cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢየሱስ ይመጣል

የ ቻናላችን ቤተሰቦች አላማችን ቤተክርስትያንን ለማነቃቃትና🎼🎼🎼 🙏🙏🙏🙏መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለማቅረብ ነው ቆይታችሁን ከኛ ጋር ያድርጉ........ ጌታ ይባርካችሁ stay tuned

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
140
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከመስመሩ በላይና በታች በኑሮ ላይ የተሰመረ ሃሳባዊ መስመር አለ። ጥቂቶች ከመስመሩ በላይ ሲኖሩ ብዙሃኑ ግን ከመስመሩ በታችን ይኖራሉ። ይህ መስመር የአስተሳሰብ መስመር ነው። ከመስመሩ በታች ለመኖር እጅግ ቀላል ነው፤ ቀላል የሆነው ምቹ ሆኖ ሳይሆን ጥረት እና ልፋት ስለማይኖርበት ነው። እራስን ለማሻሻልም ሆነ እራስን ለማነጽ ምንም አይነት ሙከራ የማይደረግበት፤ የጨለምተኝነት ጭጋግ የወረሰው ስፍራ ነው። ከመስመሩ በታች የሚኖሩ ሰዎች ትናንታቸው ከዛሬ ዛሬያቸው ከነገ ለውጥ የለውም። የሰው ልጅ ዛሬም እንደትናንት ካሰበ እንዴት የተለየ ዛሬ ሊኖረው ይችላል? ብዙ ጊዜ በህይወታችን ለውጥ ለማምጣት እንፈልግና ጥረታችን ሁሉ ከንቱ ሲሆንብን ኑሮ ልክ እንደ ክብ መንገድ ዞሮ ዞሮ የሚያመመጣን የቆምንበት ቦታ ይመስለናል። ነገር ግን ለውጥ ማምጣት የሚሳነን፤ እራስን መለወጥ ስለማይቻል ሳይሆን፤ አስተሳሰባችን ዛሬም እንደትናንት ስለሆነ ነው። ከመስመሩ በታች የሚኖሩ ሰዎች አስተሳሰባቸውን ለመቀየር ፤በህይወት ላይ ያላቸውን አመለካከት ለመለወጥ ጥረት አያደርጉም ምክንያቱም ቀላል አይደለምና። አሉታዊ አስተሳሰቦችን ማሰብ በጣም ቀላል ነው፤ በኑሮዋችን ላይ የሚያመጡትን ተጽዕኖ ተቋቁሞ መኖሩ ግን በፍጹም ግን ቀላል አይደለም። ከመሰመሩ በላይ የሚኖር ሰው አስተሳሰቡ የእጣ ፋንታ ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ እንደሆነ የሚያምን ሰው ነው ። ከመስመሩ በላይ መኖር ቀላል አይደለም ነገር ግን ህይወት የምትጋርጥብንን ፈተና ለማለፍ ግን መነገዱን ቀላል ያደርገዋል። አወንታዊ አስተሳሰብን በእለት ተለት ኑሮ ላይ ለመተግበር ቀላል አይደለም። ምክንያቱም ብዙ ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ስላሉ። ብዙ ሰዎች አንድ መጽሃፍ አንብበው እስከዛሬ የገነቡትን የህይወት ልምድ ለመቀየር ይጥራሉ። ምንም እንኳን ለጠቢብ አንድ ቃል በቂው ነው ቢባልም፤ ባህሪን እና ልምድን በቀላሉ አሽቀንጥሮ መጣል ግን ለብዙዎቻችን ይከብዳል። ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች የለውጥን ጎዳና ይጀምሩና ለውጡን በአንድ ጀንበር ሲያጡት ተስፋ ቆርጠው ተደብቀው ወደነበሩበት ጉድጓድ መልሰው የሚገቡት። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ወሳኝ ነገር አለ። አንድ ሰው አንዴ 100 ኩንታል ስለተሸከመ በአንድ ቀን ጡንቻ አያወጣም። ጡንቻ ለማውጣት አልያም ደህና የሰውነት አቋምን ለማይዝ ያ ሰው ለብዙ ጊዜ ያለማቋረጥ እንቅስቃሴ ማድረግና እራሱን ያለመታከት መጠበቅ ይኖርበታል። አይምሮም ከዚህ አይለይም፤ ጤነኛ አይምሮን ለመያዝ የዘወትር ክትትል ያስፈልጋል። አይምሮዋችን እያወቅንም ሆነ ሳናውቅ በምናከማቻቸው መረጃዎች የሚመራ ነው። በተለይ ሳናውቅ (subconsciously) እንደዘበት የምናጠራቅማቸው መረጃዎች፤ ልምድ ይሆኑብና አሁን ያለንን ማንነት እንዴት እንደያዝነው ሳናውቅ በደመነፍስ እንኖራለን። ደስ የሚለው እውነታ ግን በማንኛውም የህይወት መስመር ላይ ብንሆንም ወደምንፈልገው መንገድ ለመሄድ እድሉ አለን። የሁሉም ነገር