበት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር እጅግ ያስፈራል። ጽሁፉን ሳነብ እንደ ሌላው ጊዜ በ አጨራረሱ ከመደነቅ በላይ በ አካሄዱ ላይ እኔን እና እኖራለሁ ብዬ የማስበው ወደፊቴን እያስገባሁ መጨነቁ ነው የተረፈኝ። አላህዬ መቼም ነውራችንን የሚሰትር ጌታ ነው እና ተረፍን እንጂ ሁኔታችንማ ከማንም ጋር ባላኖረን ነበር። "ስለ "የልብ ነገር" ምን ተሰማሽ?" ተብዬ አስተያየት ብጠየቅ ልመልስ የምችለው "ባላነበብኩትና ውስጤ ሰላም በሆነ" ብዬ እመልሳለሁ። የ ድርሰቱ እውነታ እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ውድቀታችን ነው። እንዴት እንደሚስተካከል አላውቅም። ቢያንስ እንደ "ሰሚር" ወንጀላችንን ተውባህ እና መልካም ምግባርን እናስከትልበት። ሴቶች ሴትነታችንን እናክብር! ፣ ባለ ትዳር ሴቶች በቃ በአላህ ይሁንባችሁ ትዳራችሁን እና ቤታችሁን አክብሩ! ከ ባሎቻችሁ አይን ተከለላችሁ ማለት አላህ "አላየም" ማለት አይደለም። ወላሂ ቀን ቆጥራችሁ በድንያም በ አኺራም ትከፍሉበታላችሁ። ያገባ ወንድን ወይም ያገባች ሴትን በጾታዊ መንገድ የምታወሩ ደግሞ እናንተ ወላሂ ከ አላህ ታገኙታላችሁ። በ አላህ ስም እምላለሁ ትከፍሉበታላችሁ። "ፌሚንዝም"ን የምታቀነቅኑ ደግሞ ለናንተ " ፈሪሃ" ምሳሌያችሁ ትሁን። በቃ ሁላችንም አላህን እንፍራ። ያ ብቻ ነው መፍትሄው። ብቻ እንደ ማንኛውም የሰው ልጅ እውነታነቱ አስፈራኝ እንጂ ጽሁፉ ወላሂ እንከን የማይወጣለት ድንቅ ስራ ነበር። ፉዬ @fuadmu እጅህ ይባረክ! አላህ ይጠብቅህ! እናመሰግናለን። @sumeyasu @sumeyaabot
Show all...
15👍 8🥰 4
ፍቅርን በ አደባባይ በፍቅር ልኬት፣በመውደድ ሚዛን፣ መውደድ ቢለካ፣ ማፍቀር ቢመዘን፤ በርሶ ሚዛን ላይ፣ ማነው 'ሚደፋ፣ የፍቅሩ ጣዕም ፣ልቦን 'ሚያጠፋ? ማንን ይወዳሉ፥ ከሁሉ አብልጠው፣ ከአላህ በታች?" አለ ጠያቂው፥ እርሱን እንዲሉት፤ ልቡ እየሻተች። አልወላወሉም ቀጥ ባለ መልስ "ሚስቴን ዓኢሻ" "ከተባዕትስ?" "አንተን" መባልን፤ አጥብቆ እየሻ። "አባቷን" አሉ የፍቅራቸው ልክ ለአለም ሲነግሩ በርሷ በኩል ነው ስሙን 'ሚጠሩ አወይ መታደል @sumeyaasu @sumeyaabot
Show all...
