cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍሬ ማኅሌት

በቅድሚያ እንኳን ደህና መጡ።ይህ ኦርቶዶክሳዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።በውስጡም ሃይማኖታዊና አስተማሪ ነገሮች ብቻ ይለቀቁበታል። ❖ እግዚአብሔርን መስማት ያሳርፋል አለማችን እግዚአብሔርን ባለመስማት በመመላለሷ ረፍትን አጥታለች።እኛም እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ አለምን እየሰማን መቅበዝበዝን ጨምረናል፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ግን ከሁሉ የሚልቅ ይጠቅማል።ወዳጄ ሆይ እርሱን ስማ። @amdehaymanot1

Show more
Advertising posts
227
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
EOTC TV LIVE / ልዩ መግለጫ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

https://youtu.be/Wqgq1KebrOo

🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹 📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥 📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻 ለመረጃ 📞 +251985585858 ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv ➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን

https://www.facebook.com/eotctvchannel

➽የቴሌግራም ገጻችን

https://t.me/eotctvchannel

➽ የቲክ ቶክ ገጻችን

https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/

➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2

https://youtu.be/Wqgq1KebrOo

➽የትዊተር ገጻችን

https://twitter.com/EotcT/

➽የኢንስታግራም ገጻችን

https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=

#አምስቱ #አዕማደ #ምሥጢራት ማንኛውም ክርስቲያን እነዚህን ጠንቅቆ ማወቅ ይጠበቅበታል። እነዚህም የዶግማ መሠረት ናቸው። የቤተክርስቲያን ትምህርት አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት ማዕከል ያደረገ ነው። እነዚህም:- ፩) ምሥጢረ ሥላሴ ፪) ምሥጢረ ሥጋዌ ፫) ምሥጢረ ጥምቀት ፬) ምሥጢረ ቁርባን ፭) ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው። ምሥጢረ ሥላሴ እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንደሆነ የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ሥጋዌ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ አዳምን ለማዳን ሰው መሆኑን የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ጥምቀት ስንጠመቅ የእግዚአብሔር ልጆች እንደምንሆን የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ቁርባን ንስሓ ገብተን ሥጋውን ደሙን ብንቀበል ኃጢአታችን እንደሚሠረይልን የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ማንኛውም ሰው እንደ ሞተ እንደማይቀርና በምጽአት ጊዜ ሁሉም ተነሥቶ በዚህ ምድር ጽድቅ የሠሩ ወደዘለዓለም ደስታ፣ በዚህ ምድር ክፋትን ያደረጉ ደግሞ ወደዘለዓለም መከራና ሰቆቃ እንደሚገቡ የምንማማርበት ነው። #ሰባቱ #ምሥጢራተ #ቤተክርስቲያን ፩) ምሥጢረ ንስሓ ፪) ምሥጢረ ክህነት ፫) ምሥጢረ ሜሮን ፬) ምሥጢረ ተክሊል ፭) ምሥጢረ ቁርባን ፮) ምሥጢረ ጥምቀት ፯) ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው። በምሥጢረ ንስሓ ሰው ቢበድል እግዚአብሔርን በቄሱ አማካኝነት ይቅርታ ቢጠይቅ በደሉ እንደሚቀርለት የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ክህነት ከዐፃዌ ኆኅት እስከ ፓትርያርክ ያሉ ሰዎች እንዴት እንደሚሾሙ የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ሜሮን ሰው ከተጠመቀ በኋላ ማኅደረ እግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ስለሚቀባው እንዲሁም ንዋየ ቅድሳት ስለሚከብሩበት ቅዱስ ቅብዐት (ዘይት ዘጽሉይ) የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ቀንዲል ከምእመናን አንዱ ቢታመም ካህናትን ጠርቶ መብራት አብርተውለት ጸሎት ጸልየውለት እንደሚፈወስ የምንማማርበት ትምህርት ነው። ምሥጢረ ቁርባን የቁርባንን ሥርዓት የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ጥምቀትም የጥምቀትን ሥርዓት የምንማማርበት ነው። ምሥጢረ ተክሊል ደግሞ የሚያገቡ ሰዎች ሲያገቡ ሥርዓቱ ምን እንደሆነ የምንማማርበት ነው። የጋብቻን ክቡርነት የምንማማርበት ትምህርት ነው። ሁሉንም ለየብቻቸው በጥልቀት ወደፊት እንማማራቸዋለን። © በትረማርያም አበባው
Show all...
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ቤተሰቦች በዚህ ገጽ አላስፈላጊ ማስታወቂያዎችን ከመለፍ እንንቀቅ
Show all...
Show all...
"ጳጳሳቱን የሾምነው ተገደን ነው " ********************* አቡነ አብርሃም ያሁኑ ሹመት ሕገ...

