cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Awolia School

የእወሊያ ትምህርት ቤቶች የቴሌግራም ቻናል እና ግሩፕ ስልክ ቁጥር ነው! 0988489131 Awolia Schools Channel (ቻናል) 👉 t.me/awoliaschool5 Group (ግሩፕ) 👉 t.me/awoliaschool6 ARDO Channel (ቻናል) 👉 t.me/ardoeth Group (ግሩፕ) 👉 t.me/ardoethG

Show more
Advertising posts
2 889
Subscribers
No data24 hours
+107 days
+5930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ቀን ቅዳሜ ሰኔ 8/2016 ኢድ - ሙባረክ! ድርጅታችን ለመላው መምህራን እና ሠራተኞቻችን እንዲሁም ለአወሊያ ማህበረሰብ እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1445 ዓ/ሂ ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን መልካም ምኞታችንን እየገለፅን በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የመተዛዘን፣ የመረዳዳት እንዲሆን እየተመኘን በዓሉን በማስመልከት ከቅዳሜ ሰኔ 8/2016 እስከ እሮብ ሰኔ 12/2016 ዓ/ል ድርጅታችን ዝግ መሆኑን እያሳወቅን ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ/ል መደበኛ ስራ እና መደበኛ ትምህርት በሁሉም አወሊያ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የሚጀመር መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን። አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
10👍 6😭 2
ቀን ሐሙስ ሰኔ 6/2016              ዜና አወሊያ ቁ.2 (ነስር) ት/ት ቤት የአወሊያ ቁ.2 (ነስር) 4 የቀድሞ ተማሪዎች የሆኑት 1 ኪያር ከድር 2 መድን ሸምሱ 3 ሪድዋን አወል 4 አንሳር ከማል 👉 ለአወሊያ ቁ.2 አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት ከ60 ሺ ብር በላይ ዋጋ ያለቸውን የአዲሱን ስርዓት ትምህርት አጋዥ መፅሃፎችን ለቤተ መፅሃፍ ገዝተው አስረክብዋል። 👉 ከ8 ወራት በላይ በዘለቀው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ጁምዓ ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማጠናከሪያ ትምህርት ሙሉ የመምህራን ክፍያ በሙሉ በመሸፈን 👉 እንዲሁም በማጠናከሪያው ትምህርት ላይ ጥሩ ውጤት ያመጡ እና 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ ተማሪዎችን ሸልመዋል። 👉 በመጨረሻም ማጠናከሪያ ትምህርት ሲያስተምሩ ለነበሩ መምህራንን የምስጋና የምስክር ወረቀትና የተለያዩ ሽልማቶችን አበርክተዋል። አወሊያ ቁ.2 (ነስር) ት/ት ቤት አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 18 1
ቀን ሐሙስ ሰኔ 6/2016 ዜና አወሊያ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት በትላንትነው እለት ሰኔ 05/2016ዓ/ል የአወሊያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሁለት ክፍል በመለየት በኦንላይን(Online) ፈተና ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ገለፃ ከተደረገላቸው በኃላ ሲስተም ላይ ያለውን የመለማመጃ ፈተና ተለማምደው ራሳቸውን እንዲፈትሹ ተደርገዋል። አወሊያ 2ኛ ደረጀ ት/ት ቤት አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
ቀን 05/10/2016    ክፍት የሥራ ማስታወቂያ የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት በዋና መስሪያ ቤት ስር  በሚገኘው አወሊያ ጤና ጣቢያ ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ አመልካቾችን በማወዳደር ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ አንደኛ 👉 የሥራ መደብ = አዋላጅ ነርስ 👉 ብዛት = 1 👉 የት/ት ደረጃ = ቢኤስ ሲ ዲግሪ  👉 ተፈላጊ ችሎታ = በሚድዋይፈሪ የተመረቀች  👉 የሥራ ልምድ = 2 አመትና ከዚያ በላይ የሠራች ሁለተኛ 👉 የሥራ መደብ = ነርስ  👉 ብዛት = 1 👉 የት/ት ደረጃ = ቢኤስ ሲ ዲግሪ/ዲፕሎማ  👉 ተፈላጊ ችሎታ = በነስር ሙያው የተመረቀች 👉 የሥራ ልምድ = 2 ዓመትና ከዚያ  በላይ የሰራች  በተጨማሪም 👉 ደመወዝ = በድርጅቱ እስኬል መሠረት 👉 ጥቅማ ጥቅም = የትራንስፖርትና