15👍 8
ከራህመቱ ካዝና (ሱመያ ሱልጣን) ቅጥል ያለ ሙቀት ነበር። ውሃ በ አናት በ አናቱ የሚያስጠጣ፣ ሰውነትን በ ላብ የሚያጠምቅ፤ ብቻ ጭንቅ የሚል ሙቀት ነበር። ጸሃዩ ከ ጭንቅላታችን በ 1ስንዝር ርቀት ላይ ብቻ ያለ እስኪመስል ቅጥል፣ ግብግብ የሚያደርግ አይነት። ዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ይህንን ሙቀት ለማስታገስ አንዳንዱ የለበሰውን ሲቀንስ፣ አንዳንዱ ደጋግሞ በውሃ ሲነከር እና እንደኔ አይነቱ ደግሞ ያለ ማቋረጥ በ ወረቀት ስናራግብ ቀኑ ተጋመሰ እና ቀዝቀዝ ማለት ጀመረ። የሚያልፍ የሚያገድም ሁሉ "ዛሬስ ሞትን፣ የዛሬውስ ይለያል..." ምናምን እያለ ችግሩን በ ግርድፉ ያውራ እንጂ እንደ አጠቃላይ መፍትሄ የሚሰጥም የኔን ከልክ በላይ ሙቀት አንገብግቦኝ ልወድቅ መድረሴን ሊፈታልኝ አልተቻለውም። ምክንያቱም ሁሉም በራሱ ሙቀት ላይ ነውና። ብቻ የማያልፍ የማይመስለው ያ ሙቀት፣ ሃይ ባይ የሌለው የሚመስል የ ጸሃይ ቃጠሎ ሁሉም እንደቀልድ ቀስ እያለ ተረጋጋ ከዛ አላህዬ ደግሞ የባሰ ባሮቹን ሊያስደስተን ሲፈልግ ከ ራህመቱ ካዝና ዝናቡን ላከልን እና የቀኑን ሙቀት እና ቃጠሎ አስረስቶን "አልሃምዱሊላህ" አልን። 2ነገርን አስተዋልኩበት። አንዱ የቂያማ ቀን ከሚኖረው ሙቀት እና ንዳድ በ አላህ ጥላ ስር የሚያስጠልል ስራ ከሌለኝ በፍጹም እንደማልችለው ተረዳሁ። ሁለተኛው ሁሉም ሰው በራሱ የተለያየ የህይወት ቃጠሎ ውስጥ ነው። ሁሉም ሰው ህመሙን የሚያስታግስበት የተለያየ መንገድ አለው። ማንም ለማንም ሊቆም አይቻለውምና ከሰው በጭራሽ መጠበቅ የማይሆን ነገር ነው። ከዛ ግን መጨረሻ የገባኝ ነገር " በርግጥም ከ ችግር ጋር ምቾት አለ" አይዞን ሁሉም ያልፋል። ብቻ በ አላህዬ ጥላ የሚያስጠልል ስራ እየሰራን! @sumeyasu @Sumeyaabot
Show all...
24🥰 5👍 3
ሸይጣንን ስራ ማስፈታት በሱመያ ሱልጣን "ሰደቃ ስትሰጪ ግራ እጅሽ ቀኝ እጅሽ የሰጠውን አይወቅ!" አለችኝ "የጀመዓ ስራ ሲሆንስ? ማለቴ የግል ብቻ ሰደቃ ካልሆነ እና ሌሎችም የተሳተፉበት ከሆነ?" " ረሱላችን (ሰ.ዓ.ወ) ከእናታችን ሰፊያ ጋር በማታ ሲሄዱ ሰሃቦች መንገድ ላይ ሲያገኙ ሌላን ነገር እንዳያስቡ በመስጋት "ይህች እኮ ባለቤቴ ፣እናታችሁ ናት!" እንዳሉ ታውቂያለሽ? ለምን መሰለሽ? ሸይጣን የሰው ልጅ ጭንቅላት ላይ ስራውን ስለሚሰራ ነው። ክፉ ክፉውን ስለሚያሳስብ ቶሎ ቀድመሽ ነገሩን ከፊትና ማጥራት ይኖርብሻል! ስለዚህ የጀመዓ ነገር ሲሆን የተሰራውን እና የደረሳችሁበትን አሳውቁ!እና ሸይጣንን ስራ አስፈቱ!" " ግን "እዩልኝ" አይሆንም?ማለቴ ኢኽላስ አያጣም?" " እናንተ ብቻ ልባችሁን አጥሩ ሌላው የ አላህ ነው!" @Sumeyaasu @Sumeyaabot
Show all...
20👍 3🔥 3