ቁልፉ ግን አስተሳሰባችን ነው። አስቡት ማንኛቸውም ነገሮች አለማችን ላይ እውን ሆነው ከመከሰታቸው በፊት በቅድሚያ አይምሮ ውስጥ መጸነስ አለባቸው። ይህም አሁን እውን ሆኖ የምናየው እያንዳንዱ ነገር በመጀመሪያ ሃሳብ ነበር ወደሚለው መደምደሚያ ያደርሰናል። ስለዚህ አስተሳሰብ የምንም ነገር ፈጣሪ ነው ማለት ነው። ታዲያ ይህንን ትልቅ ሃይል ለመልካም ፈጠራ ብንጠቀምበትስ? ያኔ ከመስመሩ በላይ መኖር እንጀምራለን። ከመስመሩ በላይ ነጻነት፤ ደስታ እና ፍቅር እንዲሁም ተስፋ በበቂ ይኖራሉ። በቅጡ የማይመራ አስተሳሰብ ግን፤ ከመስመሩ በታች ያለነጻነት ያለተስፋ በእጣ ፋንታ ገመድ አስሮ ያኖረናል። @Binisiwe
Show all...
🔘እስቲ ደሞ እናመስግን ✍ በዚህ ሰዓት ስለማመስገን ማውራት እብድ ነህ እንዴ የሚያሰኝ የሽሙጥ አይነት ንግግር ይመስላል። ይሄን ሁሉ ችግርና ግራ የሚያጋቡ ዜናዎች በየቀኑና በየሰዓቱ እየሰማን እንዴት የማመስገን አቅም ሊኖረን ይችላል?? ጦርነቱ፣ ኮሮናው፣መከፋፈሉ፣የኑሮ ውድነቱ፣ ስራአጥነቱ ሌላም ሌላም። የኔ ጥያቄ ግን ያለንን ነገር እያሰብን ከማመስገን ይልቅ ያጣነውንና የከሰርነውን ብቻ እያወጣንና እያወረድን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታችን ወደባሰ እንቆቅልሽ ውስጥ ዘፈቀን እንጂ ምን አደረገልን የሚል ነው። እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ማህበረሰብ ብሎም እንደ አገር እልፍ ችግሮች እንዳሉብን ፀሃይ የሞቀው ሃገር ያወቀው ጉዳይ ነው። ይሁንና አይኖቻችን ተከፍተው መልካም ነገሮችን ማየት ብንችል እልፍ ግዜ እልፍ አስደናቂና ውብ እንዲሁም በጎ የሆኑ ጉዳዮችን ማስተዋል እንችላለን። ነጮቹ:-'Praise and Raise, Complain and Remain' የሚሉት በማመስገን ውስጥ ያለውን የከፍታና የድል ሚስጥር በጥቂቱም ቢሆን ከመረዳት ይመስለኛል። አመስጋኝ ሰው የአዕምሮውና የአካሉ ጤንነት ከአጉረምራሚ ሰው በብዙ ፐርሰንት እንደሚሻል ጥናቶች ያመላክታሉ። እኛ እንድናመሰግን መድፍ 21 ጊዜ መተኮስ የለበትም። ቆም ብለን ትንሽ ማሰብ ብንጀምር ማመን እስከሚያቅተን ብዙ ተዓምር የሆኑ ነገሮች በዙሪያችን አሉ። እስራኤላውያን ወተትና ማር የምታፈሰውን ከነዓንን ለመውረስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል ተገብቶላቸው ሳለ ምድር በዳ እኮ የቀሩት አጉረምራሚዎች ስለሆኑ ነው። አጉረምራሚ ሰው መውረስ አይችልም፤ የመውረስም ስብዕና ከቶ አልገነባም። በተለይ አሁን አሁን ብዙዎቻችን ቶሎ ቶሎ ሆድ እንደሚብሰው ህፃን ልጅ ስሜታችን ለማጉረምረም እጅግ ቅርብና ስስ ለማመስገን ግን በተቃራኒው በጣም እየራቀ መጥቷል። ይሄ ጤናማነት አይደለም፤ሊያሳስበንም ይገባል።ስለዚህ የሰቀልናቸውን መሰንቋችንንና ከበሮዋችንን አውርደን ማመስገን እንጀምር። ስናመሰግን እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አስነስቶ በከበደንና ባቃተን ነገር ሁሉ ላይ ይዋጋልናል። አምላካችን ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን። እርሱ በነገር ሁሉ ትክክለኛና እውነተኛ በደረሰብንም ነገር ሁሉ ቅዱስና ፃዲቅ ነው።🙏 ♣Addicted to praise and worship!! 📌መዝሙር 19 ¹ ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።² ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።³ ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።⁴ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። ዮናታን ወርቁ 15/04/21G.C.