"ጳጳሳቱን የሾምነው ተገደን ነው " ********************* አቡነ አብርሃም ያሁኑ ሹመት ሕገ ቤተክርስትያንን የጣሰ መሆኑን አሳወቁ ሹመቱ ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መመርያ መሰረት መፈጸሙን ገልጸዋል ይህንን ያደረግነውም ሌላ መከራ...

༒ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ሥላሴ ༒ እንኳን ለቅደስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የሌሊቱን ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ በዕለቱ የሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። ፩. ነግሥ / ሰላም ለአብ / ሰላም ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ፤ ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ፤ ኃይልየ ሥላሴ ወፀወንየ ሥላሴ፤ በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ። ዚቅ፦ አምላክነሰ ኃይልነ ፨ አምላክነሰ ፀወንነ ፨ አምላከ አሕዛብ ዕብነ ወዕፀ ኪነት ኢኮነ። ፪. ለአጽፋረ እግርከ / መልክአ ሚካኤል / ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤ ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤ አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡ ዚቅ፦ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘይሴባሕ እምትጉሃን ፨ ወይትቄደስ እምቅዱሳን ፡፡ ፫. ተፈሥሒ ማርያም / ማኅሌተ ጽጌ / ተፈሥሒ ማርያም እንተ ዘኢተአምሪ ብእሴ፤ ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ፤ እንዘ እዘብጥ ከበሮ ቅድመ አእላፈ ኤፍሬም ወምናሴ፤ ለተአምርኪ እነግር ውዳሴ፡ ማርያም እኅቱ ለሙሴ። ወረብ፦ ተፈሥሒ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ ተፈሥሒ ማርያም ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ ሥላሴ ዘጸገይኪ ለነ። ዚቅ ፦ ይሴብሑኪ ወይገንዩ ለስምኪ፨ ዘእምሥሉስ ቅዱስ ቃል ኃደረ ላዕሌኪ፨ ወትሰመዪ ማኅደረ መለኮት። ፬. ለህላዌክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላዌያተ፤ ለረኪበ ስሙ ኅቡእ አመ ወጠንኩ ተምኔተ፤ እምግብርክሙ #ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ፤ መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚኣክሙ ገጻተ፤ እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ። ዚቅ፦ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ አአትብ ወእትነሣእ ፨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፨ሠለስተ አሥማተ ነሢእየ እትመረጐዝ ፨ እመኒ ወደቁ እትነሣእ፨ ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት ፨ እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ ፡፡ አመላለስ ዘዚቅ ፦ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ። ፭ . ለሕጽንክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሕጽንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ ። ዚቅ፦ በአፍዓኒ አንትሙ ፨ ወበውሣጤኒ አንትሙ ፨ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለዘርዓ ያዕቆብ (ለኢያሱ) አንትሙ ፡፡ ወረብ፦ በአፍአኒ አንትሙ ወበውሣጤኒ አንትሙ/፪/ በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለኢያሱ ንጉሠ ነገሥት/፪/ ፮. ለሕሊናክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሕሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ፤ እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ፤ ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ፤ ፫ተ ዕደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ኀይምት ርእየ፤ ወለ፩ዱ ነገሮ ረሰየ። ዚቅ፦ ወጽአ አብርሃም እምድረ ካራን ፨ ወቦአ ብሔረ ከነዓን፨ ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር ፨ እንበይነዝ ጽድቀ ኮኖ ፡፡ ወረብ፦ ወጽአ እምድረ ካራን ወቦአ ብሔረ ከነዓን፤ ተአመነ አብርሃም አብርሃም በእግዚአብሔር/፪/ ፯. ለሐቌክሙ / መልክአ ሥላሴ / ሰላም ለሐቌክሙ ዘቅናተ ኂሩት ቅናቱ፤ ሊሉያነ ፆታ ሥላሴ እምአምላከ በለዓም ከንቱ፤ ኀበ መስፈርትክሙ ጽድቅ እስመ ያበጽሕ ትእምርቱ፤ ተደለዉ ከመ ይሑሩ ምሕዋረ ዕለታት ሠለስቱ፤ በዓለ መሥዋዕት አብርሃም ወይስሐቅ መሥዋዕቱ። ዚቅ፦ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ ፨ አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ፨ እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ ፨ ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል ፨ አብርሃምኒ ርእዮ በውስተ ምሥዋዕ ፨ ሕዝቅኤልኒ ርእዮ በልዑላን ፨ ሙሴኒ ርእዮ በዓምደ ደመና ፨ በነደ እሳት ፨ ፈያታዊኒ ርእዮ በዲበ ዕፀ መስቀል አምነ ፡፡ ወረብ፦ አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ፤ አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ ቤዛሁ በግዓ። ፰. ለዘበነጊድ / መልክአ ሥላሴ / ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ፤ መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ስብዐተ፤ ህየንተ ፩ዱ ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምእተ፤ ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ፤ ወዲበ ፲ቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ ። ዚቅ፦ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ፨ ስብሐት ለወልድ ለዘአክበራ ለማርያም ፨ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት። ወረብ፦ ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኲሉ ዓለም፤ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት። ፲. ለሕሊናከ / መልክአ ተክለሃይማኖት / ሰላም ለሕሊናከ ዘኮነ መምለኬ፤ ሥላሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ፤ ተክለሃይማኖት ቄርሎስ ዘላፌ ረሲዓን እለ እውጣኬ፤ ባርከኒ አባ ለወልድቅዱስ፤ኬ፤ እስመ ልማዱ ለመምህር ቡራኬ። ዚቅ፦ አንትሙሰ ከመ ዕብነ ሕይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ ፨ ወለክህነቱ ቅዱስ ፨ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ ለዘጸውዓክሙ ፨ አባ ባርከኒ ተክለሃይማኖት አባ ፨ ከመ ባረኮ አብርሃም ለይስሐቅ ወልዱ። ወረብ፦ አንትሙሰ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ወለክህነቱ ቅዱስ ታዕርጉ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ። °༺༒༻° ምልጣን °༺༒༻° ዕምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም ፤ መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም፤ እንዘ ይብሉ ይዜምሩ ፤ በልሳን ዘኢያረምም፤ አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም። አመላለስ፦ አማን በአማን ፤ መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም። °༺༒༻° እስመ ለዓለም ° ༺༒༻° ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ ፨ ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ፨ ወይቤሎ አብርሃም ንግሮ ለእግዚአብሔር ፨ እንዘ ትብል ተዘከር እግዚኦ ኪዳነከ ፨ አብርሃም ፍቊርከ ይስሐቅ ቊልዔከ ፨ ወያዕቆብሃ ዘአስተባዛሕከ ፨ ነሥአ ሙሴ ሠለስተ አስማተ ፨ ከመ ዘይወስድ አምኃ ለንጉሥ ፨ ወሰማዕትኒ ይጸውሩ ሥላሴ። ወረብ ዘአመላለስ፦ ሰአለ ሙሴ ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ፤ ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ። °༺༒༻° አቡን በ ፫ °༺༒༻° ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ እስመ በሥላሴ ትሄሉ በሰማይ ወበምድር ፤ (ሥ) ወሠናያቲሃ ይሰብክ ቃለ ኢያሱ ሐዋርያ ፍቅር ፤ ( ሥ ) ውስተ ሀገሩ ሐዳስ ደብረ ብርሃን ንግሥ አድባር ፣ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ፤ ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር ። °༺༒༻° ሰላም °༺༒༻° ሰላመ አብ ሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ ኃይለ መስቀሉ እትመረጐዝ፤ የሃሉ ማእከሌክሙ እኃው። + °༺+ °༺+༻° ተፈጸመ °༺+ °༺+ °༺ +
Show all...
ሰ🐄ሽን ለማግኘት ውስጥሽን 🦈ምኚው ከዛ 🐏ድም ቢሆን ደስተኛ ሁኚ (አፃፃፉ ገርሞኝ ነው ከtrlegram ገጽ)
Show all...
ሐምሌ ፭ ተዝካሮሙ ለአበው ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፩. ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጴጥሮስ አባቱ ዮና ይባላል።ትውልዱም በአባቱ ከነገደ ሮቤል ነው። በእናቱ ደግሞ ከነገደ ስምዖን ነው።ጴጥሮስ ማለት ዐለት ማለት ሲሆን ጴጥራ ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ነው።ከ፭ ዓመት ጀምሮ በቤተ ሳይዳ አጠገብ በቅፍርናሆም ከተማ በምኩራብ የአይሁድን ሥርዐት እየተማረ አድጓል።በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ።ለደቀ መዝሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው ፶፭ ዓመት ነበር።ለሐዋርያነት ሲመረጥም መረቡን ታንኳውንና አባቱን ትቶ ጌታን ተከትሎታል። ስለዚህም የሐዋርያት አለቃ አድርጎ ሾመው።ሁሉን ትተን ከተከተልነው ከፍ ሊያደርገን አምላካችን የታመነ ነውና።ጌታ ሰዎች ማን እንደሚሉት በቂሳርያ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች ሙሴ፣ኤርምያስ፣ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉኻል ሲሉት ጴጥሮስ ግን አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነኽ ብሎ መስክሯል።ስለዚህም ብፁዕ አንተ ስምዖን ወልደ ዮና ብሎ ብፅዕናውን ተናግሮ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼኻለሁ አለው። ማቴ ፲፮÷፲፫ ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ በዚያች ዕለት ሦስት ሺህ ሕዝብ አስተምሮ አጥምቋል። ሮሜ ገብቶ አስተምሮ ቀሌምንጦስን የሱ ደቀ መዝሙር አድርጎታል። በኋላም ቀሌምንጦስን ጵጵስና ወንድሙን ዲቁና ሹሟቸዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ በኢዮጴ፣ በልዲያ፣በፍልስጥኤም፣በሶርያ፣በጳንጦስ፣በገላትያ፣በቀጰዶቅያ፣በቢታንያና በሮም አስተምሯል።ከዮሐንስ ጋር አንጾኪያ ገብተው ሲያስተምሩ ሰዎች ክፋዎች ስለነበሩ ደብድበው ግማሽ ራሳቸውን ላጭተው እስር ቤት አስገቧቸው።