የቤት ኪራይ አበል 👉 የሥራ ቦታ = አወሊያ ጤና ጣቢያ 👉 የቅጥር ሁኔታ= ከ60 ቀን የሙከራ ጊዜ ቡኃላ በቋሚነት         ማሳሰቢያ፣ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስርጃችሁን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት በስው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። አ/ዕ/ል/ድ አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አስኮ ባለው መንገድ ዊንጌት አደባባይን አለፍ ብሎ በሚገኘው አወሊያ ዋና ቢሮ ለበለጠ መረጃ የቢሮ ስልክ፡- 0112 707916 አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 16
ቀን ቅዳሜ ሰኔ 1/2016                        ማስታወቂያ         አወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች ወላጆች በሙሉ!  የ2016 ዓ/ል የትምህርት ዘመን ሊጠናነቅ ቀናቶችን መቁጠር የጀመርን ሲሆን ተማሪዎች አመቱን ሙሉ የለፉበትን የልፋታቸውን ውጤት የሚሰበስቡበት የሆነው የሰኔ ወር የገባ ሲሆን ለሁሉም የአወሊያ ቅርንጫፍ ት/ት ቤቶች ተማሪዎች መልካም የፈተና ግዜ እና የልፋታችሁ ፍሬ የምትሰበስቡበት እንዲሆን እየተመኘን የፈተና ፕሮግራሞች 👉 የ8 ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 4 እና 5 ሲሆን 👉 የ6 ክፍል ፈተና ሰኔ 12 እስከ 14 👉 የ12 ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ/Social Science ፈተና (ከሐምሌ 3 እስከ 5) ሲሆን 👉 የ12 ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ/Natural Science ፈተና (ከሐምሌ 9 እስከ 11) ሲሆን የመደበኛ ተማሪዎች ከኬጂ ጀምሮ እስከ 11ኛ ክፍል ላሉት የሁሉም አወሊያ ት/ት ቤቶች ከሰኔ 17 እስከ 22 መሆኑን እናሳውቃለን። በመጨረሻም 👉 የልጆቻችሁን ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያ በወቅቱ ለከፈላችሁ ወላጆች በጣም ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብን! 👉 የልጆቻችሁን ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያ በወቅቱ ያልከፍላችሁ ወላጆች ባሉት ጥቂት ቀናት እንድትከፍሉ እያሳሰብን የ2016 ውዝፍ ጨምሮ እና የሰኔ ክፍያ እስከ ሰኔ 14/2016 ከፍላችሁ እንድታጠናቅቁ በጥብቅ እያሳሰብን ያልከፈለ ተማሪ ፈተና ላይ የማይቀመጥ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡                    አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 27 2
ቀን ግንቦት ጁምዓ 30/2016 አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል አዘጋጅነት በክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 16 የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተካሄደው የስን-ምግባር ተኮር ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ አወሊያ ሙስሊም 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የላቀ ተሳትፎ በማድረግ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶዎታል። አወሊያ ቴሌግራም 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 22😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢናሊላሂ ወኢና  ኢላይሂ ራጂዑን           አስደንጋጭ ዜና በአወሊያ ሙስሊም አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት የአርብኛ ቋንቋ መምህርት የነበረችው እና አሁን ላይ ደሞ የአወሊያ ኮሌጅ አርብኛ ቋንቋ በማስተማር ላይ የነበረችው ዑስታዛ በድሪያ ኑርአዲስ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 20/2016 ዓ/ል ወደ ማይቀረው ወደ ሆነው ቤታችን አኼራ ሄዳለች። አላህ ይዘንላት! ዑዝታዛችን አላህ ጀነቱል ፍርደውስ ይወፍቃት! ለቤተሰቦቿም አላህ ሰብር ይስጣቸው። አላህ ጀነተል ፊርደውስን እንዲወፍቃት ዱዓ እናድርግላት። ቀብር ነገ እሮብ ግንቦት 21/2016 ዓ/ል ኮልፌ ሲሆን ሰላተል ጀናዛ አወሊያ መስጂድ ከተሰገደ ብኋላ ኮልፌ የምትቀበር ይሆናል። ቤቷ አወሊያ ዋናው ግቢ ጉለሌ ፋና ትምህርት ቤት አከባቢ ነው!