Show all...
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰቦች _____ ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡ ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን። በዚያን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር። በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው። አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም" አለው። አግዘአብሔር መለኪያ የሌለው ምህረቱና የፍቅሩ ብዛት እንዲሁ በደላችንንና መተላለፋችንን ሸፈነልን። በቅጣት ሳይሆን በምህረት አስተማረን፤ ገመናችንን ለማንም አሳልፎ ላይሰጥ ለልጆቹ ታመነ፣ መተላለፍና ሐጢያታችንም ረሳው። ያልተገባን ሳለን እንደተገባን፣ያልበቃን ሳለን ብቁ ያደረገን፣ የቁጣ ልጆች የነበርነውን በፀጋው እንዲሁ ያዳነን፣ከዘላለማዊ ሞት ወደ አብ ቀኝ፣ወገን አልባ የነበርነውን ምርጥ ትውልድ፣… ምንም የማንችል ሆነን ይችላሉ ልጆቼ ብሎ ሁሌም የሚተማመንብን፣ ጥፋታችንን ሳይሆን እድገታችንን የሚጠብቅ አባት አለን!! #ለ5 ሰውች #ሼር
Show all...
ታዋቂነት፤ ስም፤ ዝና እና ሃብት ራሃባቻው ያልሆኑ ሰዎች አሉ! እንዚህን ነገሮች ሁሉ በአጭር ጊዜ ለማግኘት ብዙ Advantage ያላቸው ነገር ግን ስለአንድ ነገር ሁሉንም እንደ ጉዳት የቆጠሩ ሰዎች አሉ! “አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤...” — ፊልጵስዩስ 3፥8-9 ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ ጥልቅ ፍላጎትና ትልቅ ትጋት ያላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ከዚህም የተነሳ ሌላውን እንደ ጉዳት የምትቆጥሩና በእግዚአብሔር ቃል እየተፈተናችሁ የቆያችሁ ከመናፍስት አባት እግዚአብሔር የተነገረላችሁ ቃል ይመጣል በዚያን ጊዜ ንጉስ ልኮ ያስፈታችኋል! ተፈትናችሁ የጠራችሁ በምትሆኑበት ጊዜ በምድሩና በለው፤ በቤቱም ሁሉ ላይ ይሾማችኋል! ከራሱም ቀጥሎ ያከብራችኋል። #የእግዚአብሔር_ቃል_ስፈትናችሁ_አትዛሉ!
Show all...
#ለበጎ_ነው “በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው። እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ቀንዲል (ኩራዝ)፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ። አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አልፈቀደላቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ቀንዲላቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው፤ ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት። ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ #እግዚአብሔር_ምን_ያህል_መልካም_ነገርን_እንዳሰበላቸው_አስተዋሉ።በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር፤ ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” <<<< እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው። ሰይጣን ለእኛ ለበጎ እንዲሆን የሚያመጣው ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔር ግን የሁሉ የበላይ ነውና ክፉውን ወደ በጎ በመለወጥ እኛን በደስታ፣ ጠላትን በሐፍረት ይሞላዋል። አዳምና ሔዋንን በመጣሉ ሰይጣን ፈጽሞ ደስ እንዳይለው እግዚአብሔር በተስፋ ቃል መታው /ዘፍ. 3፡15/። ዛሬ የመጣል ተራ ቢያገኝ ነገ ደግሞ ደም መላሽ በሆነው በክርስቶስ እንደሚወድቅ ነግሮ አሳፈረው። #ሰይጣን_ፈጽመን_ከእግዚአብሔር_እንድንቆራረጥ_ባመጣው_ውድቀት_ክርስቶስ_ዘመዳችን_የዘላለም_ውዳችን_ሆነ። ሰይጣንን