በዚህ እያሉም ቅዱስ ጳውሎስ አጽናንቶአቸዋል። በሮም ከተማም ጴጥሮስና ጳውሎስ ለ፩ ዓመት አብረው አስተምረዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ ተአምራትን ከማድረጉ በተጨማሪ ፪መልእክታትን ጽፏል። የክርስትናው ጉዞም እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ።በዚህ ምክንያት ጴጥሮስና ጳውሎስ ተከሰው ወደ እስር ቤት ገቡ።እንደገና የሮማ ንጉሥ ኔሮን ከተማዋን በእሳት ባቃጠላት ጊዜ የሮማ አማልክት በክርስቲያኖች ሃይማኖት ስለጠቆጡ በከተማዋ እሳት ለቀቁባት ብለው ሮማውያን ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ መግደል ጀመሩ።በረከቱ ይደርብንና ቅዱስ ጳውሎስም እስር ቤት እያለ ተሰይፎ ዐረፈ። ይኽን የሰሙ ብዙ አማኞች ቅዱስ ጴጥሮስን ባይሆን አንተ ትረፍልን ብለው ላኩበትና በስውር ወደ ሌላ ቦታ ውጣ አሉት። እሱም እሽ ብሎ ቆቡን ለውጦ ከከተማ ሲውጣ በኦፕየም ጎዳና ጌታ መስቀል ተሸክሞ ወደ ሮም ከተማ እየተጓዘ ተገለጠለት።ጴጥሮስም አቤቱ ወዴት ትሄዳለህ አለው።ጌታም በሮም ከተማ ልሰቀል እሄዳለሁ አለው። "ትሰቀልኑ ዳግመ እግዚኦ"(አቤቱ ሁለተኛ ልተሰቀል ነውን!") አለው። እኔን ተሰቀል ሲለኝ ነው ብሎ ተመልሶ ወደ ሮም ከተማ ገባ። እየፈለጉት ለነበሩት ለኔሮን ወታደሮችም እንሆኝ አለ።ኔሮን እንዲሰቅሉት አዝዞ ሊሰቅሉት ሲወስዱት "እስመ እግዚእየ ንጉሠ ስብሐት ተሰቅለ ኀበ ላዕል ወሊተሰ ይደልወኒ እሰቀል ቁልቁሊተ"(የክብር ባለቤት ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ላይ ተሰቅሏልና ለኔ ደግሞ ወደታች እሰቀል ዘንድ ይገባኛል አላቸው።በሰቀሉትም ጊዜ በመስቀል ላይ ሁኖ ምእመናን በሃይማኖት እንዲጸኑ መክሮ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጥቶ በሰማዕትነት ዐረፈ።የዕረፍቱ መታሰቢያ ሐምሌ ፭ ነው።በረከቱ ይደርብን! ፪. ቅዱስ ጳውሎስ ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን አባቱ ዮአስ ይባላል።ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን የአያቱና የቅድመ አያቱ ሀገር ገሊላ ነው።በኋላ ወደ ጠርሴስ ገብተዋል።ጳውሎስ ሮማዊ ስሙ ሲሆን ሳውል ደግሞ የዕብራይስጥ ስሙ ነው።ትርጓሜው ከእግዚአብሔር የተለመነ ውሁብ ሀብተ እግዚአብሔር ዘዕውቅ ፈዳየ ዕዳ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የተወለደው በጠርሴስ ከተማ ሲሆን ድንኳን እየሰፋ ይኖር ነበር። በ፲፭ ዓመቱ ስመ ጥር ወደ ሆነው መምህር ገማልያል ተልኮ በኢየሩሳሌም የሙሴን ሕግና የአይሁድን ሥርዓት ጠንቅቆ ተማረ።በ፴ ዓመቱ የአይሁድ የሸንጎ አባል ኹኖ ለሁለት ዓመት ካገለገለ በኋላ ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ ስለነር ክርስቲያኖችን ተቃውሟል።ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ ተከሶ በቀረበ ጊዜ የተከራከረው እሱ ነበር።እስጢፋኖስን ሲወግሩት የወጋሪዎችን ልብሳቸውን ሲጠብቅ የነበረም እሱ ነው። በ፴፪ ዓመት ዕድሜው በደማስቆ ብዙ ክርስቲያኖች እንዳሉ ሲሰማ ጭፍሮችን አሰከትሎ ሲሄድ ከሰማይ የወረደ የመብረቅ ብርሃን አካባቢውን አለበሰው።ከዚያም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ።ጳውሎስም ጌታየ ሆይ እኔ የማሳድድህ አንተ ማነህ አለ። "አነ ውእቱ ኢየሱስ ናዝራዊ ዘአንተ ትሰድደኒ ይብሕሰከ ረጊጽ ውስተ ቀኖት በሊኅ" ግብ ፱:፭ (አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሃል አለው።) ያንጊዜ እየተንቀጠቀጠ አሁን ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ አለው። ከዚያም ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረውና በሐናንያ እጅ ተጠምቆ ምርጥ ዕቃ ሆነ።ቁጥሩም ከ፸፪ አርድእት ሆነ። ከዚያም ወደ ዐረብ ሀገር ሂዶ ሦስት ዓመት ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ተመለሰ።