Show all...
😭 94👍 16 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢናሊላሂ ወኢና  ኢላይሂ ራጂዑን በአወሊያ ውስጥ ረጅም አመታትን በተለያዩ የስራ ክፍሎች ሰርተው የነበሩት የቀድሞ የሁለተኛ ድረጃ ት/ት ቤት ም/ር መምህር እና ር/መምህር እንዲሁም የአወሊያ ኮሌጅ ም/ዲን በተጨማሪም የአወሊያ ዋናው ብሮ ውስጥ በሸህ አብዱረህማን ዘመን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ሰረተው ያሳለፉት ዑስታዝ አብዱልከሪም መሀመድ ወደ ማይቀረው ወደ ሆነው ቤታች አኼራ ትላንት ሐሙስ ግንቦት 15/2016 ሄደዋል። ዑስታዝ አብዱልከሪም ከሁሉም ጋር ተግባቢ እጅግ በጣም የተረጋጉ እና ነገራቶችን በሰከነ መንገድ ይመሩ የነበሩ ዑስታዝ ናቸው! አላህ ይዘንላቸው! ሶላተል ጀናዛ አለም ባንክ አከባቢ ኢማሙ አህመድ መስጂድ ከተሰግዶባቸው በኋላ ቀብራቸው አለም ባንክ አከባቢ የሚፈጸም መሆኑን መወቅ ችለናል። ዑዝታዛችን አላህ ጀነቱል ፍርደው ይወፍቃቸው! ቤተሰቦቻቸውንም አላህ ሰብር ይስጣቸው። አላህ ጀነተል ፊርደውስን ኢንዲወፍቃቸው ዱዓ እናድርግላቸው። ቤታቸው ቤተል አከባቢ ነው! አወሊያ ቴሌግራም 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
😭 57👍 10 3
ቀን ሐሙስ ግንቦት 8/2016 አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!                    ዜና አወሊያ ቁ·1 ኬጂ! ከዚህ ቀደም ከአወሊያ ውጪ ወደ ተለያዩ የሕፃናት መዝናኛ እና መጫወቻ ቦታዎች በመሄድ ሲካሄድ የነበረው የአወሊያ ቁ.1 አፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤት የተማሪዎች የጨዋታ እና የመዝናኛ ፕሮግራም ዛሬ ለየት ባለ ሁኔታ እዚው በአወሊያ ዋናው ግቢ ውስጥ በደማቅ እና ደስ በሚል ሁኔታ በተዘጋጁት የተለያዩ ሕፃናት መጫወቻዎች ሁሉም ተማሪዎች የተሳተፉበት ደማቅ ፕሮግራም ተካሂዷል። አወሊያ ቴሌግራም 👉 t.me/awoliaschool5
Show all...
👍 38 17
ቀን ሐሙስ ግንቦት 8/2016 አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!                    ዜና አወሊያ ቁ·1 ኬጂ! ከዚህ ቀደም ከአወሊያ ውጪ ወደ ተለያዩ የሕፃናት መዝናኛ እና መጫወቻ ቦታዎች በመሄድ ሲካሄድ የነበረው የአወሊያ ቁ.1 አፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤት የተማሪዎች የጨዋታ እና የመዝናኛ ፕሮግራም ዛሬ ለየት ባለ ሁኔታ እዚው በአወሊያ ዋናው ግቢ ውስጥ በደማቅ እና ደስ በሚል ሁኔታ በተዘጋጁት የተለያዩ ሕፃናት መጫወቻዎች ሁሉም ተማሪዎች የተሳተፉበት ደማቅ ፕሮግራም ተካሂዷል።
Show all...
Go to the archive of posts