እንደ አዋቂ እንስለዋለን። እርሱ ግን ጨለማና የጨለማ ሠራተኛ ነው። ሰይጣን አዋቂ ቢሆን ኖሮ የክርስቶስ ሞት የእርሱ ሞት መሆኑን አውቆ እንዳይሞት ይንከባከበው ነበር። የክርስቶስን ሞት ባፋጠነ መጠን የእርሱ ሞት ፈጣን እንደሚሆን አላወቀም ነበር። #አንድ_ሰው፡-«“ጌታ ሆይ ስለማልፍበት የሕይወት ውጣ ውረድ ለምን ቀድመህ አልነገርከኝም?”» አለው። #እግዚአብሔር_ግን፡- «««“እኔ የምናገረው የማያልፈውን እንጂ የሚያልፈውን አይደለም”»»» ብሎ መለሰለት ይባላል። የትኛውም ብርቱ መከራችን ያልፋል። ማለፍ ስለፈለገ ሳይሆን ማለፍ የተፈጥሮ ሕግ ስለሆነና አሳላፊው ጌታ በዙፋኑ ስላለ ነው። እኛ ጋር የሚቆይበትን ጊዜ የሚወስነው ራሱ መከራችን አይደለም። የጊዜ መቆጣጠሪያው ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነው። ብረቱ በማቅለጫው ውስጥ ሲያልፍ እሳቱ በዝቶ እንዳይበትነው፣ አንሶ ለመቀጥቀጥ እንዳያስቸግር የተቆጣጣሪው እጆች ያሉት በመቆጣጠሪያው ማሽን ላይ ነው። መከራው በዝቶ እንዳይገድለን፣ አንሶ መማር ያለብንን ሳንማር እንዳንቀር የሚቆጣጠረው ያ የፈጠረንና የተቸነከረልን የክርስቶስ እጅ ነው። እነዚያ ሩኅሩኅ እጆች መከራችንን እየተቆጣጠሩት ነውና መስጋት የለብንም። <<< ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ።አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ።በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት ምእመን፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድነው?” አለው። እግዚአብሔርም ሲመለስ #ለእርሱ_ባልሰጠው_ይጠፋል_ላንተ_ከሰጠሁህ_ትጠፋለህ” አለው ይባላል። እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችንን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜአችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ፍቅር ነው። ብዙ ነገሮች እንደዚህ እንደሆኑ እንጂ ለምን እንደሆኑ አናውቅም። ዘመናት ካለፉ በኋላ ግን ክፉ የሚመስለው ነገር መልካም እንደ ነበረ እንረዳለን።እግዚአብሔር የነገሮችን ዝርዝር አይነግረንም። እርሱ ንጉሥ በመሆኑ ለእኛ ዝርዝር መንገር አይጠበቅበትም፣ ደግሞም ብንሰማው የማንሸከመው ብዙ ነገር አለ። እንኳን መከራን እውነትን ለመሸከምም አቅማችን ውስን ነው /ዮሐ. 16፡12/። ያለፍነው እንዳለፍን የምናውቀው ብቻ አይደለም። ሳናውቀው ያሳለፈን እጅግ ብዙ ነው። አንዳንድ ነገሮች ካለፉ በአመቱ ስንሰማቸው እንኳ አንቀጥቅጠውናል። የምናመሰግነውም እንዳደረገልን ራሱ በሚያውቀው ልክ ነው። ዘመናት ካለፉ በኋላ ብዙ እንዳለፍን ስንረዳ፡- “ጌታ ሆይ ሰልፉን ላንተ፣ ድሉን ለእኔ ሰጠህ” ብለን በዕንባ እናመሰግናለን።ማደሪያ አጥቶ ዱር ማደር፣ ከነፋስ የተነሣ ማንበቢያው መቅረዝ መጥፋቱ፣ ቀስቃሽ ዶሮና ሠረገላዋ አህያ መበላታቸው ክፉ ነው። በዚህ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ነገርን ለበጎ በመለወጥ ሕይወትን ያጣፍጥልናል። ምናልባት ዛሬ ትንንሽ ችግራችን ከትልቅ ችግር የተጋረድንበት ይሆን? እግዚአብሔር ሞትን በሕመም ለውጦልን ይሆን? ከቤቱ እንዳንወጣ ኩነኔን በማጣት ቀይሮልን ይሆን? ለበጎ ነው።በጨለማ የሚጓዝ አንድ ሰው ዝናቡ ያበሰብሰዋል።አንድ እግሩን እልም ወዳለ ገደል ሊሰድ ሲል መብረው ብልጭ ብሎ መለሰው። ወደ ሰማይ አንጋጦ፡-“አይ ጌታዬ አንተ በመዓቱም ትምርበታለህ” ብሎ አመሰገነ። 😃ለበጎ ነው!
Show all...
☝️
Show all...
👏
Show all...
🤚🙌
Show all...
[Forwarded from https://t.me/maranataeyesuslimetanw (victor_Voice)] [ Video ] ነቢይ ዊሊያም ብራንሃም..... በምድር ላይ በነበረበት ወቅት አሁን ስላለው ወረርሽኝ የተናገረው እና መፍትሄው ብሎ የተናገረው.....
Show all...