በዚያም በፊት ሲያሳድድ የነበረውን ኢየሱስን ሲሰብክ በመስማታቸው አይሁድ ተነሡበት።ከዚያም ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጠርሴስ ገብቶ ፱ዓመት አስተማረ። ቅዱስ ጳውሎስ በ፴፮ ዓ/ም ከበርናባስ ጋር ባደረገው የስብከት ጉዞው ፲፬ ሀገሮችን አስተምሯል።በሁለተኛ ጉዞው በ፶ ዓ/ም ፲፰ ሀገሮችን አስተምሯል። በሦስተኛ ጉዞው ፲፰ ሀገሮችን አስተምሯል።እንደገና በአራተኛ ጉዞው ፲ ሀገሮችን አስተምሯል።ከዚያም ወደ ሮም ገብቶ አስተማረ።፲፬ መልእክታትንም ጻፈ። በመጨረሻም ኔሮን በጥጋቡ የሮማን ከተማ አቃጠላት።የከተማው ሕዝብም በዚህ አሳቦ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ ማሳደድ ጀመሩ።ጳውሎስም በኒቆምዲያ ሲያስተምር ተይዞ በጨለማ ቤት ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ታስሮ ከቆየ በኋላ ሩጫውን ጨርሶ በንጉሡ ትእዛዝ በ፹፬ ዕድሜው አንገቱን ተሰይፎ በሰማዕትነት አረፈ።የዕረፍቱም መታሰቢያ ሐምሌ ፭ ቀን ነው። በረከቱ ይደርብን! ምንጭ:-መዝገበ ታሪክ
Show all...
🚻🚻#እንደ_ወርቅ_በእሳት_ፈተናው🚻🚻 ......... 🚹🚻🚻🚻🚻🚻🚻🚻🚹 ✔️ሐምሌ ፪ በዓለ ታዴዎስ ሐዋርያ ለእመ ኮነ በሰንበት ✔️ሐምሌ ፭ በዓለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሐዋርያት ለእመ ኮነ በሰንበት ✔️ሐምሌ ፲ በዓለ ናትናኤል ሐዋርያ ለእመ ኮነ በሰንበት ✔️ሐምሌ ፲፰ በዓለ ያዕቆብ ሐዋርያ እኍሁ ለእግዚእነ ለእመ ኮነ በሰንበት መዝሙር አሠርገዎሙ ይባላል። 📖መዝሙር "በ፬ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ፦ አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት አሠርገዎሙ ወንጌለ መንግሥት አወፈዮሙ አሠርገዎሙ ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዓ ሎሙ አሠርገዎሙ ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ አሠርገዎሙ ወከመ ጽንሐሐ መሥዋዕት ተወክፎሙ አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት።" 👇ትርጉም የሃሌታው ትርጉም እንዳለፈው ነው። በ፬ መሆኑ፦ የ፬ቱ ጸወርተ መንበር (የ፬ቱ እንስሳ) የ፬ቱ ወንጌላውያን የ፬ቱ አፍላጋት የ፬ቱ መዓዝነ ዓለም ምሳሌ ነው። ሸለማቸው ሐዋርያትን በሰማያት ሸለማቸው የመንግሥትን ወንጌል ሰጣቸው ሸለማቸው ሰንበተ ክርስቲያንን ለዕረፍት ሠራላቸው ሸለማቸው እንደ ወርቅ በእሳት ፈተናቸው ሸለማቸው እንደ መሥዋዕት ሽታ ተቀበላቸው ሐዋርያትን በሰማያት ሸለማቸው። ✍️ማብራሪያ ✔️"ሸለማቸው" ማለት መንግሥተ ሰማያትን አወረሳቸው ማለት ነው። የሐዋርያት የአሸናፊነት ሽልማታቸው እንደ ምድራውያን ሯጮች የሚዝግ፣ የሚበላሽ፣ ዓለም ስታልፍ አብሮ የሚጠፋ የነሐስ፣ የብር ወይም የወርቅ #ሜዳልያ አይደለም። የሐዋርያትና በሃይማኖት እነሱን የመሰሉ ሁሉ ተወዳጁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ነገረን ሽልማታቸው #አክሊል የተባለች #መንግሥተ_ሰማያት ናት። "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፥ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፥ ሃይማኖቴንም ጠብቄአለሁ፤ እንግዲህስ የጽድቅ አክሊል ይቆየኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በዚያ ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም" (፪ጢሞ፬፥፯-፰) እንዲል። ✔️ለምን መንግሥተ ሰማያትን "አክሊል" አላት የሚል ቢባል በዚህ ዓለም ያሉ ነገሥታት የመጨረሻ ክብር የሚሉት ዘውድ ወይም አክሊል መድፋት ነው። ይህን ጊዜ ንጉሥ ተብለው ከሕዝቡ የተለየ ክብርን ያገኛሉ። በዚህ አምሳል በመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ የመጨረሻው ክብር መንግሥተ ሰማያት መግባት ነውና #ቅዱስ_ጳውሎስ አክሊል ይቆየኛል ነገር ግን ለእኔ ብቻ ሳይሆን እንደ እኔ ላሉት በኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ጸንተው ለሚኖሩት ጭምር ነው። ያለውን #ቅዱስ_ያሬድ ደግሞ የድካም ዋጋ ናትና መንግሥተ ሰማያትን ሽልማት አላት። መሸለም ደስ ያሰኛልና!!! ነገር ግን የሚሸለም የደከመ፣ ያሸነፈ፣ ውጤት ያመጣ እንጂ፤ ያልደከመ፣ ያላሸነፈ፣ ውጤት የሌለው አሻግሮ ተሸላሚ ጀግኖችን ከማየት ያለፈ ምንም የሚያገኘው ሽልማት እንደሌለ ሁሉ እኛም እንደ ሐዋርያት ለመሸለም እንድንተጋ ነው ሊቁ እያመሠረጠረ የሚነግረን። ✔️የመንግሥት ወንጌልን ሰጣቸው ማለት፦ ለሚሰማት፣ ለሚኖራት፣ ለሚተገብራት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ ወንጌልን እንዲያስተምሩ አደረጋቸው ወይም ሾማቸው ማለት ነው። “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ” (ማር፲፮፥፲፭) እንዲል። ✔️ሰንበተ ክርስቲያንን ለዕረፍት ሠራላቸው ማለት፦ በእሑድ ሰንበት ዕረፍተ ሥጋ እንዲያደርጉባት ፣ ክርስቶስ ትንሣኤውን ያደረገባት የነፃነት ቀን ናትና በዚህች ዕለት እየተሰባሰቡ ወንጌልን እንዲያስተምሩባት ምዕመናን እንዲማሩባት፣ ቅዳሴ አስቀድሰው ሥጋውን ደሙን እንዲቀበሉባት ፣ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑባት ፣ ንስሐ እንዲገቡባት ፣ ኅብረተ ክርስቲያን እንዲያደርጉባት ሰጣቸው ማለት ነው። ✔️ዕረፍተ ሰንበተ ክርስቲያን የዕረፍተ መንግሥተ ሰማያት ምልክት ናትና (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ)። ✔️እንደ ወርቅ በእሳት ፈተናቸው ማለት፦ ከሐዋርያት ሰማዕትነት ያልተቀበለ የለም። አንዳንዶች በሰይፍ አንገታቸውን ተሰይፈዋል አንዳንዶች በእሳት ተቃጥለዋል አንዳንዶች ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥለዋል አንዳንዶች በመስቀል ተሰቅለዋል አንዳንዶች በድንጋይ ተደብድበው ተገድለዋል አንዳንዶች ቆዳቸው ተገፏል ወዘተ ስለ እግዚአብሔር ብለው ያልተቀበሉት መከራ ሥጋ የለም። በዚህ ሁሉ ግን እጅግ ደስ ይላቸው ነበር። “እነርሱም ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ ስለ ስሙ መከራ ይቀበሉ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አድሏቸዋልና" (ሐዋ፭፥፵፩)እንዲል። መከራ ሥጋው የሚደርስባቸው እንደ እኛ ሆዳቸውን ለመሙላት ብለው ሳይሆን ንጹሕ ደሙን አፍስሶ የዋጃቸውን የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል አስበው በመከራ ሊመስሉት ስለፈለጉ ነው። “ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን”(ሮሜ ፮፥፭)እንዲል። ✔️ሌላው ወርቅ በእሳት ከአልተፈተነ ጽሩይነቱ ግብዝነቱ አይታወቅም በእሳት ከተፈተነ በኋላ ንጹሕ ወርቅ መሆኑ ይታወቃል። ሐዋርያትም ወንጌልን መስበክ ብቻ ሳይሆን እንደ ወርቅ በመከራ ተፈትነው አልፈው ነው ንጹሐን ቅዱሳን መሆናቸውን ያሳዩን። መከራ ሲመጣም አልሸሹም መከራውን በመከራ እያለፉ አሸነፉት እንጂ። መከራ ያጠራል እንጂ የሚያምኑትን ምንም ሊጎዳቸው አይችልምና። “ይህንም ጸጋ እግዚአብሔር ሰጥቷችኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልትቀበሉም ነው እንጂ ልታምኑበት ብቻ አይደለም” (ፊልጵ፩፥፳፱) እንዲል። ✔️እንደ መሥዋዕት ሽታ ተቀበላቸው ማለት፦ ስለ ስሙ መከራ ሲቀበሉ መከራቸውን ሞታቸውን ያለ ዋጋ አለማስቀረቱን ሲያይ እንደ ንጹሕ የዕጣን መዓዛ ተቀበላቸው በማለት ክብር መስጠቱን ይነግረናል። 📖ዓራራት "ኀረየ ፲ተ ወ፪ተ (አሠርተ ወክልኤተ) ሐዋርያተ፤ ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሀሩ ወስብኩ በስምየ፤ አጋንንተ አውጽኡ፤ እለ ለምጽ አንጽሑ ወሙታነ አንሥኡ።" 