cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መጽሐፍት ና የመጻሕፍ ትረካዎች

☺ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር የለም፡፡ በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ!!!!!!Enanibib....... enadamit.....!!!

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
1 083
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማረጋገጫ አለመኖር ያለመኖር ማረጋገጫ አይደለም! የምንፈልገውና የምንመኘው ነገር ዛሬ እውን አልሆነም ማለት ነገ እውን አይሆንም ማለት አይደለም። የጨለማው መድመቅ የመንጋቱን እውነታ አያደበዝዘውም። የምኞቶቻችን መዘግየት የመቅረታቸው ምልክት አይደለም። ሰው በሙሉ ልቡ ያሰበውንና በእውነት የሚገባውን ያገኝ ዘንድ ግድ ይላል። ሩሚ በአንድ ግጥሙ እንዲህ ብሎ ነበር “Longing is the Core of mystery. Longing itself brings the cure. The only rule is, suffer the pain. Your desires must be disciplined and what you want to happen in time, sacrificed.” ሰው የሚፈልገውን ማግኘቱ ሳይሆን በስተመጨረሻ ዋጋ የሚኖረው፤ የሚፈልገውን ነገር ለማገኘት የሚገነባው ማንነቱ ነው። ደረስንበት ስንል የሚርቀን ነገር፤ በመንገዳችን ልንማረውና ልናውቀው የሚገባን ነገር ስላለ ነው። ጥበቃ ትልቅ መምህር ነው። ለተኛ ሰው የሌሊቱ መጨለም አያሰጋውም ሳያውቀው ይነጋልና። ነቅቶ ለሚጠብቅ ሰው ግን ሌሊቱ ያስፈራል፤ የሚነጋና ጎህ የሚቀድ አይመስልም። ሌሊቱ ሲነጋና ብርሃን ሲፈነጥቅ፤ ተኝቶ ካደረው ይልቅ ነቅቶ የጠበቀው የበለጠ አማኝ ይሆናል። ነገሮች አልጨበት ካሉህ/ሽ፤ መጠበቁ ካደከመህ/ሽ ነቅተህ/ሽ የሌሊቱን መንጋት እየጠበቅህ/ሽ ነውና በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጥ/ጪ. ስለመንጋቱ ማረጋገጫ የለም ማለት ላለመንጋቱ ማረጋገጫ ነው ማለት አይደለም። መጠበቅ ከባድ ነው፤ የሚጠብቅ ሰው ሁሌም ማረጋገጫ ይፈልጋል፤ ሆኖም ግን ብዙ ነገሮች ለመሳካታቸው ማረጋገጫ አስቀድመው አይሰጡም። ስለዚህ በእምነት መጠበቁን እንለማመድ፤ ብዙ የጠበቀ ብዙ ይማራልና! ምኞት ለጊዜ እጅ ሲሰጥ፤ ነፍስ በትዕግስት ስትታሽ ተዓምር ይፈጠራል!!! ✍በሚስጥረ አደራው መልካም ቀን!!! @yemesehaftirekawoch
Show all...
👉ሰው የምታውቀው ፍጡር አይደለም።ሁልጊዜ ሰውን የምናውቀው ይመስለናል።እኔ ሐኪም ስከሆንኩና የአንድ ሰው አካል ቀድጄ ልቡን ስላየሁት ሰውን ያወኩት ይመስለኛል።ነገር ግን ሰው በየትኛውም ደረጃ የሚታወቅ ፍጡር አይደለም። 👉በደረቁ ሳይንስ አጥንተህ ሰው ውስጥ ያለውን ፕሮቲን እንዴት እንደሚሰራ ስላወቅህ ሰውን አውቃለሁ ማለት አይቻልም።የመማር አንደኛው ችግር ቶሎ መታበይና የምናውቀው እውቀት እኛ ያመጣነው ሳይሆን ቀድሞ በሌሎች የተፈጠረ መሆኑን የመርሳት ችግር አለብን።እኛ ያወቅነው ከእኛ በፊት የመጡት የፈጠሩትን ነው።ይህንን እንረሳና እኔ ተምሬ ሳውቅ ራሴን አዋቂና ሐሳቡን እኔ የፈጠርኩት የመምሰል ችግር አለብን። 👉ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህን ያሰፋል።የእይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው የምትሄደው። ሰፊ ከሆነው ዓለም ውስጥ አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳለህ። እያወቅክ ስትሄድ ትልቅነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው የምትረዳው። 👉ልጆች ሆነ የከበደ ሚካኤልን መጻሕፍት ሳነብ አንድ ግጥማቸው ትዝ ትለኛለች "ፍጡርን ሲያስተውሉት በፈጠሪ ፊት ምንኛ ትቢያ ነው ምንኛ ኢምንት" የምትል ግጥም አለች። ይህ ይገባሃል። በዓለም ዙርያ በተፈጠረው እውቀት ውስጥ አንተ ትንሽ መሆንህ ይገባሃል። ይህ ትህትናን ያመጣል።ትህትና የምልህ ከሰው ጋር ለመኖር ሳይሆን ከራስህ ጋር በሰላም ለመኖር ነው።. 👉ከራስህ የምትጠብቀውን ነገር እንድትመዝን፣የምትችለውና የምትገኘው ነገር የተራራቀ መሆኑን እንድታውቅ ስለሚያደርግ መማሩ፣ማወቁ ጠቃሚ ነው። የቱንም ያህል ብታውቅ ዓለምን አትጨብጥም።እንደውም ብዙ የማታውቀው ነገር እንዳለ ነው የምትረዳው።አወቅሁት የምትለው ሳይሆን የማታውቀው እንደሚበዛ እንድታውቅ ነው የሚረዳህ። -ፍልስምና ፬፣ ገጽ 13 መልካም ቀን!!! @yemesehaftirekawoch
Show all...
🔺ከሌለን ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበልጣል። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ..ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ። ⏺ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው።አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነው። ⏺አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ⏺ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን በመኖርህ ብቻ ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ! ውብ ቀን!!!
Show all...
እንኳን ለመውሊድ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! ኢድ ሙባረክ!
Show all...
የራስ በራስ ትግል ብዙ ሰዎች ወደ አንድ ነገር አልፈው መሄድ እንዳለባቸው በሚገባ ያውቁታል፤ በነገሩም ያምኑበታል፡፡ የእነሱ ችግር የሚሄዱበትን አለማወቅና ለመሄድ ያለመፈለግ አይደለም፡፡ ችግራቸው ያሉበትን ለመልቀቅ እንደማይችሉ የማሰብ ወይም ያለመወሰን የራስ በራስ ትግል ነው፡፡ ፈረንጆቹ፣ “You can’t have the cake and eat it too” ይላሉ፣ ኬኩን ለሌላ ጊዜ ማስቀመጥም አሁን መብላትም አትችልም፣ ወይ ታስቀምጠዋለህ ወይም ደግሞ አሁን ትበላዋለህ እንደማለት ነው፡፡ ወደ አንድ አቅጣጫ ለመሄድ አንድን ነገር ትቶ መሄድን የመጠየቁ ጉዳይ ግን መቼም ሊለወጥ የማይችል ሃቅ ነው፡፡ መሄድንና ባሉበት መሆንን በአንድ ላይ ማስተናገድ በፍጹም አይቻልም፡፡ አንድን ነገር ለመያዝ ሌላን ነገር መልቀቅ ይፈልጋል፡፡ አንድን ነገር ለመያዝ መፈለግንም የያዙትንም አለመልቀቅንም በአንድ ላይ ማስተናገድ አይቻልም፡፡፡ በአንድ የስራ መስክ ለመሰማራት በእጃችን ያለውን ስራ መልቀቅ ይጠይቃል፡፡ አዲስ ስራ መጀመርንና ያሉበት ስራ አለመልቀቅን አንድ ላይ ማስተናገድ አይቻልም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ወደተሻለ ነገር መዝለቅ ይፈልጋሉ፣ ያሉበትን ነገር ግን ትተው መሄድ አይፈልጉም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ስኬትን ከሩቅ ያዩትና ያሉበትን ትቶ መሄድ ስለማይፈልጉ ወይም እንደማይችሉ ስለሚያስቡ ግን እዚያው ይቀራሉ፡፡ ሆኖም፣ ምንም እንኳን ጎዳናውና ሽግግሩ ከባድ ቢሆንም፣ የላቀ ነገር ለማግኘት አናሳውን መሰዋት የግድ ነው፡፡ የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ያሉበትን ውስን ቀጠና ትቶ ለመሄድ መቁረጥ የግድ ነው፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ "ትልቁ የብስለት ምልክት መልቀቅ ነው፣ በመልቀቅ ቅፅበት ውስጥ ደመናው ተገልጦ ጨረቃ በግልፅ ታበራለች" https://t.me/yemesehaftirekawoch
Show all...
መጽሐፍት ና የመጻሕፍ ትረካዎች

☺ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር የለም፡፡ በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ!!!!!!Enanibib....... enadamit.....!!!

መልካም አዲስ አመት !!! 2014
Show all...
ንቃ! ፍርሃት ውስጥ አትደበቅ። በፍርሃት ራስህን አትቅበር።ፍርሃት ጥሩም መጥፎም ነው። የፍርሃት ጥሩነት ለዝግጅት ማንቃቱ ነው። የፍርሃት ክፉነት ማስጨከኑ ነው። የፍርሃት መጥፎነት ግን የማይረባን ችግር አግዝፎ ማብከንከኑ፣ ለውሳኔ ጊዜ መብላቱ፣ በየምክንያቱ ማስደንበሩና ተጠራጣሪ ማድረጉ ነው። ንቃ እንጂ አትፍራ! ፈሪ ሰው ያጋጠመውን ሰው ሁላ ይጠራጠራል፣ ይሸሻል፣ ያስቀይማል። ፈሪ ሰው ጠላት ያበዛል። የፍርሃት መድሃኒቱ ንቃት፣ እውቀትና ተግባር ነው። የምትፈራውን ነገር ለመረዳት ሞክር። ፍርሃትህን ለመቋቋም ሆነ ለመከላከል ተነስና ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርግ። Just take one step at a time. And move on. መጠራጠር ለጥንቃቄ አጋዥ ቢሆንም የበዛ ጥርጣሬ ግን ነፍስህን ደስታ ይነፍጋታል፣ ምሬትህን ያበዛል፣ አይጠቅምህም። የበዛ ጥርጣሬ የተበላሸ የአእምሮ ስዕል ውጤት ነው። በአእምሮህ የምትስለውን ስዕል አስተካክል።በአእምሮህ ጥሩና ቆንጆ ስዕል ሳል። እመነኝ!፣ በእውንም ነገሮች ያንኑ ሆነው ታገኛቸዋለህ። ከተጠራጠርክም እንደዚያው ነው። "የፈሩት ይደርሳል፣ የጠሉት ይወርሳል" ሲባል አልሰማህም?"ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ" ሲባልስ? ሁለቱም ዓይነት አለ። ልዩነቱ ያለው እምነትህ ላይ ነው። እምነትህን አስተካክል። ያመንከው ይሆናል!እምነትህንና የአእምሮ ስዕልህን አስተካክል። ንቃ እንጂ አትፍራ! @yemesehaftirekawoch
Show all...