👇ትርጉም አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት መረጠ፤ ሂዱ ስሜ ሕይወት መድኃኒት እንደሆነ አስተምሩ፤ በስሜ አጋንንትን አውጡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ ሙታንን አስነሡ ብሎ ላካቸው። "ሄዳችሁም፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ የተቀበላችሁትን በከንቱ ስጡ"(ማቴ፲፥፯-፰)እንዲል። ✔️መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ማለት መንግሥተ ሰማያት በልጅነት ፣ ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለች ማለት ነው። 📖ዕዝል "ኀረየ ፲ተ ወ፪ተ ሐዋርያተ፤ ሤሞሙ ኖሎተ፤ ወይቤሎሙ ዕቀቡ ሰንበትየ፤ ዱያነ ፈውሱ በስምየ።" 👇ትርጉም አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት መረጠ፤ እረኝነትን/ጠባቂነትን ሾማቸው፤ ሰንበቴን ጠብቁ፣ ድውያነ ሥጋን በተአምራት ፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት ፈውሱ አድኑ አላቸው። በጎቼን ጠቦቶቼን ግልገሎቼን ጠብቁ ብሎ ሾሟቸዋልና ሤሞሙ ኖሎተ አለ። (ዮሐ፳፩፥፲፭) 📖ሰላም
Show all...
"ዘአጽንዓ ለምድር ዲበ ማይ፤ ወወሀቦሙ ሥልጣነ ለሐዋርያት፤ ወሀቦሙ ሥልጣነ ይፈውሱ ዱያነ፤ በሰላም አዕረፉ፤ ወተፈሥሑ በዕለተ ሰንበት።" 👇ትርጉም ምድርን በውኃ ላይ ያጸና "ዘአጽንዓ ለምድር ዲበ ማይ" (መዝ፻፴፮፥፮) እንዲል። ለሐዋርያት ዱያነ ፈውሱ ሙታነ አንሥኡ እለ ለምጽ አንጽሑ አጋንንተ አውጽኡ ዘዓሠርክሙ በምድር ይኩን ዕሡረ በሰማያት ወዘፈታሕክሙ በምድር ይኩን ፍቱሐ በሰማያት ብሎ ሥልጣነ ክህነትን ሰጣቸው። በሰላም አረፉ፤ በዕለተ ሰንበትም ደስ አላቸው ማለት ዕረፍተ ሰንበት ምሳሌዋ በሆነች በመንግሥተ ሰማያት ደስ አላቸው። ምነው አሁንማ ያሉት በገነት አይደለም መንግሥተ ሰማያትማ መቼ ተሰጠች ገና አይደለችም❓ የሚል ቢኖር ዛሬ ገነት የገባ ሁሉ ኋላ መንግሥተ ሰማያትን እንደሚወርስ የተረጋገጠ ነውና። ✍️አያችሁ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ወንጌልን እንዴት እንደሚተረጉመው በማኅሌት የምናገለግል ሊቃውንት በማስተዋልና በፍቅር ከአገለገልን ምን ያህል ክብር እንዳለው ምሥጢሩ ራሱ ያስረዳናልና በፍቅር አገልግለን አንድንጠቀም አምላከ ቅዱስ ያሬድ ይርዳን! የሊቁ በረከት አይለየን!!! አሜን!!!!!!! ተጻፈ በመምህር ዳንኤል አለባቸው የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር
Show all...
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ + እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? +  ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንህ እንዴት "አባታችን" ብለህ በአንድነት ተጠራዋለህ? + ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? + ልብህ ከእሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠረኸው "ስምህ ይቀደስ "እንዴት ትለዋለህ? + ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግስትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? + መከራን  በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትለዋለህ? + ለራስህ ሆድ እንጅ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን"እንጀራችንን"ስጠን ትላለህ? + በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? + የኃጢአት አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተነ አታግባን" እንዴት ትለዋለህ? + ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ"ከክፉ አድነን"እንዴት ትለዋለህ? + ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ  እንዴት" አሜን" ትላለህ? +++ "መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"       ቅዱስ ባስልዮስ
Show all...